Minber TV
44.6K subscribers
15.3K photos
2.36K videos
36 files
7.99K links
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
ይከታተሉ፣ ለወዳጅዎ ያጋሩ!

📡 ሳተላይት ፡ EthioSAT 11545/45000/H
📱 የሶሻል ሚድያ አድራሻዎቻችን ፡ https://linktr.ee/minbertv
Download Telegram
ልዩ ኸበር - ለሐጅ የሚደረገው ‘ሌላኛው ፍልሚያ’
ልዩ ኸበር - ለሐጅ የሚደረገው ‘ሌላኛው ፍልሚያ’

ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 29 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 29 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

ሳዑዲ ዐረቢያ በዘንድሮው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ለመሳተፍ ከመላው ዓለም ሀገራት የተነሱ ምዕመናንን መቀበሏን እንደቀጠለች ነው፡፡ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ይፋ ያደረጓቸው መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ እስካሁን ድረስ ሳዑዲ ዐረቢያ የገቡ ምዕመናን ቁጥር አንድ ሚሊዮን ደርሷል፡፡ ከአንድ ሳምንት በታች ለቀረው የሐጅ ክንውን፣ በቀጣይ ቀናት ሌሎች አንድ ሚሊዮን ምዕመናን ወደ ሀገሪቱ ይዘልቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሳዑዲ ዐረቢያ እንግዶቹን የምታስተናግደው ለሥነ ሥርዐቱ ብቻ በሚል የተለየ ቪዛ አዘጋጅታ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት የሐጅ ቪዛ ከያዙ ምዕመናን ውጪ ሌሎች እንግዶች ወደ ሀገሬ ቢገቡም ወደ ቅድስቲቱ መካ ከተማ እንዲዘልቁ አልፈቅድም በማለት የከተማዋን በሮች ቆልፋለች፡፡

ሀገሪቱ ከዚህ ቀደም እንዳስታወቀችው፣ የመካ በር ከተቆለፈ በኋላ ማንኛውም ምዕመን በየትኛውም ምክንያት በድንገት መካ ከተማ ውስጥ ያለ ሐጅ ቪዛ ቢገኝ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ ሳዑዲ መቀጮ የሚያስከፍለውን ደንብ ያወጣችው በሥነ ሥርዐቱ ወቅት ሊከሰት የሚችለውን መጨናነቅ ለመቀነስ ነው፡፡ ሳዑዲ ዐረቢያ ይህን እርምጃ ይበልጥ ያጠናከረችው ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ሚና ላይ አደጋ ከተከሰተ በኋላ ነው፡፡ ምዕመኑን ብቻ ሳይሆን የትራንስፖርት አገልግሎት የሰጡትንም ጭምር የሚያስቀጣውን ደንብ የጣሱ ምዕመናን፣ በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሳዑዲ ዐረቢያ ጋዜጦች መዘገብ ጀምረዋል፡፡

ሳዑዲ ቁጥጥሩን ጠበቅ ብታደርግም፣ የመጣውን ለመቀበል የቆረጡ ከመላው ዓለም የተለያዩ ሀገራት ቀደም ብለው የተነሱ ምዕመናን የሐጅ ቪዛ በእጃቸው ሳያስገቡ መካ ውስጥ እንደሚገኙ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡ እነዚህ ምዕመናን መካ ውስጥ የሚገኙት ሐጅ ሲጀመር ሥነ ሥርዐቱን ለመከወን ነው፡፡ ምዕመናኑ ይህን መንገድ የመረጡት በአብዛኛው ከገንዘብ ጋር በተገናኘ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

ከእነዚህ ውስጥ የሆነው መገናኛ ብዙኃኑ የአባቱን ሥም ያልጠቀሱት ግብጻዊው ሙሐመድ፣ በአሁኑ ወቅት መካ ውስጥ በሚገኝ አፓርታማ ውስጥ በመቀመጥ የሐጅ ሥነ ሥርዐት እስኪጀመር ድረስ እየተጠባበቀ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ሙሐመድ ለምን ይህን እንዳደረገ ሲጠየቅ፣ ወጪ ቆጣቢ ሐጅ ለመፈጸም ነው ብሏል፡፡ የሙሐመድ ሀገር ግብጽ ለሐጅ ሥነ ሥርዐት 175 ሺሕ (የግብጽ) ፓዉንድ ታስከፍላለች፡፡ ሙሐመድ ከዚህ በተጨማሪም ሌላ ምክንያት ይጠቅሳል፤ ግብጽ በምከተለው የሐጅ አሠራር መሠረት ለአሥር ዓመት የሐጅ ዕድል ለማግኘት ዕጣ ይደርሰኛል ብሎ ቢጠባበቅም አልተሳለትም፡፡ ስለዚህ በቱሪስት ቪዛ መካ በመግባት ቀኑ እስኪደርስ ራሱን ከፀጥታ አካላት መሸሸግ መርጧል፡፡


ሳዑዲ ዐረቢያ በየዓመቱ የሐጅ ቪዛ ሰጥታ ከምታስተናግዳቸው እንግዶች ውጪ ቢያንስ 100 ሺሕ ምዕመናን ሳይፈቀድላቸው በሥነ ሥርዐቱ ላይ እንደሚታደሙ ትገልጻለች፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=8329

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍162
ዱንያ ላይ ካሉ ቀናት ሁሉ በላጮቹና እጅግ ተወዳጆቹ የዙልሒጃ አስር ቀናት ደጅ ላይ ቆመን፤ ስለ ቀናቱ ትሩፋትና አጠቃላይ ስለ ሐጅ ዓላማና የአፈጻጸም ሥርዓት የተወያየንበት ተወዳጁ የኸሚስ ምሽት ፕሮግራማችን ምሽት ከ2፡00 ጀምሮ ወደናንተ ይደርሳል፡፡

ሸይኻችን በሰዓታቸው ለሐጅ ጉዞ የተመረጡ አማኞች የሐጅ ተግባራትን በአግባቡ አከናውነው ካጠናቀቁ በኋላ በተለይ በመዲና በሚኖራቸው የዚያራ ቆይታ ጨርሶ መዘንጋት የሌለባቸውን ስፍራዎችና አዳቦች እያወሱ የሚቆዩ ሲሆን፤ ተወዳጁ ኡስታዛችን ኡስታዝ በድር ሁሴን ደግሞ የአሥርቱን የዙልሒጃ ቀናት ደረጃና የሐጅን ዐቢይ ግብና ዓላማዎች ካለንበት ተጨባጭ ጋር እያስተሳረ ውብ ሃሳቦቹን ያካፍለናል፡፡

#ለይሉ_ጁምዓ_ነው!
#ፕሮግራሙ_ደግሞ_ኸሚስ_ምሽት!

ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 29 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 29 - 1445
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍244
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፆም ነፍሳችንን ያንጻል!
ነፍሳችን ከተስተካከለች ደግሞ ሙሉ ህይወታችን ይስተካከላል።

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/nnrG4c_CtPg 🔗

#ፆም #ነፍስያን_መግራት
#በይቱል_ሐቢብ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍6🥰1
የዙልሒጃ ወር ነገ ጁመዓ እንደሚጀምር ታወቀ

በሂጅሪ አቆጣጠር 12ኛው የዙልሒጃ ወር የመጀመሪያ ቀን ነገ ጁመዓ እንደሚሆን የታወቀው በዛሬው እለት አዲስ ጨረቃ በመታየቱ ነው። በዚህም መሠረት ዛሬ ሐሙስ የዙልቀዕዳ ወር የመጨረሻ ቀን ይሆናል።

በሌላ በኩል የዘንድሮው ዓመት የዒድ አል አድሓ በዓል በወሩ አሥረኛው ቀን እሑድ ሰኔ 9/2016 ይከበራል።
👍10132🥰15🙏4👏1
ጁምዓ ሙባረክ!

إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَـٰٓئِكَتَهُۥ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِىِّ ۚ يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ صَلُّوا۟ عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا۟ تَسْلِيمًا (56)
"አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ። እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ። የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ።" - (ሱረቱል አሕዛብ 33፡56)

የተከበሩት የዙልሒጃ አስቱ ቀናት መጀመርያ ላይ እንገኛለን። ቀኑም ጁምዓ ነው። ሶላዋት በማውረድ እና ኸይራት በማብዛት መልካም ምንዳ እንሸምት።

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍187
የሬሜዲያል ፈተና የጊዜ ሠሌዳ ለውጥ ማድረጉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

• የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የጊዜ ሠሌዳውን በተመለከተ ቅሬታ ማቅረቡ ተሰምቷል

የትምህርት ሚኒስቴር የሬሚዲያል (የማካካሻ) ትምህርት የማጠቃለያ ፈተና ላይ የጊዜ ሠሌዳ ለውጥ ማድረጉን ዛሬ ጁመዓ ግንቦት 30/2016 አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ የፈተና ቀን ለውጡን ያደረገው ከዒድ አል አድሓ በዓል ጋር በተመሣሣይ ቀን በመዋሉ ነው ብሏል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ቀድሞ ባስቀመጠው ጊዜያዊ የጊዜ ሠሌዳ ላይ ፈተናው የሚሰጠው ከሰኔ 3 እስከ 10/2016 የነበረ ቢሆንም፣ በአዲሱ የጊዜ ሠሌዳ የአንድ ቀን ጭማሪ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሠረት ሰኔ 9 ይሰጥ የነበረው ፈተና ወደ ሰኔ 11 ተዘዋውሯል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር የቀን ለውጥ ያደረገው ሰኔ 9/2016 የዒድ አል አድ በዓል ስለሚከበር መሆኑን ገልጧል፡፡

የትምህር ሚኒስቴር ቀድሞ ያወጣውን የጊዜ ሠሌዳ በተመለከተ ከዒድ አድሓ በዓል ጋር በተመሳሳይ ቀን ከመዋሉ ጋር በተገናኘ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቅሬታ ማቅረቡን ሚንበር ቲቪ ከምክር ቤቱ ኃላፊዎች ሰምቷል፡፡

የትምህር ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ከእስልምና በዓላት ጋር በተመሳሳይ ጊዜ በሚያወጣው የፈተና የጊዜ ሠሌዳ ተደጋጋሚ ቅሬታ የሚቀርብበት ነው፡፡

ዝርዝሩን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://minbertv.com/?p=8346

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍19🥰2
የ2017 ረቂቅ በጀት አዋጅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲመራ ተደረገ

ዕለተ ጁመዓ ግንቦት 30 - 2016 | ዙል ሒጃ 1 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2017 ረቂቅ በጀት አዋጅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲመራ ያደረገው ዛሬ ጁመዓ ግንቦት 30/2016 ባካሄደው ስብሰባ ነው፡፡

ምክር ቤቱ የ2017 የፌደራል መንግሥት በጀት የተዘጋጀው የአሥር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነውን የ2016-2018 የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችንና የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊስካል ማዕቀፍን ማስፈጸም እንዲቻል በሚያደርግ መልኩ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የ2016 የፌደራል መንግሥትን የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ፤ የመንግሥት የፋይናንስ አቅም እና ተጠባቂ ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም አስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች የተሰጣቸውን ተልዕኮና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በመገምገም እንዲዘጋጅ መደረጉንም ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

በዚሁ መሠረት ለፌዴራል መንግሥት መደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ወጪዎች፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ እና ተጠባባቂ ወጪን ጨምሮ ወደ አንድ ትሪሊዮን የሚጠጋ በጀት ለምክር ቤቱ መቅረቡ ተገልጧል፡፡

ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግሥት የ2017 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል ነው የተባለው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=8343

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍51
የጁመዓ ልዩ ኸበር- የሸይኽ ዐብዱረሕማን ሱደይስ የጁመዓ መመርያ
👍7
የጁመዓ ልዩ ኸበር- የሸይኽ ዐብዱረሕማን ሱደይስ የጁመዓ መመርያ

ዕለተ ጁመዓ ግንቦት 30 - 2016 | ዙል ሒጃ 1 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

ከአዲሷ ጨረቃ ጋር ዛሬ ጁመዓ የዙልሒጃ ወር ጅማሬ ሆኗል፡፡ የሐጅ ሥነ ሥርዐት መጀመሪያ እና መጨረሻ ቀናትም ይፋ ተደርገዋል፡፡ ከመላው ዓለም ለሐጅ የሚሰባሰቡ ምዕመናንን የምታስተናግደው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የተቀበለቻቸው የአላህ እንግዶች ብዛት 1.2 ሚሊዮን ደርሰዋል፡፡ ቀሪ እንግዶች በቀጣይ ቀናት ወደ መዲና እና መካ ከተሞች መጓዝ ይቀጥላሉ፡፡

የእንግዶቹ መዳረሻ ሳዑዲ ዐረቢያ ቀድሞም የአየር ንብረቷ ግለት የሚወቅ ቢሆንም፣ ሑጃጆቹ በደረሱበት በዚህ ወቅት ይበልጥ ከፍ ማለቱ ባለሥልጣናቱን ያሳሰባቸው ይመስላል፡፡ የሳዑዲ ዐረቢያ የሜትሮሎጂ መሥሪያ ቤት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ባወጣው መረጃ፣ በተያዘው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት በሚከናወንበት በዚህ ወቅት ከእኩለ ቀን በኋላ በመካ የሚጠበቀው የሙቀት መጠን ከ45 እስከ 48 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሊደርስ የሚችል ነው፡፡

የመሥሪያ ቤቱ ኃላፊ አይመን ቢን ሳሊም ጉላም ሙቀቱ እጅግ የበረታ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ ጉላም በዚህ የሐጅ ወቅት ዝናብ የመፈጠር ዕድል ይኖር ይሆን ወይ በሚል ተጠይቀው፣ አነስተኛ መሆኑን በመጥቀስ ምናልባት ደመና ሊመዘገብ የሚችለው በጣኢፍ አካባቢ ነው የሚል ትንበያ መኖሩን ጠቁመዋል፡፡

ባለሥልጣናቱ ምዕመናንን ከፀሓይ ግለት ለመከላከል ዓለም የደረሰትን ከፍተኛ ቴክኖሎጂ አዘጋጅተናል ብለዋል፡፡ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያሳየው፣ ምዕመናኑ በብዛት በሚገኙባቸው ሥፍራዎች ላይ አየር ማቀዝቀዣ ተከላ እየተከናወነ ነው፡፡

ሳዑዲ ዐረቢያ ምዕመናኑን ከፀሓዩ ግለት ለመከላከል ሌላም ርምጃ ያስፈልጋል በሚል ወስናለች፡፡ ለዚህ እንዲያግዝ የሁለቱ ቅዱሳን ሥፍራ መስጅዶች ፕሬዝዳንት እና የመስጅድ አል-ሐረም ኢማም የሆኑት ሸይኽ ዐብዱረሕማን ሱደይስ ትናንት ሐሙስ አዲስ መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡ ሸይኽ ሱደይስ ያስተላለፉት መመሪያ በዛሬው ጁመዓ የሚደረገው ኹጥባ እና የሰላት ርዝማኔ እንዲያጥር የሚል ነው፡፡ ይህ በመካም ሆነ በመዲና መስጂዶች የሚተገበር ይሆናል ተብሏል፡፡

የዛሬው ጁመዓ የመስጂድ አል ሐረም ኹጥባ የሚደረገው በሸይኽ ያሲር ደውሰሪ ሲሆን፣ የመዲናው መስጂድ አል ነበዊ ኻጢብ ሸይኽ ዓብደላህ አል ቡዓይጃን ይሆናሉ ተብሎ ተጠብቋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)
በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=8338

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍162
በሕይወት በኑሮና በጊዜያት ሽግግር የሰው ልጆችን በየዘመናቱ የሚፈታተኑና ከእምነቱ መርህ ጋር የሚጣረሱ አዳዲስ ግኝቶችና ሙከራዎች ይኖራሉ። ይህ መልኩን እየቀያየረ የሚኖር እንጂ ፈፅሞ የማይከስም ሂደት፤ ጉዳዩን በቅርበት በሚያውቁና ተዛማጅ የኾነ ጥልቅ ንባብ ባላቸው ዓሊሞችና ምሁራን መፍትሄ ካልተበጀለት መዘዙ ከባድ እንደሚኾን አያጠያይቅም።

በዛሬው የ"ጥያቄ አለኝ" ዝግጅታችን በትዳር ሕይወት ዙሪያ ካነሳናቸው የተለያዩ ንዑስ ጉዳዮች አንዱ ኾኖ የቀረበው "መህሬ ቁርኣን ነበር! ወደ ገንዘብ ብቀይረውስ?" በሚል ርዕስ በሸሪዓችን ከተሰጠው ብይን በመነሳትና የተለያዩ ዑለሞችን ምላሾች መሠረት በማድረግ ተወዳጁ ዐሊም ሸይኽ አህመድ አወሉ ዛሬ ምሽት ከ3:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ በሚቀርበው "ጥያቄ አለኝ" ፕሮግራም ላይ ምላሽ የሚሰጡበት ይኾናል።

ያላችሁን ጥያቄዎች በፅሁፍ በ 0948992121 ወይም በ9282 ላይ YS ን በማስቀደም ልታደርሱን ትችላላችሁ!!

#ጥያቄ_አለኝ
#መህሬ_ቁርኣን_ነበር!
#በገንዘብ_ብቀይረውስ?

ዕለተ ዓርብ ግንቦት 30 - 2016 | ዙል ሒጃ 1 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍152
ዘመን የማይሽረውን የቁርኣንን ልቅና በተለያዩ ማዕዘናት እያሳየና፤ የተከበረውን የአላህ (ሱ.ወ) ቃል በልባቸው ላይ አትመው ከሚኖሩ በርካታ እንግዶቹ ጋር ቆይታ እያደረገ ዘወትር ጁሙዓ ምሽት ከ 2፡00 ጀምሮ ሲቀርብ የቆየው መዓል ቁርኣን ፕሮግራማችን፤ እነሆ በአዲስ ቅርፅና ይዘት ተመልሷል፡፡ በአዲሱ ምዕራፋችን ቁርኣን የሚነበብ ብቻ ሳይሆን ለሁለት ዓለም ስኬት የሚያበቃ የህይወት መንገድ መሆኑን ከንባብና ኑሯቸው እየመዘዙና፤ እንደ ሙስሊም ከቁርኣን ጋር ስላላቸው ትይይዝ ሃሳብ እየሰጡ የሚቆዩ የተለያዩ እንግዶችን እየጋበዘ እንደዚሁም የአዘጋጁን ተወዳጅ ምጥን ቁርኣናዊ መልዕክት አካቶ ዘወትር ጁሙዓ ምሽት ከ 2፡00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ወደናንተ መድረሱን ጀምሮዋል፡፡

በዛሬው መዓል ቁርኣን ዝግጅታችን ለየት ባለ የአቀራር ስልቱ ከምናውቀው ከዶ/ር ሚስባህ ጋር ቆይታ የምናደርግ ሲሆን፤ ከቁርኣን ጋር የነበረውን ጉዞና ይህን የሀበሻ ዜማ የሚባለውን አቀራር ከየት እንደተማረ አውግቶናል። በተጨማሪም መድረሳዎች ላይ የምንመለከተውን ክፍተት ምንጭ እና መፍትሄው ላይ አውርተናል።

ዛሬ ምሽት ከ02፡00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይቀርብላችኋል፡፡

#ከሂፍዝ_በኃላስ?
#ከቁርአን_ጋር

ዕለተ ዓርብ ግንቦት 23 - 2016 | ዙል ሒጃ 1 – 1445

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍118
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዶክተሩ እና የሻንጣው ቂሷ 😂
የጭንቀት ስሜት ሲጎበኘን እጅ መስጠት የለብንም!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/HIKMVJg41lw 🔗

#ዶክተሩ_እና_ሻንጣው
#የሸይኻችን_ሰዓት
#ኸሚስ_ምሽት

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍12🥰8
#የጁምዓ_ኹጥባ
ከአዲሱ የሙጀመዕ አት ተቅዋ መስጂድ
በኡስታዝ ካሚል ሸምሱ

ዛሬ ጁምዓ በአዲሱ የሙጀመዕ አት ተቅዋ መስጂድ በኡስታዝ ካሚል ሸምሱ የቀረበውና፤ በዋናነት ስለ "አሥርቱ የዙል ሒጃ ውድ ቀናት ትሩፋቶች" ሃሳብ የቀረበበት መልዕክት ዛሬ ከሰዐት ከ11:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ የሚቀርብላችሁ ይሆናል።

#የጁምዓ_ኹጥባ
#ኡስታዝ_ካሚል_ሸምሱ

ዕለተ አርብ ግንቦት 30 - 2016 | ዙል ሒጃ 1– 1445 | ሚንበር ትቪ
★   ★   ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | 45000 | H
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ#Minber_TV
👍18
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከቁርአን ጋር - ዘወትር ጁምዓ ከምሽቱ 2፡00 ጀምሮ!

#ከቁርአን_ጋር

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍21👌2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከአስርቱ የዙልሒጃ ቀናት የበለጠ መልካም ስራ የሚወደድባቸው ቀናት የሉም!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/50vZ5aCVWhM 🔗

#አስርቱ_የዙልሒጃ_ቀናት
#ቢስሚከ_ነሕያ
#ኸሚስ_ምሽት

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍242🥰2😢1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቀብር ቅጣት ባይኖርብንም ቀብር በራሱ ቅጣት ነው!
- ትልቅ ማስታወሻ

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/HIKMVJg41lw 🔗

#ቀብር_ጎብኙ
#የሸይኻችን_ሰዓት
#ኸሚስ_ምሽት

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍38
#የበረታው_ሙቀት እና ሌሎችም...

በዛሬው የሰሞነ ሐጅ መሰናዶ ከሐጅ ጋር የተያያዙ ሃሳቦችን ስለ በረታው የሳዑዲ ሙቀት እና ሌሎችንም መረጃዎች ወደ እናንተ ያደርሳል።

#ሰሞነ_ሐጅ ክፍል 8
ዛሬ ምሽት 01፡00 በሚንበር ቲቪ!

ዕለተ ቅዳሜ ሰኔ 1- 2016 | ዙል ሒጃ 2 - 1445
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
7👍6
የመጨረሻዎቹ ኢትዮጵያውያን ሑጃጆች በዛሬው እለት ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ በረራ ያከናውናሉ ተባለ

ለ1445ኛ ዓ.ሂ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የመጨረሻዎቹን ሑጃጆች ዛሬ እንደሚሸኝ አስታወቀ። ምክር ቤቱ ይህን ያስታወቀው ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 1/2016 በጽሕፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ነው።

ምክር ቤቱ በመግለጫው ከግንቦት 13/2016 አንስቶ የተጓዙ ሑጃጆች በረራ ያደረጉት በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በሳዑዲ አየር መንገድ መሆኑን ገልጿል።

መግለጫውን ከሰጡት መካከል የሆኑት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዐብዱልፈታህ ሙሐመድ፣ በርካታ ሑጃጆች ጉዞ ያደረጉት በኢትዮጵያ አየር መንገድ መሆኑን ገልፀዋል። ምክር ቤቱ ከላካቸው 12 ሺሕ ምዕመናን ውስጥ በአየር መንገዱ የበረሩ ሑጃጆች ቁጥር 8 ሺሕ 500 መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው፣ ቀሪዎች 3 ሺሕ 500 ሑጃጆች በሳዑዲያ አየር መንገድ በረራ ማድረጋቸውን አብራርተዋል። (ሚንበር ቲቪ)

(በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ ይታከልበታል)
🥰11👍42
አቢሲንያ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን በሚሰጥበት አቢሲንያ አሚን በኩል እያዘጋጀ በሚንበር ቲቪ የሚያቀርበው 2ተኛው ዙር አሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር፤ በተሳታፊዎች መካከል ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ለመሻገርና አንድ ሚሊየን ብር ለመሸለም የሚደረገው ብርቱ ፉክክር እንደቀጠለ ይገኛል።

ዛሬ ምሽት ከ1:30 ጀምሮ የሁለተኛው ምዕራፍ ዝግጅት ከአዳዲስ ተሳታፊዎችና የሥራ ፈጠራ ሃሳቦች እንዲሁም የተግባር ሙከራዎች ጋር ይቀርብላችኋል!!

#አቢሲንያ_አሚን
#ዕሴትዎን_ያከበረ!!
#አሚን_አዋርድ_2
#የሥራ_ፈጠራ_ውድድር

ዕለተ ቅዳሜ ሰኔ 1 - 2016 | ዙል ሒጃ 2 – 1445
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍11😍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አደራ እንዳትጭበረበሩ❗️

ሂጅራ ዘገባ

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/RM6pNAlCKOs 🔗

#የማጭበርበር_ወንጀል
#ሂጅራ_ዘገባ #ሂጅራ_ቢዝነስ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍4