ለፍልስጤማዊያን ሰማዕታት ቤተሰቦች ተጨማሪ የሐጅ ዕድል ተፈቀደ
ዕለተ ሰኞ ሰኔ 3 - 2016 | ዙል ሒጃ 4 – 1445 | ሚንበር ቲቪ
ሳዑዲ ዐረቢያ ከዚህ ቀደም ከነበረው በተጨማሪ ሌሎች አንድ ሺሕ ፍልስጤማዊያን ሰማዕታት ቤተሰቦች የሐጅ ዕድል እንዲያገኙ ፍቃድ መስጠቷን አስታወቀች፡፡ ሀገሪቱ ለፍልስጤማዊያኑ ተጨማሪ መስጠቷን ያስታወቀችው ዛሬ ሰኞ ነው፡፡
በንጉሥ ሰልማን ቢን ዓብዱልዓዚዝ አማካይነት የተሰጠው የሐጅ ዕድል፣ በዘንድሮው ዓመት የሐጅ ዕድል ያገኙ የፍልስጤማዊያን ሰማዕታት ቤተሰቦችን ቁጥር ሁለት ሺሕ ያደርሰዋል፡፡
ሁለቱን ቅዱሳን ሥፍራዎች የያዘችው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ ከመላው ዓለም የተለያዩ ሀገራት እስከ ቅዳሜ ድረስ 1.3 ሚሊዮን ምዕመናንን ተቀብላለች፡፡ ሀገሪቱ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ለአንድ ሺሕ ፍልስጤማዊያን ሰማዕታት ቤተሰቦች የሐጅ ዕድል ሰጥታ ነበር፡፡
ሳዑዲ ዐረቢያ ከዚህ ቀደም እንዳስታወቀችው፣ ከፍልስጤማዊያን ውጪ ከመላው ዓለም ከ88 ሀገራት የተውጣጡ 1 ሺሕ 300 ምዕመናን የሐጅ ዕድሉን ሰጥታለች፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የተካተቱት 22 ምዕመናን ተጣብቀው የተወለዱና በተለያዩ ጊዜያት በሀገሪቱ ሕክምና አግኝተው እንዲነጣጠሉ የተደረጉ መንትያ ሕፃናት ቤተሰቦች ናቸው፡፡
ሳዑዲ ዐረቢያ በዘንድሮው 1445 ዓ.ሂ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ከመላው ዓለም ከሁለት ሚሊዮን በላይ ምዕመናንን ትቀበላለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዚህ ሳምንት ለሚፈጸመው የሐጅ ክንውን፣ በቀጣይ ቀናት ሌሎች አንድ ሚሊዮን ምዕመናን ወደ ሀገሪቱ እንደሚገቡ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገልጸዋል፡፡
የ1445 ዓ.ሂ የሐጅ ሥነ ሥርዐት መከናወን የሚጀምረው ከፊታችን ጁመዓ ዙልሒጃ 8 አንስቶ ባሉት ተከታታይ ቀናት መሆኑ ይታወቃል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)
ዝርዝሩን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡-https://minbertv.com/?p=8368
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

👏14👍9
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"እብዶች" ሰው ቢፈነክቱ ተጠያቂ ይሆናሉ?
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/7FELdSXUj9Q 🔗
#አንዲት_አንቀጽ
#መወዳ_መዝናኛ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/7FELdSXUj9Q 🔗
#አንዲት_አንቀጽ
#መወዳ_መዝናኛ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍10❤3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለምን ፈተና ይበዛብናል?!
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/T_A4_h876JM 🔗
#የዱንያ_ፈተና #ሴቶች_በ10ቱ_ቀናት
#ሰሞነ_ሐጅ

👌8👍7
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ህፃናት ሂጃብ መልበስ አጀንዳቸው እንዲሆን ብለን በማሰብ ነው የምንቀሳቀሰው"
- ብሩህ ልጆች
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/0rMi8BWd-y4 🔗
#ብሩህ_ልጆች #የህፃናት_ሒጃብ
#መወዳ_መዝናኛ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
- ብሩህ ልጆች
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/0rMi8BWd-y4 🔗
#ብሩህ_ልጆች #የህፃናት_ሒጃብ
#መወዳ_መዝናኛ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍18
የስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና በአዲስ አበበባ እና በክልሎች በዛሬው እለት መሰጠት ተጀመረ
ዕለተ ማክሰኞ ሰኔ 4 - 2016 | ዙል ሒጃ 5 – 1445 | ሚንበር ቲቪ
የስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና በአዲስ አበባ እና በክልሎች መሰጠት ጀመረ። ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 4/ 2016 መሰጠት የጀመረው ፈተና፣ በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች በሚገኙ የመፈተኛ ጣቢያዎች እየተሰጠ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የፈተናውን ሒደት የሚመሩ ፈታኞች እና ተቆጣጣሪዎች በ182 የመፈተኛ ጣቢያዎች ተመድበዋል፡፡ በተጨማሪም 86 ሺሕ 672 ተፈታኞች ፈተናውን እንደሚወስዱ የትምህርት ቢሮ ቀደም ሲል ባወጣቸው መግለጫዎች አሳውቋል፡፡
በከተማው በዛሬው እለት እየተሰጠ የሚገኘው ፈተና በጧቱ ክፍለ ጊዜ አማርኛ እና እንግሊዝኛ የሚሰጥ ሲሆን፣ በከሰዓቱ ክፍለ ጊዜ የዜግነት ትምህርት እና ሒሳብ መሆኑ ታውቋል፡፡ በከተማው በነገው እለት በጧቱ ክፍለ ጊዜ ማኅበራዊ ሣይንስ እና አጠቃላይ ሣይንስ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ፈተናው በተመሣሣይ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በኦሮሚያ፣ ጋምቤላ እና በአማራ ክልሎች መሰጠት መጀመሩን የክልሎቹ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡ ፈተናውን እየሰጡ ከሚገኙት ውስጥ በአማራ ክልል 184 ሺሕ 393 ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ እና በክልሎች የስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና ሲጠናቀቅ የስድስተኛ ክፍል ፈተና በቀጣይ እንደሚሰጥ የከተማ አስተዳደሩ እና የክልሎቹ ትምህርት ቢሮ ቀደም ብሎ አስታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ የስድስተኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 12/2016 እንደሚጀመር የተያዘው የጊዜ ሠሌዳ ያመለክታል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)
ዝርዝሩን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://minbertv.com/?p=8376

👍11
የአባታችን ነብዩላህ ኢብራሒም(ዐ.ሰ) ታሪክን መለስ ብሎ እየቃኘ የእናታችን ሐጀራ ታሪክ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ከታሪኩ ባሻገር ያለውን የታሪኩን መነገር ዋና ዓላማ ሊያስታውስ ተዘጋጅቷል።
አሁን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ ለሚስተዋለው ተስፋ መቁረጥና ድባቴ ተጠያቂው ማነው? መፍትሄውስ? ሲል እየጠየቀ ከሐጀራ የሕይወት ታሪክ ጋር በማጣመር "#የሐጀራ_ጽናት" በሚል ርዕስ ያዘጋጀነውን ልዩ መሰናዶ በዛሬው የሰሞነ ሐጅ ፕሮግራማችን ምሽት ከ3:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይቀርብላችኃል!
#ሰሞነ_ሐጅ
#የሐጀራ_ጽናት
ዕለተ ማክሰኞ ሰኔ 4 - 2016 | ዙል ሒጃ 5 - 1445
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
አሁን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ ለሚስተዋለው ተስፋ መቁረጥና ድባቴ ተጠያቂው ማነው? መፍትሄውስ? ሲል እየጠየቀ ከሐጀራ የሕይወት ታሪክ ጋር በማጣመር "#የሐጀራ_ጽናት" በሚል ርዕስ ያዘጋጀነውን ልዩ መሰናዶ በዛሬው የሰሞነ ሐጅ ፕሮግራማችን ምሽት ከ3:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይቀርብላችኃል!
#ሰሞነ_ሐጅ
#የሐጀራ_ጽናት
ዕለተ ማክሰኞ ሰኔ 4 - 2016 | ዙል ሒጃ 5 - 1445
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍7😍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የተቀቀለ እንቁላል የተሻለ የፕሮቲን ይዘት አለው!
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/GABWHfHGbEE 🔗
#እህል_ውሃ #ጤናማ_ህይወት
#መወዳ_መዝናኛ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/GABWHfHGbEE 🔗
#እህል_ውሃ #ጤናማ_ህይወት
#መወዳ_መዝናኛ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍2
የሕዝብ በዓላት እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣው ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ
ዕለተ ማክሰኞ ሰኔ 4 - 2016 | ዙል ሒጃ 5 – 1445 | ሚንበር ቲቪ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሔደው መደበኛ ስብሰባው የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጸደቀ። በረቂቅ አዋጁ ላይ አንዳንድ የሀይማኖት ተቋማት ውይይት እንዳላደረጉና ቅሬታ እንዳላቸው ገልጸዋል ተብሏል።
ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 4/2016 የጸደቀውን አዋጅ ላለፉት ሦስት ወራት በዝርዝር ሲመለከቱ የነበሩት የጤና፣ ማኅበራዊ ልማትና ስፖርት ጉዳዮች እና የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች በጋራ ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ ለምክር ቤቱ ማቅረባቸው ተገልጿል።
የምክር ቤቱ አባላት በረቂቅ አዋጁ ላይ ሐሳብና ጥያቄ ማቅረባቸውን የገለፀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ አንዳንድ የሃይማኖት ተቋማት በረቂቅ አዋጁ ላይ ውይይት እንዳላደረጉና ቅሬታ እንዳላቸው ጠቁመዋል ብሏል። ሆኖም የሃይማኖት ተቋማቱን በሥም አልጠቀሰም።
በምክር ቤቱ የጤና፣ ማኅበራዊ ልማትና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ወርቀሥሙ ማሞ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ መስጠታቸው ሲገለጽ፣ ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት የተወከሉ የሀይማኖት አባቶች በረቂቅ አዋጁ ላይ ስለመወያየታቸው አስረድተዋል ተብሏል።
አዲሱ አዋጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ በዓላት እና የበዓላትን አከባበር የሚመለከት ሲሆን፣ ክልሎች በራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ሕግ አውጥተው በክልል ደረጃ የሚከበሩ አዋጆችን አከባበር መወሰን እንደሚችሉም ተገልጿል።
ምክር ቤቱ የሕዝብ በዓላት እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅን በአንድ ድምፀ ተቅቦና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡
ዝርዝሩን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፦ https://minbertv.com/?p=8386

👍7❤1
ልዩ “ኸበር” - ናይጄሪያዊቷ ምዕመን ለሐጅ በተጓዘችበት የበኩር ልጇን ተገላገለች
ዕለተ ማክሰኞ ሰኔ 4 - 2016 | ዙል ሒጃ 5 – 1445 | ሚንበር ቲቪ
የናይጄሪያ መገናኛ ብዙኃንን ያለፉት ሁለት ሳምንታት ትኩረት ያገኘው ጉዳይ የሀገራቸው ዜጎች ለሐጅ ተጉዘው ሕይወታቸው ማለፉ ነበር፡፡ የ68 ዓመቱ ኦሎሾግቦ ኢድሪስ እና ተወከልቱ አሊኮ ለ1445 ዓ.ሂ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ገብተው ብዙም ሳይቆዩ ነበር ወደ ቀጣዩ ዓለም የተሻገሩት፡፡ ኢድሪስም ሆነ ተወከልቱ አሊኮ ኅልፈታቸው ድንገተኛ መሆኑ አስደንጋጭ ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡
ኢድሪስ ማዕድ ላይ፣ አሊኮ ደግሞ ወደ ገበያ ማዕከል እየገባች ነበር የወደቁት፡፡ ሁለቱም ናይጄሪያዊያን ሞታቸው ለወዳጅ ዘመድ በሀገሪቱ የሐጅ ባለሥልጣናት ይፋ ተደርጎ፣ ኅልፈታቸው በሆነበት የሳዑዲ ምድር ሥርዐተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡ ዜጎቿን በሞት የተነጠቀችው ናይጄሪያ፣ አሁን ደግሞ እዚያው በሳዑዲ መሬት ላይ አዲስ ልጅ ተወልዶላታል፡፡ አዲሱ ልጅ ሙሐመድ ይባላል፡፡ ሙሐመድ የናይጄሪያ መገናኛ ብዙኃንን የሞት ዜና ወደ ሕይወት መልሷል፡፡
ከትናንት ምሽት አንስቶ የናይጄሪያ እና ሳዑዲ ዐረቢያ መገናኛ ብዙኃንን ሽፋን ያገኘው ሙሐመድ፣ ከ30 ዓመቷ ናይጄሪያዊት ምዕመን የተገኘ ነው፡፡ ናይጄሪያቷ የበኩር ልጇን ሙሐመድን የተገላገለችው ለሐጅ ሥነ ሥርዐት በተጓዘችበት ነው፡፡ ሥሟ ያልተጠቀሰው ምዕመን የተነሳችው ከቦርኖ ግዛት እንደሆነም ተሰምቷል፡፡ ሙሐመድ በዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት ላይ የተወለደ ቀዳሚው ጨቅላ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
የሙሐመድ እናት ቀድማ እንዳሰበችው ቢሆን ኖሮ ልጇ ወደ ምድር የሚመጣበት ጊዜ ጥቂት ሳምንታት ይቀሩት ነበር፡፡ ሆኖም ያሰበችው ቀረና ያላሰበችው ምጥ በድንገት አጣድፏት ሙሐመድ በእርግዝናው 31ኛ ሳምንት መካ ከተማ ውስጥ ተወልዷል፡፡
ናይጄሪያዊቷ ምዕመን ሙሐመድ ያለ ጊዜው ቢመጣባትም የወሊድ ሒደቱ ግን አስቸጋሪ አልነበረም ብላለች፡፡ ሙሐመድ በአሁኑ ሰዓት ልዩ እንክብካቤ እያገኘ መሆኑ ተነግሯል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)
በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=8397

👍18😍10❤4
የሦስቱ በዓላት አከባበር በአዲሱ አዋጅ ባለበት እንዲቀጥል ተደረገ
ዕለተ ማክሰኞ ሰኔ 4 - 2016 | ዙል ሒጃ 5 – 1445 | ሚንበር ቲቪ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባፀደቀው የሕዝብ በዓላትና የበዓላትን አከባበር በሚደነግገው አዋጅ ላይ ዒድ አልፊጥር፣ ዒድ አል አድሓ እና የመውሊድ በዓላት አከባበር ባሉበት እንዲቀጥሉ ተደረገ። አዋጁ የሕዝብ በዓላትን በሦስት ምድብ ከፋፍሏል።
ምክር ቤቱ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 4/2016 ያፀደቀው አዋጅ ሕዝባዊ በዓላትን በሦስት ምድብ የሚከፍል ነው። አዋጁ በሦስት የከፈላቸው በዓላት ተከብረው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት፣ ታስበው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት እና ሃይማኖታዊ በዓላት ናቸው።
በሃይማኖታዊ በዓላት ምድብ ስምንት በዓላትን የዘረዘረው አዋጁ፤ ዒድ አል ፊጥር፣ ዒድ አል አድሓ እና መውሊድን አስቀምጧል።
ይኸው አዋጅ ተከብረው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላትን የዘረዘረ ሲሆን፣ እነዚህ አራት በዓላት የዘመን መለወጫ፣ የዐድዋ ድል፣ የላብ አደሮች ቀን እና የአርበኞች በዓል ናቸው።
አዋጁ የካቲት 12 የሚከበረውን የሰማዕታት ቀን እና ሕዳር 29 የኢትዮጵያ ሕብረ ብሔራዊነት (የብሔረሰቦች ቀን) ታስበው የሚውሉ በዓላት እንደሆኑ አሥፍሯል።
አዲሱ አዋጅ በሃይማኖታዊ እና ተከብረው በሚውሉ በዓላት ቀን የመንግሥት እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ እንደሚሆኑ ደንግጓል።
በአንጻሩ ታስበው በሚውሉ በዓላት ሥራ ሳይዘጋ ቀኑ በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች ታስቦ እንደሚውል ሠፍሯል።
በአዋጁ ላይ የተቀመጡት በዓላት በሙሉ በውጭ አገር የሚገኝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ውስጥም ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸውን በጠበቀ ሁኔታ እንደሚከበሩ ተቀምጧል።
በዛሬው እለት የፀደቀው የሕዝብ በዓላትና የበዓላትን አከባበር የሚደነግገው አዋጅ በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ ነው የፀደቀው።
ሊንኩን ተከትለው ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://minbertv.com/?p=8431

👍18🥰1👌1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከአሽር አል አዋኺር እና ከአስርቱ የዙል ሂጃ ቀናት የትኞችሁ ይበልጣሉ?
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/50vZ5aCVWhM 🔗
#ዙል_ሒጃ #ረመዳን
#ቢስሚከ_ነሕያ
#ኸሚስ_ምሽት
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/50vZ5aCVWhM 🔗
#ዙል_ሒጃ #ረመዳን
#ቢስሚከ_ነሕያ
#ኸሚስ_ምሽት
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍10❤2
የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመጪው ሐምሌ ወር መጀመሪያ እንደሚሰጥ ተገለጸ።
የትምህርት ሚኒስቴርና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፈተናውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት፤ የዘንድሮው ዓመት የ12ኛ ክፍል ፈተና ከትግራይ ክልል ውጭ ባሉ አካባቢዎች ሐምሌ 3 ቀን 2016 ይጀመራል።
በዚህም መሠረት ከሐምሌ 3 እስከ 5 የሶሻል ሳይንስ ፈተና የሚሰጥ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ነው የገለፁት።
በትግራይ ክልል ደግሞ በሁለት ዙር ፈተናው የሚሰጥ ሲሆን ሐምሌ 2 ተጀምሮ ሐምሌ 12 እንደሚጠናቀቅ ጠቁመዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ዲጂታላይዜሽንና የአይሲቲ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዘላለም አሠፋ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የዘንድሮው ዓመት የ12ኛ ክፍል ፈተና በኦንላይንና በወረቀት እንደሚሠጥ ተናግረዋል።
በዘንድሮው ዓመት 701ሺህ 489 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተናን እንደሚወስዱ ተገልጿል።
ትምህርታቸውን ዘግይተው የጀመሩና በተለያዩ ምክንያቶች በዚህ መርኃ ግብር መሰረተ ፈተና ላይ መቀመጥ ለማይችሉ ተማሪዎች ሁለተኛ ዙር ፈተና እንደሚዘጋጅም ጠቁመዋል። (ኢዜአ)

👍12
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ላፕቶፕ እንዲገዙ ታዘዋል መባሉን የትምህርት ሚኒስቴር “ፍጹም ሐሰት” ነው አለ
ዕለተ ማክሰኞ ሰኔ 4 - 2016 | ዙል ሒጃ 5 – 1445 | ሚንበር ቲቪ
የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የጊዜ ሠሌዳ ይፋ ባደረገበት ወቅት በኦንላይን ለሚሰጠው ፈተና ተፈታኞች ላፕቶፕ እንዲገዙ ታዘዋል መባሉን “ፍጹም ሐሰት” ነው አለ። የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3/2016 ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 4/2016 በሰጠው መግለጫ፣ ፈተናውን በወረቀትና በኦንላይን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።
በኦንላይን ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ቴክኖሎጂውን እንዲያውቁት የተግባር ልምምድ ፈተናዎች በሶፍትዌሩ እንደተጫነ የገለፀው ትምህርት ሚኒስቴር፣ ለፈተናው የኔትወርክ እና የመብራት መጠባበቂያ ኃይል ያላቸውን ተቋማት መምረጡን ጠቅሷል።
የትምህርት ሚኒስቴር በመግለጫው ለዩኒቨርሲቲዎችና ከዩኒቨርሲቲ ውጪ ላሉ ተቋማት በክላስተር በማድረግ በፈተና ወቅት አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርጉ ባለሞያዎች እንደተመደቡም ነው የገለፀው።
በዛሬው መግለጫ ላይ የተገኙ ኃላፊዎች በተለይ በኦንላይን ለሚሰጠው ፈተና የግብዓት ዝግጅትን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ኃላፊዎቹ በመንግሥት በኩል አስፈላጊው የግብዓት ዝግጅት መደረጉን በመጥቀስ፣ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ተማሪዎች ላፕቶፕ ገዝተው እንዲያመጡ ታዘዋል መባሉ ፍጹም ሐሰት ነው ሲሉ አጣጥለውታል። የኃላፊዎቹ መግለጫ የመጣው በተለይ በግል ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ላፕቶፕ እንዲያመጡ መታዘዙ ከተነገረ በኋላ ነው።
ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ባወጣው የ2016 የ12ኛ ክፍል ፈተና የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ከትግራይ ክልል በስተቀር ፈተናው ከሐምሌ 3/2016 ጀምሮ የሚሰጥ ይሆናል።
በጊዜ ሠሌዳው ላይ እንደተቀመጠው በቀዳሚነት ከሐምሌ 3 እስከ 5/2016 ለፈተና የሚቀመጡት የማኅበራዊ ሣይንስ ተማሪዎች ናቸው። የተፈጥሮ ሣይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ይሰጣል።
በሁለት ዙር ፈተናው ይሰጥበታል በተባለው ትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ሐምሌ 2 ተጀምሮ ሐምሌ 12/2016 ይጠናቀቃል ተብሏል።
እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ በ2016 የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት 701 ሺሕ 489 ነው።
በድረ ገጽ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፦ https://minbertv.com/?p=8436

👍13
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አላህ ዘንድ ትልቅ ቦታ የተሰጣቸው 10ቱ የዙልሒጃ ቀናት!
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/nWhqvQr5OhY 🔗
#ዙል_ሒጃ
#የጁሙዓ_ኹጥባ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/nWhqvQr5OhY 🔗
#ዙል_ሒጃ
#የጁሙዓ_ኹጥባ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍12❤3🥰2🙏1
ሐጅ - የህይወት ዘመን ዒባዳ - Minber TV.pdf
4.6 MB
ለውድ የሚንበር ቲቪ ቤተሰቦች
🕋 🕋 🕋 🕋 🕋 🕋 🕋
የሐጅ አጠቃላይ መረጃዎችን እና ቅደም ተከተላዊ ሒደቶችን በPDF ያዘጋጀን መኾናችንን እየገለጽን፤ የተከበረውን የሐጅ ሥርዓት ለመከወን በዝግጅት ላይ የምትገኙ፣ እንደዚሁም ለሥርዓቱ ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው የሚጠባበቁ ወዳጅ፣ ቤተሰብና ዘመድ ያላችሁ ስለ ሐጅ ሥርዓት ጠቃሚ መረጃዎችን የያዘውን ይህንን ዶክመንት እንድትጠቀሙና ለሌሎችም እንድታጋሩ በአክብሮት ጋብዘንዎታል፡፡
ድረገጻችን ላይ ለማንበብ ፡ https://minbertv.com/?p=8390

🙏14👍11❤2😍1