የቁርኣን ተፍሲር በሐረሪ ቋንቋ - በሸይኽ የሕያ እስማዒል (ረ)
ሱረቱል ሩም 38-51
ዛሬ ምሽት 01:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ
#ቁርኣን #ተፍሲር #ሐረሪ
#ሸይኽ_የሕያ_እስማዒል_ረ
ዕለተ ረቡዕ ግንቦት 28 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 28 - 1445
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

💔2❤1
አያታቸው ሸይኽ አባታቸው ሸይኽ እሳቸው ቃዲ
ሸይኽ ዑመር ሁሴን የጎንደሩ ፈርጥ።
ሐጅ ሙሐመድ ሳኒ ወደ አኼራ እንደሄዱ የመጅሊስ መሪ የነበሩት ሸይኽ ዑመር ሁሴን ነበሩ። ባለፉበት የሕይወት መንገድ ሁሉ ለሀገር ያበረከቱት አስተዋጾ ይህ ነው የሚባል አይደለም። በንጉሡ ዘመን የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኛ በደርግ ዘመን የሸሪአ ፍርድ ቤት ቃዲ፣ የሐገር ሽማግሌ ታላቅ ሰው ዛሬ በሕይወት ገጽ ፕሮግራም ሕይወታቸውን ታሪካቸውን በክፍል-2 እንዳስሳለን። ምሽት ከ03:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን!
#የሕይወት_ገጽ #ሸይኽ_ዑመር_ሁሴን #የጎንደሩ_ፈርጥ

👍9
ለ12ኛ ክፍል ፈተና ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ በመታዘዙ ጫና ውስጥ መግባታቸውን ወላጆች ተናገሩ
ዕለተ ረቡዕ ግንቦት 28 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 28 – 1445 | ሚንበር ቲቪ
የትምህርት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ መረብ ለመስጠት እቅድ በያዘለት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና፣ በግል ትምህርት ቤት ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ወላጆች ልጆቻቸው የመፈተኛ ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ በመታዘዙ ጫና ውስጥ መግባታቸውን ተናገሩ፡፡
ሚኒስቴሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት በነበረው አሠራር በመንግሥትም ሆነ በግል ትምህርት ቤት የሚማሩ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞችን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲፈተኑ ቢያደረግም፣ በተያዘው ዓመት ከመደበኛው አሠራር በተጨማሪ ተማሪዎችን በተመረጡ አካባቢዎች በበይነ መረብ ለመፈተን እቅድ ይዟል፡፡ ለዚህ እንዲያግዝም ትምህርት ቤቶች ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ ትዕዛዝ መተላለፉንም የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሆኖም “በቂ የሆነ የላፕቶፕ አቅርቦት የለንም’ ያሉ አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ተፈታኞች በራሳቸው እንዲያሟሉ መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡ “ሚንበር ቲቪ” ያናገራቸው የተማሪዎች ወላጆች ይህ ውሳኔ ከፍተኛ ጫና ውስጥ እንደከተታቸው ተናግረዋል፡፡
በዘንድሮው ዓመት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የመንግሥትም ሆነ የግል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ለማስፈተን የመፈተኛ ላፕቶፖችን እና ከኔትዎርክ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ግብዓቶች ማሟላት እንደሚገባቸው ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ገልጧል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ያስተላለፈው ትዕዛዝ በራሳቸው በትምህርት ቤቶቹም ላይ ጫና ማሳረፉን “ሚንበር ቲቪ” ከትምህርት ቤቶች አስተዳደር ሠራተኞች ሰምቷል፡፡
አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ለመፈተኛ የሚውለውን የግል ላፕቶፕ ባለባቸው የአቅም ውስንነት ሙሉ ሉሙሉ ማቅረብ ባለመቻላቸው፣ ተማሪዎቹ በግል ላፕቶፕ ይዘው እንዲመጡ ማዘዛቸውን በተለያየ አካባቢ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤት አስተዳደር እና ርእሰ መምህራን ለ”ሚንበር ቲቪ” ገልጸዋል፡፡
ከትምህርት ቤቶቹ ውስጥ በዘንድሮው ዓመት 115 ተማሪዎችን ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተማሪዎችን የሚያስቀምጠው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የአወሊያ ትምህርት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰዒድ አስማረ፣ ለፈተና የሚያስፈልገው ላፕቶፕ ትምህርት ቤቱም ሆነ ተማሪዎቹ ላይ ጫና ማሳደሩን ለሚንበር ቲቪ ተናግረዋል፡፡ በዚህም ትምህርት ቤቱ ጫናውን ለመጋራት ተማሪዎች ላፕቶፑን በራሳቸው እንዲያሟሉ ትዕዛዝ ቢተላለፍም ትምህርት ቤቱ በተለይ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎችን የሚጠበቅበትን ለማሟላት ጥረቱን መቀጠሉን ጠቁመዋል። ሥራ አስኪያጁ ትምህርት ቤቱ የሚያደርገው ጥረት ሊሳካ የሚችል መሆኑን ርግጠኛ ሆኖ መናገር እንደማይቻል አክለዋል፡፡
የአዲስ አበባ የግል ትምህርት ቤቶች ማኅበር ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ ሐረገወይን ገረሱ በርካታ ትምህርት ቤቶች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባዘዘው መሠረት ዝግጅት እያደረጉ ቢሆንም አገልግሎቱ የመጀመሪያ በመሆኑ በፈተና ወቅት የኢንተርኔት መቆራረጥና ተመሣሣይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ያላቸውን ሥጋት ለመገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ትዕዛዙን ካስተላፈው የትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ 25 አካባቢዎች በበይነ መረብ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በወረቀት ከሐምሌ 3 እስከ 11/2016 ፈተናውን እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡ የማኅበራዊ ሣይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5/2016 ለፈተና የሚቀመጡ ሲሆን የተፈጥሮ ሣይንስ ተማሪዎች ደግሞ ከሐምሌ 9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ይወስዳሉ፡፡
ዝርዝሩን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://minbertv.com/?p=8308

👍10😱5❤1
#እናስታውስዎ
ከቀናት ሁሉ በላጮቹ የዙልሒጃ አሥር ቀናት እየደረሱ ነው!
ቀናቱን በተለያዩ የዒባዳ ተግባራት ማሳለፍ ድርብርብ ምንዳን የሚያስገኝ ሲሆን፤ ተከታዮቹን ዚክሮች (ላ ኢላሃ ኢለሏህ፣ አላሁ አክበርና አልሐምዱሊላህ) ማለትን ማብዛት እጅግ ተወዳጅ ተግባር መሆኑ በመልዕክተኛው (ﷺ) ሃዲስ ተወስቷል።
ተጨማሪ ለማንበብ ድረገጻችንን ይጎብኙ።
👉🏾 https://minbertv.com/?p=8324
#10ቱ_የዙልሒጃ_ቀናት
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ

👍22
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚሰጠው የስድስተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የጊዜ ሠሌዳ ላይ ለውጥ ተደረገ
ዕለተ ረቡዕ ግንቦት 28 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 28 – 1445 | ሚንበር ቲቪ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተቃውሞ የቀረበበት የስድስተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የጊዜ ሠሌዳ ላይ ለውጥ መደረጉ ታወቀ፡፡ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ፈተናው ከዒድ አል አድሐ በዓል ሁለት ቀናት በኋላ እንዲካሄድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የፈተና ቀን ለውጥ ያደረገው፣ የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ቀድሞ የተቀመጠው የፈተና የጊዜ ሠሌዳ ከዒድ አል አድሓ በዓል ጋር በመግጠሙ በተማሪዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳርፍ በመግለጽ የተቃውሞ ደብዳቤ ከጻፈ በኋላ ነው፡፡
የክልሉ እስልምና ጉዳዮ ከፍተኛ ምክር ቤት ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ደብዳቤ የጻፈው ግንቦት 21/2016 ነበር፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፣ የፈተናው ቀን ከበዓሉ ጋር በአንድነት መሰጠቱን በሕገ መንግስሥቱ የተቀመጠውን “የሃይማኖትን እኩልነት የሚጥስ” እንደሆነም ጠቅሷል፡፡
ለክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተቃውሞ ደብዳቤ ምላሽ የሰጠው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ የጊዜ ሠሌዳው ላይ ማሻሻያ በማድረግ የስድስተኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 12/2016 እንዲሰጥ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ትምህርት ቢሮው ውሳኔውን በደብዳቤ ማሳወቁን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሐጂ ያሲን ኸድር ለሚንበር ቲቪ ገልጸዋል፡፡ ከትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት መካሄዱን ያስታወሱት ፕሬዝዳንቱ፣ ቢሮው ውሳኔውን በክልሉ ለሚገኙ 12 ዞኖች እንዲደርስ ማድረጉንም ጠቁመዋል፡፡
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ስምንተኛ ክፍል ላይ ብቻ ይሰጥ የነበረውን ክልል አቀፍ ፈተና ከባለፈው የ2015 ትምህርት ዘመን አንስቶ ለስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች መስጠት መጀመሩ የሚታወቅ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)
በድረ ገጽ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://minbertv.com/?p=8311

👍5
🔴 የጥንቃቄ መልዕክት 🔴
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሁለት የወተት ምርቶች ላይ ባካሄደው የናሙና ምርመራ የጥራት መስፈርት ሳያሟሉ መገኘታቸውን አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ የጥራት መስፈርት አላሟሉም ያላቸው SULTAN INSTANT FULL CREAM MILK POWDER እና Nura Super Instant Full Cream Milk Powder የተባሉ የወተት ምርቶችን ነው፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በገበያ ላይ በመገኘት የገበያ ኢንስፔክሽን ሥራ በማከናወን ከገበያ ከተወሰደው ወካይ ናሙና ላይ በተደረገው የላቦራቶሪ ፍተሻ ውጤት መሠረት፣ የተደነገገውን የጥራት መስፈርት ሳያሟሉ የተገኙ ምርቶች በመሆናቸው ኅብረተሰቡ በ400 ግራም ባች ቁጥር የጠቀሰባቸውን ምርቶች እንዳይጠቀም ሲል አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀመው ያለው የSULTAN INSTANT FULL CREAM MILK POWDER ወተት የተመረተበት ጊዜ 19/02/2024፣ የሚያበቃበት ጊዜ ደግሞ 18/02/2015 ባች ቁጥሩ 56 ነው፡፡ በተመሳሳይ Nura Super Instant Full Cream Milk Powder የምርት ጊዜው 01/11/2023 እና የሚያበቃበት ጊዜ 31/10/2025 እንዲሁም የባች ቁጥሩ BT 23246006 የሆነውን ምርት ኅረተሰቡ እንዳይጠቀም ተብሏል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከላይ የተጠቀሱት ምርቶች በገበያ ቦታ እና ሱፐር ማርኬት ማንኛውም ነጋዴ ሆነ ግለሰብ ሲሸጥ ከተገኘ አስፈላጊው አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ ርምጃዎች እንደሚወሰድ ገልጧል፡፡

👍6👌6❤3🙏3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የተጣለ ምግብ ታጥቦ ድጋሚ ለምግብነት የሚቀርብበት ቦታ! 🥲
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/72fFhkGP3Wg 🔗
#ድህነት #አሳዛኝ
#ዳር_እስከ_ዳር #መወዳ_መዝናኛ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/72fFhkGP3Wg 🔗
#ድህነት #አሳዛኝ
#ዳር_እስከ_ዳር #መወዳ_መዝናኛ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስቃዪ ከሚበዛብሽ እስልምና ቢቀርብሽስ? | በእምባ ያራጨን ጥያቄ! 😭
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/eOidvKsEgsY 🔗
#ሂዳያ #ኢስላም
#የኔ_መንገድ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/eOidvKsEgsY 🔗
#ሂዳያ #ኢስላም
#የኔ_መንገድ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍23❤8😢7🙏2
ፍልስጤማዊው የቀድሞ የሜታ ባልደረባ በኩባንያው ላይ ክስ መሠረተ
ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 29 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 29 – 1445 | ሚንበር ቲቪ
ግዙፎቹን የማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ፌስቡክ፣ ዋትሳፕ እና ኢንስታግራምን የሚያስተዳድረው ሜታ ኩባንያ፣ በፍልስጤማዊ አሜሪካዊው የቀድሞ ባልደረባው ክስ ተመሠረተበት፡፡ የኩባንያው የቀድሞ ባልደረባ ሜታ ፍልስጤምን ከተመለከቱ ይዘቶች ጋር በተገናኘ አላግባብ እንዳሰናበተው ጠቅሷል፡፡
ፈራህ ሐማድ የተባለው የቀድሞው የሜታ ባልደረባ፣ ክሱን የመሠረተው በካሊፎርንያ ግዛት ነው፡፡ በኩባንያው ውስጥ እ.እ.አ ከ2021 አንስቶ ያገለገለው የምሕንድስና ባለሞያው ፈራህ ሐማድ፣ በኩባንያው ውስጥ በሚሠራበት ጊዜ በባልደረቦች መካከል ፍልስጤምን በተመለከተ የሚደረጉ የመልዕክት ልውውጦች ይሰረዙ እንደነበር ተናግሯል፡፡
የቀድሞው የሜታ ባልደረባ ይሰረዙብን ነበር ካላቸው መልዕክቶች ውስጥ በጋዛ የሚገኙ ዘመዶቻቸውን ኅልፈት የሚያረዱ ይገኙበታል፡፡ ሐማድ ከባልደረቦቹ ጋር በነበረው ልውውጥ የፍልስጤምን ሰንደቅ የያዘ ስሜት ገላጭ ምሥል (emoji) መጠቀማቸውም ምርመራ እንዲካሄድባቸው ማድረጉንም በክሱ ላይ አስቀምጧል፡፡ ሐማድ እንደገለጸው ከሆነ ኩባንያው ፍልስጤምን ለተመለከቱ የመልዕክት ልውውጦች እርምጃ ቢወስድም፣ ሌሎች ባልደረቦች በተመሳሳይ አውድ ውስጥ የእስራኤል አልያም የዩክሬንን ሰንደቅ ሲጠቀሙ በዝምታ አልፎታል፡፡
ሐማድ ለፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ የቀድሞ አሠሪው ሜታ ፍልስጤምን የተመለከቱ ቪድዮዎችን ከአውድ ውጪ በመተርጎም ፀያፍ ይዘት ካላቸው ምድብ ውስጥ እንደሚያካትት የገለጸ ሲሆን፣ ለዚህ በማሳያነት የጠቀሰው በፍልስጤማዊው የፎቶ ጋዜጠኛ ሞታዝ አዛይዛ የተቀረጸ በጋዛ የሚገኝ ሕንጻ ሲወድም የሚያሳይ ምሥልን ነው፡፡ ሐማድ በኩባንያው ይካሄዳሉ ያላቸውን ድርጊቶች ለማረም ሲንቀሳቀስ ሜታ እንዳሰናበተውም አስታውቋል፡፡
ግዙፉ ሜታ እስራኤል በጋዛ እየፈጸመች የምትገኘውን ጥቃት ተከትሎ ከባልደረቦቹ ተመሳሳይ ክስ የሚቀርብበት ነው፡፡ ኩባንያው በተደጋጋሚ ለፍልስጤም ድጋፍ የሚሰጡ ድምጾች እንዲታፈኑ ያደርጋል በሚል ነው ክሱ የሚሰማበት፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም ቁጥራቸው ወደ 200 የሚጠጋ የኩባንያው ሠራተኞች ለባለቤቱ ማርክ ዙከርበርግ የቅሬታ ደብዳቤ ጽፈዋል፡፡
እስራኤል ባለፉት ወራት በጋዛ እየፈጸመችው በሚገኘው ጥቃት ሕፃናት እና እናቶችን ጨምሮ ቢያንስ 35 ሺሕ ንጹሐን ተገድለዋል፡፡ እስራኤል የምትፈጽውን ጥቃት አሉታዊ ምሥል ለመስጠት በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ላይ ሐሰተኛ መልዕክት የሚያሠራጩ ቦቶችን እንደምትጠቀም በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

👍13😱1
🗣 #እናስታውስዎ!
ምናልባት ዛሬ የወሩ መጨረሻ ከሆነ:-
ከዛሬ ዕለተ ሐሙስ በኋላ «ኡዱሒያ» ማድረግ የፈለገ ሰው
ከፀጉሩም ይሁን ከጥፍሩ ምንም ነገር መንካት አይፈቀድለትም።
ስለዚህ...
💇♂️ ፀጉሩን መቁረጥ፣
✂️ ጥፍሩን መቁረጥ፣
✂️ ቀድሞ ቀመሱን ማሳጠር፣
✂️ ሌላ አካሉ ላይ ያሉ ፀጉሮችን ማስወገድ
የፈለገ ሰው ከዛሬ ሐሙስ ማሳለፍ የለበትም።
ውዱ ነብያችን የአላህ ሰላትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና እንዲህ ይሉናል፦
«إذا دخلت العشر، وأراد أحدكم أن يُضحي فلا يمس من شعره وبشره شيئًا»
«አስሩ ቀናት ሲገቡ ከእናንተ አንደኛችሁ ኡዱሒያ ማድረግ ከፈለገ ከፀጉሩም ይሁን ከሰውነቱ ምንም ነገር እንዳይነካ።»
ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 29 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 29 - 1445

👍20
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሰሃባን ትውልድ ማየት የፈለገ ፍልስጤምን ይመልከት!
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/fd5JHb4uXls 🔗
#ፍልስጤም
#ሰሞነ_ሐጅ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/fd5JHb4uXls 🔗
#ፍልስጤም
#ሰሞነ_ሐጅ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍22
ልዩ ኸበር - ለሐጅ የሚደረገው ‘ሌላኛው ፍልሚያ’
ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 29 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 29 – 1445 | ሚንበር ቲቪ
ሳዑዲ ዐረቢያ በዘንድሮው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ክንውን ለመሳተፍ ከመላው ዓለም ሀገራት የተነሱ ምዕመናንን መቀበሏን እንደቀጠለች ነው፡፡ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ይፋ ያደረጓቸው መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ እስካሁን ድረስ ሳዑዲ ዐረቢያ የገቡ ምዕመናን ቁጥር አንድ ሚሊዮን ደርሷል፡፡ ከአንድ ሳምንት በታች ለቀረው የሐጅ ክንውን፣ በቀጣይ ቀናት ሌሎች አንድ ሚሊዮን ምዕመናን ወደ ሀገሪቱ ይዘልቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሳዑዲ ዐረቢያ እንግዶቹን የምታስተናግደው ለሥነ ሥርዐቱ ብቻ በሚል የተለየ ቪዛ አዘጋጅታ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት የሐጅ ቪዛ ከያዙ ምዕመናን ውጪ ሌሎች እንግዶች ወደ ሀገሬ ቢገቡም ወደ ቅድስቲቱ መካ ከተማ እንዲዘልቁ አልፈቅድም በማለት የከተማዋን በሮች ቆልፋለች፡፡
ሀገሪቱ ከዚህ ቀደም እንዳስታወቀችው፣ የመካ በር ከተቆለፈ በኋላ ማንኛውም ምዕመን በየትኛውም ምክንያት በድንገት መካ ከተማ ውስጥ ያለ ሐጅ ቪዛ ቢገኝ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ ሳዑዲ መቀጮ የሚያስከፍለውን ደንብ ያወጣችው በሥነ ሥርዐቱ ወቅት ሊከሰት የሚችለውን መጨናነቅ ለመቀነስ ነው፡፡ ሳዑዲ ዐረቢያ ይህን እርምጃ ይበልጥ ያጠናከረችው ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ሚና ላይ አደጋ ከተከሰተ በኋላ ነው፡፡ ምዕመኑን ብቻ ሳይሆን የትራንስፖርት አገልግሎት የሰጡትንም ጭምር የሚያስቀጣውን ደንብ የጣሱ ምዕመናን፣ በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሳዑዲ ዐረቢያ ጋዜጦች መዘገብ ጀምረዋል፡፡
ሳዑዲ ቁጥጥሩን ጠበቅ ብታደርግም፣ የመጣውን ለመቀበል የቆረጡ ከመላው ዓለም የተለያዩ ሀገራት ቀደም ብለው የተነሱ ምዕመናን የሐጅ ቪዛ በእጃቸው ሳያስገቡ መካ ውስጥ እንደሚገኙ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡ እነዚህ ምዕመናን መካ ውስጥ የሚገኙት ሐጅ ሲጀመር ሥነ ሥርዐቱን ለመከወን ነው፡፡ ምዕመናኑ ይህን መንገድ የመረጡት በአብዛኛው ከገንዘብ ጋር በተገናኘ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡
ከእነዚህ ውስጥ የሆነው መገናኛ ብዙኃኑ የአባቱን ሥም ያልጠቀሱት ግብጻዊው ሙሐመድ፣ በአሁኑ ወቅት መካ ውስጥ በሚገኝ አፓርታማ ውስጥ በመቀመጥ የሐጅ ሥነ ሥርዐት እስኪጀመር ድረስ እየተጠባበቀ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ሙሐመድ ለምን ይህን እንዳደረገ ሲጠየቅ፣ ወጪ ቆጣቢ ሐጅ ለመፈጸም ነው ብሏል፡፡ የሙሐመድ ሀገር ግብጽ ለሐጅ ሥነ ሥርዐት 175 ሺሕ (የግብጽ) ፓዉንድ ታስከፍላለች፡፡ ሙሐመድ ከዚህ በተጨማሪም ሌላ ምክንያት ይጠቅሳል፤ ግብጽ በምከተለው የሐጅ አሠራር መሠረት ለአሥር ዓመት የሐጅ ዕድል ለማግኘት ዕጣ ይደርሰኛል ብሎ ቢጠባበቅም አልተሳለትም፡፡ ስለዚህ በቱሪስት ቪዛ መካ በመግባት ቀኑ እስኪደርስ ራሱን ከፀጥታ አካላት መሸሸግ መርጧል፡፡
ሳዑዲ ዐረቢያ በየዓመቱ የሐጅ ቪዛ ሰጥታ ከምታስተናግዳቸው እንግዶች ውጪ ቢያንስ 100 ሺሕ ምዕመናን ሳይፈቀድላቸው በሥነ ሥርዐቱ ላይ እንደሚታደሙ ትገልጻለች፡፡ (ሚንበር ቲቪ)
በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=8329

👍16❤2
ዱንያ ላይ ካሉ ቀናት ሁሉ በላጮቹና እጅግ ተወዳጆቹ የዙልሒጃ አስር ቀናት ደጅ ላይ ቆመን፤ ስለ ቀናቱ ትሩፋትና አጠቃላይ ስለ ሐጅ ዓላማና የአፈጻጸም ሥርዓት የተወያየንበት ተወዳጁ የኸሚስ ምሽት ፕሮግራማችን ምሽት ከ2፡00 ጀምሮ ወደናንተ ይደርሳል፡፡
ሸይኻችን በሰዓታቸው ለሐጅ ጉዞ የተመረጡ አማኞች የሐጅ ተግባራትን በአግባቡ አከናውነው ካጠናቀቁ በኋላ በተለይ በመዲና በሚኖራቸው የዚያራ ቆይታ ጨርሶ መዘንጋት የሌለባቸውን ስፍራዎችና አዳቦች እያወሱ የሚቆዩ ሲሆን፤ ተወዳጁ ኡስታዛችን ኡስታዝ በድር ሁሴን ደግሞ የአሥርቱን የዙልሒጃ ቀናት ደረጃና የሐጅን ዐቢይ ግብና ዓላማዎች ካለንበት ተጨባጭ ጋር እያስተሳረ ውብ ሃሳቦቹን ያካፍለናል፡፡
#ለይሉ_ጁምዓ_ነው!
#ፕሮግራሙ_ደግሞ_ኸሚስ_ምሽት!
ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 29 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 29 - 1445
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
ሸይኻችን በሰዓታቸው ለሐጅ ጉዞ የተመረጡ አማኞች የሐጅ ተግባራትን በአግባቡ አከናውነው ካጠናቀቁ በኋላ በተለይ በመዲና በሚኖራቸው የዚያራ ቆይታ ጨርሶ መዘንጋት የሌለባቸውን ስፍራዎችና አዳቦች እያወሱ የሚቆዩ ሲሆን፤ ተወዳጁ ኡስታዛችን ኡስታዝ በድር ሁሴን ደግሞ የአሥርቱን የዙልሒጃ ቀናት ደረጃና የሐጅን ዐቢይ ግብና ዓላማዎች ካለንበት ተጨባጭ ጋር እያስተሳረ ውብ ሃሳቦቹን ያካፍለናል፡፡
#ለይሉ_ጁምዓ_ነው!
#ፕሮግራሙ_ደግሞ_ኸሚስ_ምሽት!
ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 29 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 29 - 1445
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍24❤4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፆም ነፍሳችንን ያንጻል!
ነፍሳችን ከተስተካከለች ደግሞ ሙሉ ህይወታችን ይስተካከላል።
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/nnrG4c_CtPg 🔗
#ፆም #ነፍስያን_መግራት
#በይቱል_ሐቢብ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
ነፍሳችን ከተስተካከለች ደግሞ ሙሉ ህይወታችን ይስተካከላል።
ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/nnrG4c_CtPg 🔗
#ፆም #ነፍስያን_መግራት
#በይቱል_ሐቢብ
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍6🥰1
ጁምዓ ሙባረክ!
إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَـٰٓئِكَتَهُۥ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِىِّ ۚ يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ صَلُّوا۟ عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا۟ تَسْلِيمًا (56)
"አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ። እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ። የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ።" - (ሱረቱል አሕዛብ 33፡56)
የተከበሩት የዙልሒጃ አስቱ ቀናት መጀመርያ ላይ እንገኛለን። ቀኑም ጁምዓ ነው። ሶላዋት በማውረድ እና ኸይራት በማብዛት መልካም ምንዳ እንሸምት።

👍18❤7
የሬሜዲያል ፈተና የጊዜ ሠሌዳ ለውጥ ማድረጉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
• የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የጊዜ ሠሌዳውን በተመለከተ ቅሬታ ማቅረቡ ተሰምቷል
የትምህርት ሚኒስቴር የሬሚዲያል (የማካካሻ) ትምህርት የማጠቃለያ ፈተና ላይ የጊዜ ሠሌዳ ለውጥ ማድረጉን ዛሬ ጁመዓ ግንቦት 30/2016 አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ የፈተና ቀን ለውጡን ያደረገው ከዒድ አል አድሓ በዓል ጋር በተመሣሣይ ቀን በመዋሉ ነው ብሏል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ቀድሞ ባስቀመጠው ጊዜያዊ የጊዜ ሠሌዳ ላይ ፈተናው የሚሰጠው ከሰኔ 3 እስከ 10/2016 የነበረ ቢሆንም፣ በአዲሱ የጊዜ ሠሌዳ የአንድ ቀን ጭማሪ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሠረት ሰኔ 9 ይሰጥ የነበረው ፈተና ወደ ሰኔ 11 ተዘዋውሯል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር የቀን ለውጥ ያደረገው ሰኔ 9/2016 የዒድ አል አድ በዓል ስለሚከበር መሆኑን ገልጧል፡፡
የትምህር ሚኒስቴር ቀድሞ ያወጣውን የጊዜ ሠሌዳ በተመለከተ ከዒድ አድሓ በዓል ጋር በተመሳሳይ ቀን ከመዋሉ ጋር በተገናኘ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቅሬታ ማቅረቡን ሚንበር ቲቪ ከምክር ቤቱ ኃላፊዎች ሰምቷል፡፡
የትምህር ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ከእስልምና በዓላት ጋር በተመሳሳይ ጊዜ በሚያወጣው የፈተና የጊዜ ሠሌዳ ተደጋጋሚ ቅሬታ የሚቀርብበት ነው፡፡
ዝርዝሩን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://minbertv.com/?p=8346

👍19🥰2