Minber TV
44.3K subscribers
15.8K photos
2.49K videos
37 files
8.25K links
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
ይከታተሉ፣ ለወዳጅዎ ያጋሩ!

📡 ሳተላይት ፡ EthioSAT 11545/45000/H
📱 የሶሻል ሚድያ አድራሻዎቻችን ፡ https://linktr.ee/minbertv
Download Telegram
በቁም ነገርና በጥበብ ሥራዎች 🎨 ደምቆ በሚከወነው ተወዳጁ የምርኩዝ መድረክ ፤ በሥነ ግጥም ውድድር ተሳትፈው 🏃‍♂️ በማሸነፍ የዑምራ ጉዞ ተሸላሚ ይሁኑ! 🕋

የህልም የትጋትና ስኬትን ትስስር እያጎላ 33 ዙሮችን በድምቀት ሲከናወን የቆየው ተወዳጁ የምርኩዝ መድረካችን፤ የፍጥረታቱን ዓይነታ♥️፣ የዓለሙን መድኅንና ❤️‍🩹 የከውኑን ሞገስ 💫 አብዝቶ በሚያወሳበትና፤ በቅርቡ በሚያዘጋጀው 34ኛው መድረኩ ላይ "በሱናዎ ላይ…" በሚል ዐቢይ ርዕስ ልዩ የሥነ ግጥም ውድድር አዘጋጅቷል፡፡

በመሆኑም ተወዳዳሪዎች በግጥም ሥራዎቻቸው ላይ ✍️ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱናዎች የቃላት ወይም የልማድ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆኑ፤ ለአንድ ሙስሊም ሙሉ የህይወቱ መመሪያና መስታወት መሆናቸውን፣ በሱናቸው ላይ መፅናት ደግሞ የእውነተኛ ስኬትና የልብ እርጋታ መሆኑን መግለፅና፤ ያለ እርሳቸው (ሰ.ዐ.ወ) ፈለግ እስልምናን በትክክል መረዳትና መተግበር የማይቻል መሆኑን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡
በውድድሩ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ገጣሚያን፤ ከታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

1️⃣  ተወዳዳሪዎች ለውድድር የሚያቀርቡት የግጥም ድርሰት ባለቤቶች እነርሱ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ©️

2️⃣  ለውድድር የሚቀርበው የግጥም ድርሰት በሌሎች ማናቸውም ዓይነት መድረኮች፤ እንዲሁም በየትኞቹም ዓይነት የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በምስልም ኾነ በድምፅ ያልቀረበ መሆን ይኖርበታል። 🗞

3️⃣  ለውድድር የሚቀርበው የግጥም ስንኝ ብዛት ከሃምሳ (5️⃣0️⃣) ያልበለጠና በኮምፒዩተር የተተየበ 💻 መሆን ይኖርበታል።

4️⃣  ተወዳዳሪዎች የግጥም ሥራዎቻቸውን ከሐምሌ 14/ 2018  እስከ ሐምሌ 22/ 2018 ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በሚንበር ቲቪ የቴሌግራም አድራሻ @minbertv1 📬 ብቻ መላክ ይኖርባቸዋል።

5️⃣  የውድድሩ ተሳታፊዎች አዘጋጁ አካል የሚያወጣቸውን ደንቦች እና መመሪያዎች ⚠️ እንደዚሁም የዳኞችን ውሳኔዎች አክብረው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

6️⃣  ደንብና ሁኔታዎች ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል። 🤝

በዚህ ታላቅ ዝግጅት ላይ፤ እንደ ቀደሙት ሁለት ዙሮች ሁሉ ዘንድሮም የሥነ ፅሁፍ ተሰጥዖና ብቃት ያላቸውን ተወዳዳሪዎች በማሳተፍ በየደረጃው ለሚያሸንፉ ተወዳዳሪዎች ሽልማት የምናበረክት ሲሆን 🏆፤ በዳኞችና በታዳሚዎች ድምር ድምፅ :
🥇 አንደኛ ደረጃን ለሚያገኘው ተወዳዳሪ የዑምራ ጉዞ🕋
🥈 ሁለተኛ ደረጃን ለሚያገኘው ተወዳዳሪ የብር ሃምሳ ሺህ ሽልማትና፤ 💰
🥉 ለሶስተኛ ደረጃ አሸናፊ የብር ሰላሳ ሺህ ስጦታ የሚበረከት ይሆናል፡፡ 💰

🌴 ምርኩዝ 34
8️⃣ የከውኑ ሞገስ 8
✍️  በሱናዎ ላይ ...
💭 ህልም 🏃‍♂️ትጋት 🎯ስኬት
🌄 ምርኩዝ!!
13👍2
የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አዲስ ፕሬዝዳንት ተሾመለት

ለዝርዝሩ፦ https://t.me/minberkheber/4955
👍6
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የወረቀት አመራረት…

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/uroddyZmIOc 🔗

#መወዳ_መዝናኛ #መወዳ_ኦንላይን

★ ★ ★
Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #MinberTV
👍6
📌 ምዝገባ ሊጠናቀቅ ነው!

ከቤተሰብ በላይ ይሁኑ! — የበጎ ፈቃደኞች ጥሪ!

ሚንበር ቲቪ ተወዳጅ መልዕክቶቹንና ስራዎቹን ለተመልካቾች ተደራሽ ለማድረግ ከሳተላይት ስርጭት በተጨማሪ በዲጂታል ሚዲያ አማራጮች በርካታ ተከታዮችን ማፍራት ችሏል። አሁን ደግሞ ከተከታታዮቻችን መካከል በዲጂታል ሚዲያዎቻችን ላይ በንቃት የሚሳተፉ ወዳጆቻችንን የዚህ ትልቅ ጉዞ አካል እንዲሆኑ ልንጋብዛቸው ዝግጅታችንን ጨርሰናል።

የሚንበር ቲቪ የዲጂታል ፕላትፎርሞችን በበጎ ፈቃደኝነት በማገዝ አብራችሁን ለመስራት ለምትፈልጉ ሁሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የምንፈልጋቸው ክፍት የክህሎት ዘርፎች፦

👥 የገጽ አስተዳደር እና ሞደሬተር (Admin & Moderator)

✍️ የይዘት ኤዲተር እና ጸሐፊ (Content Editor & Writer)

🎨 ግራፊክስ ዲዛይነር እና ቪዲዮ ኤዲተር

📈 የዲጂታል ማርኬቲንግ እና ስርጭት ስራዎች

እንዴት ማመልከት ይቻላል?
የዚህ የበጎ ፈቃደኞች ስብስብ አባል ለመሆን እና ዝርዝር መስፈርቶቹን ለማየት፣ ከታች ያለውን የጉግል ፎርም ሊንክ በመጫን እስከ ሐምሌ 23 ምዝገባ ያጠናቁ፦
🔗 [https://forms.gle/6GZQkVdASNuggsLd8]

*ማስታወሻ*፡ ቅጹን ለሞሉ እና የመጀመሪያውን ማጣሪያ ለሚያልፉ አመልካቾች ብቻ በቴሌግራም አድራሻቸው @minbertv1 በኩል ምላሽ የምንሰጥ ይሆናል።

#HappilyVolunteer #በጎፈቃድበደስታ #MinDigital #MinberTV
15
ወደ ደቡብ አፍሪካ አደገኛ ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪው አድነው ባሻው ውዳሞ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋለ

ለዝርዝሩ፦ https://t.me/minberkheber/4961
9
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሙስሊም ዋነኛ የህይወት ግብ ምንድን ነው?

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/nBoLgYl9aV0 🔗

#ሚንበሩል_ዒልም #ሐቂቀቱ_ተውሒድ

★ ★ ★
Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #MinberTV
2👍2
የዳንጎቴ ወራሾች ባለጠጋው በሸሪዓ የውርስ ሕግ መሠረት በተዘጋጀ ሠነድ አንድ ሦስተኛውን ለበጎ አድራጎት ለመስጠት ያስቀመጡትን እቅድ ደገፉ

ለዝርዝሩ፦ https://t.me/minberkheber/4963
😍126👏5
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለሐጅ ጉዞ መሳካት አስተዋጽዖ አድርገዋል ላላቸው አካላት የዕውቅናና ምሥጋና መርሐ ግብር አካሄደ

ለዝርዝሩ👉https://t.me/minberkheber/4972?single
3👍2
ዛሬም በተወዳጁ የኸሚስ ምሽት ፕሮግራማችን ከቀደመው ሳምንት ያሳደርነውን ሃሳብና በጅሕልና የሚተገበርን የዒባዳ ሥራ አሳዛኝ ፍፃሜ ከአዳዲስ ጉዳዮች ጋር ይዘን በሰዓታችን እንቀርባለን።
የጉዞ ማስታወሻቸውን በረጋ አንደበት ሲያጋሩን የቆዩት እንግዳችን ኢማም ሐጅ አብዱልሐዲ ሸይኽ አህመድ ደግሞ ከረጅም ዓመታት መለያየት በኋላ ከወላጅ እናታቸው ጋር ለመገናኘት የነበራቸው ጉጉት በምን መልኩ ፍፃሜውን እንዳገኘ እያወጉንና፤ በወራቤ ከተማ አመሰራረትና በተለያዩ የኸይር ተግባራት ላይ የነበራቸውን ደማቅ ተሳትፎ እያስታወሱን ከኛ ጋር ይቆያሉ።

ለይሉ ጁምዓ ነው!
ፕሮግራሙ ደግሞ ተወዳጁ ኸሚስ ምሽት!! እንደሁልጊዜውም በዚክርና በሰለዋት ድምቅ ያለ ለይል ይሁንላችሁ።
ምሽት ከ02:30 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን!

#ኸሚስ_ምሽት #ለይሉ_ጁምዓ_ነው
#የሸይኻችን_ሰዓት #ከመዲና_ሰማይ_ስር
#ሸይኻችን #ሐጂ_አብዱልሃዲ
★ ★ ★
Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ!
9👍2