Minber TV
44.6K subscribers
15.3K photos
2.37K videos
36 files
7.99K links
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
ይከታተሉ፣ ለወዳጅዎ ያጋሩ!

📡 ሳተላይት ፡ EthioSAT 11545/45000/H
📱 የሶሻል ሚድያ አድራሻዎቻችን ፡ https://linktr.ee/minbertv
Download Telegram
እነሆ አዲስ ምዕራፍ ከቢልኮር፣ የ9ኛ ዙር ስልጠና  በአዲስ ስፍራ!!

ቢልኮር የአመራርነት ስልጠናና የምርምር ተቋም ባለፉት 8 ተከታታይ ዙር ስልጠናዎች ከ700 በላይ ተማሪዎችን  በተለያዩ ስልጠናዎች በስኬት አሰልጥኗል ። እርሶም የዚህን ዙር ልዩ ስልጠናዎች በመታደም የስኬት መንገድዎን እውን ያደርጉ ዘንድ ይጋብዛል!!

በዚህ ዙር የያዝናቸው ስልጠናዎች:-

1.The Art of Emotional Intelligence and Success(የስሜት ብልህነት እና ስኬት)

2. The Art of Self Leadership (ራስን የመምራት ጥበብ)

📍ማሳሰቢያ:- ስልጠናው ሰኔ 1/2016ዓ. ል ይጀምራል!!

እንዲሁም ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪም ለድርጅትዎ Organizational Leadership ስልጠናዎች አዘጋጅተናል!

📍የስልጠና ቦታ:-ብስራተ ገብርኤል አዶት ሲኒማ  4ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር
☎️ 0979963535 ይደውሉ!!

አሊያም:-
ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን አሁኑኑ ፈጥነው ይመዝገቡ!!!

https://surveyheart.com/form/662f5d3b782cd61bd419fa55
👍7
በትምህርት ተቋማት ውስጥ ከሚደረግ አለባበስ ጋር በተገናኘ አፈጻጸሙ በትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ እንዲወሰን ተደረገ
👍17
በትምህርት ተቋማት ውስጥ ከሚደረግ አለባበስ ጋር በተገናኘ አፈጻጸሙ በትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ እንዲወሰን ተደረገ
 
ዕለተ ማክሰኞ ግንቦት 27 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 27 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

በሰላም ሚኒስቴር የቀረበው የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ በትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚኖረውን አለባበስ የተመለከተውን አፈጻጸም ትምህርት ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ እንዲወሰን አደረገ፡፡ በተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተከናወነ የመጨረሻ የተባለ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ቅሬታውን አቅርቧል፡፡

በሚኒስቴሩ ከዚህ ቀደም የተረቀቀው አዋጅ በስድስት ክፍሎች እና በ32 አንቀጾች የተዘጋጀ ነበር፡፡ ቀዳሚውን ረቂቅ አዋጅ የተቃወመው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ “ነባር ችግሮችን ከመቅረፍ ይልቅ የሚያባብሱና ተጨማሪ ችግሮችን የሚያስከትሉ” አንዳንድ ድንጋጌዎች እንዳሉበት ጠቁሞ ነበር፡፡

ምክር ቤቱ በወቅቱ በዋና ጸሐፊው ሐጂ ሐሚድ ሙሣ በጻፈው ደብዳቤ፣ ረቂቅ አዋጁ የእስልምናን “ልዩ የአምልኮ ባሕርያት ተረድድቶ ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ይልቅ አምልኮ መከልከል ላይ” ያተኮረ ነው በሚል ትችት አቅርቦበታል፡፡ የሰላም ሚኒስቴር የአዋጁን ረቂቅ ለምክር ቤቱ በጽሑፍ ሳያደርስ መቅረቱም በወቅቱ በቅሬታ የቀረበ ጉዳይ ሆኖ አልፏል፡፡

ባቀረበው ረቂቀ አዋጅ ላይ ቅሬታ የተሰማበት የሰላም ሚኒስቴር፣ ባለፈው ሳምንት ግንቦት 20/2016 የተሻሻለው ነው ያለውን ረቂቅ በማቅረብ የመጨረሻውን የግብዓት ማሰባሰብ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ አካሄዷል፡፡ በዚህ የግብዓት ማሳባሰቢያ ላይ ከእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አምስት ተወካዮች መሳተፋቸውን “ሚንበር ቲቪ” ሰምቷል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙ የምክር ቤቱ ተወካዮች በዋነኛነት ቅሬታ ካቀረቡባቸው ጉዳዮች ውስጥ በአንቀጽ 15 ላይ የተጠቀሰው የአምልኮ እና አስተምህሮ አተገባበር ይገኝበታል፡፡ “ሚንበር ቲቪ” የተመለከተውና ተሻሽሎ በቀረበው አዋጅ ላይ የተካተተው አንቀጽ “በመኖሪያ አካባቢዎች፣ ማጓጓዣዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የአየር መንገድ ተርሚናሎች፣ ወታደራዊ ካምፕ፣ ሕክምና ቦታዎች፣ በሕዝብ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች” ላይ ሃይማኖታዊ ተግባራትን ማከናወን ከልክሏል፡፡ የምክር ቤቱ ተወካዮች በዚህ አንቀጽ ውስጥ በተካተቱት ዝርዝሮች ላይ ያላቸውን ተቃውሞ በማሰማት አንቀጹ እንዲሰረዝ አቤቱታ ማቅረባቸው ነው የታወቀው፡፡  

በተመሳሳይ ረቂቅ አዋጁ በአንቀጽ 17 ላይ የመንግሥት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ረቂቁ በዚህ አንቀጽ ስር “በመንግሥት ተቋም ቅጥር ግቢ ወይም ቢሮ ውስጥ በመሆን ሃይማኖታዊ ትምህርትን ማስተማር ወይም በቡድን የአምልኮ ተግባር ማከናወን” የተከለከለ መሆኑን አስፍሯል፡፡

በሌላ በኩል በአዋጁ አንቀጽ 19 የተቀመጠው ከዚህ ቀደም በተለይ በሙስሊም ተማሪዎች ቅሬታ ሲቀርብበት የቆየው “መደበኛ ትምህርት እና ሃይማኖታዊ ተግባራት”ን የተመለከተው ጉዳይ ነው፡፡ የሰላም ሚኒስቴር መጀመሪያ ባዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ በዚህ አንቀጽ ስር በማንኛውም የትምህርት ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ ሃይማኖታዊ ትምህርትን ማስተማር ውም በቡድን ማምለክን ይከለክል ነበር፡፡

ሃይማኖታዊ አለባበስን በተመለከተም “ማንነትን ለመለየት በሚያስችል መልኩ” ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚገባ ጠቅሶ ነበር፡፡ ሆኖም በተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ ላይ በትምህርት ተቋም ቅጥር ግቢ የሚደረገው ሃይማኖታዊ ተግባር “የመንግሥትና ሃይማኖትን መለያየት መርህን እና የሃይማኖት ነጻነትን በጠበቀ መልኩ መከናወን አለበት” በሚል የተካ ቢሆንም የዚህ አንቀጽ ዝርዝር አፈጻጸም የተተወው ትምህርት ሚኒስቴር ለሚያወጣው መመርያ ነው፡፡

“ሚንበር ቲቪ” ያናገራቸውና በግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሕግ ክፍል ባልደረባ የሆኑት የሕግ ባለሞያው አቶ ሳቢር ይርጉ፣ አዋጁ ወደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ከመመራቱ በፊት ለውይይት መቅረቡን በአዎንታዊ ቢጠቅሱም አዋጁ አሻሚ ጉዳዮች እንዳሉበት ገልጸዋል፡፡

አቶ ሳቢር በረቂቅ አዋጁ ላይ በርካታ ጉዳዮች በቀጣይ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ለሚወጡ መመርያዎች መተዉ ቀድሞ የነበረውን ሙስሊሞች ቅሬታ ሲያቀርቡበት የቆዩትን አሠራር የሚደግም እንዳይሆን ያላቸውን ሥጋትም አጋርተዋል፡፡ የሕግ ባለሞያው በዚህ አዋጅ ላይ የተካተቱ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚወጡ መመሪያዎች የግለሰብ ፍላጎቶችን ማራመጃ እንደነበሩም በማስታወስ ጉዳዩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው መድረክ ላይ በቅሬታ መነሳቱንም አስረድተዋል፡፡  

የሰላም ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት የመጨረሻ ያለውን ግብዓት በሰበሰበበት መድረክ የተነሱ ሐሳቦችን በግብዓትነት በመውሰድ በቀጣይ ለሚመለከተው አካል የሚቀርበውን ረቂቅ አዋጅ እንደሚያዘጋጅ አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ በተለያዩ ሁለተኛ ደረጃ እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለበርካታ ዓመታት ሙስሊም ተማሪዎች ከአለባበስ እና ሰላት ጋር በተገናኘ በሚደረጉ ክልከላዎች ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ እንዲሆኑ ጫና ማሳደሩ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ ጉዳዩ በተማሪዎች፣ በማኅበረሰብ ተወካዮች እንዲሁም በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላ ምክር ቤት የማስተካከያ ርምጃ እንዲወሰድ ሲጠየቅበት የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍184
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እነሆ አዲስ ምዕራፍ ከቢልኮር፣ የ9ኛ ዙር ስልጠና  በአዲስ ስፍራ!!

ቢልኮር የአመራርነት ስልጠናና የምርምር ተቋም ባለፉት 8 ተከታታይ ዙር ስልጠናዎች ከ700 በላይ ተማሪዎችን  በተለያዩ ስልጠናዎች በስኬት አሰልጥኗል ። እርሶም የዚህን ዙር ልዩ ስልጠናዎች በመታደም የስኬት መንገድዎን እውን ያደርጉ ዘንድ ይጋብዛል!!

በዚህ ዙር የያዝናቸው ስልጠናዎች:-

1.The Art of Emotional Intelligence and Success(የስሜት ብልህነት እና ስኬት)

2. The Art of Self Leadership (ራስን የመምራት ጥበብ)

📍ማሳሰቢያ:- ስልጠናው ሰኔ 1/2016ዓ. ል ይጀምራል!!

እንዲሁም ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪም ለድርጅትዎ Organizational Leadership ስልጠናዎች አዘጋጅተናል!

📍የስልጠና ቦታ:-ብስራተ ገብርኤል አዶት ሲኒማ  4ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር
☎️ 0979963535 ይደውሉ!!

አሊያም:-
ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን አሁኑኑ ፈጥነው ይመዝገቡ!!!

https://surveyheart.com/form/662f5d3b782cd61bd419fa55
👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሳይንሳዊ የጾም ጥቅሞች!
ፆም አላህ ያዘዘልን መድሃኒት ነው!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/nnrG4c_CtPg 🔗

#ጾም #ዙልሒጃ #ዓረፋ
#በይቱል_ሓቢብ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍5
ከስምንት ሺሕ በላይ ኢትዮጵያዊያን ሑጃጆች ሳዑዲ ዐረቢያ መድረሳቸው ታወቀ
👍15🥰1👌1
ከስምንት ሺሕ በላይ ኢትዮጵያዊያን ሑጃጆች ሳዑዲ ዐረቢያ መድረሳቸው ታወቀ

ዕለተ ማክሰኞ ግንቦት 27 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 27 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

የኢትየጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እስከ ዛሬው እለት ድረስ 8 ሺሕ 190 ምዕመናንን ወደ ሳዐዲ ዐረቢያ መላኩን አስታወቀ፡፡ እንግዶቹን የምታስተናግደው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ ወደ ሀገሯ የገቡ ምዕመናን ቁጥር አንድ ሚሊዮን እየደረሰ መሆኑን ገልጻለች፡፡

ለዘንድሮው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ኢትዮጵያ 12 ሺሕ ምዕመናንን እንደምትልክ ይታወቃል። ከምዕመናኑ ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ተጓዦች ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ያመሩት ግንቦት 13/2016 ነበር።

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተከናወነው በረራ 8 ሺሕ 190 ኢትዮጵያውያን ምዕመናን ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ መጓዛቸውን በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ እና የሐጅ ኮሚቴ የሲስተም ተጠሪ አቶ አንዋር ሙስጠፋ ለሚንበር ቲቪ ገልጸዋል።

ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 27/2016 ሌሊት በረራዎች እንደሚከናወኑ የጠቆሙት አቶ አንዋር፣ በነዚህ በረራዎች ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ምዕመናን ቁጥር ወደ ዘጠኝ ሺሕ እንደሚጠጋ አስረድተዋል። ምክር ቤቱ ሑጃጆቹን የሚልከው እስከ ሰኔ 2/2016 ድረስ መሆኑንም ከዚህ ቀደም አስታውቋል፡፡

ከግንቦት 1 አንስቶ ከመላው ዓለም ምዕመናንን የምትቀበው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ እስካሁን ድረስ ወደ አንድ ሚሊዮን እየደረሱ መሆኑ አስታውቃለች። የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ይፋ ያደረጉት እስከ እሑድ የመጨረሻ ሰዓት ድረስ ያለውን መረጃ ነው።

ባለሥልጣናቱ ይፋ ባደረጉት አሐዝ መሠረት ከተለያዩ ሀገራት ሳዑዲ የደረሱ ምዕመናን ቁጥር 935 ሺሕ 966 ነው፡፡ በባሕር፣ በየብስ እና በአየር ወደ ሳዑዲ ከገቡት ምዕመናን ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት በአየር ተሳፍረው መዲና የደረሱት ናቸው፡፡ እነዚህ ምዕመናን ቁጥራቸው 896 ሺሕ 287 መሆኑን የገለጹት የሳዑዲ ዐረቢያ ባለሥልጣናት፣ 37 ሺሕ 280 በየብስ እንዲሁም 2 ሺሕ 399 ምዕመናን ደግሞ በባሕር ሀገራችን ገብተዋል ብለዋል፡፡

ሳዑዲ ዐረቢያ በዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት ከመላው ዓለም የምትቀበላቸው ምዕመናን ብዛት ከሁለት ሚሊዮን ይሻገራል ተብሎ ይጠበቃል።

በድረ ገጽ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፦ https://minbertv.com/?p=8290

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
7👍5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#እናስታውስዎ

ከቀናት ሁሉ በላጮቹ የዙልሒጃ አሥር ቀናት እየደረሱ ነው!
ቀናቱን በተለያዩ የዒባዳ ተግባራት ማሳለፍ ድርብርብ ምንዳን የሚያስገኝ ሲሆን፤ ተከታዮቹን ዚክሮች (ላ ኢላሃ ኢለሏህ፣ አላሁ አክበርና አልሐምዱሊላህ) ማለትን ማብዛት እጅግ ተወዳጅ ተግባር መሆኑ በመልዕክተኛው (ሰ ዐ ወ) ሃዲስ ተወስቷል።

#10ቱ_የዙልሒጃ_ቀናት
#እናስታውስዎ

ዕለተ ማክሰኞ ግንቦት 27 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 27 - 1445
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍222
በአዲሱ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ መሠረት ውል መፈፀም ሊጀመር ነው
በአዲሱ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ መሠረት ውል መፈፀም ሊጀመር ነው

ዕለተ ማክሰኞ ግንቦት 27 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 27 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግል ቤት አከራይ እና ተከራይ በአዲሱ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ መሠረት ውል መፈፀም የሚጀምሩበትን ቀን ይፋ አደረገ። የከተማ አስተዳደሩ ውል ለመፈፀም የአንድ ወር ጊዜ አስቀምጧል።

የከተማ አስተዳደሩ ውል ለመፈፀም የጊዜ ሠሌዳው ያስቀመጠለት አዲሱ አዋጅ፣ በመጋቢት ወር መገባደጃ በሕዝብ ተወካዮች ምክር የፀደቀ መሆኑ ይታወቃል። በአዋጁ ድንጋጌዎች ላይ ከዚህ ቀደም የተደረገ ማንኛውም የአከራይ እና ተከራይ ስምምነት እንዲቋረጥ ካልተደረገ በስተቀር በአግባቡ መረጋገጥ እና መመዝገብ እንዳለበት ሠፍሯል።

ውሉ መመዝገብ እና መረጋገጥ ያለበት በአዲሱ አዋጅ መሠረት የሚቋቋመው ተቆጣጣሪ አካል በተሰየመ በ30 ቀናት ውስጥ እንደሆነ የተቀመጠ ቢሆንም የውል ማረጋገጫ እና የምዝገባ ጊዜውን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ ሦስት ወር ድረስ ሊራዝም እንደሚችልም ተደንግጓል።

በዚህ መሠረት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አዋጁን በመመሪያ በማስደገፍ  ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅት ማጠናቀቁን ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 27/2016 አስታውቋል። ቢሮው የግል መኖሪያ ቤት አከራይ እና ተከራይ ሰነዶቻቸውን በማሟላት ከሰኔ 1 እስከ ሰኔ 30/2016 ድረስ ውል መፈፀም እንደሚችሉ ገልጿል። የውል መፈፀሙ ሒደት ከሥራ ሰዓት ውጪ በምሽት ጭምር የሚካሄድ መሆኑንም የቢሮው ኃላፊዎች ጠቁመዋል።

በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እንዲሁም በክልሎች የሚቋቋም ተቆጣጣሪ አካል በሚወስነው መሠረት ተግባራዊ በሚደረገው አዋጅ፣ የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ የሚቻለው በየዓመቱ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ ዓመት በሚጸና ተመን ነው። የተቆጣጣሪ አካሉ ጭማሪውን የሚያደርገው የሀገሪቱን ነባራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነም ተቀምጧል።

በድረ ገጽ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፦ https://minbertv.com/?p=8300

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍207👏2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሓፊዝ ስትሆን ቁርአንን በልብህ መያዝ አለብህ!

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/kvWkM595H_Y 🔗

#ሓፊዝ #ቁርአን
#ከቁርአን_ጋር

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍16😍21👏1
የቁርኣን ተፍሲር በሐረሪ ቋንቋ - በሸይኽ የሕያ እስማዒል (ረ)

ሱረቱል ሩም 38-51

ዛሬ ምሽት 01:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ

#ቁርኣን #ተፍሲር #ሐረሪ
#ሸይኽ_የሕያ_እስማዒል_ረ  

ዕለተ ረቡዕ ግንቦት 28 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 28 - 1445
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
💔21
አያታቸው ሸይኽ አባታቸው ሸይኽ እሳቸው ቃዲ
ሸይኽ ዑመር ሁሴን የጎንደሩ ፈርጥ።

ሐጅ ሙሐመድ ሳኒ ወደ አኼራ እንደሄዱ የመጅሊስ መሪ የነበሩት ሸይኽ ዑመር ሁሴን ነበሩ። ባለፉበት የሕይወት መንገድ ሁሉ ለሀገር ያበረከቱት አስተዋጾ ይህ ነው የሚባል አይደለም። በንጉሡ ዘመን የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኛ በደርግ ዘመን የሸሪአ ፍርድ ቤት ቃዲ፣ የሐገር ሽማግሌ ታላቅ ሰው ዛሬ በሕይወት ገጽ ፕሮግራም ሕይወታቸውን ታሪካቸውን በክፍል-2 እንዳስሳለን። ምሽት ከ03:00 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን!

#የሕይወት_ገጽ  #ሸይኽ_ዑመር_ሁሴን #የጎንደሩ_ፈርጥ

ዕለተ ረቡዕ ግንቦት 28 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 28 - 1445
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍9
ለ12ኛ ክፍል ፈተና ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ በመታዘዙ ጫና ውስጥ መግባታቸውን ወላጆች ተናገሩ
💔10
ለ12ኛ ክፍል ፈተና ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ በመታዘዙ ጫና ውስጥ መግባታቸውን ወላጆች ተናገሩ

ዕለተ ረቡዕ ግንቦት 28 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 28 – 1445 | ሚንበር ቲቪ


የትምህርት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ መረብ ለመስጠት እቅድ በያዘለት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና፣ በግል ትምህርት ቤት ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ወላጆች ልጆቻቸው የመፈተኛ ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ በመታዘዙ ጫና ውስጥ መግባታቸውን ተናገሩ፡፡

ሚኒስቴሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት በነበረው አሠራር በመንግሥትም ሆነ በግል ትምህርት ቤት የሚማሩ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞችን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲፈተኑ ቢያደረግም፣ በተያዘው ዓመት ከመደበኛው አሠራር በተጨማሪ ተማሪዎችን በተመረጡ አካባቢዎች በበይነ መረብ ለመፈተን እቅድ ይዟል፡፡ ለዚህ እንዲያግዝም ትምህርት ቤቶች ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ ትዕዛዝ መተላለፉንም የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሆኖም “በቂ የሆነ የላፕቶፕ አቅርቦት የለንም’ ያሉ አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ተፈታኞች በራሳቸው እንዲያሟሉ መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡ “ሚንበር ቲቪ” ያናገራቸው የተማሪዎች ወላጆች ይህ ውሳኔ ከፍተኛ ጫና ውስጥ እንደከተታቸው ተናግረዋል፡፡


በዘንድሮው ዓመት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የመንግሥትም ሆነ የግል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ለማስፈተን የመፈተኛ ላፕቶፖችን እና ከኔትዎርክ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ግብዓቶች ማሟላት እንደሚገባቸው ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ገልጧል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ያስተላለፈው ትዕዛዝ በራሳቸው በትምህርት ቤቶቹም ላይ ጫና ማሳረፉን “ሚንበር ቲቪ” ከትምህርት ቤቶች አስተዳደር ሠራተኞች ሰምቷል፡፡

አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ለመፈተኛ የሚውለውን የግል ላፕቶፕ ባለባቸው የአቅም ውስንነት ሙሉ ሉሙሉ ማቅረብ ባለመቻላቸው፣ ተማሪዎቹ በግል ላፕቶፕ ይዘው እንዲመጡ ማዘዛቸውን በተለያየ አካባቢ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤት አስተዳደር እና ርእሰ መምህራን ለ”ሚንበር ቲቪ” ገልጸዋል፡፡

ከትምህርት ቤቶቹ ውስጥ በዘንድሮው ዓመት 115 ተማሪዎችን ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተማሪዎችን የሚያስቀምጠው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የአወሊያ ትምህርት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰዒድ አስማረ፣ ለፈተና የሚያስፈልገው ላፕቶፕ ትምህርት ቤቱም ሆነ ተማሪዎቹ ላይ ጫና ማሳደሩን ለሚንበር ቲቪ ተናግረዋል፡፡ በዚህም ትምህርት ቤቱ ጫናውን ለመጋራት ተማሪዎች ላፕቶፑን በራሳቸው እንዲያሟሉ ትዕዛዝ ቢተላለፍም ትምህርት ቤቱ በተለይ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎችን የሚጠበቅበትን ለማሟላት ጥረቱን መቀጠሉን ጠቁመዋል። ሥራ አስኪያጁ ትምህርት ቤቱ የሚያደርገው ጥረት ሊሳካ የሚችል መሆኑን ርግጠኛ ሆኖ መናገር እንደማይቻል አክለዋል፡፡

የአዲስ አበባ የግል ትምህርት ቤቶች ማኅበር ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ ሐረገወይን ገረሱ በርካታ ትምህርት ቤቶች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባዘዘው መሠረት ዝግጅት እያደረጉ ቢሆንም አገልግሎቱ የመጀመሪያ በመሆኑ በፈተና ወቅት የኢንተርኔት መቆራረጥና ተመሣሣይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ያላቸውን ሥጋት ለመገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ትዕዛዙን ካስተላፈው የትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡


የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ 25 አካባቢዎች በበይነ መረብ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በወረቀት ከሐምሌ 3 እስከ 11/2016 ፈተናውን እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡ የማኅበራዊ ሣይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5/2016 ለፈተና የሚቀመጡ ሲሆን የተፈጥሮ ሣይንስ ተማሪዎች ደግሞ ከሐምሌ 9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ይወስዳሉ፡፡


ዝርዝሩን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://minbertv.com/?p=8308

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍10😱51
#እናስታውስዎ

ከቀናት ሁሉ በላጮቹ የዙልሒጃ አሥር ቀናት እየደረሱ ነው!
ቀናቱን በተለያዩ የዒባዳ ተግባራት ማሳለፍ ድርብርብ ምንዳን የሚያስገኝ ሲሆን፤ ተከታዮቹን ዚክሮች (ላ ኢላሃ ኢለሏህ፣ አላሁ አክበርና አልሐምዱሊላህ) ማለትን ማብዛት እጅግ ተወዳጅ ተግባር መሆኑ በመልዕክተኛው (ﷺ) ሃዲስ ተወስቷል።

ተጨማሪ ለማንበብ ድረገጻችንን ይጎብኙ።
👉🏾 https://minbertv.com/?p=8324

#10ቱ_የዙልሒጃ_ቀናት
#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ
👍22
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚሰጠው የስድስተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የጊዜ ሠሌዳ ላይ ለውጥ ተደረገ
7
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚሰጠው የስድስተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የጊዜ ሠሌዳ ላይ ለውጥ ተደረገ

ዕለተ ረቡዕ ግንቦት 28 - 2016 | ዙል ቀዕዳህ 28 – 1445 | ሚንበር ቲቪ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተቃውሞ የቀረበበት የስድስተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የጊዜ ሠሌዳ ላይ ለውጥ መደረጉ ታወቀ፡፡ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ፈተናው ከዒድ አል አድሐ በዓል ሁለት ቀናት በኋላ እንዲካሄድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የፈተና ቀን ለውጥ ያደረገው፣ የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ቀድሞ የተቀመጠው የፈተና የጊዜ ሠሌዳ ከዒድ አል አድሓ በዓል ጋር በመግጠሙ በተማሪዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳርፍ በመግለጽ የተቃውሞ ደብዳቤ ከጻፈ በኋላ ነው፡፡

የክልሉ እስልምና ጉዳዮ ከፍተኛ ምክር ቤት ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ደብዳቤ የጻፈው ግንቦት 21/2016 ነበር፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፣ የፈተናው ቀን ከበዓሉ ጋር በአንድነት መሰጠቱን በሕገ መንግስሥቱ የተቀመጠውን “የሃይማኖትን እኩልነት የሚጥስ” እንደሆነም ጠቅሷል፡፡

ለክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተቃውሞ ደብዳቤ ምላሽ የሰጠው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ የጊዜ ሠሌዳው ላይ ማሻሻያ በማድረግ የስድስተኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 12/2016 እንዲሰጥ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ትምህርት ቢሮው ውሳኔውን በደብዳቤ ማሳወቁን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሐጂ ያሲን ኸድር ለሚንበር ቲቪ ገልጸዋል፡፡ ከትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት መካሄዱን ያስታወሱት ፕሬዝዳንቱ፣ ቢሮው ውሳኔውን በክልሉ ለሚገኙ 12 ዞኖች እንዲደርስ ማድረጉንም ጠቁመዋል፡፡

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ስምንተኛ ክፍል ላይ ብቻ ይሰጥ የነበረውን ክልል አቀፍ ፈተና ከባለፈው የ2015 ትምህርት ዘመን አንስቶ ለስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች መስጠት መጀመሩ የሚታወቅ ነው፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

በድረ ገጽ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://minbertv.com/?p=8311

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍5
🔴 የጥንቃቄ መልዕክት 🔴

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሁለት የወተት ምርቶች ላይ ባካሄደው የናሙና ምርመራ የጥራት መስፈርት ሳያሟሉ መገኘታቸውን አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ የጥራት መስፈርት አላሟሉም ያላቸው SULTAN INSTANT FULL CREAM MILK POWDER እና Nura Super Instant Full Cream Milk Powder የተባሉ የወተት ምርቶችን ነው፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በገበያ ላይ በመገኘት የገበያ ኢንስፔክሽን ሥራ በማከናወን ከገበያ ከተወሰደው ወካይ ናሙና ላይ በተደረገው የላቦራቶሪ ፍተሻ ውጤት መሠረት፣ የተደነገገውን የጥራት መስፈርት ሳያሟሉ የተገኙ ምርቶች በመሆናቸው ኅብረተሰቡ በ400 ግራም ባች ቁጥር የጠቀሰባቸውን ምርቶች እንዳይጠቀም ሲል አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀመው ያለው የSULTAN INSTANT FULL CREAM MILK POWDER ወተት የተመረተበት ጊዜ 19/02/2024፣ የሚያበቃበት ጊዜ ደግሞ 18/02/2015 ባች ቁጥሩ 56 ነው፡፡ በተመሳሳይ Nura Super Instant Full Cream Milk Powder የምርት ጊዜው 01/11/2023 እና የሚያበቃበት ጊዜ 31/10/2025 እንዲሁም የባች ቁጥሩ BT 23246006 የሆነውን ምርት ኅረተሰቡ እንዳይጠቀም ተብሏል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከላይ የተጠቀሱት ምርቶች በገበያ ቦታ እና ሱፐር ማርኬት ማንኛውም ነጋዴ ሆነ ግለሰብ ሲሸጥ ከተገኘ አስፈላጊው አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ ርምጃዎች እንደሚወሰድ ገልጧል፡፡
👍6👌63🙏3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የተጣለ ምግብ ታጥቦ ድጋሚ ለምግብነት የሚቀርብበት ቦታ! 🥲

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/72fFhkGP3Wg 🔗

#ድህነት #አሳዛኝ
#ዳር_እስከ_ዳር #መወዳ_መዝናኛ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስቃዪ ከሚበዛብሽ እስልምና ቢቀርብሽስ? | በእምባ ያራጨን ጥያቄ! 😭

ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል።
🔗 https://youtu.be/eOidvKsEgsY 🔗

#ሂዳያ #ኢስላም
#የኔ_መንገድ

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV
👍238😢7🙏2