ህይወቴ
8 subscribers
1 link
ህይወቴ
Download Telegram
ህይወቴ
አመመኝ
አመመኝ ስል ይሄ ሁሌም በመድሀኒት የሚድነው በሽታ ሳይሆን ውስጥ ውስጡን የሚያሳምመው ናፍቆት የተባለ በሽታ ነው የሚያመኝ ወይ አይድን ወይ አይገል ህመም ብቻ ሆኖ የሚቀር በሽታ
ህይወቴ
አመመኝ ስል ይሄ ሁሌም በመድሀኒት የሚድነው በሽታ ሳይሆን ውስጥ ውስጡን የሚያሳምመው ናፍቆት የተባለ በሽታ ነው የሚያመኝ ወይ አይድን ወይ አይገል ህመም ብቻ ሆኖ የሚቀር በሽታ
የዚህ በሽታ መድሀኒቱ "ተናፋቂው" ሰው ሲመጣ ነው ካልሆነ ግን ትዝታ በተባለ virus እያገረሸ እስከ ዘላለሙ እንደ cancer የማይድን በሽታ ሆኖ ይቀራል
መኖር የደከመሽ 'ለት ማታ......አይንሽን ቀና አድርገሽ ከዋክብቶቹን አውሪያቸው እንደሌሎቹ.... ለምን? አይሉሽም.... "እኛም" ይሉሻል እንጂ.... ከዛ እንግዳ የሆነ ስሜት ይወርሻል ስሜትሽን ሲጋሩሽ ግኡዛን ከነሱ በላይ ጓደኞችሽ እንደሆኑ ሲገባሽ ሌቱ በቆየ ቀኑ ባጠረ ትያለሽ
በዚህ አለም ውስጥ ሁሉም ነገር በሚባል ሁኔታ ተቃራኒ ነው look
"እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" አለች አህያ
But አህያዋም ሞተች ሰርዶውም በቀለ እርግማኗም አፈር በላው ልክ እንደሷ!
ዘመኑ ከፍቷል
ህይወቴ
ዘመኑ ከፍቷል
በቀደም እለት ልጁን በዚህ ሌሊት የት እየሄድክ ነው?ስለው
ልጁ---ስለት ላስገባ
እኔ---እኮ ቤተስኪያን?
ልጁ---ኧረ አይደለም...ብሎ *ስለት ማውጣት*
ሰው ሁሉ ሌላ ሰው ነው
ውጪው ሌላ ውስጡ ሌላ
ኑሮው ሌላ ህልሙ ሌላ
ልቡ ሌላ አፋ ሌላ
'ሁላችንም ሌላ ሰው ነን'
ህይወት እንደ መረብ ነው አይደል
የሚገናኝ የማይመስለው ይገናኛል

አዳም ረታ
ያዩት የሰሙት ሁሉ አይነገር
መች ከብዶት ለሆድ ነገር ማሳደር
ሞት
ህይወቴ
ሞት
ድሮ እናቶቻችን ትልቁ ሞት ሰውን ማጣት ይሉኝ ነበር። ያኔ በልጅነቴ እንደ ምንም ነገር አልቆጠርኩትም ነበር ግን ሁሉን ነገር የሚገባን ለአቅመ ሄዋን/አዳም ስንደርስ እና ሲደርስብን ነው
ህይወቴ
ሞት
ሞት የምንወደዉን ሰው ያሳጣናል ምንም ማድረግ ስለማንች ከትዝታቸው ጋር እንከርማለን ግን ይሄ ትዝታ እያደር ቁስል ይሆናል
የቀዘቀዘው ልቤ ፀሀይ የሚሞቀው እድለቢሱ ግምባሬ
ለምዶበት እንጂ ማመስገን አፌ ....
በመኖር እና በመሞት መሀል መዋዠቅ
ህይወቴ
በመኖር እና በመሞት መሀል መዋዠቅ
ወደሞት መሄድ ባይቀርም መንገዳችንን ለማሳመር መፍጨርጨር
ልክ ትልቅ ሰፊ ባህር ውስጥ እየሰመጥኩ ያክል ይሰማኛል እኔን ብቻ ነው ግን?
አይ አይመስለኝም ምክንያቱ ቢለያይም አብዛኞቻችን እየሰመጥን ነው። ግን ደግሞ ማነው ለመውጣት እየሞከረ ያለው?
እንኳን ለመውጣት መሞከር እየሰመጠ መሆኑን ያላወቀ ስንት ሰው አለ እንደኔ ከሆነ የውሀው ግፊት አስጨንቆን ማብቂያው ላይ ከምንባንን አሁን ማለትም አሁን መውጣት አለብን።


.................................. ይመስለኛል።