Minber TV
45K subscribers
14.9K photos
2.25K videos
35 files
7.77K links
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
ይከታተሉ፣ ለወዳጅዎ ያጋሩ!

📡 ሳተላይት ፡ EthioSAT 11545/45000/H
📱 የሶሻል ሚድያ አድራሻዎቻችን ፡ https://linktr.ee/minbertv
Download Telegram
አህለን ረመዳን

መድረኩን ካደመቁት፣ በዜማም በግጥምም ካስዋቡት ፕሮግራሞች አንዱ የነበረውና የረመዳን ቀለማት 7 ምረኩዝ 33 ውበት የሆነው "አህለን ረመዳን" በኦሮምኛ የተዘጋጀው ነሺዳ ነበር።

ነሺዳውን ሐሩን ከድር፣ ሰዓድ አሕመዲን፣ ኡወይስ ኢብራሂም እና ሰሚር ሙሐመድ አቅርበውታል።

💡 ህልም... 🏃‍♂️‍➡️ ትጋት... 🏅ስኬት...
ምርኩዝ!

#ምርኩዝ
#ምርኩዝ33
#የረመዳንቀለማት7
27👍6
የቱርክ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን አዲስ አበባ ገቡ

ለዝርዝሩ👉https://t.me/minberkheber/3215
27
ሐጂ ሙጅተባ በሚንበር ቲቪ የሐሙስ ምሽት ድንቅ ወዳጅ የሚንበር ተቆርቋሪ፣ የምርኩዝ ቀዳሚ ታዳሚ ናቸው። ኸሚስ ምሽት ፕሮግራምን አይተው በማግስቱ አዘጋጆችን ለመዘየር ጁምዓ የሚሰግዱበት መስጅድ በመሄድ የአድናቆት መልዕክታቸውን አቅርበው ለልጆቻችሁ ከረሜላ፣ ማስቲካ አምጥቻለሁ በማለት ሐዲያ ይሰጣሉ።

ምርኩዝ 33 ሻሸመኔ እንደሚዘጋጅ ሲሰሙ ከአንድ ቀን ቀደም ብለው ሻሸመኔ በመገኘት ለፕሮግራሙ ያላቸውን ክብር ለየት ባለ መንገድ አሳይተዋል።

ለዚህም ክብራቸው ከምርኩዝ አዘጋጆችና ከሻሸመኔ ወጣቶች ልዩ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

💡 ህልም... 🏃‍♂️‍➡️ ትጋት... 🏅ስኬት...
ምርኩዝ!

#ምርኩዝ
#ምርኩዝ33
#የረመዳንቀለማት7
👏1613👍2👌1
በወርሐ ረመዳን የኢፍጣር ሰዓት በያላችሁበት እየደረስን፤ እነሆ ድፍን አሥር ዓመት ሞላን!!
ውድ ቤተሰቦቻችን ከኛ ጋር ስለነበራችሁ እጅግ በጣም እናመሰግናለን!!

ዛሬም እንደ ትላንት በአብሮነታችን ደምቀን እንቀጥላለን!!

#አብሮነት_በረመዳን_አሥር_!
#አሥሮቹ_!

#ረመዳን_ሙባረክ
#Remedan_Mubarak
#Minber_TV
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ
37👍5😍5👏1
ሳዑዲ ዐረቢያ የረመዳን ወር ጨረቃ ዛሬ ማክሰኞ አመሻሽ ታይቷል ስትል በይፋ አውጃለች። በመሆኑም የመጀመሪያው የጾም ቀን ነገ ረቡዕ የካቲት 11/2018 ይሆናል። የመጀመርያው የተራዊህ ሰላት ዛሬ ማታ ከዒሻ ሰላት በኋላ ይጀምራል ሲል ኢስላሚክ ኢንፎርሜሽን ዘግቧል፡፡

ሚንበር ቲቪ ለመላው ሙስሊም ማኅበረሰብ መልካም የረመዳን ጾም እንዲሆን ይመኛል!
🥰7547👍24🙏9👏6
እንኳን ለ1447 ኛው (ዓ.ሂ) የረመዷን ወር በሰላም አደረሳችሁ!

ወርሐ ረመዷን በተለያዩ የዒባዳ ተግባራት የምንደምቅበት፣ ኅብረትና ወንድማማችነታችን ከምንግዜውም በላቀ የሚፈካበትና በሁለንተናዊ የሕይወት እንቅስቃሴዎቻችን ስኬትን የምንጎናጸፍበት እንዲኾን ሚንበር ቲቪ ይመኛል።

ረመዳን ሙባረክ!

ሚንበር ቲቪ
ሁለንተናዊ ከፍታ!!!

#ረመዳን_ሙባረክ
#Remedan_Mubarak
#Minber_TV
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ
🥰4424🙏5😍4
ሲቢኢ ኑር “አብሮነት እና በጎነት በረመዳን” በሚል መሪ የረመዳን ንቅናቄ መርኅ ግብር አስጀመረ

ለዝርዝሩ👉https://t.me/minberkheber/3219
24🥰3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዚህ ረመዳን ይህንን እናድርግ…

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/0DBfRcDRyCA 🔗

#ኸሚስ_ምሽት #ቢስሚከ_ነሕያ

★ ★ ★
Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #MinberTV
18👍11🙏1
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ!

እንኳን ለ1447 ዓ.ሂ የረመዳን ወር በሰላም አደረሰን!

የምንናፍቀው ረመዳን መጥቶልናል፤ አልሃምዱሊላህ! በሕይወት ለመታደስ ከረመዳን የተሻለ አጋጣሚ አይኖርም። ወሩ ለሁላችንም በአላህ (ሱ.ወ) ምሕረት የምንታደስበት ያድርግልን። ረመዳን በመንፈሣዊነት እንደ አዲስ የመወለድና የአዲስ ማንነት ጅማሮም ነው፡፡ ሁላችንም በአላህ (ሱ.ወ) መልካም ፍቃድ እንደ አዲስ የምንወለድበት እንዲሆንም እመኛለሁ፡፡ ይህ መልካም ምኞት የ“ሚንበር ቲቪ” ጭምር ነው፡፡

“ሚንበር ቲቪ” እንደተለመደው በረመዳንን ወር “በአብሮነት” ከተመልካቾች ጋር አብሮ ይዘልቃል፡፡ የዘንድሮ ቆይታችን ዐሥረኛው ነው፡፡ ስለዚህ ለእኛ ልዩ ትርጉም አለው፡፡ ያለፉትን ዓመታት አብረውን የዘለቁ ተመልካቾች፤ ዘንድሮም አብረውን እንደሚጓዙ በመተማመን ወሩን የሚመስሉ መሰናዶዎችን አጠናቀናል፡፡ ቀሪው መደተመልካቾች መድረስ ነው፡፡ አብረን እንድንቆይ በአክብሮት እጋብዛለሁ!

በድጋሚ መልካም ረመዳን ይሁንልን!

አዩብ አደም
የሚንበር መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ

ሚንበር ቲቪ
ሁለንተናዊ ከፍታ!!!

#ረመዳን_ሙባረክ
#Remedan_Mubarak
#Minber_TV
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ
71🥰12👍7🙏1
#በረመዳን ሳዑዲ ዐረቢያ የረመዳን አዲስ ጨረቃ መታየቱን ካሳወቀች በኋላ ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 10/2018 ምሽት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢ በሚገኙ መስጂዶች የመጀመርያው የተራዊህ ሰላት ተሰግዷል። እንደ ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ ዐረቢያ ሁሉ ኳታር፣ ዩናይትድ  ዐረብ ኤምሬትስ፣ ባሕሬን፣ ፍልስጤም፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲም በነገው እለት ጾም እንደሚጀምሩ አሳውቀዋል። ኢራቅም እንዲሁ ጾም የምትጀምረው ነገ ረቡዕ ነው።

በአንጻሩ በጆርዳን፣ ሶሪያ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ፓኪስታን፣ ኢራን፣ ቱኒዝያ እና በማሌዥያ ጾም የሚጀመረው ሐሙስ ይሆናል። ቱርክ፣ ኦማን፣ ሲንጋፖር እና አውስትራሊያም ሐሙስ ከሚጀምሩት መካከል ተካተዋል። (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #MinberTV
30👍8
#በረመዳን ዛሬ በመስጂደል ሐረም የመጀመርያው የተራዊህ ሰላት አራት ረከዓ የተመራው በሸይኽ በድር ቢን ሙሐመድ አት ቱርኪ ነው። ተከታዩን አራት ረከዓ ያስሰገዱት አል ወሊድ ቢን ኻሊድ አሽ ሸምሳን ናቸው። የመጨረሻውን ሁለት ረከዓና የዊትር ሰላትን ደግሞ ሸይኽ ዓብዱረሕማን አስ ሱደይስ መርተውታል። (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #MinberTV
116👌20🥰7
በተያዘው ረመዳን ወር ዘካ ማሰባሰብ ለሚጀምረው የዘካና አውቃፍ ኮሚሽን ተግባራዊ ምላሽ ተጠየቀ

ለዝርዝሩ👉https://t.me/minberkheber/3225?single
👍206😁4