Mindset-Empire
44 subscribers
35 photos
1 video
82 links
At Mindset empire, we empower personal growth through mindfulness, meditation, and emotional intelligence. Join us to cultivate inner peace, resilience, and meaningful connections for a balanced, harmonious life.
Download Telegram
"እውቀት ለወሲብ የሚያነሳሳቸው ሰዎች"

ከላቀ ውበታቸው እና ከንቃታቸው ደረጃ የተነሳ ወንድን አማርጠው ምርኮኛቸው እንደሚያደርጉ የምንመሰክርላቸው ሴቶች አይን ውስጥ የማይገባ መናኛ ወንድ ላይ ሲወድቁ አይተን እናውቃለን።

መልከ ጥፉ የሆኑ ፥ ኪሳቸው የጎደለ ፥ በባህሪም ቢሆን 'ምስጉን' ከሚባሉት ወገን ያልሆኑ፥ ቀልድ አዋቂነት የደረሰበት ያልደረሱ ፥ ዝነኛነትም ያልጎበኛቸው ወንዶች በውበትዋ የተጨበጨበላትን ሴት በፍቅር ሲያንበረክኩ አይተን "ምን አይነት መተት ይሆን?" ብለን ይሆናሉ። ነገሩ መተት አይደለም። በቅርቡ የተደረሰበት የስነልቦና ሳይንስን ጉዳዩን "ሳፒዮ ሴክሽዋል" ብሎ በይኖታል።

ሳፒዮ ሴክሽዋል ከምንም ነገር በላይ እውቀት ለወሲብ የሚያነሳሳቸው ሰዎች መጠሪያ ነው።
አዎ እውቀት ብቻውን ለወሲብ የሚቀሰቅሳቸው፥ በፍቅርም የሚጥላቸው ሰዎች አሉ።

እርግጥ መጠኑ ይለያይ ይሆናል እንጂ ሁሉም ሰው እውቀት ይመስጠዋል። ነገር ግን ለአንዳንድ ሰዎች መመርመር የሚወድ ሰው በተለየ መንገድ ወሲባዊ መነቃቃትን ይፈጥርበታል። ሳፒዮ ሴክሽዋል የሆኑቱ የላቀ እና በከፍተኛ እወቀት የታገዘ ንግግር ሲሰሙ ፥ ሳይንሳዊ ዶክመንተሪ ሲመለከቱ ፥ በእውቀት የታጨቀ መፅሐፍ ሲያነቡ ለወሲብ ይነሳሳሉ።
የማሰብ ችሎታ ለወሲብ ይገፋቸዋል፥ በፍቅርም ይጥላቸዋል!

"ሳፒዮሴክሹዋል" በቅርቡ የታዋወቀ ሃሳብ ነው። ቃሉ "ሳፔር" ከሚለው የላቲን ግሥ የተገኘ ሲሆን "ጥበበኛ መሆን፥ ማስተዋል" የሚል አቻ ትርጓሜ አለው።

ይህ ዝንባሌ ያላቸው ሰዎች አስደናቂ የማሰብ ችሎታ ካለው ሰው ጋር ለመዋሰብ ምንም አይነት ስሜታዊ ግንኙነት አያስፈልጋቸውም።

የማያውቁት ሰው እውቀት አዘል ንግግር ሲሰጥ በመመልከት ብቻ ስሜታቸው ይነሳሳል።

ይህ ዝንባሌ ያላቸው ሰዎች ከወሲብ በፊት ከሚደረግ አካላዊ ንክኪ ይልቅ ጥልቅ ውይይት ፥ ምሁራዊ ማብራሪያ ስሜት ይሰጣቸዋል።
የትኛውም አይነት የሚወደድ ባህሪ ያለው ሰው በእውቀት ጉዳይ ደካማ ከሆነ ከህይወታቸው ለማስወጣት ሁለቴ አያስቡም።
https://t.me/Mindsetempiree
የትምህርት ቤት ክፍያ

አንዳንድ ሰዎች ለምን እንደማይማሩ ሲጠየቁ፣ “ትምህርት ቤት መማር ብዙ ዋጋ ያስከፍላል” ይላሉ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ልክ ነው መማር ያስከፍላል - ገንዘብን፣ ጊዜን፣ እንቅልፍን፣ ጉልበትን . . . ያስከፍላል! ነገር ግን መማር ከሚያስከፍለው ይልቅ አለመማር ያስከፍላል፡፡ መማር አሁን ያስከፍልና ነገ ይከፍላል፤ አሁን ያደክምና ነገ ያሳርፋል፡፡ አለመማር ግን፣ “አሁን ዘና በል” በማለት ነጻ ይለቀንና እድሜ ልካችንን እያስከፈለና እየገዘገዘን ያከርመናል፡፡

ከላይ የተጠቀሰው የመደበኛ ትምህርት ሂደት እውነታ መደበኛ ባልሆነው የየእለት የሕይወት ትምህርትም አንጻር ያው ነው፡፡ ለነገው ሕይወታችን ጥበብን፣ ልምድንና የሕይወት ተሞክሮ ተግባራዊ እውቀትን የምናገኝበት ብቸኛ መንገድ ዛሬ አዳዲስ ነገሮችን በመሞከር ከምንሰራቸው ስህተቶች የተነሳ ነው፡፡ በሌላ አባባል ሲገለጽ፣ ስህተት ማለት ለነገ የሕይወት ስኬት ዛሬ የምንከፍለው የትምህርት ቤት ክፍያ ነው፡፡

“በሕይወታችን ሁለት ፍላጎቶች ብቻ ናቸው ያሉን፡፡ አንደኛው ሁል ጊዜ መማር ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሁል ጊዜ ሳይሳሳቱ ትክክል መሆን” (Errol Gerson)፡፡ እነዚህን ሁለቱንም ነገሮች ግን በአንድ ላይ ማስኬድ አንችልም፡፡

ሁል ጊዜ ትክክል መሆን ከፈለግን አዳዲስ ነገሮችን መሞከር እናቆማለን፡፡ ያን ጊዜ ሕይወት ይቆማል - ትልቁና የመጨረሻው ስህተት!፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ሁል ጊዜ አዳዲስ ነገሮችን ከሞከርን መሳሳታችን አይቀርም - ታላቁና ውጤታማው ስኬት መንገድ!
ሁል ጊዜ አዳዲስ ነገሮችን የመሞከርን መንገድ የመረጥን ጊዜ ሕይወት በብዙ ልምድ፣ ልምምድ፣ ጥበብና እውቀት ታሸበርቃለች፡፡

ዛሬ አዳዲስ ነገሮችን በመሞከር የምንከፍለው ዋጋ ለነገው ሕይወታችን ስኬታማነት የሚከፈል ስለሆነ ማለት ነው፡፡

ተንቀሳቀሱ! ጀምሩ! ስሩ! ከተሳሳታችም ከስህተታችሁ በመማር ለነገ የተሻለ ማንነት ያዙ!
መልካም ሰኞ❤
https://t.me/Mindsetempiree
በዚህ ሀሳብ ትስማማላችሁ?

“አብዛኛው ሰዎች ለእናንተ ታማኝ አይደሉም፤ ይልቅ በእናንተ ላይ ባላቸው ፍላጎት ውስጥ ታማኝ ናቸው። ታድያ ፍላጎታቸው ሲቀየር ለእናንተ ያላቸው ታማኝነት አብሮ ይቀየራል!።”

ካህሊል ጅብራን

https://t.me/Mindsetempiree
ሠላም Mindset Empire አባላቶች እንደምን አላችሁ??

ይሄን ቻናል እንድከፍት ያነሳሳኝ ነገር በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት ያልተለመደውን ሳይኮሎጂ ወይም  የስነ ልቦና ምክር በቀላሉ እና ለብዙ ሠዎች ምቹ  በሆነ ሁኔታ እንዲደርስ ታስቦ የተከፈተ ነው።
    በተለይም እኛ ወጣቶች በህይወታችን ላይ ያሉትን አስቸጋሪና ፈታኝ ሁኔታዎች እንዴት እናልፋቸዋለን???? እንዴትስ እንወጣቸዋለን የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ነው።

፨ በጣም እፈራለው
፨ተስፋ ቆርጫለው
፨ከቤተሠቦቼ ጋር አልስማማም
፨ደስተኛ አይደለሁም
፨ብቸኝነት ይሰማኛል
፨በሠዎች ዘንድ ተፈላጊ አይደለሁም
፨ከሠዎች ጋር መግባባት አልችልም
፨ህይወቴን አልወደውም

እንዴት እነዚህን ነገሮች እንደምናስተካክል በቆይታችን መልስ እንሰጥባቸዋለን።
ይህን ቻናል ሌሎችም እንዲጠቀሙበት ለ ጉዋደኞቻችሁና ላላችሁበት group share እንድታረጉ በታላቅ ፍቅር እጠይቃለው❤️❤️❤️❤️❤️
https://t.me/Mindsetempiree
ሠላም እንደምን አደራችሁ ውድ የ Mindset-Empire ቻናል አባላት???
  ዛሬ በዚች ውብና ያማረች ማለዳ ቀናችንን እንዴት በደስታ እንደ ምናሳልፍ በትንሹ እናያለን፦

    አብዛኛዎቻችን ወጣቶች ማለዳ ከእንቀልፋችን ስንነቃ ምንም ነገር ከመከወናችን በፊት ስልካችንን በአንድም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ መጎብኘታችን የተለመደ ነው። ለነገሩ ዛሬ እንኩአን ጎበኘነው። ምናልባት ይሔን ምክር ሊያሳየን ይሆን🤔🤔🤔🤔🤔

 
   ፨  ስንቶቻችን ነን ማታ ስንተኛ ጠዋት እንደምንነሳ እርግጠኛ ሆነን አልጋችን ውስጥ የገባነው???
፨ ስንቶቻችንስ ነን ዛሬ ጉአደኛችንን እንደምነገኘው እርግጠኛ ሆነን ቀጠሮ ያስያዝነው?????

🤔ታድያ ጠዋት ስንነሳ ስንቶች ሊያዩት የተመኙትን ማለዳ እኛ በማየታችን በራሱ ደስታን ሚፈጥር ነገር አይደለም??? ወይስ ማለዳን ማየት ልማድ ሆነብንና ደስታችን አለቀ?????
 
   አንዳንዴ  ከጉአደኞቼ  ጋር ሳወራ ዛሬ ምን አዲስ ነገር አለ በዬ ጠይቃለው ፤ እናም የሚሰጡኝ ምላሽ በጣም ይገርመኛል🤓🤓🤓🤓🤓 ምንም አዲስ ነገር የለም ፤ ሁሉም ያው ነው ይሉኛል። ታዲያ እኔ ሳስበው እነዚህ ልጆች በጣም ያሳዝኑኛል😔😔😔😔 እሚያሳዝኑኝ በዛሬዋ ቀን ላይ አዲስ ነገር ስለሌላቸው ሳይሆን፤ አዲስ ነገር እያለ ማየት ባለመቻላቸው ነው።

    እነሡ ያላዩት አንተ ያየኸው አዲስ ነገር ምንድነው ልትሉኝ ትችላላችሁ.......
መልሡ አጭርና ግልፅ ነው...እሡም የዛሬው ቀን ነው😁😁😁😁😁 ያስቃል አይደል????
  እስቲ መልሡልኝ......የዛሬውን ቀን ከዚህ  ቀደም ኖራችሁት ነበር ??? የዛሬዋን ጠዋት ትላንት አይታችሁዋት ነበር🙄🙄🙄🙄🙄🙄🙄🙄 መቼም ካላበዳችሁ በስተቀር መልሳችሁ አልነበረም ነው።

  
፨ስለዚህ የዛሬዋ ቀን አዲስ ናት😇😇😇😇😇 ሁሉም ሠው ጋር ያለው አዲስ ነገር የዛሬው ቀን ነው። ታድያ ይሄን ማሠቡ በራሱ አይደለም የዛሬዋን ቀን ቀሪው ዘመናችንን ደስተኛ አያደርገንም ????? ለዚህ እኮ ነው ያለንን ብናውቅ የጎደለን የለም እሚባለው🤡🤡🤡🤡🤡🤡
 
  👉 አሁን ካላችሁበት ተነሡና መስታወት ፊት ቁሙ ። ምን ያክል እድለኛ እንደሆናችሁ ታውቃላችሁ። በመስታወቱ ውስጥ እራሳችሁን እያያችሁ ስማችሁን እየጠራችሁ ፦ ሁሌም ደስተኛ መሆን እችላለው..... የትኛውንም ትልቅ ተራራ መጋፈጥ እችላለው......... ብላችሁ ለራሳችሁ ተናገሩ።  ከዛ እውነተኛ ደስታ parry መሄድ gf or bf መያዝ መኪና መንዳት ወዘተ.... እንዳልሆነ ትረዳላችሁ።


🤠 ደስታ ከውጭ ሳይሆን ከውስጣችን
        ያለ የፈጣሪ ስጦታ ነው።
🤠 በህይወትህ ስኬታማ መሆን
       ከፈለክ ፈጣሪህን ከፊት
       በማስቀደም አንተ ተከተለው።



🙏🙏 መልካም የ ደስታ ቀን ይሁንልን። አሜን........
https://t.me/Mindsetempiree
፨፨የሶቅራጥስ 3ቱ ጥያቄዎች!፨፨

አንድ ሠው ወደ ሶቅራጠስ ሄዶ እንዲህ አለው...
‹‹ሶቅራጥስ ወዳጄ፣ እገሌ ስለተባለው ወዳጅህ የሠማሁት ደስ አይልም›› አለው፡፡ ሶቅራጥስ ግን ዝም አለ፡፡
ሠውየውም እንደገና፡- ‹‹ይገርማል ከእርሱ አይጠበቅም፤ በጣም ገርሞኛል›› አለ፡፡ ሶቅራጥስም ይህ ሰው እንደማይለቀው ስለተረዳ አንድ መደራደሪያ ሀሳብ አቀረበለት፡፡ ‹‹ስለ ወዳጄ ልትነግረኝ የፈለግከውን ልሠማው የምችለው ሶስት ጥያቄዎች አሉኝ፤ እነርሱን ስትመልስልኝ ብቻ ነው›› አለው፡፡ ሠውየውም ተስማማ፡፡

▶የመጀመሪያው ጥያቄዬ የእውነት ጥያቄ ነው፡፡ ስለወዳጄ የሠማኸው መቶ በመቶ እውነት ነው ወይ?›› አለው፡፡ ሠውየውም፡- ‹‹መቶ በመቶ እንኳን እርግጠኛ መሆን አልችልም›› አለው፡፡ ሶቅራጥስም፡- ‹‹ልትነግረኝ የፈለግከው እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው ማለት ነው፡፡

▶ ሁለተኛው ጥያቄዬ የመልካምነት ነው፡፡ የምትነግረኝ መልካም ነገር ነው ወይ?›› አለው፡፡
ሠውየውም፡- ‹‹እርሱማ መልካም አይደለም›› አለው፡፡
ሶቅራጥስም፡- ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠና መልካም ያልሆነ ነገር ልትነግረኝ ፈልገሃል ማለት ነው፡፡

▶ ሶስተኛውና የመጨረሻው ጥያቄዬን ልጠይቅህ?›› አለው፡፡
ሠውየውም፡- ‹‹እሺ›› አለ፡፡
ሶቅራጥስም፡- ‹‹የምትነግረኝ ነገር ለእኔ የሚጠቅመኝ ነገር አለው ወይ?›› አለው፡፡
ሠውየውም፡- ‹‹የለም›› ብሎ መለሠ፡፡ ሶቅራጥስም በመጨረሻ፡- ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፤ መልካም ያልሆነ፤ ለእኔ የማይጠቅም ነገር አልሠማም›› አለው ይባላል፡፡
©ከዕውቀት_አድማስ


👇ሼር👇ጆይን👇ሼር👇
https://t.me/Mindsetempiree
ምንምነት ውስጥ ምንም ነገር አለ።
፧
፧
ሀሳብ አለ።
… እሚታሰብ እሚንሰለሰል ። ሳትፈልገው ሚፈልግህ…… ሳታልመው
እሚያልምህ…… በአንተ ዙሪያ እየዘወረ እሚዘውረወህ…… ሀሳቡን
ተረድተህ ለመሰደር ብትባዝንም ምንጩንና ፍንጩ የማይገለጥልህ
ግዜ አለ……… ታወጣ ታወርድና ይህን ሀሳብህን ለሚካፈልህ ጓደኛ
ትሻለህ… …ለመረዳት ሀሳብህን ለመካፈል የመጣው ጓድህ " ምን
ገጠመህ ጓዴ? " ይልሀል። የገጠመህ እክል አታውቀውም ግን
ጨንቆሀል……ግን ደብቶሀል…… ግን ያባዝንሀል…… የተምታታ ስሜት
ውስጥህ ሰርፇል። እንዲህ ነው ብለህ ተንፍሰህ ነገሩን ሀሳቡን
ማቅለል ያዳግትሀል።
፤
……ያሳለፍካቸውን ቀናት እየተመለስክ ውሎህን አዳርህን
እያስታወስክ የተገበርካቸውን ትሰልላለህ ። ምንም አታገኝም ወይም
ከስሜቱ ጋር እየታገልክ መንስኤው ይጠፋሀል። ዝም ብሎ ውስጥህ
ይነጫነጫል ንጭንጭህን  ተባዕት ወይም እንስት በታገኝ
አግኝተውህ የውስጥህን ስላልተነፈስክ ይከብዳቸዋል።እንዲህ
ይገጥማል ሀቅ ነው ። መንስኤ አለው ወይም ደርሰህ ተደብተሀል።፤
፤
☞ ………ምንም ባልነው ነገር ምንም ያላልነው ነገር ይፈተላል።
ምንም ማለት ባዶ አይደለም ባዶ ያልነውም ምንም አይደለም ማለት
አይደለም። ባዶነትም አንድ ምንነት ነውና።ግን ምን ሆኛለሁ? ምንም
አልሆንኩም አልልም ባዶ ሆኛለሁና።
።
እናም
☞ ማንኛውም ሀሳብ ሀሳብ ሆኖ… ሀሳብነቱ ገዝፎ ሀሳብን አጨንግፎ
እሱ ሲያንሰራራ… …አንሰራርቶ ሀሳብ ሀሳብነቱን የሚረዳ ሀሳቡ
ደርሶበት ያረፈበት ሰው ላይ ነው።
※
ደግሞም
ምንም ነገር ውስጥ ምንም ነገር አለ
✔ ምንም ነገር ያለምንም ነገር አይነሳምና።

https://t.me/Mindsetempiree
ውድ ቤተሠቦች እንደምን አላችሁ?  ዛሬ በዚች ማለዳ ደስ የሚል አጭር ታሪክ አቀርብላችሁዋለው......

👉 ሽማግሌው ቀራፂ ከመንደሩዋ የጥበብ ማእከል ተነስቶ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲያመራ ደማቋ የበጋ ፀሀይ ሙቀቷን በነፋሻማው የካሪቢያን ደሴት ላይ ያለስስት እየረጨች ነበር። በመንገዱ ላይ ነጭ የተንጣለለ ቪላ ቤት ያለው ግዙፍ የ እርሻ መሬት ባለቤት ከሠራተኞቹ ጋር በመሆን ለብዙ ትውልድ ከሀይለኛው ፀሀይ ከለላ ይሠጥ የነበረውን እድሜ ጠገብ ዛፍ ሲጥሉ ያያል። ሽማግሌው ቀራፂ ቆሞ ድርጊታቸውን ለአፍታ ሲመለከት ቆየና ወደ ሠውዬው በመጠጋት "እነዚህን የወዳደቁ የዛፍ ግንዶች ምን ታደርግባቸዋለህ? " ሲል ጠየቀው።
    ባለ ፀጋውም አለ ፦ "እንጨቶቹ ከማገዶነት ባለፈ ለምንም አይረቡኝም"

    ሽማግሌው ቀራፂም  አጋጣሚውን በመጠቀም ከወዳደቁት የዛፍ ግንዶች አንዱን እንዲሠጠው ጠይቆ አዎንታዊ መልስ ስላገኘ፣ ትልቁን የዛፉን ቅርንጫፍ በጥንቃቄ አንስቶ በትከሻው ከተሸከመ በኋላ ወደ መኖሪያ ቤቱ መንገዱን ቀጠለ።

     ጎጆ ጋ እንደደረሠ የዛፉን ቅርንጫፍ  በቤቱ ወለል መሀል አስቀመጠውና ባለፀጋው "ረብ የለውም"  ያለውን እንጨት እያዟዟረ በጥሞና ያስተውለው ገባ። ድንገት አንዳች ሀሳብ መጥቶለት መጋዝና መሮውን ያነሳ ጊዜ የተሸበሸበ ፊቱ ላይ እንግዳ የሆነ ፈገግታ ይታይበት ነበር። ፀሀይና ዝናብ ሲፈራረቁበት ከኖረው ጉጥ የበዛበት የዛፍ ቅርንጫፍ ውስጥ አንድን ነገር ከረብ-የለሽነት ነፃ ለማውጣት የሚጥር በሚመስል መልኩ መትጋቱን ተያያዘው።

     🌞 በነጋታው ጠዋት የወጣችው ፀሀይ ቀራፂውን በውብ ሁኔታ ከእንጨቱ የሠራትን ውብ ወፍ እንዳቀፈ ተኝቶ አገኘችው ። ቀራፂው ከአድካሚው ጥረትና ትጋት በኋላ ወፏን " የማይረባ እንጨት" ከመሆን ነፃ አውጥቶአታል። በኋላ ላይ ቀራፂው ይህቺን ወፍ የቤቱ በረንዳ ላይ አስቀምጦ ረሳት።

    ከሳምንት በኃላ ባለፀጋው ለጉብኝት መጥቶ ወፏን በረንዳ ላይ እንዳለች ተመለከታት። ወዲያውኑም ሽማግሌውን ቀራፂ በጠየቀውና በፈለገው ዋጋ ወፏን እንዲሸጥለት  ጠየቀው። አናም ባለፀጋው ሠውዬ የተጠየቀውን ዋጋ ደስ እያለው ከፍሎ በእርካታ ስሜት ወፏን ደረቱ ላይ እንዳቀፋት ወደ ቪላው ተመለሠ። ሽማግሌው ቀራፂ በደሳሳ ጎጆው ደጃፍ ተቀምጦ ብሩን እየቆጠረ  "አይረቤነት እንደ ተመልካቹ ነው ። አንዳንዶች ይመለከታሉ ፣ ሌሎች ግን ያስተውላሉ" ብሎ አሠበ ።🤠



     ስለዚህ አንድን ነገር ከመመልከት አልፋችሁ ማስተዋልን ተካኑ ። የዛሬ መልእክታችን ነው ። ሠናይ ጊዜ.......
https://t.me/Mindsetempiree
ሕይወት ምንድን ናት ዓላማዋስ ? ለእኔ የሕይወት ዘመን ጥያቄዬ ነው፡፡ ግን ህልውና ተችሮን ስንፈጠር ከሆነ ህይወት ምንጭ ስንፈልቅ፤ መኖር በሚባለው የህይወት ጅርት እየፈሰስን በመስኩ እየተገማሸርን፤ ቁልቁለቱን እየተዳፋን፤ አቀበቱን እንጠማዘዛለን፡፡

ሕይወት እና መንገድ

መሄድ መሄድ መሄድ. . . .

መውጣት እና መውረድ. . .

በቁልቁለቱ ስንዳፋ ህይወትንና ዓላማዋን እንደ እንደቁልቁለቱ እየበየንን፤ከመስኩ ስናርፍም ብያኔያችንን እያሳረፍን፡፤ አቀበት ገጥሞ መንገድ ሲያስለቅቀን የህይወትንም ብያኔ እንዲሁ  እየለቀቅን እየቀየርን የመኖርን ጅረት ዞረን እንቅላለን፡፡ ከምንጭ ወጥተን በመኖር ጅረት ፈሰን ከማብቂያው ምንጭ መልሰን እንጠልቃለን ፡፡ በየመሃሉም የምንሆነውን እንሆናለን፡፡ ህይወት ሁኔታዊ በዚያው መጠን ቅፅበታዊ፡፡ ያለፈውን ትዝታ አድርገን የመጪውን ተስፋ ሰንቀን በዚያ ተስፋ ግን ቅፅበትን እንኖራለን፡፡ የገባኝ ህይወት ይህ ነው፡፡ ቅፅበት፡፡ ቅፅበቷን የምናልፍበትና የምናሳልፍበት፡፡ ከህይወት ምንነት በላይ ትርጉም፤ ከህይወት ዓላማም በላይ ግብ ነው፡፡ ያችን ቅፅበት በፍቅር፡፡ የህይወት ትርጉም ፍቅርና ቅፅበት ሆነ ማለት ነው፡፡

ህይወት ቅፅበት ቢሆንም በቅፅበቷ የማንገፋው ጋራ የለም፡፡ እናም ታዲያ ለህይወት ዳገት ምርኩዝ፣ ለተዳፋቱ ድጋፍ. . . አቀበት ያለ ምርኩዝ መግፋት ምንኛ ፈታኝ ነው? ያለ ድጋፍስ ቁልቁለት ምን ያህል አስቸጋሪ ነው?

በመውጣት መውረዱ የህይወት ምጥጥኖሽ፣ሚዛን ልኬቶች አሁንም የህይወት ቅመሞች፡፡ የህይወትን ዳገት በተሰበረ ቅስም፣ በላሻቀ ሞራል መግፋት አስቸጋሪ ፈታኝ  ባስ ሲልም የመጨረሻዋን ህቅታ የሚጠይቅም ይሆናል፡፡ ለዚህ ግዜ ታዲያ ማለፊያ ድልድይ፣ ማረፊያ መስክ ድጋፍ ምርኩዝ በህይወት የሚያስፈልግን፡፡ የህይወት ቅመም፡፡

ህይወት መልካም ናት፤ ከነግሳንግሷ፡፡ ህይወት ውብምናት ተለዋዋጭ ልይዩ፡፡ በህይወት የተቃራኒ ጎኗ፣ ደስታ፣ ሃሴት ተድላ . . . ለዚህም ታዲያ የይህወት ቅመም. . . ደስታን ለብቻ መግፋት ይቻል ይሆን? አቅፈን የምንስመው፣ ጮኸን የምናስደነግጠው፣ አብስረን የምናፍነከንከው ለደስታችን አድማቂ ቀለም፣ አጣፋጭ ቅመም . . . .ለህይወት፡፡

ሕይወት ልይዩ ናት፡፡ ይህም አንዱ ቅመም፡፡ የህይወት መንገዱ አንድ ፣  መድረሻው አንድ፣  ስሌት ቀመሩም አንድ ቢሆን ኖሮ . . . ሕይወት ማስጠሎ ፡፡ በመኖር ጅረት ስንፈስ በማናውቀውና  በማይገመት ሂደት ዳና እየፈጥርን በተተለመው የህይወት መንገድ ስንፈስ ካሰብነው ስንደርስ ግብ የመታን የህይወትን ትግል ያሸነፍን ሲመስለን እንደገና አዲስ. . .  አዲስ. . .  አዲስ. . . ህይወትን ክለሳ፡፡ የህይወት ቅመም. . . .

ዑድቱን ጠብቆ . . . ሕይወት ይቀጥላል በምህዋሩ ይዞራል ቅመማት ባይኖሩስ ምንኛ ያስጠላል. . .
https://t.me/Mindsetempiree
- - " #የህይወት_ህግጋቶች " - -

ከመናገርህ በፊት | ☞ አስብ ★
ከመፈረምህ በፊት | ☞ አንብብ
ከማስተማርህ በፊት | ☞ ተማር ★
ከመምከርህ በፊት | ☞ ተግብር ★
ከመቁረጥህ በፊት| ☞ ለካ ★
ከማጉደልህ በፊት | ☞ ተካ ★
ከመዋጥህ በፊት | ☞ አላምጥ ★
ከመገንዘብህ በፊት | ☞ አድምጥ ★
ከማመንህ በፊት | ☞ አረጋግጥ ★
ከመረከብህ በፊት | ☞ ቁጠር ★
ከመወሰንህ በፊት | ☞ መርምር ★
ከመስራትህ በፊት | ☞ አቅድ ★
ከመተኮስህ በፊት | ☞ አልም ★
ከመተቸትህ በፊት | ☞ አጣራ ★
ከመብላትህ በፊት | ☞ ስራ ★
ከመሞትህ በፊት | ☞ ነሰሃ ግባ ★
ከመሄድህ በፊት | ☞ተስፋ ሰንቅ ★
ስትወያይ-----☞ ሁን አስተዋይ ★
ስትናደድ---- ☞ ቶሎ ብረድ ★
ስትናገር---- ☞ በቁምነገር ★
ስትቸገር---- ☞ መላ ፍጠር ★
ስትቀመጥ---- ☞ ቦታ ምረጥ ★
ስትወስን---- ☞ ቆራጥ ሁን !!
☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆
ለላቀ ህይወት !
https://t.me/Mindsetempiree
❤1
ሠላም ውድ የMindset-Empire ቤተሠቦች ዛሬ በእሁድ ማለዳ የአንድ ፈላስፋ ግለ ታሪክ እና የፍልስፍና አመለካከቱን አቀርብላችሁዋለው።🤠

   ጆርጅ በርክሌይ (1685-1753) አየርላንዳዊ ነው፤ ፈላስፋም ነው፤ ቄስም ነው፤ ከቄስም ኤጲስ ቆጶስነት ያገኘ ቄስ።          የበርክሌይ ፍልስፍና አስገራሚ ያደረገው በምድር በሠማይ የሚገኙ ነገሮች በሙሉ ቁሳዊ ህልውና የላቸውም ማለቱ ነው። በተለምዶ እንደምንረዳው ቁስ አካል (matter) ማለት ከሠው ሕሊና፣ ሀሳብ፣ ፈቃድ፣ ውሳኔ እና ህልውና ውጪ በራሱ (ከሠው) ነፃ ሆኖ መኖር የሚችል ማለት ነው።  ለበርክሌይ ግን ቁስ አካል እሚባል ነገር የለም ከሠው ህሳቤ እና ህውስታ ውጪ (በስሜት ህዋሳቶቻችን ከሚሠማን ስሜት) ውጪ ምንም ነገር የለም። መሬት ብንል ሠማይ፤ እሣት ብንል አተክልቶች፤ ህይወት ያለውም የሌለውም.......መኖር ይኖራል እሡን መካድ አይቻልም.......ነገር ግን ከሠው ህሳቤ ውጪ መኖር አይችልም። ይህን አመለካከት በግልፅ ቋንቋ እንረዳው ካልን ህልውና ያለው በቁስ አካል ውስጥ ሳይሆን በሠው ሀሳብ ውስጥ ነው ። በዚህ መሠረት ዛፍ፣ ተራራ፣ ወንዝ........ስንል ሀሣብ የሆነ ዛፍ ፤ ሀሳብ የሆነ ተራራ ፤ ሀሳብ የሆነ ወንዝ ማለታችን ነው እንጂ ከሠው ሀሳብና ስሜት ውጪ የሚኖር ዛፍ፣ ተራራ እና ወንዝ አሉ ማለታችን አይደለም ይለናል በርክሌይ።
 
በርክሌይ ሲናገር ከእኛ ውጪ የሚኖሩ ነገሮች ይኖራሉ ብለን ለመረዳት የቻልነውን ያህል ጥረት ባደረግን ቁጥር ተመልሠን የምናገኘው የራሣችንን ሀሣብ ነው ። "when we do our utmost to conceive the existence of external bodies we are all the while contemplating our own ideas". ብሎአል።
    መልካም እሁድ ይሁንላችሁ።
https://t.me/Mindsetempiree
#መሮጥክ የመቆምክ ውጤት ነው፡፡
👉መኪና ሰው ከመጫኑ በፊት ይቆማል ከዛ ጭኖ ይሄዳል፡፡
👆ለምን እየሄደ አይጭንም??
👉ምክንያቱም ለመሄድ ያለው አማራጭ መቆም ስለሆነ ካልሆነ ግን ሰው ሊሞት ይችላል፣ መኪናውም ሊጎዳ ይችላል፡፡
✍ስለዚህ በየትኛውም ጊዜ መሮጥ ከፈለክ ቆም ብለክ አላማክን አስብ፡፡ቤተሰብክን ተሸክመክ ይሆናል፣ ብዙ ከአንተ ሚጠብቁ ይኖራሉ፡፡ እናም ወንድሜ ከመሮጥክ በፊት ቁም በአንተ ውስጥ ብዙዎች አሉና፡፡
https://t.me/Mindsetempiree
❤2
ሠላም ሠላም ውድ ቤተሠቦች እንዴት አላችሁ ? ዛሬ በእለተ ሰኞ ማለዳ ስለ ፍርሀት እናወራለን መልካም ቆይታ።

      😱ፍርሀት
  የሠው ልጅ የህይወት ዘመኑ ትልቁ ፍርሀቱ የሚመጣው ባለፈው ህይወቱ በተፈጠሩ ነገሮች አልያም ደግሞ አሁን አየተፈጠሩ ባሉት ነገሮች ሳይሆን ከዚህ ቀጥሎ ምን ይሆን የሚፈጠረው በሚል ሀሣብ ስለሚወጠር ነው። ምክንያቱም ሠው ወደ ትላንቱ ስለማይመለስ ትላንቱን አይፈራውም፤ዛሬውንም የአሁኗን ሠአት ምን እየተፈጠረ እንዳለ በከፊል ስለማያውቅ አይደነግጥም። ነገር ግን ከዚህ በኋላ ስለሚፈጠረው ነገር ምንም ስለማያውቅ ውስጡ በሽብር ይሞላል።😱
    ለዚህ ነው አብዛኛዎቹ ሠዎች የነገን ባለማወቅ በዛሬው ቀን ላይ ከዛሬም በአሁኗ ሠአት ላይ ውሣኔን ለመወሠን የሚከብዳቸው። ምክንያቱም እንዲ ባደርግ በኋላ እንዲ ቢፈጠርስ? እንዲ ብወስን በኋላ ውጤቱ እንዲ ቢሆንስ? በማለት ውስጣቸውን ያሥጨንቃሉ።😨🤯
  በመሠረቱ ፍርሀት ከሠው ልጆች የሚጠፋ የአካል ቅርፅ አይደለም። ሠው ፍርሀቱን ማሸነፍ ይችላል። ነገር ግን ፍርሀቱን ሲያሸንፍ ቀጣይ ሚመጣው ሌላ ፍርሀት ነው።   ፍርሀትን የማሸነፊያ ብቸኛው መንገድ የፈሩትን ነገር በጥበብ መጋፈጥ ብቻ ነው። 🤗

  መልካም ቀን
https://t.me/Mindsetempiree
#ሰው ማለት ያሰበውን ያንኑ ነው!!
✍የትኛውም አይነት ሁኔታዎች ድርጊት ከመሆናቸው በፊት በሀሳብ ወደ አዕምሮ ውስጥ ይገባል፡ ዋናው ነገር ግን ሀሳቡን የምንረዳበት መንገድ ነው🤔.......መልካም ያሰበ መልካም ነው፣ መጥፎ ያሰበ መጥፎ ነው፡፡ ምክንያቱም "ሰው ማለት ያሰበውን ስለሆነ" በምድር ላይ ያሉት ነገሮች በሙሉ ሊባል ይችላል አዕምሮ ላይ ነው ሚሰራብን ምክንያቱም ዋናው ነገር አዕምሮ ስለሆነ፡ ስለዚህ አስተሳሰባችንን ሰፋ ማድረግ አለብን፡፡✿ላለማሰብ ምክንያት አያስፈልግም!!!!
👉 ሰው የተባለው ሰው ማሰብ አለበት?ማሰብ የሰውነት ሚዛን ሊሆን ይችላል?
፠ ሰው ሲፈጠር ማሰቢያ እንጂ ሀሳብ አልተሰጠውም፡፡ ማለትም ሀሳብ ሁሉም ቦታ አለ፡፡ ለምሳሌ እናንተ ያሰባችሁትን ሌላ ሰው ሲናገርባችሁ ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት አንተ እሱን ወይም እሱ አንተን ስለሆነ አይደለም፡ ሀሳብ ሁሉም ቦታ ስላለ እንጂ..........................ስለዚህ ሀሳብ በፊትም የነበረ አሁንም ያለ ወደፊትም የሚኖር ነው፡፡ እና እናስብ ምክንያቱም "ሰው ከአንገት በላይ ያለውን ያንኑ ነውና"
https://t.me/Mindsetempiree
ሠላም ውድ የ Mindset-Empire ቤተሰቦች እንዴት ናቹ? እረፍት ፣ ውሎ አሪፊ ነው? ሁሉ ነገር በስኬት ይለፍላቹ🙏
            እስከዛሬ ድረስ እኛ ካለን እውቀት እንደተረዳነው መጠን ስናካፍላቹ ቆይተናል፡፡ እናንተም ተጠቅማቹበት ይሆናል፡፡ እና "ለውጥ የሚመጣው
በአንድ ሰው ንግርት ብቻ ሳይሆን በመላሹም ጭምር ነው"
እናም ፡ ስለ ቻናሉ ሀሳብ ካላቹ ፣
         ፡ ስለ ሂወት ጥያቄ ካላቹ
                       ፠
                      

                       ፠
https://t.me/+g1zJmcSOJnZmYmU0
        👆በዚህ ላይ መናገር ትችላላቹ፡፡


         መልካም ምሽት🙏
😇ትልቁ በሽታ😇

ሠዎች ለምን ብቸኛ መሆን ይፈልጋሉ ?
በብቸኝነትስ ለመኖር የሚያነሣሣቸው ምንድነው ? እውነት ብቸኝነትስ ለሠው ለጆች መልካም ነገር ነውን ?

   ፈጣሪ የሠውን ልጆች ሲፈጥር ወንድ እና ሴት አድርጎ ፈጥሮአል። ይህ የአፈጣጠር ሂደት የመብዛት እና የመባዛትን ህግ የተከተለ ነው።  ታድያ የፈጣሪ ስራን ስንመለከት የሠውን ልጅ ብቸኝነት አምርሮ የሚጠላ መሆኑን ለመረዳት ጊዜ አይወስም።  ሥለዚህ ሠው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም።

😇 ብቸኝነት በጣም ክፉ በሽታ ነው። ምክንያቱም ከአምሳሎቻችን እንድንለይ ስለሚያደርገን ነው። ከአምሣሎቻችን መለየታችን ደግሞ በስተመጨረሻ ወይ ያሣብደናል ወይ ደግሞ ይገድለናል።😱

    ለምሣሌ ያክል የአለም መንግስታት በጣም አደገኛ የተባለ ወንጀለኛን የሚቀጣው  ብቻውን በአንድ ክፍል ውስጥ በማድረግ ነው። ይህ ለአንድ ሠው በጣም ትልቅ ቅጣት ነው፤ በዚህ አይነት ቅጣት የከረሙ ሠዎችን ስንመለከት ብዛት ያላቸው ሠዎች ከእስራቸው ሲፈቱ ያብዳሉ አልያ ደግሞ እራሳቸውን ያጠፋሉ። ይህ የሚሆነው ለረጅም ጊዜ ከሠው ተለይተው ብቻቸውን በማሣለፋቸው ነው። የብቸኝነት ትልቁ በሽታ ጭንቀት እና ድብርት የተባሉ ከፍተኛ የአይምሮ መቃወስ በሽታ ነው። በዚህ በሽታ የሚያዙ ሠዎች ታድያ በአደንዣዥ ዕፅ ፣ በወንጀል እና በተለያዩ ከባድ ሡሶች የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው.........
            ፨ይቀጥላል....
ሠናይ ጊዜ ይሁንላችሁ።
https://t.me/+g1zJmcSOJnZmYmU0
አንዲት ሴት በጣም አስተዋይ ናት፣ ጠንካራ ናት፣ ማንንም ወንድ አትሰማም።ግን አንድ ወንድ ይመጣና በሳምንት ውስጥ አእምሮዋን፣ ልቧንና አካሏን ይቆጣጠራል።

ይሄ ወንድ ሬክ ይባላል።ሴቶች በህይወታቸው የሚጠሉት ነገር ቢኖር "ለብ ያለ ስሜትን"  ነው።አብዛኛው ወንድ ስሜቱን ይደብቃል፣ ይፈራል፣ ወይም በልክ ይወዳል።ሬክ ግን እንደዛ አይደለም። እሱ ልክ እንደ እሳት ነው።ነገር ስራው ሁሉ እብደት ነው።

እወድሻለሁ" ለማለት አይፈራም። ለሴቷ የሚነግራት ነገር በሙሉ ልክ ከፊልም ላይ የተወሰደ ድርሰት ይመስላል። "አንቺ እኮ የህይወቴ ትርጉም ነሽ" ይላታል።ምናልባት ውሸት ሊሆን ይችላል፣ ግን እውነት እስኪመስል ድረስ በስሜት ይናገረዋል።

አይን አይኗን ያያል። ወደ እሷ ሲሄድ ግድግዳ አፍርሶ ነው። ይህ "የማይገታ ፍላጎት" ሴቷን ያስደንቃታል።ቆንጆ ባይሆን እንኳን  አለመውደድ አትችልም።"ዋው! ይሄ ወንድ እኮ ለእኔ ብሎ አበደ!" ብላ ታስባለች።

ሪኮች "ሴት አዳኝ" ተብለው ይታወቃሉ።የሚገርመው ግን ይህ ስም ሴቶችን ከእነሱ አያርቅም፤ሴቶቹ የበለጠ ይስባቸዋል! ምክንያቱም አንደኛ "ምን ቢኖረው ነው ሴቶች የሚወዱት?" ብለው ለማወቅ ይጓጓሉ። ሁለተኛ "እኔ ቀይረዋለሁ" ብለው ይፎካከራሉ።ከዛም በሪኮች የፍቅር ወጥመድ ውስጥ ይገባሉ።ግን ማወቅ ያለባችሁ ነገር ሪኮች የእውነት ካፈቀሩ ለፍቅራቸው ሟች ናቸው።

📚ርዕስ፦የመማረክ ጥበብ(The Art of Seduction)
🗣ደራሲ፦ሮበርት ግሪን

ትርጉም https://t.me/+g1zJmcSOJnZmYmU0
“መፈወስ የሚጀምረው መደበቅን ትተህ ታማኝነትን በመረጥክ ቅጽበት ነው።
ብዙ ሰዎች በሃፍረት እና በጥፋተኝነት ስሜት ይነሳሉ፣ ግን ሃፍረት ማንንም ፈውሶ አያውቅም።
ጠዋትህን የምትጀምረው በመቃብር ውስጥ ሳይሆን በጦርነት ውስጥ እንዳለህ በማስታወስ ነው።
ትግልህ አያሳንሰህም — ያዘጋጃል እንጂ።
ወደ ዛሬው ቀን ግልጽነት፣ ዓላማ እና በልብህ ውስጥ ንጹህ ‘ዳግም ጅምር’ ይዘህ ግባ።”
https://t.me/+g1zJmcSOJnZmYmU0
😇ትልቁ በሽታ😇 ክፍል 2

......ብቸኝነት በራሱ መጥፎ አይደለም ።ከባዱ ነገር በህይወታችን ላይ በምንወስናቸው የትኛዎቹም ውሳኔዎች ላይ አመዛዝነን እንዳናይ እና ሀሳብ  ሠጪ ወገን ስለሚያሳጣን ነው።

   ሠዎች በተለይም ወጣቶች ብቸኝነትን የሚመርጡበት ዋናው ምክንያት በራስ መተማመን ማጣት(self confidence) ጉድለት ነው። ለምሳሌ ያክል በሠው ዘንድ ታማኝኘትን ማጣት ፣ ሠውን ማስደሠት አለመቻል እና አነርሡም በሠዎች መደሠት ሲያቅታቸው ፣ ሌላው ደግሞ የሚስጥር አለመጠበቅ ናቸው። ይህ ሁሉ ታድያ በአንድ ቃል ሲጠቃለልኀ በራስ መተማመን አለመቻል በመባል ይጠራል። ብቸኝነትን የሚመርጡ ሠዎች ሀላፊነትን መሸከም እማይወዱ እና የሚሠጣቸውን ሀላፊነት መወጣት የማይችሉ አድርገው እራሳቸውን የሚያስቡ  ናቸው😔😔😔😔 ። ስለዚህ ብቸኛ በመሆን የራሣቸውን አለም በመፍጠር ደሥተኛ መሆን እንደሚችሉ አድርገው ያስባሉ። ነገር ግን ይህ ከእውነታ የራቀና ስህተት የሆነ አስተሳሰብ ነዉ ። ብቸኛ በመሆን ደስታን ወደራሳችን መጥራት አንችልም። ለጊዜው ደስተኛ የሆንን ሊመስለን ይችላል ።ነገር ግን ዘላቂ አይደለም።  
ፈለግንም አልፈለግንም ወደድንም አልወደድንም በአንድም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ኑሮአችን ከሠው ጋር ነው🤷‍♂። ሥለዚህ ከሠው ከመሸሽ ይልቅ እንዴት ይበልጥ መቅረብ እንደምንችል ማሠቡ የተሻለ ነው።
     ሀገራችን ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ያዳበረችው አንድ ባህል አላት። እርሡም " ህብረት አብሮነት" ይባላል። በህብረት መብላት ፣ በህብረት መሥራት ፣ በህብረት ማዘን ፣ በህብረት መደሠት እና ሌላም ሌላም። ይህ የአንድነት መኖር ደግሞ እራስን ብቻ ሳይሆን ሀገርንም እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል ካለፉት አባቶቻችን ታሪክ መማር ይቻላል። ለዚህ ነው የሀገሬ ሠው "ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሀኒቱ "  ብለው የተረቱት.........
       ይቀጥላል....
መልካም እለተ እሮብ ይሁንልን እወዳችሁዋለሁ።😘😘😘
https://t.me/+g1zJmcSOJnZmYmU0