የመዝሙር ግጥም እና ዜማ
109 subscribers
91 photos
8 videos
17 links
➢ ሰላም የክርስቶስ ቤተሰቦች ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን መዝሙሮችን ግጥም እና ዜማ ለእናንተ የምናደርስበት ቻናል ነው።
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምሮና ስርአት የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ከነዜማቸው በየቀኑ ወደናንተ ያቀርባል፡፡
እንዲለቀቅላችሁ የምትፈልጉትን መዝሙር @Questiontochannel
ለ ቻናሉ @mezmurdebeter
Download Telegram
Audio
🎼 እኛን ከወደደበት

ዘማሪ ገብረ ዮሐንስ

🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
https://t.me/mezmurdebeter
https://t.me/mezmurdebeter
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺

⚠️ይቀላቀሉን⚠️

📌መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇

🎵 መዝሙር ለመላክ👉 @Its1me2you3are4not
እኛን ከወደደበት ከጥልቅ ፍቅሩ የተነሳ
በደላችን ተሻረ ሀዘናችን ተረሳ(2)
አዝ -------------------------
ፅድቃችን ሆኖን እንደ መርገም
ነብሳችን ዝላ በሞት ሸክም
ስለወደደን ጌታ ፈቅዶ
ይኸው አዳነን እንዲው ወዶ
አዝ -------------------------
ከጥልቁ ጉድጓድ ተጥለን
ፅኑ መከራ ውስጥ ሳለን
ክርስቶስ በስጋ ተገልጦ
ህይወትን ሰጠን ሞትን ውጦ
አዝ -------------------------
ታስሮ ወረደ በፍቅር
መዳፉን ሰጠ ለችንካር
የባዘነውን ሰበሰበ
ርቀን ነበር አቀረበ
አዝ -------------------------
ቁጥር የለውም ለዘመኑ
ድንበር የለውም ለማዳኑ
ይኸው ሞትን አሰናበተ
ሰማይ በደሙ ተከፈተ
👇JOIN👇
https://t.me/mezmurdebeter
👆JION👆
#ቤተክርስቲያን_እና_መጽሐፍ_ቅዱስ

መጽሐፍ ቅዱስ የቤተ ክርስቲያን የዶግማዋ፤ የቀኖናዋ፤ የትውፊቷ፤ የባህሏ እንዲሁም የዝማሬዋ ወዘተ መገኛ ነው፡፡
በጥቅሉ መጽሐፍ ቅዱስ ፡-
1ኛ.የመሰረተ እምነትዋ(ዶግማ) ምንጭ እና መገኛ ነው
2ኛ.የሥርዓትዋ ምንጭ ነው
3ኛ የባህልዋ ምንጭ ነው
4ኛ የዝማሬዋ ምንጭ ነው
5ኛ የጸሎትዋ ምንጭ ነው፡፡

1ኛ #የመሰረተ_እምነትዋ_ምንጭ_ነው፡-
ይህንን ስንል የቤተክርስቲያን መሠረተ እምነት የምንለው አምስቱን አዕማደ ምስጢር እና ሰባቱን ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ራሱን መጽሐፍ ቅዱስንም ጨምሮ ነው፡፤ ቅዱስ ጳውሎስም አምስቱ አዕማደ ምስጢራት የቤተክርስቲያን መሰረታዊ የእምነት ትምህርተ እንደሆኑ ለማስረዳት‹‹በማኅበር እልፍ ቃላት ከምናገር ይልቅ በአእምሮዬ አምስት ቃላትን ብናገር እወዳለሁ›› ብሎ ያስተማረው 1ቆሮ14÷19፡፡ እነዚህም በጥቂቱ ሲዘረዘሩ፤ ስለ ምስጢረ ሥላሴ ዘፍ1÷26 ዘፍጥ18÷1 ማቴ 28÷19 ቆሮ13÷13 እና በመሳሰሉት ተዘርዝሯል፡፡ ምስጢረ ሥጋዌ የአምላክ ሰው መሆን ምስጢር ነው ይህንንም የተማርነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው መዝ. 8÷2 መዝ.113÷3 መዝ131÷6 ሉቃ2÷10 ዮሐ1÷14፤ የምስጢረ ጥምቀትንም ትምህርት የተማርነው ከመጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን ለማየት እነዚህንና የመሳሰሉትን ጥቅሶች ማየት ጠቃሚ ነው ማቴ. 3÷16 ዮሐ 3÷5 ማቴ 28÷19 ምስጢረ ቁርባንንም የተማርነው እንዲሁም የምንማረው እና የምናስተምረው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው ዘጸ12÷1 ማቴ. 26÷26 1ኛቆሮ. 11÷26 ምስጢረ ትንሳኤ ሙታንንም የተማርነው የምንማር እና ምናስተምረው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው 1ተሰ. 4÷13-17 2ኛተሰ.2÷1 የምስጢራተ ቤተክርስቲያን መገኛ ምንጭ መሰረትም መጽሐፍ ቅዱስ ነው ይህንንም በምሳሌ እንይ ምሳሌ የምስጢረ ጥምቀት ሥርዓትን በተመለከተ ማቴ 28÷19 ሮሜ 6÷3 የምስጢረ ሜሮንን ሥርዓት በተመለከተ ደግሞ ዘፍ 28÷18 ያዕቆብ ተንተርሶት የነበረውን ድንጋይ ዘይት መቀባቱ አዲስ ቤተክርስቲያን ሲመረቅ በሊቃነ ጳጳሳቱ አማካይነት በሜሮን ለመክበሩ፤ ምዕመናን በሜሮን አማካኝነት ጸጋ መንፈስ ቅዱስን እንደሚያገኙ የሚያስረዳ ትምህርት ነው፡፡ የምስጢረ ቁርባንን ሥርዓት በተመለከተ ዮሐ. 6÷53 መዝ 4÷7 1ኛቆሮ.11÷27 ላይ ተጽፏል፡፡ የምስጢረ ክህነት ትምህርትንም ያገኘነው ከሊቀ ካህናት ክርስቶስ ነው፡፡ ማቴ16÷19 በምድር የምታስረው በሰማይ የታሰረ ይሆናል በምድር የምትፈታው በሰማይ የተፈታ ይሆና በማለት ዮሐ. 20÷22 ስለ ሥርዓተ ክህነት ሲመተ ክህነት 1ኛጢሞ.3÷8 ምስጢረ ንስሐን በተመለከተ ደግሞ በማቴ 9÷13 ሕዝ.18÷27 ሉቃ.15÷4 ማቴ.8÷4 ራስህን ለካህን አሳይ በማለት ሊቀ ካህናት መምህራችን እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡ የምስጢረ ተክሊልን ሥርዓት በተመለከተ ማቴ.19÷5 ሁልጊዜ በሥርዓተ ተክሊል ላይ የሚነበበብ ነው፡፡ኤፌ.5÷28-32 የምስጢረ ቀንዲልን ሥርዓት በተመለከተ ኢሳ.1÷6 ያዕ.5÷14 ተጽፎ እናገኛለን፡፡

2ኛ- #የቤተክርስቲያን_የሥርዓትዋ_ምንጭ_ነው፡-
የሥርዓተ ቅዳሴው መገኛ ምንጩ በሥርዓተ ቅዳሴ ሚከናወነው ሚነበበው ሚዜመው ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ በቅዳሴ መግቢያ ላይ ምዕመናኑ ከካህናቱ ጋር በኅብረት ‹‹በቅዳሴ ወቅት ከምዕመናን መካከል ወደ ቤተ ክርስቲያን የገባ ቢኖር ሥርዓተ ቅዳሴው እስኪያልቅ የማይታገስ ቅዱሳት መጻህፍትን የማይሰማ ቅዱስ ቁርባንን የማይቀበል ቢኖር ከቤተ ክርስቲያን ይውጣ ሐዋርያት አብጥሊስ በተባለ መጽሐፋቸው እንዲህ እንዳስተማሩን›› እያልን ምንዘምረው ከሰማንያ አንዱ በመጽሐፈ አብጥሊስ ቅዱሳት መጻሕፍት በአንዱ እንዲህ ስለተጻፈ ነው፡፡ ስለዚህ መጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ መሐሉ መጽሐፍ ቅዱስ ማጠናቀቂያው መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ በሥርዓተ ቅዳሴ መጽሐፍ ቅዱስ የማይነበብበት ክፍል የለም፡፡ የሐዲስ ኪዳንን ቅዳሴ የጀመረውም ጌታ ነው፤ ‹‹አመስግኖም ይህ ሥጋዬ ነው ብሎ ሰጣቸው›› እንዲል ማቴ 26÷26፡፡ መንበሩን እየዞሩ የሚያጥኑት ሲያጥኑም የሚናገሩት በመጽሐፈ ኢያሱ ምዕራፍ 6÷13-15 የተጻፈውን እየደገሙ ነው፡፡ የዕጣኑም ሥርዓት በራእ8÷3-4 ካህናት የሚለብሱት ልብስ፤ ሲካኑ የሚፈጸመው ሥርዓት መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ዘጸ 39÷1 ዮሐ 20÷22

3ኛ- #የቤተክርስቲያን_የባህሏ_ምንጭ_ነው፡-
የለቅሶ ባህል ምንጩ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ሰው ሲሞት ፍትሐት ምንፈታው ከእናንተ ያዘነ ቢኖር ይጸልይ መጽሐፍ ቅዱስ ስላስተማረን ነው ያዕ5÷13 ሥርዓተ ታቦት ዘንግስ፤ ታቦታቱን ካህናቱ አክብረው ሲወጡ ምዕመኑ እልል እያለ እየተከተለ የሚሄደው ለታቦቱ የሚሰግደው በታቦቱ ላይ ስመ እግዚአብሔር ስለሚጻፍ ለሱም መስገድ እንደሚገባን መጽሐፍ ቅዱስ ስላስተማረን ነው ፊል2፤10 ታቦታቱን ተከትለን የምንዞረው ተከተሉ ተብለን መበጽሐፍ ቅዱስ ስለታዘዝን ነው ኢያሱ3፤3 የምግብ ሥርዓታችን ምንጩ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ይህን ብሉ ይህን አትብሉ ተብለን ታዘናልና ዘሌ11፤1ጀምሮ፡፡ የበዓላቶቻችን ምንጭ መገኛ መሰረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ዘሌ 23÷1

4ኛ. #የጸሎትዋ_ምንጭ_መገኛው_ነው፡-
ከጸሎት መጻህፍት አንዱና ዋነኛው መዝሙረ ዳዊት ሲሆን መዝሙረ ዳዊት በቤተክርስቲያን የማይጸለይበት አንድም ቀን የለም አይኖርምም፡፡ ሌላው በሁሉም ምዕመናን የሚወደድ ጸሎት እና የጸሎት መጽሐፍ ውዳሴ ማርያም ምንጩ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ለምሳሌ የሐሙስ ውዳሴ ማርያም ለእስራኤል የነገሠ ዳዊት ከቤተልሔም ምንጭ ውሃ ሊጠጣ ወደደ 2ኛ ሳሙ 23÷15-17፤ 1ኛዜና.11÷17-19

5ኛ- #የዝማሬዋ_ምንጭ_መሰረት_ነው፡-
በቤተክርስቲያናችን ትምህርት የዜማ ቤት ትምህርት ከውዳሴ ማርያም ቀጥሎ የሚሰጠው የዜማ ትምህርት መዝሙረ ዳዊት ነው የቅዱስ ያሬድ አምስቱ የዜማ መጻህፍቶቹ ምንጭ መገኛቸው መጽሐፍ ቅዱስ ነው ለዚያውም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ለምሳሌ ማቴ24 ላይ ጌታችን ምሳሌውን ከበለስ ተማሩ ያለውን ቅዱስ ያሬድ በድጓዋው በለስ ያላት ቤተ እስራኤልን ነው ብሎ ተርጉሞታል፡፡
የሰዓታት ዜማ ምንጭ መገኛው መጽሐፍ ቅዱስ ነው ‹‹ኢሰማዕነ ወኢርኢነ ወኢነገሩነ አበዊነ ከመቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌከ አልሰማንም አላየንም አባቶቻችንም አልነገሩንም ካንተ በቀር ሌላ ባእድ አምላክ አናመልክም›› ይህም በዘዳ. 4÷35 ተጽፏል፡፡

(በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ዋና ክፍል የተዘጋጀ፡፡)
፧፧ እኔ ከሚስቀው ዓለም አይለሁም ፧፧

በአንድ ወቅት ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ በግብፅ ፓርላማ ላይ እንዲገኙ ጥሪ ደረሳቸው። ታዲያ አንድ እሚያውቃቸው ሰው ከሰው ጋር እንዲመሳሰሉ ስብሰባው ላይ የክህነት ልብሳቸውን ልብስ ትተው ሱፍ ማድረግ እንዳለባቸው ነገራቸው አለበለዚያ ግን መሳቂያ ይሆናሉ አላቸው። ይህንን የሰሙት ብጹዕነታቸው "እኔ ያለሁት ከሚስቀው ዓለም ጋር ሳይሆን ከሚሳቅበት ከክርስቶስ ጋር ነው። ስለዚህ አይደንቀኝም ዓለም ምንም ይበል!!! አሉት ይባላል። ከክርስቶስ ጋር የሚኖር ሰው ስለምድራዊ ክብር አይጨነቅም ተሰደብኩ ተነቀፍኩ ተዋረድኩ አይልም ለምን? ሁልጊዜም ቀራንዮ በአይኑ አለ እኛም በዓለም ፊት ዓለምን በክርስቶስ ፊት ክርስቶስን ከመምሰል ከንቱ መመላለስ እንድን ዘንድ የቅዱሳን አበው ማስተዋሉን ያድለን የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍፁምም የሆነውን ነገር ምን እንደሆነ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህንን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12:2


የአባቶቻችን ጸጋ በረከት ይደርብን አሜን፫
፠ አብ የተከለው አይነቀልም ፠

አብ የተከለው አይነቀልም
ያድጋል በፀጋ ለዘለዓለም
የወይን ግንዱን የተደገፈ
ያልፍል ሁሉንም እያሸነፈ

እርኛው ሲመታ መንጋው ሲበታተን
እስከ ሞት ታምነናል እንደገና ሲየን
እፍ ያለብን መንፈስ ሀይልን አስታጥቆናል
እየተገደልን ህያዋን ሆነናል

በእሳት ላንቃ ያልጠፍነው /2/
በጌታ ቃል ስር ሰደን ነው /2/

በደርቤለሽ ጠራን ኖርን በቤርያ
ሠላሙን አወጂን ብለን ሃሌ ሉያ
ስደት ሲከተለን በሃይማኖት ፀንተን
የገባንን እውነት ለዓለም አደርስን
በመገፍት ያተርፍነው /2/
መክበርና መባርክ ነው /2/

ለአህዛብ ተሰብኮ ተገልጧል ማዳኑ
ኢየሱስ ህይወት ነው በስሙ ላመኑ
በስር ቤት ተዘግቶ ወንጌል አይከደን
ሰሰለቱ እስኪ ወድቅ እርሱን እሰብካለን
የዝምታ ቀን የለንም ሳንመሰክር አንኖርም /2/

በክርስቶስ ጥበብ ያለሽ ክርስትና
የገሃነብ ደጆች አይችሏትምና
ሁለን ነገር አልፈን ዛሬ ቀና ያልነው
ለማታልፈው መንግስት ስለተከለን ነው
ያሻገርን ክንደ ብርቱ አስተምሮናል በህይወቱ /2/

ዘማሪ ገ/ ዮሃንስ
አንድ በጣም ትልቅ ቆሻሻ የጫነ ጋሪ የሚገፋ ሰው ወደ ቤትህ መጥቶ "እባክህ በርህን ክፈትልኝና ይህን ቆሻሻ አንተ ቤት ላራግፈው?" ቢልህ፣ "ውይ የሚጥልበት ቢያጣ ነው። ባይቸገር ወደ እኔ አይመጣም ነበር" ብለህ ደጅህን ከፍተህ ታስገባዋለህ? በፍጹም፤ እንደውም "እንዴት ብታስበኝ ነው? ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም? እንዴት ሰው በሚኖርበት ቤት ቆሻሻ ካልደፋሁ ትላለህ? ስትል ለጠብ ትጋበዛለህ። መደፈርህ እያንገበገበህ "እምቢ!" ብለህ ትቆጣለህ። በእርግጥም ያስቆጣል።

ግን ሌላ የሚከፋ ሽታ ያለው ቆሻሻን ጭኖ ለመጣ ባላጋራ እኮ በፈቃድህ የከፈትከው ቤት አለ። "የምን ቤት?" ብለህ ብትጠይቀኝ "ልብህ ነዋ" ብዬ እመልስልሃለሁ፤ "ማን ይኖርበታል?" ካልኸኝም "እግዚአብሔር ነዋ" እልሃለሁ።

አንተ ለመኖሪያ ቤትህ ጽዳት የምትጠነቀቀውን ያህል የያዕቆብ አምላክ ለሚያርፍበት ኅሊናህ ተጠንቅቀህ ታውቃለህ? ሰይጣን ጭኖ የሚያመጣውን የኃጢአት ቆሻሻ ሁሉ እሺ ብለህ ወደ ልብህ በማስገባት የፈጣሪህን መቅደስ ለምን ታቆሽሻለህ? ንጹሑ እግዚአብሔር የሚያድርበትን ቤት ሊያቆሽሽ በመጣ ሰይጣን ላይ እንዴት አልተቆጣህም? ድፍረቱ ለምን አላብከነከነህም?

እግዚአብሔር አንተ ልትኖርበት ከምትፈልገው ንጹሕ ቤት የበለጠ ጽዱ መቅደስ የማይፈልግ ይመስልሃል?

(Dn Abel Kassahun Mekuria )
#እኔ_በእግዚአብሔር_ፊት_የምቆመው_ገብርኤል_ነኝ (ሉቃ 1፥19)
#ይህ_ገብርኤል_ነው

በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ
#ይህ_ገብርኤል_ነው

የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤ የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ
#ይህ_ገብርኤል_ነው

ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው
#ይህ_ገብርኤል_ነው

ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳናቸው
#ይህ_ገብርኤል_ነው

ወደ ዘካሪያስ የተላከ የዮሐንስ ልደት ያበሰረ
#ይህ_ገብርኤል_ነው

ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ
#ይህ_ገብርኤል_ነው

ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው
#ይህ_ገብርኤል_ነው

ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው
#ይህ_ገብርኤል_ነው

ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ
#ይህ_ገብርኤል_ነው

የብርሃን ወርቅ የተቀዳጀ
#ገብርኤል_ነወ

የአሸናፊና የኃይል መልአክ
#ገብርኤል_ነው

ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ
#ገብርኤል_ነው

#የመልአኩ_የቅዱስ_ገብርኤል_ጥበቃና_ረድኤት_አይለየን
አሜን አሜን አሜን

#መልካም ቀን

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

💚 •✥• @Z_TEWODROS •✥•💚
💛 •✥• @Z_TEWODROS •✥•💛
💖 •✥• @Z_TEWODROS •✥• 💖
Audio
ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
#ክብሬ_ነው

ክብሬ ነው ክብርህን መናገሬ
ፅድቄ ነው ፍቅርህ መመስከሬ
ጌታዬ አምላኬ እልሃለሁ (2)
ስጠራህ ሳመልክህ እኖራለሁ (2)
#አዝ
አይቼ የእጅህን ታምራት
ሰምቼ የቃልህን ትምርት
ሆኛለሁ ምስክር ላዳኝነትህ
ስጋን ተዋህደህ ለኛ መገለጥህ (2)
#አዝ
ተከተልኩ ሁሉን ነገር ንቄ
መድኃኒት መሆንክን አውቄ
ከመልካሟ ቤትህ ተጠልያለሁ
የእጅህን በረከት ካንተ እጠግባለሁ (2)
#አዝ
እርፍ ይዤ ላላርስ ወደኅውላ
እያየው መረቤን ስትሞላ
እመካብሃለሁ ባንተ መድህኔ
አምላኬ ነህና የምትራራ ለኔ
አባቴ ነህና የምታስብ ለኔ
#አዝ
ቸርነት ምረት ከበዛልኝ
ለስምህ ውዳሴ ቅኔ አለኝ
ክብሬና ሞገሴ አንተ ነህ ጌታ
ተመስገን (2) ጠዋትና ማታ (2)

በቀሲስ ዘማሪ ምንዳዬ

•✥•🍁 @Z_TEWODROS 🍁•✥•
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ     ⎙ㅤ    ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
☞ጌታ ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የሰጠው ቃልኪዳን፡፡
☞ሰው ሁሉ ወደ ሥጋዊ ተግባርም ሆነ ወደ መንፈሳዊ ተግባርም ቢሆን ሲሄድ
ይህ የመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ነው ብሎ ቅጽሩን፤ ገራገሩን
ቢሳለም የተሳለመውን ሰው ቢኖር እኔ መንበረ መንግሥቴን አሳልመዋለሁ፡፡
☞የገድልህንም መጽሐፍ የተሳለመ ቢኖር እኔ መንበረ መንግሥቴን
አሳልመዋለሁ፡፡
☞የገድልህ የተአምርህ መጽሐፍ የተነበበትን ውኃ እኔ እንደተጠመቅሁበት እንደ
ማዮርዳኖስ አደርገዋለሁ፡፡ የገድልህ መጽሐፍ በተነበበት ውኃ የተጠመቀበት
ሰው ቢኖር የሰማንያ ዓመት ኃጢአቱን አስተሠርይለታሁ፡፡
☞ወንድን የአርባ ቀን ሴቷን የሰማንያ ቀን ሕፃን አደርጋቸዋለሁ፤እኔ
በተጠመቅሁበት ማየ ዮርዳኖስ እንደተጠመቀ ሆኖለት ከኃጢአቱ ይነጻል፡፡
☞ሰውም ሆነ እንስሳ ቢታመም በጹኑ እምነት ይደረግልኛ ብሎ አምኖ ያለ
ጥርጥር ውኃ አቅርቦ የገድልህን መጽሐፍ በላዩ ላይ አንብቦ የተነበበትን ውኃ
ቢታጠብበት ወይንም ቢጠጣ ያለ ጥፋት ፈጥኖ ከደዌው ይፈወሳል፡፡
☞የገድልህን መጽሐፍ የተነበበትን ማየ ጸሎት በቤቱ ውስጥ ቢረጭ ከዚያ ቤት
በረከቴን እመላበታለሁ፤ ተድላን፤ ደስታን፤ ጥጋብን በዚያ ቤት አሳድራለሁ፤ እሰከ
ዘላለሙ ድረስ በቤቱ ውስጥ የእህል መታጣትና ርሃብ፤ የውኃ ጥማት፤ተላላፊ
በሽታ አይገባበትም፤ፈጽሜም አላመጣበትም፡፡
☞ሥጋዬን ደሜን መቀበል ያልተቻለሁ ሰው ቢኖር ለመታሰቢያህ ዝክር
ከተደረገው ፍርፋሪ ይቅመስ፤ ሥጋዬን ደሜን እንደተቀበለ እኔ አደርግለታለሁ፡፡
☞ፍርፋሪ ባያገኝ እንጀራውና ዳቦውን የተበላበትን ገበታ፤ ጠላው የተጠጣበትን
ጽዋ በምላሱ ይላስ፤ እኔ ኢየሱስ ቃል የሚያብለው ሥጋዬን ደሜን እንደተቀበለ
አደርገለታለሀ፤ ሰለ እምነቱ ሥጋዬን ደሜን ለመቀበል የሚያበቃውና
እውነተኛውን ምግባር የጽድቅ ሥራ እንዲሠራ አደርገዋለሁ ቡሎጌታ
ለመጥምቀ መለኮት ቃል ኪዳን ስጥቷል፡፡
☞(ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ)
☞እኛም የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የቃልኪዳኑ ተከፋይ ያድርገን
በጸሎቱ ይማረን፡፡
#ሐምሌ_7

#ቅድስት_ሥላሴ

ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡

አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡

ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡

እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን!

(ስንክሳር ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ፔጅ)
ጾመ ፍልሰታ እንኳን አደረሳችሁ / አደረሰን አሜን

ጾመ ፍልሰታ

<ፍልሰታ > የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል። ይህም የእመቤታችንን ሥጋ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ስር ከነበረበት መነሳቱን ለማመልከት ይነገራል።

ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፷፬ ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን መነሳቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው። ጾሙ ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን ሲጾም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ከደነገገቻቸው ሰባቱ አጽዋማትም አንዱ ነው።

ኃይማኖታዊ መሠረት

እመቤታችን ከአባቷ ከኢያቄም እና ከናቷ ከሐና ነሐሴ ፯ ቀን ተጸንሳ ግንቦት ፩ ቀን በሊባኖስ ተወልዳለች። <እምሊባኖስ ትወጽዕ መርአት ፦ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች > እንደተባለ ። እምቤታችን በእናት አባቷ ቤት ሦስት ዓመት፤ በቤተ መቅደስ አሥራ ሁለት ዓመት፤ ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ፡ ከዮሐንስ ወልደዘብዴዎስ ዘንድ አሥራ አራት ዓመት ከዘጠኝ ወር ቆይታ በ ፷፬ ዓመት ዕድሜዋ በ፵፱ ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። የእመቤታችንን ስም የሚገልጹ የውዳሴ ጽሑፎችም በእድሜዋ ልክ ተደርሰዋል። ለምሳሌ የውዳሴ ማርያም ቁጥር ፷፬ ነው፤ የመልክአ ማርያም ቁጥርም ፷፬ ነው።[1]

ባረፈች ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያት ተሰባስበው አስከሬኗን ይዘው ወደ ጌቴሴማኒ መቃብር ለማሳረፍ ሲሄዱ አይሁድ ለተንኮል አያርፉምና ተተናኮሏቸው። ቀድሞ ልጇ ሞቶ ተነሳ፣ አረገ እያሉ ሲያስቸግሩን ይኖራሉ: ደግሞ አሁን እሷም ተነሳች፣ አረገች ሊሉ አይደል በማለት አይሁድ ተሰባስበው አስከሬኗን ለማቃጠል ሲተናኮሉ እግዚአብሔር በተአምር ከነዚያ አይሁዶች አድኗቸዋል ። የእመቤታችንንም አስከሬን ነጥቆ ከሐዋርያው ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት በዕፀ ህይወት ስር አኑሯቸዋል ። ከዚያ በኋላ ሐዋርያት ሥጋዋን አግኝተው ይቀብሩት ዘንድ በአረፈች በስምንተኛው ወር ከነሐሴ ፩ ጀምሮ እስከ ነሐሴ ፲፬ ቀን ድረስ ሁለት ሱባዔ ይዘው በአሥራ አራተኛው ቀን ሥጋዋን ከጌታ ተቀብለው በጸሎትና በምህላ በፍጹም ደስታ በጌቴሰማኔ አሳረፉት ። በ ሦስተኛውም ቀን ተነስታ ስታርግ ከሰኡቃዊያን ወገን የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ አያት። እርሱም በቀብር ስርዓቱ ጊዜም አልነበረም። ሀገረ ስብከቱ ህንድ ስለነበር ሊያስተምር ወደዛው ሂዶ ነበርና። በዚያም ሲያስተምር ሰንብቶ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ያገኛታል። ትንሳኤዋን ከርሱ ሰውራ ያደረገች መስሎት አዝኖ «ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነውን ?» ብሎ ቢያዝንባት እመቤታችንም ከርሱ በቀር ማንንም ትንሳኤዋን እንዳላየ ነግራ አጽናናችው። ለሌሎቹ ሐዋርያትም እንዲነግራቸው ለምልክትም /ለምስክርም እንዲሆነው ሰበኗን /መግነዟን ሰጥታው አረገች። ቶማስም ኢየሩሳሌም ደርሶ ሐዋርያትን «የእመቤታችን ነገርስ እንደምን ሆነ?» ሲል ቢጠይቅ «አግኝተን ቀበርናት እኮ» አሉት። እርሱ ምስጢሩን አዉቆ ደብቆ «ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር» እንዴት ይሆናል ? አይደረግም ይላቸዋል። ሊያሳያቸውም መቃብሩ ዘንድ ሂደው ቢከፍቱት አጧት። እርሱም «አታምኑኝም ብዬ እንጂ እርሷስ ተነስታ አርጋልች» በማለት ሁኔታውን ተረከላቸውና ለምስክር ይሁንህ ብላ የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው። ከዚህ በኋላ ለበረከት ይሆናቸው ዘንድ ሰበኑን ተካፍለው ወደየአህገረ ስብከታቸው ሄዱ። ዛሬ በቅዳሴ ጊዜ ዲያቆኑ በሚይዘው የመጾር መስቀል ላይ በሁለት ቀዳዳዎች አልፎ ተጠምጥሞ የምናየው መቀነት መሰል ጨርቅ የዚያ ሰበን ምሳሌ ነው።

በዓመቱ ሐዋርያት ከያሉበት ተሰባስበው ቶማስ ትንሳኤሽን አይቶ እኛስ እንዴት ይቀርብናል ብለው ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምርው ሱባዔ ቢይዙ ከሁለት ሱባዔ በኋላ እንደገና ትንሳኤዋንና እርገቷን ለማየት በቅተዋል። ሐዋርያዊት የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናም ምእመኖቿ ከእመቤታችን በረከትን እንዲያገኙ ይጾሙ ዘንድ ይህን ሐዋርያት የጾሙትን ጾም እንዲጾሙ አዉጃለች። ምእመናንም በተለየ መልኩ በጾም በጸሎት በሱባዔ ጽሙድ ሆነው ይህን ወቅት ያሳልፋሉ።

የእመቤታችን ትንሳኤ ድንገት እንደእንግዳ ደራሽ እንደ ዉሀ ፈሳሽ የተደረገ ሳይሆን በቅዱሳት መጻሕፍት በትንቢተ ነቢያት የተገለጸ ነው። ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር ፻፴፩ ቁጥር ፲ ላይ «አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦትም» ይላል። በዚህም ምዕመናንን ወደ ምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህ ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነስ አለ። ታቦት የጽላት ማደርያ እንደሆነ ሁሉ እምቤታችንም ለክርስቶስ ማደርያ በመሆኗ አማናዊት ታቦት ትባላለች።

ንጉስ ሰሎሞንም በመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲ ላይ «ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፤ ወዳጄ ሆይ ተነሽ፡ ውበቴ ሆይ ነይ» ብሏል። እዚህ ላይ «ወዳጄ …ዉበቴ»“ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ። ክቡር ዳዊት መዝሙር ፵፬ ቁጥር ፱ ላይ «በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች» እንደሚል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛነቱን ከፈጸመ በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ እንዳረገ እመቤታችን ቅድስት ድንገል ማርያምም በቀኙ ትቀመጥ ዘንድ «ተነሽ ነይ» አላት ። እንግዲህ ይህንና የመሰለዉን ሁሉ ይዘን የእናታችንን እረፍቷን ትንሳኤዋን እንዘክራለን እንመሰክራለንም።

https://t.me/mezmurdebeter