Minber TV
40.4K subscribers
5.27K photos
265 videos
17 files
4.15K links
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!

ይከታተሉ፣ ለወዳጅዎ ያጋሩ!

#ሚንበር_ቲቪን ለማግኘት

📡 በኢትዮሳት ይከታተሉ:– 👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 30000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★
Download Telegram
🎊🎊አዲስ ነገር ከብሩህ ልጆች🎉🎉
ጥራት ምቾትና ውበትን የተጎናፀፉ ሂጃቢ የተሰኘ የልጆች ሂጃብ ቀርቦላችሗል!
🛍🛍🛍
📌 ከ 8 በላይ የከለር አማራጮች የተዘጋጀ።
📌 ለዩኒፎርም መጠቀም የሚችሉት!
📌 ውብ በሆነ ፓኬጅ የተዘጋጀ!
📌 በአስተማማኝ ጥራት ጥንቅቅ ተደርጎ የተመረተ
📌 ለልጆች ምርጥ ስጦታ
⛳️አድራሻ ⛳️
ቤተል AJ ሞል
እንቁላል ፋብሪካ ፓዌ ህንፃ
በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ለማከፋፈል 📞📞0903389999 ይደውሉ።
🎁🎁🎁
በተጨማሪም የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ:–https://t.me/bruh_ljoch_toys
#ብሩህ_ልጆች
#የቁርአን_ተፍሲር
#በሐረሪ_ቋንቋ

ዛሬ ምሽት 01:30 በሚንበር ቲቪ!
ዕለተ ረቡዕ ግንቦት 23 | 2015

የማህበራዊ ድህረ ገጽ አማራጮቻችንን
ይወዳጁ ለወዳጅም ያጋሩ። 👇

YouTube 👉
http://youtube.com/@minbertv1

Facebook👉
https://www.facebook.com/minbertv/

Telegram👉
https://t.me/minbertv

Website 👉
https://www.minbertv.com/

Tiktok 👉
https://vm.tiktok.com/ZMNq6UnLm/

#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
የእስልምና አምስተኛ ማዕዘን የሆነው ሐጅ መከወኛ ጊዜ ላይ እየተቃረብን እንገኛለን። በዚህ ወቅት ስለ ሐጅ አፈፃፀም መወያየትና መማማር ተገቢ ይኾናል። ይህንን ዐቢይ ጉዳይ እያነሳሳ የሚቆየውና የሐጅን አጠቃላይ ሥርዓት የምንቃኝበት "ኪታቡል ሐጅ"  ፕሮግራማችን "ተልቢያ ላይ ሴቶች ድምጻቸውን ማጉላት ይችላሉን?" የሚሉ የጥያቄዎችና ምላሻቸው ጋር በተወዳጁ ሸይኽ አህመድ አወሉ ተዘጋጅቶ ምሽት ከ02:30 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይቀርብላችኋል።

ዕለተ ረቡዕ ግንቦት 23 | 2015

★★★★★
📡 የሚንበር ቲቪ ስርጭት በትዮሳት
ለመከታተል:– 👇
ፍሪኩዌንሲ:- 11545
ሲምቦልሬት:- 30000
ፖላራይዜሽን:- ሆሪዞንታል
★★★★★!
ሐሙስ ምሽት በሚንበር ቲቪ የቴሌግራም ቻናል የሚቀርቡ አሸላሚ ጥያቄዎቻችን 25ኛ ዙር ላይ ደርሰዋል! ዛሬ በኢትዮዽያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 03:00 ሰዓት ጀምሮ ወደናንተ ይደርሳሉ።

የሚንበር ቲቪ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ይሳተፉ! ይመልሱ! ይሸለሙ! ለወዶጆዎም ያጋሩ ⤴️

ቴሌግራም ሊንክ 👉 https://t.me/minbertv

#ሼር_ይደረግ! 😊
ዛሬ በተወዳጁ ኸሚስ ምሽት ፕሮግራማችን ሸኽ ሙሐመድ ኢብራሒም በሰዓታቸው ለቅርብ ሰዎች እንጂ ጨርሶ መነገር ስለማይኖርባቸው ጉዳዮች እያነሳሱ፣ ኡስታዝ በድር ሁሴን በቢስሚከ ነሕያ ዝግጅቱ ምሉዕ ሰው የመኾንን ምስጢራት እያጋራን የሚቆይ ሲኾን በመዲና ሠማይ ሥር የምንቆየው ደግሞ በርካቶችን በነሺዳ ሥራዎቻቸው የመዲናን ናፍቆት ሲዘሩ ከቆዩትና በቅርቡ ጦይባ ደርሰው ከተመለሱት ሙንሺድ ተውፊቅ ዩሱፍና ሙንሺድ ኢምራን ጣሂር ጋር ይሆናል።

እርስዎም በዱዐ፣ በሶለዋትና በእስቲግፋር ምሽቱን ከእኛ ጋር
እንዲያሳልፉ ተጋብዘዋል።

#ለይሉ_ጁምዓ_ነው
#ፕሮግራሙ_ደግሞ_ኸሚስ_ምሽት_ነው!

ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 24 | 2015

#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
Minber TV
Photo
ከአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተላለፈ መልእክት

ግንቦት 24, 2015

የከተማችን ህዝበ ሙስሊም የነገን ጁመዐ በሰላም እንዲያሳልፍ የተላለፈ ጥሪ

ህዝበ ሙስሊሙ ከዚህ ቀደም ሀይማኖታዊ መብቱን ለማስከበር  ብሎም በሀገር ደረጃ ለተደረገው የስርአት ለውጥ  ፈር ቀዳጅ በመሆን  ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ቀድሞ የነበረውን አምባገነን ስርአት ለመለወጥ ፊት-አውራሪ በመሆን ታግሏል።

የስረአት ለውጥ ከተስተዋለ ወዲህ በተለይ በጠቅላይ ሚነስትራችን በክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ የሚመራው የሀገራችን መንግስት  ለህዝበ ሙስሊሙ ቀድሞ የነበሩ የሀይማኖት መብት ረገጣዎች እንዲቀንሱ ፣ ህዝባችን ከመንግስት ጋር የነበረው ግንኙነት እንዲሻሻል ፣ ማህበረሰባችን ለሌሎች መጠቀሚያ  እንዳይሆን በማድረግ መንግስታዊ ሀላፊነቱን በመወጣት በመሪ ድርጅቱ ስር  እንዲጠለል አስተዋፆ አበርክቷል።

መንግስትም ህዝበ ሙስሊሙ ሲጠይቃቸው ከነበሩ ጥያቄዎች መካከል ተቋሙን በአዋጅ የማቋቋም  መብት፣ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ፣የእምነት ተቋማት ቦታዎችን በህጋዊ መልኩ የማግኘት መብት በማመቻቸት ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎችን አበርክቷል።

ከላይ በጥቂቱ የተጠቀሱ ፋይዳዎች ለምን ለሙስሊሙ ማህበረሰብ እንደ ዜጋ ተከበረለት ፣ ለምን ተጠቃሚ ሆነ የሚሉ በእምነቱ ላይ የውስጥ ጥላቻ ያነገቡ፣የግል ፍላጎት ያላቸው፣ድብቅ የፖለቲካ አስተሳሰባቸውን ለማሳካት እንዲሁም ሙስሊሙ ማህበረሰብ ተጠቃሚነቱ ከጎላ ፣ሰላሙን ከተጎናፀፈ ማየትን የማይችሉ መስማትን የማይወድ ፣አካላት ሌት ተቀን በመስራት ማህበረሰባችንን ከመንግስት ለመነጠል እየሰሩ ይገኛሉ ።

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት  በሸገር ከተማ (ሲቲ) የመስጅድ ፈረሳ ጋር በተያያዘ ማህበረሰባችን ያቀረበውን ህገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄዎች ማለትም  የመስጅድ ፈረሳው ሙሉ በሙሉ እንዲቆም ፣የፈረሱትም መስጅዶች ወደ ቀድሞው ቦታቸው እንዲመለስ መሪ ድርጅታችን መጅሊስ ዘጠኝ አባላት ያሉት ኮሚቴ በማቋቋም በጉዳዩ ዙሪያ  ውይይት በተለያዩ ደረጃዎች ከሚገኙ የመንግስት አካላት ጋር እያደረገ ይገኛል።

በመሆኑም መንግስትም የፍትህን መጓደል የጥያቄውን አሳሳቢነት፣በሸገር ሲቲ አስተዳደር በውይይት ላይ ያልተመሰረተን አካሄድን ከግንዛቤ በማስገባት ለተከሰተው የመብት ጥሰት ፍትህ የማስፈን ሚናውን በአፋጣኝ እንደሚወጣ  ተስፋ እናደርጋለን።

በመጨረሻም ህዝባችን ኮሚቴው የደረሰበትን እስኪያሳውቀን ድረስ  ውጤቱን በትእግስትና በዱአ እንዲጠባበቅ  ጥሪያችንን እያቀረብን

የነገ የጁመአ ሰላት የከተማችን ሙስሊሞች  በሁሉም መስጅዶች በሰላም ሰግዶ ወደ ቤቱ በሰላም እንዲመለስ መልእክታችንን እያስተላለፍን ፣
በከተማችን የሚገኙ ኢማሞች በሰላምና በትእግስት ዙሪያ የጁመአ ኹጥባ እንዲያደርጉ እናሳስባለን።

መንግስትም ጉዳዩን በፍጥነት እልባት እንዲሰጥ እና ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ከእስር እንዲለቅ አጥብቀን እንጠይቃለን።
#ጥያቄ_25

የአህዛብ ጦርነት ሌላኛው ስሙ ምንድነው?

ይመልሱ! ይሸለሙ! 🎁

ትክክለኛውን መልስ ቀድመው ለመለሱ
ሶስት ተሳታፊዎቻችን ተሸላሚ ይሆናሉ!

🎁 መላሾቻችንም እያንዳንዳቸው ለአንድ ወር የሚቆይ
2GB ኢንተርኔት ፓኬጅ ተሸላሚ ይሆናሉ!

📌 #የጥያቄው_ሕግና_ደንብ 👇

1. መልስ መመለስ የሚቻለው በሚንበር ቲቪ የቴሌግራም ግሩፕ ብቻ ነው!
2. መልሱን ከመመለሶዎ በፊት ጥያቄውን በደንብ ያንብቡ
3. አሸናፊውን የምንለየው ትክክለኛውን መልስ ቀድመው በመለሱ ነው።
4. የመለሱትን መልስ edited ማድረግ አይቻልም።
5. አሸናፊዎቻችን በዚሁ የቴሌግራም ቻናል የምናሳውቅ ይሆናል!
6. የጥያቄውን ትክክለኛ መልስ አያይዘን የምንፖስት ይሆናል!

Telegram link:- 👉 https://t.me/minbertv

#መልካም_ዕድል 🥳

#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክቶ  መግለጫ ሰጥቷል።

የመግለጫው ሙሉ  ቃል  እንደሚከተለው ይሆናል
ግንቦት 24/15

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ አስተዳደር የፈረሱ 19 መስጂዶች አስመልክቶ ግንቦት 19/2015 ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በጉዳዩ ዙሪያ በሰፊው በመወያየት ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡
ይሄውም፡-
1. ከፌ/እ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ፣ከኦሮሚያ እ/ጉ/ከ/ም/ቤት እና ከአዲስ አበባ እ/ጉ/ከ/ም/ቤት የተውጣጡ 9 ዓባላት ያሉት ኮሚቴ ማዋቀሩ የሚታወቅ ነው፤
2. ጠቅላይ ም/ቤታችን በተዋቀረው ኮሚቴ አማካኝነት ከፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በተጠናከረ ሁኔታ እየተወያየን መሆኑን ህዝበ ሙስሊሙ እንዲገነዘብ እናሳውቃለን፡፡ ይህንንም ተከትሎ ማህበረሰባችን የጀመርነው ውይይት እልባት እስከሚያገኝ በትእግስት እንዲጠባበቅ
3. የኦሮሚያ መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያውጠው መግለጫ ፍፁም ሙስሊሙን ማህበረሰብ የማይመጥን ስለሆነ ጠቅላይ ም/ቤታችን የማይቀበለው መሆኑን እንገልፃለን፡፡
4.  በአሁኑ ወቅት የተከሰተውን የመስጂዶች መፍረስ ከላይ በተጠቀሱት ሁኔታዎች ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ባለበት  ሁኔታ አንዳንድ አካላት ጉዳዩን ለፖለቲካ አላማቸው መጠቀሚያ ለማድረግ እየሞከሩ ስለሆነ ህዝበ ሙስሊሙ ይህንን በመገንዘብ አላማቸው በመጥፎ ጎኑ እንዳይጠቀሙበት ሰላሙን አጠናክሮ የጠቅላይ ም/ቤታችንን ውሳኔ እንዲጠባበቅ እየጠየቅን  ከእንደዚህ ዓይነት ችግሮች እራሱንና ተቋሞቹን እንዲከላከል  በተለመደው ጨዋነትና እስላማዊ አደብ በተላበሰ መልኩ ከማንኛውም ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ተቆጥቦ የጠቅላይ ም/ቤቱንና የ9ኙን ኮሚቴ ውጤት እንዲጠባበቅ አንጠይቃለን፡፡
ግንቦት 24/2015
وَقَالَ ٱلرَّسُولُ يَٰرَبِّ إِنَّ قَوۡمِي ٱتَّخَذُواْ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانَ مَهۡجُورٗا
መልክተኛውም «ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ ይህንን ቁርኣን የተተወ
ነገር አድርገው ያዙት» አለ፡፡

(ሱረቱል ፉርቃን 25:30)

አላህ ሆይ የቁርኣን ቤተሰብ አድርገን።
اللهم اجعلنا عائلة من القرآن.🤲

#ጁሙዓ_ሙባረክ! 😇

#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
Channel photo updated
وَلَا تَحْسَبَنَّ الَّذِينَ قُتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَمْوَاتًا ۚ بَلْ أَحْيَاءٌ عِندَ رَبِّهِمْ يُرْزَقُونَ
እነዚያን በአላህ መንገድ የተገደሉትን ሙታን አድርገህ አትገምታቸው፡፡ በእርግጥ እነርሱ እጌታቸው ዘንድ ሕያዋን ናቸው፤ ይመገባሉ፡፡

(ሱረቱል ኢምራን 3:169)

#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!