Mind Morning/ ማይንድ ሞርኒንግ
6.62K subscribers
1.33K photos
15 videos
9 files
509 links
-ስልጠናዎቹ ህይወት ለዋጭ ናቸው!
-የሬድዮ ፕሮግራሙ ራስን አመልካች ነው!
-ጥናቶቹ ችግር ፈቺ ናቸው!
-ምክክሮቹ አሃ የሚያስብሉ ናቸው!
-ዓላማው ሰዎች የራሳቸውን ታላቅነትና ያላዩትን አቅማቸውን እንዲያዩት ማስቻል ነው!
ቤተሰብ ይሁኑ!
@mindmorning
Download Telegram
#ልጅዎ #በቂ እና #ጤናማ #የእንቅልፍ ጊዜ እንዲኖረው/እንዲኖራት የሚረዱ አስር ዘዴዎች(እድሜያቸው ከ 1 አመት በላይ ለሆኑ ህፃናት)
🔸🔸🔸🔸🔹🔹🔹🔹🔹🔸🔸🔸🔸🔸🔸

👉 ህፃናት በቂ እንቅልፍ ካላገኙ የአይምሮ እና የአካል ብቃታቸው ሊቀንስ ይቺላል:: ለህፃናት በቂ እንቅልፍ ሰአት የሚባለዉ እንደየ እድሜያቸው ይለያያል:: በዝርዝር እንመልከተው

✔️ እድሜያቸው 1-2 አመት : 11-14 ሰአት ቢተኙ ይመከራል
✔️ እድሜያቸው 3-5 አመት : 10-13 ሰአት
✔️እድሜያቸው 6-12 አመት : 8- 12 ሰአት
✔️ ከ 7 አመት በላይ : 8 ሰአት

❤️ ስለዚህ ህፃናት በቂ እንቅልፍ እንዲያገኙ ወይም እንዲተኙ ምን ማድረግ አለብን❓️

👉 1. ከ እንቅልፍ በፊት ሰውነትን የሚያዝናኑ የመኝታ ጊዜ ተግባራትን(Bed time routines) ያስለምዱ ለምሳሌ

🔹 መፅሐፍ ማንበብ
🔹 ለብ ባለ ዉሃ መታጠብ
🔹 ለስ ለስ ያለ መዝሙር/ዜማ መስማት

👉 2. በየቀኑ የሚተኙበትን ሰዓት እና ጠዋት ከእንቅልፍ የሚነቁበት ሰአት ተመሳሳይ ያድርጉ

🔹 ህፃናት ከሰኞ እስከ እሁድ ትምህርት ቤት ብሄዱም ባይሄዱም ሰዓታቸው ተመሳሳይ መሆን ይኖርበታል::
🔹 ይህ መንገድ የህፃናት አይምሮ ተመሳሳይ ተፈጥሯዊ ሰአት (Biologic clock) እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል::

👉 3. ከ መኝታ ሰአት በፊት የጸጥታ ጊዜን ይመድቡ ከፍተኛ ድምፅ ያላቸው አስፈሪ ፊልሞችን ወይም ጌሞችን ያስወግዱ

🛑 መኝታ ክፍል ዉስጥ ፀጥታ እና ቀነስ ያለ ብርሃንን ይጠቀሙ

👉 4. የመኝታ ክፍል ዉስጥ ቴሌቭዝን ላፕቶፕ እና ሞባይል አለማሰገባት እና አለመጠቀም
✔️ ማንኛዉም screen ያላቸዉ ነገሮች ለምሳሌ
✔️ ሞባይል ቴሌቭዝን ላፕቶፕ ሰማያዊ ብርሃንን ስለሚለቁ ጭንቅላታችን ዉስጥ የሚመረተውን ሜላቶኒን የሚባለው የእንቅልፍ አምጭ ሆርሞንን ይቀንሳሉ::
✔️ በዝህም ምክንያት ልጆዎ በቂ እንክልፍ ላያገኝ ይችላል

👉 5. #ልጆዎ ከ መተኛቱ በፊት በበቂ መጠን ምግብ እንደወሰደ ያረጋግጡ
🔹 በጣም መጥገብም ወይም መራብም የለበትም

👉 6. የሚያነቃቁ ምግቦችን እና መጠጦችን(ካፌን ያላቸው)ከ ሰአትን ጀምሮ ማታ ማታ አይስጡ ::

🔘 ለምሳሌ: ቡና ፣ሻይ፣ ቸኮሌት ኮካ እና የመሳሰሉት ☕️

👉 7. ልጆዎ ቀን ቀን መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(በቀላል ጨዋታዎች) እንዲሰራ/እንድትሰራ ያድርጉ

👉 8. ከጠዋት ጀምሮ ልጆዎ ተፈጥሯዊ የሆነውን የ ፀሐይ ብርሃን እንዲያገኙ ያድርጉ::

❤️ የፀሐይ ብርሃን ለሰውነታችን ወሳኝ የሆነውን ቪታሚን ዲ ከመስጠቱ ተጨማሪ ህፃናት ቀን ቀን ንቁ ፈጣን ሆነው እንዲውሉ እና ማታ ደሞ እንቅልፋቸው በ ቀላሉ እንዲመጣ ያረጋል

9. የሕፃን መኝታ ክፍል በጣም ሞቃት በጣም ቀዝቃዛ መሆን የለበትም
🔺 ምቹ የሚባለው የመኝታ ክፍል የሙቀት መጠን 22-24 ሴልሽየስ ነው

10. ልጆዎ መኝታ ክፍሉ/ክፍሏ ዉስጥ ደህንነት እንዲሰማው እንዳይፈራ እና እንዳይጨነቅ ያድርጉ

#አስተውሉ ❗️መኝታ ክፍልን ለቅጣት(time out) አይጠቀሙ❗️

❤️ ጠቃሚ መረጃ ነው ብለው ካሰቡ በቅንነት #share ያድርጉት::❤️