መዝገበ ቅዱሳን
24.2K subscribers
1.97K photos
9 videos
6 files
26 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
††† እንኳን ለእናታችን ቅድስት መሪና ሰማዕት እና ቅዱስ ለንጊኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ታላቋ ቅድስት መሪና ሰማዕት (SAINT MARINA THE GREAT) †††

††† እናታችን ቅድስት መሪና ስም አጠራራቸው ከከበረ : ተጋድሏቸው ካማረ ታላላቅ ሴት ሰማዕታት አንዷ ናት:: ተወልዳ ያደገችው ከዋናው ዘመነ ሰማዕታት በፊት በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን ሶርያ አካባቢ ነው:: አባቷ ዳኬዎስ የሚባል ጣዖት አምላኪ ቢሆንም እናቷ ግን ክርስቲያን ነበረች::

ነገር ግን እናቷ ገና በ5 ዓመቷ ሞተችባትና ለሞግዚት ተሰጠች:: የእግዚአብሔር ጥበብ ሆኖ ሞግዚቷ ደግ ክርስቲያን ነበረችና ለ10 ዓመታት ሃይማኖተ ክርስቶስን እና ምግባረ ጽድቅን አስተማረቻት:: ዕድሜዋ 15 ዓመት ሲሆን አባቷ ዳኬዎስ አረፈ::

በዘመኑ ዳኬዎስ የሚሉት (ቅዱስ መርቆሬዎስን የገደለው) ክፉ ንጉሥ ነበርና ክርስቲያኖችን አሳደዳቸው:: ይህን ዜና ቅድስት መሪና ስትሰማ ደስ አላት:: እጅግ ባማረ ንጽሕና እንደ ኖረች ሁሉ በክርስቶስ ስም ደሟን ለማፍሰስ አስባ ወደ ንጉሡ መኮንን ሔደች::

††† አበው እንዳስተማሩን ከሴቶች ሰማዕታት በውበትና ደም ግባት እንደ ቅዱሳት:-
*መሪና
*አርሴማ እና
*ጣጡስ የሚያክል የለም:: ዐይንን ማፍዘዝ የሚችል ውበት ነበራቸው::

መኮንኑ መልኩዋን ዐይቶ ሰውነቱ ተናወጠ:: "ጣዖት አምልኪና የእኔ ሚስት ሁኚ" አላት:: እርሷ ግን መኮንኑን ከነ ጣዖቱ አቃለለችው:: "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ" አለችው::

መኮንኑ ካነጋገሯ የተነሳ ተቆጥቶ ይገርፏት ዘንድ አዘዘ:: መሬት ላይ ጥለው በብረት ዘንግ ቢመቷት አካሏ እየተቆረጠ ብዙ ደም ፈሰሰ:: ወስደውም ጨለማ ውስጥ ጣሏት:: ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ አድኗት: አጽንቷትም ዐረገ::

በማግስቱ በመጋዝ አካሏን ቆራርጠው ጣሉ:: ዳግመኛ ሊቀ መላእክት አዳናት:: ወደ ጨለማ ክፍል ወስደው ሲጥሏት ትልቅ ዘንዶ መጣባት:: እጆቿ ተዘርግተው እጸለየች ዋጣት:: እርሷ ግን ጸሎቷን ቀጠለች:: ከደቂቃዎች በሁዋላ ግን ዘንዶው ለ2 ተሰነጠቀና እጆቿ እንደተዘረጉ ወጣች::

በሌላ ቀን ግን ሰይጣን ፊት ለፊት መጥቶ ታገላት:: ከሰማይ ነጭ ርግብና መስቀል ወርዶላታልና አልቻላትም:: ከእግሯ በታች ጥላ ደጋግማ ረገጠችው:: ሰይጣንም በሐፍረት እየጮኸ ሔደ::
"ለሰይጣን ኬደቶ ከመ አሣዕን በእግር" እንዲል:: (እንዲህ ነበሩ የቀደመው ዘመን እናቶቻችን)

መኮንኑ ከክርስትና ያስወጣት ዘንድ በትልቅ ጋን ውሃ አስፈልቶ "በዚያ ላይ ቀቅሏት" አለ:: ድንገት ግን ከሰማይ ነጭ ርግብ ወርዳ: ውሃውን አቀዝቅዛ: 3 ጊዜ በውሃው አጠመቀቻት:: (እስከዚህ ሰዓት ድረስ አልጠመቀችም ነበርና)

ርግቧ የብርሃን ልብስ አልብሳ: አክሊለ ክብር ደፋችላት:: መኮንኑ ተስፋ ስለ ቆረጠ "አንገቷን በሰይፍ ምቱ" አለ:: በዚያች ሰዓት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ "ብጽዕት መሪና ብጽዐን ይገባሻል" አላት::

"ስምሽ በሚጠራበት: መታሰቢያሽ በሚደረግበት ሁሉ በዚያ ረድኤት: በረከት ይበዛል:: አንቺን ያከበረውን አከብረዋለሁ:: ከርስትሺም አስገባዋለሁ" ብሏት ጌታችን ዐረገ::

ወታደሮቹ አንገቷን በሰየፉ ጊዜ ታላቅ መነዋወጽ ሆነ:: ድውያን ተፈወሱ: ዕውሮች አዩ: አንካሶች ረቱ: የማይሰሙትም ሰሙ:: ቅዱሳን መላእክትም ከሰማያት ወርደው የቅድስት መሪናን ነፍስ በዝማሬ አሳረጉ::

††† ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት †††

††† ለንጊኖስ ማለት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስብከት ዘመን የዺላጦስ ወታደር የነበረ ሰው ነው:: ስለ ጌታችን ተአምራት በየጊዜው ይሰማ ነበር:: ሔዶ እንዳያገኘው ግን አይሁድን ይፈራ ነበር:: እነርሱ "በክርስቶስ ያመነ ሁሉ ከምኩራብ ይባረር" ብለው ነበርና:: (ዮሐ. 9:22)

ጌታችን በተሰቀለባት ዕለተ ዐርብ ግን ጭንቅ ሆነበት:: ጌታን እንዲሰቅሉ ከታዘዙ ወታደሮች እንደ አንዱ ተመርጦ ነበርና በዘዴ "አሞኛል" ብሎ እስከ 9 ሰዓት ድረስ ቆየ::

በሁዋላ ግን አይሁድ "በክርስቶስ ሞት ያልተባበረ ሁሉ ወንጀለኛ ነው" የሚል አዋጅ በማስነገራቸው እየፈራ ቀራንዮ ሲደርስ "ጐኑን ውጋው" ብለው ረዥምና ጥቁር ጦር ሰጡት:: ለንጊኖስ ወደ ጌታችን ዐይን ተመለከተ:: እያየው እንዳልሆነ ገመተ::

ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ ለይቷልና ጦሩን ጨብጦ ወደ ጌታ ጐን ልኮ ወጋው:: ከጌታ ቀኝ ጐንም በ"ለ" አምሳል ትኩስ ደምና ውሃ ፈሰሰ:: አንዷ ፍንጣቂ ሔዳ የታወረች ዐይኑ ላይ ዐርፋ ዐይኑን አበራች::

ለለንጊኖስ ታላቅ ደስታ ሆነ:: ለእኛ ግን ማየ ገቦና ደመ ገቦ ፈለቀልን:: የጌታችን ትእግስቱና ቸርነቱ ግን ይደንቃል::
"ከመ ኢየሐስብ ቦቱ ዘኩናተ እዱ ርግዘቶ::
በኃጣውኢሁ ለዘኢፈቀደ ሞቶ::
ምሕረቶ እሴብሕ ወዐዲ ትዕግስቶ::" እንዳሉ ሊቃውንት::

ጌታችን ከተነሳ በሁዋላ ለንጊኖስ ወደ ቅዱስ ዼጥሮስ ዘንድ ሒዶ ስለ እውነት : ስለ ሃይማኖትም ተማረ:: ተጠምቆ: ምድራዊ ወታደርነቱን ትቶ እየሰበከ ከኢየሩሳሌም ወደ ቀዸዶቅያ ወረደ:: ለዘመናትም ጌታችን ክርስቶስን በሥርዓተ ወንጌል አገለገለ::

በመጨረሻም በጢባርዮስ ቄሣር ዘመን አይሁድ አሳደዱት: አንገላቱት:: የነርሱ ወገን ስለነበረም መከራ አጸኑበት:: የጽድቅ አርበኛና የክርስቶስ ሐዋርያ ቅዱስ ለንጊኖስ ግን ጸና:: በዚህች ዕለትም አይሁድ አንገቱን ቆርጠውት ለሰማዕትነት በቃ:: ቅዱሱ በሕይወቱም በዕረፍቱም ተአምራትን ሠርቷል::

††† እግዚአብሔር በቸር ጥሪው ሁላችንም ወደ ቀናው የጽድቅ ጐዳና ይጥራን:: ከሰማዕታቱም ረድኤት በረከት ይክፈለን::

††† ሐምሌ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት መሪና እናታችን (ታላቋ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ለንጊኖስ ሐራ (ሐዋርያና ሰማዕት)
3.ቅዱስ አብጥልማዎስ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
6.አባ ሳሙኤል
7.አባ ስምዖን
8.አባ ገብርኤል

††† "ወደ ጌታ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም:: ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጐኑን በጦር ወጋው:: ወዲያውም ደምና ውሃ ወጣ:: ያየውም መስክሯል : ምስክሩም እውነት ነው:: እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ : እርሱ እውነት እንዲናገር ያውቃል:: ይህ የሆነ:-
"ከእርሱ አጥንት አይሰበርም" የሚል የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው:: ደግሞም ሌላው መጽሐፍ:-
"የወጉትን ያዩታል" ይላል::" †††
(ዮሐ. 19:33)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
@petroswepawulos
ታላቋ ቅድስት መሪና ሰማዕት
(SAINT MARINA THE GREAT)

እናታችን ቅድስት መሪና ስም አጠራራቸው ከከበረ ተጋድሏቸው ካማረ ታላላቅ ሴት ሰማዕታት አንዷ ስትሆን ሐምሌ 23 እረፍቷ ቀን ነው። ተወልዳ ያደገችው ከዋናው ዘመነ ሰማዕታት በፊት በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን ሶርያ አካባቢ ነው። አባቷ ዳኬዎስ የሚባል ጣዖት አምላኪ ቢሆንም እናቷ ግን ክርስቲያን ነበረች።

ነገር ግን እናቷ ገና በ5 ዓመቷ ሞተችባትና ለሞግዚት ተሰጠች። የእግዚአብሔር ጥበብ ሆኖ ሞግዚቷ ደግ ክርስቲያን ነበረችና ለ10 ዓመታት ሃይማኖተ ክርስቶስን እና ምግባረ ጽድቅን አስተማረቻት። ዕድሜዋ 15 ዓመት ሲሆን አባቷ ዳኬዎስ አረፈ።

በዘመኑ ዳኬዎስ የሚሉት (ቅዱስ መርቆሬዎስን የገደለው) ክፉ ንጉሥ ነበርና ክርስቲያኖችን አሳደዳቸው። ይህን ዜና ቅድስት መሪና ስትሰማ ደስ አላት። እጅግ ባማረ ንጽሕና እንደ ኖረች ሁሉ በክርስቶስ ስም ደሟን ለማፍሰስ አስባ ወደ ንጉሡ መኮንን ሔደች።

አበው እንዳስተማሩን ከሴቶች ሰማዕታት በውበትና ደም ግባት እንደ ቅዱሳት፦ መሪና፣ አርሴማ እና ጣጡስ የሚያክል የለም። ዐይንን ማፍዘዝ የሚችል ውበት ነበራቸው።

መኮንኑ መልኩዋን ዐይቶ ሰውነቱ ተናወጠ:: "ጣዖት አምልኪና የእኔ ሚስት ሁኚ" አላት:: እርሷ ግን መኮንኑን ከነ ጣዖቱ አቃለለችው:: "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ" አለችው::

መኮንኑ ካነጋገሯ የተነሳ ተቆጥቶ ይገርፏት ዘንድ አዘዘ:: መሬት ላይ ጥለው በብረት ዘንግ ቢመቷት አካሏ እየተቆረጠ ብዙ ደም ፈሰሰ:: ወስደውም ጨለማ ውስጥ ጣሏት:: ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ አድኗት: አጽንቷትም ዐረገ::

በማግስቱ በመጋዝ አካሏን ቆራርጠው ጣሉ:: ዳግመኛ ሊቀ መላእክት አዳናት:: ወደ ጨለማ ክፍል ወስደው ሲጥሏት ትልቅ ዘንዶ መጣባት:: እጆቿ ተዘርግተው እጸለየች ዋጣት:: እርሷ ግን ጸሎቷን ቀጠለች:: ከደቂቃዎች በሁዋላ ግን ዘንዶው ለ2 ተሰነጠቀና እጆቿ እንደተዘረጉ ወጣች::

በሌላ ቀን ግን ሰይጣን ፊት ለፊት መጥቶ ታገላት:: ከሰማይ ነጭ ርግብና መስቀል ወርዶላታልና አልቻላትም:: ከእግሯ በታች ጥላ ደጋግማ ረገጠችው:: ሰይጣንም በሐፍረት እየጮኸ ሔደ። "ለሰይጣን ኬደቶ ከመ አሣዕን በእግር" እንዲል:: (እንዲህ ነበሩ የቀደመው ዘመን እናቶቻችን)

መኮንኑ ከክርስትና ያስወጣት ዘንድ በትልቅ ጋን ውሃ አስፈልቶ "በዚያ ላይ ቀቅሏት" አለ:: ድንገት ግን ከሰማይ ነጭ ርግብ ወርዳ: ውሃውን አቀዝቅዛ: 3 ጊዜ በውሃው አጠመቀቻት:: (እስከዚህ ሰዓት ድረስ አልጠመቀችም ነበርና)

ርግቧ የብርሃን ልብስ አልብሳ: አክሊለ ክብር ደፋችላት:: መኮንኑ ተስፋ ስለ ቆረጠ "አንገቷን በሰይፍ ምቱ" አለ:: በዚያች ሰዓት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ "ብጽዕት መሪና ብጽዐን ይገባሻል" አላት::

"ስምሽ በሚጠራበት: መታሰቢያሽ በሚደረግበት ሁሉ በዚያ ረድኤት: በረከት ይበዛል:: አንቺን ያከበረውን አከብረዋለሁ:: ከርስትሺም አስገባዋለሁ" ብሏት ጌታችን ዐረገ::

ወታደሮቹ አንገቷን በሰየፉ ጊዜ ታላቅ መነዋወጽ ሆነ:: ድውያን ተፈወሱ: ዕውሮች አዩ: አንካሶች ረቱ: የማይሰሙትም ሰሙ:: ቅዱሳን መላእክትም ከሰማያት ወርደው የቅድስት መሪናን ነፍስ በዝማሬ አሳረጉ።

(#Deacon_Yordanos_Abebe)

(ይህቺ ቅድስት እናት በእኛ አገር ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ እያልን ምስሏን እንጠቀመዋልን ይህ ፈጽሞ ስህተት መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል)
@petroswepawulos
††† እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ዘዮሐንስ እና ለሰማዕቱ አባ ኖብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ †††

††† ኢትዮጵያዊው ጻድቅ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ሃገረ ሙላዳቸው ሸዋ (መርሃ ቤቴ) ነው:: ወላጆቻቸው ዘካርያስ እና ሶፍያ እግዚአብሔርን የሚፈሩ : እመ ብርሃንን የሚወዱና ለነዳያን የሚራሩ ነበሩ::

ደጉ ዘካርያስ መስፍን ሲሆን እርሱ በሌለበት የሸዋ ገዢ ሊያገባት በመሞከሩ ቅዱስ ገብርኤል ቀስፎታል:: ሕዝቡ ገዢነቱን ለዘካርያስ ሰጥተውታል:: ከቆይታ በኋላም ድንግል ማርያም የተባረከ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን "ዮሐንስ" አሉት:: በሒደት ግን ዘዮሐንስ (የዮሐንስ) ተብሏል::

ቅዱሱ ዘዮሐንስ እስከ ሰባት ዓመቱ ድረስ በእናቱ እቅፍ ቆይቶ ወደ ትምሕርት ገብቷል:: ጸጋ እግዚአብሔር ጠርቶታልና በአጭር ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቀ:: አደን ይወድ ነበርና ሊያድን ሲወጣ 'ብርሕት ደመና' ድንገት ነጥቃ ከኢትዮጵያ (ሽዋ) ወደ ኢየሩሳሌም (ጐልጐታ) አደረሰችው::

ደስ ብሎት ቅዱሳት መካናትን ተሳልሞ ደመናዋ ወደ ሃገሩ መለሰችው:: ከጥቂት ጊዜ በኋላም ከሰማይ ነቢዩ ኤልያስና መጥምቁ ወርደው ባረኩትና "ክፍልህ ከእኛ ጋር እንዲሆን መንን" አሉት::

ዘዮሐንስ ወላጆቹንና ቤተ ክርስቲያንን እያገለገለ (ዲቁና ነበረውና) ሃያ አምስት ዓመት ሞላው:: ያን ጊዜ ወላጆቹ "እንዳርህ" ቢሉት "የለም! አይሆንም" አላቸው:: አርጅተው ነበርና ስለእነርሱ ዕረፍት ጸለየ:: ፈጣሪም ሰምቶታልና ሁለቱም በክብር ተከታትለው ዐረፉ::

ሕዝቡ በወላጆቹ ፈንታ "እንሹምሕ" ቢሉት "እንቢ" ብሎ ወርቁን : ብሩን : ርስቱን : ቤቱን ሁሉ ለነዳያን አካፍሎ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገባ::
ጊዜው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ባረፉ በሃምሳ ዓመት አካባቢ ሲሆን አባ ሕዝቅያስ አበ ምኔት ነበሩ::
(ከዚህ በኋላ አንቱ እያልን እንቀጥል)

አባ ዘዮሐንስ ለሰባት ዓመታት ገዳሙን ረድተው መነኮሱ:: እንደ ልማዱ ደመና ነጥቆ ወስዷቸው ከኢየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳሳት ቅስና ተቀብለዋልና በደብረ ሊባኖስ ለሃያ አምስት ዓመታት አገለገሉ:: ቤተ መቅደሱን በመዓልት ሰባት ጊዜ በሌሊት ሰባት ጊዜ ያጥኑ : እልፍ እልፍ ይሰግዱ : ተግተው ይጸልዩ : ይታዘዙም ነበር::

ከዚያም በፈጣሪ ትዕዛዝ በትግራይና በሌሎቹ የሃገራችን ክፍሎች ወንጌልን ሰብከዋል:: እድሜአቸው ሰባ በሆነ ጊዜ ወደ ጌታ መቃብር (ጐልጐታ) ሔደው ተሳልመው በእርሱ (በጌታ) ትዕዛዝ ወደ ደራ (ጣና ዳር) ተመለሱ::

በአካባቢውም ገብርኤልና መስቀል ክብራ የሚባሉ ደጋግ ባለ ትዳሮች ነበሩና በእንግድነት ከቤታቸው አደሩ:: ቤቱ በቅጽበት በበረከት ሞላ:: እነርሱም የጻድቁን አምላክ አመሰገኑ::

ቀጥሎም በመስቀል ክብራ መሪነት ጻድቁ ዘዮሐንስ ወደ ክብራን ገብርኤል ደሴት ገቡ:: (በነገራችን ላይ ደሴቱ ክብራን የተባለ መስቀል ክብራ በምትሰኘው ደግ ሴት ስም ነው:: እርሷና ባሏ ገብርኤል የተቀደሱ ሰዎች ነበሩና::)

ጻድቁ አቡነ ዘዮሐንስ ወደ ደሴቶቹ (ክብራንና እንጦንስ ኢየሱስ) እንደ ገቡ ደሴቶቹ በግማሹ የስውራን ቤት : እኩሉ ደግሞ የጣዖት (ዘንዶ) አምላኪዎች መኖሪያ ነበር:: ጻድቁ ክብራን ገብርኤልንና እንጦንስ ኢየሱስን የመሠረቱት በ1315 ዓ/ም አካባቢ በዐፄ ዓምደ ጽዮን ዘመን ነው:: በአካባቢው ዘንዶ ይመለክ ነበርና ያንን በጸሎታቸው አጥፍተው ሕዝቡን አጥምቀዋል::

በዚያም ገዳሙን የወንድና የሴት ብለው ከፈሉ:: የወንዶች ክብራን ሲሆን ሴት አይገባበትም:: አበ ምኔቱም ራሳቸው ጻድቁ ነበሩ::
የሴቶች እንጦንስ ኢየሱስ ከካህናት በቀር ወንድ አይገባበትም:: እመ ምኔቷም እናታችን ቅድስት ክብራ (መስቀል ክብራ) ሆነች::

ጻድቁ አቡነ ዘዮሐንስ በክብራን ለሰላሳ አምስት ዓመታት ተጋድለዋል:: ለጸሎት ከመቆማቸው ብዛት እግራቸው አብጦ : ቆሳስሎ ነበር:: የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወትር ይገለጽላቸው : ያነጋግራቸውም ነበር::

እጅግ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ሠርተው: ለወንጌል እንደሚገባ ኑረው: በተወለዱ በመቶ አምስት ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: ጌታችንም በስማቸው ለተማጸነና ገዳማቸውን ለሳመ የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል:: ልደታቸው ደግሞ ኅዳር 13 ቀን ይከበራል:: ገዳማቸው (ክብራን ገብርኤልና እንጦንስ ኢየሱስ) ድንቅ ነውና እንድታዩት ተጋብዛቹሃል::

††† ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት †††

††† በምድረ ግብጽ ከታዩ ታላላቅ ከዋክብት አንዱ ቅዱስ ኖብ በሃገረ ንሒሳ ተወልዶ ያደገ ሲሆን ዘመኑም ዘመነ ሰማዕታት (3ኛው መቶ ክ/ዘመን) ነው:: ወላጆቹ በልጅነቱ ብዙ ሃብት ትተውለት ያርፋሉ:: ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ካህኑ ስለ ምናኔና ሰማዕትነት ሲሰብክ ይሰማዋል::

ገና በአሥራ ሁለት ዓመቱ በቤቱ የነበረውን ሁሉ ለነዳያን አካፍሎ መስቀለ ክርስቶስን ሊሸከም ወደ ዐውደ ስምዕ (የምስክርነት አደባባይ -የክርስቲያኖች መገደያ ቦታ) ተጓዘ:: በዚያም በጉባዔ መካከል ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ ምክንያት በሰብዓዊ አካል ሊሸከሙት የማይችሉትን መከራ በልጅ ገላው ተቀብሏል::

በዚያው ልክም ብዙ ተአምራትን ሰርቷል:: በተአምራቱና በጣዕመ ስብከቱም ከመቶ ዘጠና ሺህ በላይ አሕዛብን ወደ ክርስትና መልሶ ሁሉም ተሰይፈዋል:: በእሳት: በስለት: በሰይፍ: በባሕርና በየብስ መከራን ከተቀበለ በኋላ በዚህች ቀን አክሊለ ክብርን ይቀበል ዘንድ አንገቱን ተከልሏል::

ጌታችን የገባለት ቃል ኪዳኑ ግሩም ነውና ዛሬ በግብጽ በድምቀት ይከበራል:: ምንም በእድሜ ልጅ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን አባ (አባታችን) ኖብ ትለዋለች::

††† ቸር ጌታ መድኃኔ ዓለም በጻድቁና በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

††† ሐምሌ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን (ኢትዮጵያዊ)
2.ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት
3.መቶ ዘጠና ሺህ ሰማዕታት (የአባ ኖብ ማኅበር)
4.አባ ተክለ አዶናይ ዘደብረ ሊባኖስ
5.አቡነ ተወልደ መድኅን (ኢትዮጵያዊ)
6.አባ ስምዖን ጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት
7.ቅድስት ክብራ (መስቀል ክብራ) ዘእንጦንስ ኢየሱስ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤጲስቆጶስ)
3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
4.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
6.ሃያ አራቱ ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
7.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮጵያዊ)

††† "ስለዚህ እኔ ደግሞ በእናንተ ዘንድ ስለሚሆን በጌታ በኢየሱስ ስለማመንና ለቅዱሳን ሁሉ ስለሚሆን መውደድ ሰምቼ ስለ እናንተ እያመሰገንሁ ስጸልይ ስለ እናንተ ማሳሰብን አልተውም::" †††
(ኤፌ. ፩፥፲፭)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
@petroswepawulos
ቅዱሳት መጻህፍትን ማግኘት ይፈልጋሉ እንግዳዉስ Join ብለው ይቀላቀሉን
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈሰ ቅዱስ ስም አሜን
ሐምሌ 24-ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ አባ ኖብ በብዙ መከራ ሰማዕትነቱን በድል ፈጸመ፡፡ ከእርሱም ጋር 190 ሺህ ማኅበርተኞቹ በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡
+ ጣና ክብራን ገብርኤል ገዳምን የመሠረቱት አቡነ ዘዮሐንስ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ ቅዱሳን አባቶቻችን አቡነ ተክለ አዶናይ እና አቡነ ተወልደ መድኅን ዕረፍታቸው መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡
አባ ኖብ ሰማዕት ዘታህታይ ግብፅ፡- አባ ኖብ ከደቡባዊ ግብፅ ከንሂሳ ገዳም የተገኙ ሰማዕት ናቸው፡፡ በተወለዱ በ5ኛ ቀናቸው መልአክ ሲያነጋግራቸው ወላጆቻቸው አይተው በአንክሮ እያዩ አሳደጓቸው፡፡ ምግባር ሃይማኖታቸውና እጅግ ጽኑ የሆነው ተጋድሎአቸው "አባ" አስባላቸው እንጂ ገና የ12 ዓመት ሕፃን ናቸው፡፡ የነበሩበት ዘመን የክርስቲያኖች ደም እንደ ውኃ በሚፈስበት በከሃዲው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ስለነበረ አባ ኖብ ወደ ሰማዕትነቱ በፈቃዱ ሄደው በከሃዲው ንጉሥ ፊት ስለ ክርስቶስ ለመመስከር ሄዱ፡፡ ሲሄዱም አንድ ጻድቅ ‹‹አባ አትሂዱ›› ቢላቸው ‹‹የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻ ቁልፍ ልቀበል ነው የምሄደው›› ብለውት ሄዱና በሃዲዎቹ ነገሥታት ፊት የአምላካቸውን ክብር መሰከሩ፡፡ የታሰሩ ክርስቲያኖችን በክርስቶስ ማመናቸውን እስከመጨረሻው አጽንተው የተዘጋጀላቸውን የጽድቅ አክሊል እንዲወርሱ ይመክሯቸው ነበር፡፡
አባ ኖብም የወላጆቻቸውን ሀብት ለድሆች መጽውተው ወደ ሰማዕትነቱ ሲሄዱ መኰንኑ አገኛቸውና ‹‹ክርስቶስን ክደህ ለጣዖቶቻችን ስገድ›› ቢላቸው ከንቱነቱን ነግረው አስተማሩት፡፡ በብዙ አሰቃቂ መከራዎችም በእጅጉ አሠቃያቸው፡፡ የታዘዘ መልአክም መጥቶ ፈወሳቸውና ወደፊት የሚደርስባቸውን ነገራቸው፡፡ ከዚህም በኋላ መኰንኑ ወደ አትሪብ በመርከብ ይዟቸው ሲሄድ በመርከቡ ምሰሶ ላይ ዘቅዝቆ በመስቀል ሥጋቸው እስኪቆራረስ ድረስ በብረት በትር አስገረፋቸው፡፡ መኰንኑም በእሳቸውን እያስገረፈ እርሱ ተቀምጦ ሊበላና ሊጠጣ በፈለገ ጊዜ እመገባለሁ ቢል ምግቡ ድንጋይ ሆነበት፡፡ የአሽከሮቹም ዐይን ታወረ፡፡ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ከስቅላታቸው አውርዶ ቁስላቸውንም ፈውሶ ደማቸውን ጠረገላቸው፡፡ አባ ኖብም ጸልየው የታወሩትን ሰዎች የዐይናቸውን ብርሃን መልሰውላቸው አስተምረው ወደ ሃይማኖትም መለሷቸው፡፡ እነርሱም መስክረው ሰማዕት ሆነው ተሰይፈዋል፡፡
ወደ አትሪብም ከደረሱ በኋላ አባ ኖብን ግን ስቃዩ ይጥናባቸው ብለው በብረት ችንካሮች ቸንክረዋቸው በብረት አልጋ ላይ አድርገው እሳት አነደዱባቸው፣ በመጋዝም ሰነጠቋቸው፣ ሰውነታቸውን ቆራርጠው ጣሉት፡፡ አሁንም መልአኩ መጥቶ አዳናቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ወሰዷቸውና ብዙ አሠቃዩአቸው፡፡ ለመርዛማ እባቦች ቢሰጧቸውም ምም አልነኳቸውም ይልቁንም አንዱ እባብ ሄዶ በመኰንኑ አንገት ላይ ተጠምጥሞ ነድፎ ለሞት አደረሰው፡፡ ሟርተኞቹ እንዳላዳኑት ካወቀ በኋላ አባታችን እባቡን ከአንገቱ ላይ እንዲወርድ አድርገው ፈወሱት፡፡
መኰንኑም ዳግመኛ በእሳት እንዲያቃጥሏቸው ቢያዝም እሳቱ እሳቸውን ማቃጠልን እምቢ አለ፡፡ መኰንኑ ማሠቃየቱ በሰላቸው ጊዜ አንገታቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዘ፡፡ አባ ኖብ ስለ ክርስቶስ እየመሰከሩ ጽኑ መከራን እየተቀበሉ ለብዙ ዓመታት ከተሠቃዩና ከጌታችን ታላቅ ቃልኪዳን ከተቀበሉ በኋላ ሐምሌ 24 ቀን አንገታቸውን ተሰይፈው ሰማዕትነታቸውን ፈጽመዋል፡፡ 190 ሺህ ሰማንያ አራት የአባ ኖብ ማኅበርተኞችም እንዲሁ በሐምሌ 24 ተሰይፈው ሰማዕት ሆነዋል፡፡ ቅዱስ ሥጋቸውም ወደ ገዳመ ንሒሳ ሲላክ እጅግ አስገራሚ ተአምራት ተፈጽመዋል፡፡ የሰማዕቱ የአባ ኖብ ቤተክርስቲያናቸው በሀገራችን ሸዋ ቡልጋ ኢቲሳ ውስጥ ይገኛል፡፡ አባ ኖብ በመከራ ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው ስማቸውን ቢጠራ ከመከራው ፈጥኖ እንደሚድንባቸው ከጌታችን ቃልኪዳን የተሰጣቸው ታላቅ የበረከት አባት ናቸው፡፡ የአባ ኖብ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
ክብራን ገብርኤል ገዳምን የመሠረቱት አቡነ ዘዮሐንስ፡- አባቱ ዘካርያስና እናቱ ሶፍያ እግዚአብሔርን በማመን የተመሰገኑ ምግባር ሃይማኖታቸው የቀና ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ የሀገር ሰዎችም መክረው ዘካርያስን በእነርሱ ላይ ጌታና ገዥ አደረጉት፡፡ እርሱም በጥሩ አገዛዝ በፍቅር ገዛቸው፡፡ እነርሱም እንደ አሽከሮች ሆኑት፣ እርሱም እስከ አማራ ጠረፍ ድረስ ለሸዋ ሰዎች እንደ ቸር እረኛ ሆናቸው፡፡ ዘካርያስና ሚስቱ ሶፍያም በጎ ሥራን ሁሉ አላቋጡም፡፡ ምጽዋትን መስጠትን፣ ከገንዘባቸውም ከፍለው ለእግዚአብሔር አሥራት መስጠትን አላቋረጡም፡፡ የተቸገሩትን፣ የተራቡትንና የተጠሙትን ሁሉ ያበላሉ፣ ያጠጣሉ፡፡ ይህንንም ሲሄዱም ሲመለሱም ሁልጊዜ ያደርጋሉ፡፡ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስንና የቅድስት ድንግል ማርያምን፣ የጻድቃንና የሰማዕታን መታሰቢያም ያድርጋሉ፡፡ ልጅም አልነበራቸውምና ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ይማፀኑ ነበር፡፡ ሶፍያም ጠዋት ማታ እንዲህ እያለች ትጸልይ ነበር፡- ‹መካን ለነበረች ለሐና ልጅ እንደሰጠኻት፣ ለአብርሃም ሚስት ለሣራም፣ ለጸጋ ዘአብ ሚስት እግዚእ ኀረያም እንደሰጠኻቸው አቤቱ እንደ እነርሱ አንተን ደስ የሚያሰኝህን ልጅ ስጠኝ› እያለች እመቤታችንንም እየተማፀነች ታለቅስ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም መጥምቁ ዮሐንስን የመሰለ ልጅ ‹አባ ዘዮሐንስ› የተባለ ቅዱስ ልጅ ሰጣቸው፡፡ እሱም በሸዋ፣ በመራቤቴ እስከ አማራ ጠረፍ ድረስ የሚያበራ መብራት ሆነ፡፡›› በኋላም በጣና ሐይቅ ላይ የሚገኘውን ‹‹ክብራን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን›› የመሠረቱት እኚህ አባ ዘዮሐንስ የተባሉ ጻዲቅ ናቸው፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ታሪካቸውንና የተሰጣቸውን አስደናቂ ቃልኪዳን እንመለከት፡- ለአባ ዘዮሐንስ በጌታ ዘንድ ታዘው ነቢዩ ኤልያስና ዮሐንስ በእኩለ ሌሊት ተገልጠውላቸው አስኬማና ቆብ ሰጥተዋቸዋል፡፡ እመቤታችንም ተገልጣላቸው ወደ ደብረሊ ሊባኖስ ሄደው እንዲመነኩሱ ነግራቸው ኤልያስና ዮሐንስ እየመሩ ከቦታው አድርሰዋቸዋል፡፡ ሰባት ዓመትም በዚያ ሲያገለግሉ ኖሩ፡፡ ስግታቸውም ሁልጊዜ ስምንት ሺህ ነበር፡፡ ጌታም በደብሊባኖስ ሲያጥኑ ተገልጦላቸው ስምህ ‹‹ዘዮሐንስ ይሁን›› ብሎ ትልቅ ቃልኪዳን ተጥቷቸዋል፡፡ ደመናም ተሸክማ ወስዳ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም አድርሳቸው በዚያም ከቆዩ በኋላ ደመናዋ መልሳ ወደ ሸዋ አምጥታቸዋለች፡፡ በትግራይ ለራሳቸው መጠለያ ሲሠሩ የጌታ ፈቃድ አልነበረምና ከባድ የሆድ ሕመም መጣባቸው፡፡ ደመናዋም ደራ ሮቢት አደረሰቻቸው፡፡ በዚያም እንደደረሱ ገብርኤልና መስቀል ክብራ በሚባሉ እግዚአብሔርን በሚወዱ ደጋግ ባለትዳሮች ቤት ዕረፍት አደረጉ፤ ለሰባት ቀናትም በዚያ ቆዩ፡፡ ከዚያም መልአኩ ተገልጦ ወደ ደሴቷ እንዲሄዱና እርሷም ዕጣ ክፍላቸው እንደሆነች ነገራቸው፡፡
አባ ዘዮሐንስም በደሴቷ ላይ በጾም በጸሎት ጸንተው ተቀመጡ፣ ትሎችም ሰውነታቸውን እንዲመገቡ ያድርጉ ነበር፡፡ ገብርኤልና መስቀል ክብራ የተባሉትም ደጋግ ባለትዳሮች የሚያስፈልጋቸውን ይወሰዱላቸው ነበርና ባገኙዋቸው ጊዜ ትሎቹን ከሰውነታቸው ላይ ሲያራግፉላቸው ‹‹ተዋቸው እኔን ሊመገቡ ተፈቅዶላቸዋል›› አሏቸው፡፡ አባታችን አንድ ቀን የሰው ድምፅ ሰምተው ወደ ውጭ ወጥተው ሲመለከቱ የአካባቢው ሰዎች አንድ ማድጋ ወተት፣ አንድ በግና አንድ ከብት ለዘንዶ ሲገብሩ አይተው ያንን ዘንዶ በሥላሴ ስም በመስቀል ምልክት አማትበው ከሰዎቹ ፊት ገደሉት፡፡ ይህን የሰማውና ሰዎቹን እንዲገብሩ የላካቸው ጃን ቹሐይ የተባለው ጣኦት አምላኪ የአገሩ ሹም ‹‹የማመልከውን ዘንዶ እንዴት
​​?›› በማለት እንዲታሰሩ አደረጋቸው፡፡ ንጉሥ ዐምደ ፅዮንም ይህን ሲሰማ ሠራዊቱን ልኮ ያንን ጣኦት አምላኪ የአገሩን ሹም ገድለው አባ ዘዮሐንስ እንዲፈቷቸው አደረገ፡፡ አባ ዘዮሐንስም ወንጌልን እያስተማሩ፣ ሙትን እያስነሱና ታላላቅ ተአምራትን እያደረጉ በደሴቷ ላይ ተወስነው ተቀመጡ፡፡ በደመናም ተጭነው ወደ ኢየሩሳሌም ሄደው ታቦተ ቅዱስ ገብርኤልን አምጥተው በደሴቷ ላይ ክብራን ገብርኤል ገዳምን መሠረቱ፡፡ ደመናም ደሴቷ ላይ ስታደርሳቸው ኤልያስና ዮሐንስ በቀኝ በግራው እየተራዱአቸው እርሳቸው ሠራዒ ቄስ ሆነው ቀደሱ፡፡ ደሴቷንም መጀመሪያ እንደመጡ ባሳረፈቻቸው ገደኛ ሴት ስም ሰየሟት፡፡ ለሴቶች መነኮሳት ከዚያው አጠገብ የሚገኘውን እንጦንስ ገዳምን አድርገው ክብራን ገብርኤልን ለወንዶች ብቻ አደረጓት፡፡
‹‹አንድ ቀን አባ ዘዮሐንስ በደብረ ሊባኖስ መሥዋዕት ለማቅረብ እያጠነ ሳለ ለስም አጠራሩ ክብርና ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሌላ ሀገር የመጣ እንግዳ ሰው መስሎ ታየውና ‹ሰላም ለአንተ ይሁን› አለው፡፡ አባታችን ዘዮሐንስም ‹ወንድሜ ሆይ! የእግዚአብሔር ፍቅር አንድነት ከአንተ ጋር ይሁን› አለው፡፡ ‹አንተ እንግዳ ሰው ከየት ሀገር የመጣህ ነህ? ከዚህ በፊት አላውቅህም› አለው፡፡ ጌታችንም ከልቡናው ፍግግ አለና ‹ከእናትህ ማኅፀን ሳትወጣ እኔ አውቅሃለሁ› አለው፡፡ ይህንንም ብሎ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ ያደረገለትን ከመወለዱም አስቀድሞ የሆነውን ሁሉ፣ ከተወለደም በኋላ እስከዚያ ቀን ድረስ ያደረገለትን፣ አባቱንም በአመፀኛው በጎዶልያ እጅ ከመሞት እንዳዳነው፣ እናቱንም ዕቁባቱ ሊያደርጋት እንደነበረ ምሥጢሩንም ሁሉ ነገረው፡፡ ይህንንም ብሎ ዳግመኛ ተነጋገረው፡- ‹ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ዘዮሐንስ ይሁን፣ አንተ የዓለሙ ሁሉ ደስታ ነህና የሚያለቅሱም በአንተ ደስ ይላቸዋል› አለው፡፡›› ‹‹በደመናም ተጭነው ኢየሩሳሌም ደርሰው ታቦተ ቅዱስ ገብርኤልን አምጥተው ክብራን ገብርኤል አስገብተው በዚያም ሲኖሩ በጣም አርጅተው ነበርና ራሳቸውን ወደ ምድር አጎንብሰው ይሄዱ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ሐምሌ 10 ቀን ለዓርብ አጥቢያ ሲጸልዩና በግንባራቸው ወደ ምድር ሲሰግዱ ለስም አጠራሩ ስግደት የሚገባው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክረስቶስ ሚካኤልንና ገብርኤልን አስከትሎ መጥቶ ‹ወዳጄ አባ ዘዮሐንስ ሆይ! ከድካም ወደ ዕረፍት፣ ከበሽታ ወደ ሕይወት፣ ከዚህ ዓለም ዐይን ወዳላየውና ጆሮ ወዳልሰማው ተድላ ደስታ ወዳለበት ገነት አሳርፍህ ዘንድ ወደ አንተ መጣሁ› አለው፡፡ ይህንንም ብሎ ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ከእርሱ በረከት እንደማይጠፋ ቃልኪዳን ሰጠው፡፡ ‹ገድልህን የሚጽፍ ወይም የሚያነብ እኔን እንደመሰለ እንደ መልከጼዴቅ ካህን በእኔ ዘንድ የተመረጠና የተወደደ ይሆናል፣ በበዓልህ ማኅሌት የቆመ የመላእክት ባልንጀራ ይሆናል፣ እነዚህን ልጆችህንም የመላእክት አምሳያ አደርጋቸዋለሁ› አለው፡፡ ‹ይህችን ደሴት እንደ ኢየሩሳሌም ሀገሬ፣ እንደ ደብረ ዘይትና ለባሪያዬ ለሙሴ ሕግን እንደ ሰጠሁባት እንደ ደብረ ሲና አድርጌያታለሁ፣ በረከቴም ከእርሷ አይታጣም፣ እኔም ከእርሷ አልለይም ይልቁንም በተጠመቅሁባት ቀን ከዚህች ገዳምህ አልለይም፣ የዚህች ደሴትና የሀገሬ የኢየሩሳሌም መክፈቻ በአንድ ላይ አንድ ይሁን› አለው፡፡ ‹ከዚህች ሀገርም ያለንስሓ የሕፃናትና የጎልማሶች ሞት አይሁን፣ እስከ ዘለዓለምም ድረስ ጸሎት ከእርሷ አይቋረጥ› አለው፡፡ ጌታችንም ለአባ ዘዮሐንስ ይህን ከተናገረው በኋላ ቡራኬ ሰጥቶት ከቅዱሳን መላእክት ጋር ወደቀደመ ቦታው ዐረገ፡፡›› ጻድቁ በ105 ዓመታቸው ሐምሌ 24 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡ የአባ ዘዮሐንስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
@petroswepawulos
​​በዚኽች ዕለት ሐምሌ 24 በዕረፍታቸው በዓል ታስበው የሚውሉት አቡነ ዘዮሐንስ የገደሙት ጣና ክብራን ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም እና በሀገራችን ሰሜን ሸዋ ውስጥ የሚገኘው የሰማዕቱ የቅዱስ አባ ኖብ ቤተ ክርስቲያን!
ጻድቁ አቡነ ዘዮሐንስ 8 ሺህ ስግደትን በየቀኑ ይሰግዱ የነበሩ ሲኾን መካነ መቃብራቸውና ይለብሱት የነበረው የብረት ሰንሰለት ልብሳቸው በዚኹ ገዳም ውስጥ ይገኛል፡፡ ነቢዩ ኤልያስና መጥምቁ ዮሐንስ በእኩለ ሌሊት ተገልጠውላቸው አስኬማና ቆብ የሰጧቸው አቡነ ዘዮሐንስ በዚኽች በጣና ደሴት ላይ በጾም በጸሎት ጸንተው ሲኖሩ ትሎች ሰውነታቸውን እንዲመገቡ ያድርጉ ነበር፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ምእመናን የሚያስፈልጋቸውን ይዘውላቸው ሲመጡ ጻድቁ እንደተለመደው ሰውነታቸውን ለትሎች ሲመግቡ አገኟቸው፡፡ ሰዎቹም ትሎቹን ከአባታችን ሰውነት ላይ ሊያራግፉላቸው ሲሉ አቡነ ዘዮሐንስ ግን ‹‹...ተዋቸው እኔን ሊመገቡ ተፈቅዶላቸዋል›› ነው ያሏቸው፡፡ ከበዓለ ዕረፍታቸው በረከት ያድሉን!
+ + +
ሰማዕታት ሐዋርያ ናቸው፡፡ የሰማዕታት ሐዋርያዊ ተልዕኮ ምን እንደሚመስል የአባ ኖብ ገድል በተግባር ያሳየናል፡፡ አባ ኖብ በተአምራታቸውና በትምህርታቸው አሳምነው ለክርስቶስ መንግሥት ያበቋቸው ሰዎች ብዛት ከ190 ሺህ በላይ ናቸው፡፡ ከዚህ በላይ ምን ዓይነት ሐዋርያዊ ተልዕኮ አለ?
2ኛ ሌላው የሰማዕታት ሐዋርያዊ ተልዕኮ ሰማዕታት አስቀድመው ጠንቋዮች የነበሩትን አሳምነው ለሰማዕትነት ያበቋቸው መሆኑ ነው፡፡ የአባ ኖብንና የሦስቱን ኃይለኛ ጠንቋዮች ታሪክ እናያለን፣
3ኛ ሌላው ከአባ ኖብ ገድል የምናገኘው የተለያዩ ገቢረ ተአምራትን በማድረግ እልፍ ከሃዲያንን እንዳሳመኑ፣
4ኛ ሕፃናትም ጭምር ለሰማዕትነት እንደተመረጡ፣
5ኛ ሰማዕትነት የክርስቶስን ፍቅር በማሰብ በራስ ነጻ ፈቃድ እንደሚፈጸም፣
6ኛ ሰማዕታት በመከራቸውና በዕረፍታቸው ጊዜ ጌታችን ቅዱሳን መላእክቱን እየላከ ሰማዕታትን ከቊስላቸው እንደሚፈውሳቸው ነው፡፡ የተወሰኑትን በዝርዝር እንያቸው፡-
ሰማዕታት አስቀድመው ጠንቋዮች የነበሩትን አሳምነው ለሰማዕትነት እንዳበቋቸው፡- ሰማዕቱ ቅዱስ አባ ኖብን መኰንኑ ብዙ ካሰቃያቸው በኋላ ወደ አትሪብ በመርከብ ይዟቸው ሲሔድ በመርከቡ ምሰሶ ላይ ዘቅዝቆ በመስቀል ሥጋቸው እስኪቆራረስ ድረስ በብረት በትር አስገረፋቸው፡፡ መኰንኑም በእሳቸውን እያስገረፈ እርሱ ተቀምጦ ሊበላና ሊጠጣ በፈለገ ጊዜ እመገባለሁ ቢል ምግቡ ድንጋይ ሆነበት፡፡ የአሽከሮቹም ዐይን ታወረ፡፡ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ከስቅላታቸው አውርዶ ቍስላቸውንም ፈውሶ ደማቸውን ጠረገላቸው፡፡ አባ ኖብም ጸልየው የታወሩትን ሰዎች የዐይናቸውን ብርሃን መልሰውላቸው አስተምረው ወደ ሃይማኖትም መለሷቸው፡፡ እነርሱም መስክረው አንገታቸውን ተሰይፈው በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡
ወደ አትሪብም ከደረሱ በኋላ አባ ኖብን በብረት ችንካሮች ቸንክረዋቸው በብረት አልጋ ላይ አድርገው እሳት አነደዱባቸው፣ በመጋዝም ሰነጠቋቸው፣ ሰውነታቸውን ቆራርጠው ጣሉት፡፡ አሁንም የታዘዘ መልአኩ መጥቶ አዳናቸው፡፡ ከዚኽም በኋላ ወደ እስክንድርያ ወሰዷቸውና በዚያም ብዙ አሰቃዩአቸው፡፡ መኰንኑም በአገሪቱ በሥራይ ሥራቸው የታወቁ ኃይለኛ ጠንቋዮችን ጠርቶ አባ ኖብን በሥራያቸው እንዲገድሉለት አዘዛቸው፡፡ ጠንቋዮቹም ‹‹ሥራያችንን በመርዛማ እባቦች ላይ አሳድረን እንገድለዋለን›› በማለት አባ ኖብ በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲታሠሩ በማድረግ በገዳይነታቸው የሚታወቁ መርዛማ እባቦችን አባ ኖብ ወደታሠሩበት ክፍል እንዲገቡ አደረጉ፡፡ አባ ኖብም መርዛማ እባቦቹን በቃለ እግዚአብሔር ስላሰሯቸው ምንም አልነኳቸውም ነበር፡፡ ይልቁንም አንዱ እባብ ሄዶ በመኰንኑ አንገት ላይ ተጠምጥሞ ነድፎ ለሞት አደረሰው፡፡ ሟርተኞቹ እንዳላዳኑት ካወቀ በኋላ አባታችን እባቡን ከመኮንኑ አንገት ላይ እንዲወርድ አድርገው ፈወሱት፡፡ ይህንን ታላቅ ተአምር ያዩት እነዚያ ኃይለኛ ሥራየኞችም ‹‹የአባ ኖብ አምላክ እርሱ እውነተኛ አምላክ ነው፣ እኛም በእርሱ አምነናል›› ብለው መሰከሩ፡፡ መኮንኑም በዚህ ጊዜ በታላቅ ቁጣ ሆኖ ራስ ራሶቻቸውን እያሰፈ በሰማዕትነት ገደላቸው፡፡ የክብር አክሊልንም ተቀዳጁ፡፡
ጌታችን ቅዱሳን መላእክቱን እየላከ ሰማዕታትን ከቊስላቸው እንደሚፈውሳቸው፡- ሰማዕታት ሰማዕትነታቸውን በክብር እስኪፈጽሙ ድረስ ጌታችን ቅዱሳን መላእክቱን እየላከ ሰማዕታትን ከቍስላቸው እንደሚፈውሳቸው ይፈውሳቸዋል፡፡ የሰማዕቱ የአባ ኖብ ገድል አንዱ ማሳያ ነው፡፡
የወላጆቻቸውን ሀብት ለድኆች መጽውተው ወደ ሰማዕትነት አዳባባይ ሔደው በከሃዲው መኰንን ፊት ቆመው የጌታችንን አምላክነት ስለመሰከሩ መኮንኑ ይዞ በብዙ አሠቃቂ መከራዎች በእጅጉ አሠቃያቸው፡፡ በዚኽም ጊዜ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ አባ ኖብን ፈወሳቸው፡፡ ከዚኽም በኋላ መኰንኑ ወደ አትሪብ በመርከብ ይዟቸው ሲሄድ በመርከቡ ምሰሶ ላይ ዘቅዝቆ በመስቀል ሥጋቸው እስኪቆራረስ ድረስ በብረት በትር አስገረፋቸው፡፡ መኰንኑም በእሳቸውን እያስገረፈ እርሱ ተቀምጦ ሊበላና ሊጠጣ በፈለገ ጊዜ እመገባለሁ ቢል ምግቡ ድንጋይ ሆነበት፡፡ የአሽከሮቹም ዐይን ታወረ፡፡ ዳግመኛ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ አባ ኖብን ከስቅላታቸው አውርዶ ቍስላቸውንም ፈውሶ ደማቸውን ጠረገላቸው፡፡ አባ ኖብም ጸልየው የታወሩትን ሰዎች የዐይናቸውን ብርሃን መልሰውላቸው አስተምረው ወደ ሃይማኖት መለሷቸው፡፡ እነርሱም መስክረው ሰማዕት ሆነው ተሰይፈዋል፡፡ ወደ አትሪብም ከደረሱ በኋላ አባ ኖብን ክፉዎች ይዘው በብረት ችንካሮች ቸንክረዋቸው በብረት አልጋ ላይ አድርገው እሳት አነደዱባቸው፣ በመጋዝም ሰነጠቋቸው፣ ሰውነታቸውን ቆራርጠው ጣሉት፡፡ ነገር ግን የዘወትር ጠባቂያቸውና በመከራ ጊዜ የሚያጸናቸው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል አሁንም መጥቶ አዳናቸው፡፡ አባ ኖብ በተአምራታቸውና በትምህርታቸው ካሳመኗቸው ከ190 ሺህ ማኅበርተኞቻቸው ጋር አንገታቸውን ተሰይፈው ሰማዕትነታቸውን በድል ፈጽመው የክብርን አክሊል እስከተቀበሉ ድረስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ሁልጊዜ ከቍስላቸው እየፈወሰ መከራውን ያስታግሣቸው ነበር፡፡
የአቡነ ዘዮሐንስ እና የሰማዕቱ የቅዱስ አባ ኖብ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
@petroswepawulos
🌺 ንስሐ ገብተን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋን ክቡር ደሙን በመቀበል የሚገኘው ጥቅም ምንድን ነው?

✥ በቅድሚያ እንኩዋን ለአቡነ ተክለሃይማኖት ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ.. ስለ ጻድቃን እንዲህ ተጽፉዋል ✥ " አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፥ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና።"(ዕብ11:16) በጸሎታቸው ይማረን።

✥ ወደ ርዕሳችን ስንመለስ ንስሐ ገብተን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋን ክቡር ደሙን በመቀበል የሚገኘው ጥቅም ምንድን ነው? የሚለውን እናያለን።

🍍''ወዮ! ከአንቺ የተገኘ ኅብስት በማመን ከእርስሱ ለሚቀበሉት ሕይወትንና ድኅንነትን የሚሰጥ ነው፤ ወዮ! ከአንቺ የተገኘ ኀብስት በማመን ከእርሱ ለማይቀበሉ ሰዎች የማይላመጥ ጽኑዕ ነው፤ ይኸውም ፍጹም ኃላይ የሚሆን የአድማስ ደንጊያ ነው፤ ወዮ! ከአንቺ የተገኘ ጽዋዕ በማመን ከእርሱ ለሚጠጡ ሰዎች ጥበብን የሚገልጽ ሕይወትን የሚሰጥ ነው፤ ወዮ! ከአንቺ የተገኘ ጽዋዕ በማመን ከእርሱ ለማይጠጡ ሰዎች ኃጢአትን ስለማስተስረይ ፈንታ ኃጢአትን የሚጨምር ነው'' (ቅዳሴ ማርያም)

#ክርስቶስ_በእኛ_ውስጥ_ይኖራል

👉 ሕይወታችን ጣፋጭና ለሰዎች መልካም መዓዛ የሚሆነው ፈጣሪያችን በእኛ ውስጥ ሲኖር ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ውስጥ የሚኖረው እኛም በእርሱ ውስጥ የምንኖረው ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ስንቀበል ነው። " ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።"(ዮሐ 6:56) እንዲል።

#ኃጢአታችን_ይሰረይልናል

👉 የቆሸሸን ልብስ ውኃና ሳሙና እንደሚያነጹት በኃጢአት የጎሰቆለው ሰውነታችን በንስሐ ጸድቶ የክርስቶስን ሥጋና ደም በመቀበል ከኃጢአት የምንነጻ መሆኑን ጌታ " ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።''(ማቴ 26:28) በማለት ተናግሯል።

#የነፍስና_የሥጋን_በረከት_እናገኛለን

👉 ፈጣሪያችን ኢየሱስን ክርስቶስ " ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።"(ዮሐ 6:35) በማለት የነፍስና የሥጋ በረከት እንደምናገኝ ረኃብና ጥም እንደማይገጥመን፣ በመንፈሳዊ ሕይወት እውቀት የምንበለጽግበት ታላቅ ምሥጢር መሆኑን ተናግሯል።

#የክርስቶስ_መከራ_ያሳስበናል

👉 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንቶስ ላሉ ክርስቲያኖች ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም ምሥጢር ሲያስረዳ " ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፥ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና።"(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:26) በማለት ተናግሯል። በክርስቶስ የሚያምኑ ሥጋውንና ደሙን የተቀበሉ ሁሉ የክርስቶስን ሕማም ሞት ለእኛ ያደረገውን ውለታ ያስባ ፤ ያደረገውንም ውለታ ለዘላለም ሲመሰክሩ እንደሚኖሩም ተናግሯል።

#የዘላለምን_ሕይወት_እናገኛለን

👉 ''ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና።'' (ዮሐ 6:54-55) በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዘላለም ሕይወትን የምናገኘው ሥጋውንና ደሙን ስንቀበል መሆኑን ተናግሯል። ሥጋውንና ደሙን ካልተቀበልን ግን የዘላለም ሕይወት እንደሌለን ተናግሯል " ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።"(ዮሐ 6:53)

👉 የክርስቶስን ሥጋና ደም በመቀበላችን ሁላችን አንድ አካል፣ አንድ ሐሳብ፣ አንድ ዓላማ ይኖረናል። " አንድ እንጀራ ስለ ሆነ፥ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን፤ ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና።"(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10:17)

ይቆየን። ሼር ያድርጉት።

ሰላም ለኢትዮጵያ 💙

@petroswepawulos
በዚኽች ዕለት ሐምሌ 24 በዕረፍታቸው በዓል ታስበው የሚውሉት አቡነ ዘዮሐንስ የገደሙት ጣና ክብራን ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም እና በሀገራችን ሰሜን ሸዋ ውስጥ የሚገኘው የሰማዕቱ የቅዱስ አባ ኖብ ቤተ ክርስቲያን!
ጻድቁ አቡነ ዘዮሐንስ 8 ሺህ ስግደትን በየቀኑ ይሰግዱ የነበሩ ሲኾን መካነ መቃብራቸውና ይለብሱት የነበረው የብረት ሰንሰለት ልብሳቸው በዚኹ ገዳም ውስጥ ይገኛል፡፡ ነቢዩ ኤልያስና መጥምቁ ዮሐንስ በእኩለ ሌሊት ተገልጠውላቸው አስኬማና ቆብ የሰጧቸው አቡነ ዘዮሐንስ በዚኽች በጣና ደሴት ላይ በጾም በጸሎት ጸንተው ሲኖሩ ትሎች ሰውነታቸውን እንዲመገቡ ያድርጉ ነበር፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ምእመናን የሚያስፈልጋቸውን ይዘውላቸው ሲመጡ ጻድቁ እንደተለመደው ሰውነታቸውን ለትሎች ሲመግቡ አገኟቸው፡፡ ሰዎቹም ትሎቹን ከአባታችን ሰውነት ላይ ሊያራግፉላቸው ሲሉ አቡነ ዘዮሐንስ ግን ‹‹...ተዋቸው እኔን ሊመገቡ ተፈቅዶላቸዋል›› ነው ያሏቸው፡፡ ከበዓለ ዕረፍታቸው በረከት ያድሉን!
+ + +
ሰማዕታት ሐዋርያ ናቸው፡፡ የሰማዕታት ሐዋርያዊ ተልዕኮ ምን እንደሚመስል የአባ ኖብ ገድል በተግባር ያሳየናል፡፡ አባ ኖብ በተአምራታቸውና በትምህርታቸው አሳምነው ለክርስቶስ መንግሥት ያበቋቸው ሰዎች ብዛት ከ190 ሺህ በላይ ናቸው፡፡ ከዚህ በላይ ምን ዓይነት ሐዋርያዊ ተልዕኮ አለ?
2ኛ ሌላው የሰማዕታት ሐዋርያዊ ተልዕኮ ሰማዕታት አስቀድመው ጠንቋዮች የነበሩትን አሳምነው ለሰማዕትነት ያበቋቸው መሆኑ ነው፡፡ የአባ ኖብንና የሦስቱን ኃይለኛ ጠንቋዮች ታሪክ እናያለን፣
3ኛ ሌላው ከአባ ኖብ ገድል የምናገኘው የተለያዩ ገቢረ ተአምራትን በማድረግ እልፍ ከሃዲያንን እንዳሳመኑ፣
4ኛ ሕፃናትም ጭምር ለሰማዕትነት እንደተመረጡ፣
5ኛ ሰማዕትነት የክርስቶስን ፍቅር በማሰብ በራስ ነጻ ፈቃድ እንደሚፈጸም፣
6ኛ ሰማዕታት በመከራቸውና በዕረፍታቸው ጊዜ ጌታችን ቅዱሳን መላእክቱን እየላከ ሰማዕታትን ከቊስላቸው እንደሚፈውሳቸው ነው፡፡ የተወሰኑትን በዝርዝር እንያቸው፡-
ሰማዕታት አስቀድመው ጠንቋዮች የነበሩትን አሳምነው ለሰማዕትነት እንዳበቋቸው፡- ሰማዕቱ ቅዱስ አባ ኖብን መኰንኑ ብዙ ካሰቃያቸው በኋላ ወደ አትሪብ በመርከብ ይዟቸው ሲሔድ በመርከቡ ምሰሶ ላይ ዘቅዝቆ በመስቀል ሥጋቸው እስኪቆራረስ ድረስ በብረት በትር አስገረፋቸው፡፡ መኰንኑም በእሳቸውን እያስገረፈ እርሱ ተቀምጦ ሊበላና ሊጠጣ በፈለገ ጊዜ እመገባለሁ ቢል ምግቡ ድንጋይ ሆነበት፡፡ የአሽከሮቹም ዐይን ታወረ፡፡ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ከስቅላታቸው አውርዶ ቍስላቸውንም ፈውሶ ደማቸውን ጠረገላቸው፡፡ አባ ኖብም ጸልየው የታወሩትን ሰዎች የዐይናቸውን ብርሃን መልሰውላቸው አስተምረው ወደ ሃይማኖትም መለሷቸው፡፡ እነርሱም መስክረው አንገታቸውን ተሰይፈው በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡
ወደ አትሪብም ከደረሱ በኋላ አባ ኖብን በብረት ችንካሮች ቸንክረዋቸው በብረት አልጋ ላይ አድርገው እሳት አነደዱባቸው፣ በመጋዝም ሰነጠቋቸው፣ ሰውነታቸውን ቆራርጠው ጣሉት፡፡ አሁንም የታዘዘ መልአኩ መጥቶ አዳናቸው፡፡ ከዚኽም በኋላ ወደ እስክንድርያ ወሰዷቸውና በዚያም ብዙ አሰቃዩአቸው፡፡ መኰንኑም በአገሪቱ በሥራይ ሥራቸው የታወቁ ኃይለኛ ጠንቋዮችን ጠርቶ አባ ኖብን በሥራያቸው እንዲገድሉለት አዘዛቸው፡፡ ጠንቋዮቹም ‹‹ሥራያችንን በመርዛማ እባቦች ላይ አሳድረን እንገድለዋለን›› በማለት አባ ኖብ በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲታሠሩ በማድረግ በገዳይነታቸው የሚታወቁ መርዛማ እባቦችን አባ ኖብ ወደታሠሩበት ክፍል እንዲገቡ አደረጉ፡፡ አባ ኖብም መርዛማ እባቦቹን በቃለ እግዚአብሔር ስላሰሯቸው ምንም አልነኳቸውም ነበር፡፡ ይልቁንም አንዱ እባብ ሄዶ በመኰንኑ አንገት ላይ ተጠምጥሞ ነድፎ ለሞት አደረሰው፡፡ ሟርተኞቹ እንዳላዳኑት ካወቀ በኋላ አባታችን እባቡን ከመኮንኑ አንገት ላይ እንዲወርድ አድርገው ፈወሱት፡፡ ይህንን ታላቅ ተአምር ያዩት እነዚያ ኃይለኛ ሥራየኞችም ‹‹የአባ ኖብ አምላክ እርሱ እውነተኛ አምላክ ነው፣ እኛም በእርሱ አምነናል›› ብለው መሰከሩ፡፡ መኮንኑም በዚህ ጊዜ በታላቅ ቁጣ ሆኖ ራስ ራሶቻቸውን እያሰፈ በሰማዕትነት ገደላቸው፡፡ የክብር አክሊልንም ተቀዳጁ፡፡
ጌታችን ቅዱሳን መላእክቱን እየላከ ሰማዕታትን ከቊስላቸው እንደሚፈውሳቸው፡- ሰማዕታት ሰማዕትነታቸውን በክብር እስኪፈጽሙ ድረስ ጌታችን ቅዱሳን መላእክቱን እየላከ ሰማዕታትን ከቍስላቸው እንደሚፈውሳቸው ይፈውሳቸዋል፡፡ የሰማዕቱ የአባ ኖብ ገድል አንዱ ማሳያ ነው፡፡
የወላጆቻቸውን ሀብት ለድኆች መጽውተው ወደ ሰማዕትነት አዳባባይ ሔደው በከሃዲው መኰንን ፊት ቆመው የጌታችንን አምላክነት ስለመሰከሩ መኮንኑ ይዞ በብዙ አሠቃቂ መከራዎች በእጅጉ አሠቃያቸው፡፡ በዚኽም ጊዜ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ አባ ኖብን ፈወሳቸው፡፡ ከዚኽም በኋላ መኰንኑ ወደ አትሪብ በመርከብ ይዟቸው ሲሄድ በመርከቡ ምሰሶ ላይ ዘቅዝቆ በመስቀል ሥጋቸው እስኪቆራረስ ድረስ በብረት በትር አስገረፋቸው፡፡ መኰንኑም በእሳቸውን እያስገረፈ እርሱ ተቀምጦ ሊበላና ሊጠጣ በፈለገ ጊዜ እመገባለሁ ቢል ምግቡ ድንጋይ ሆነበት፡፡ የአሽከሮቹም ዐይን ታወረ፡፡ ዳግመኛ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ አባ ኖብን ከስቅላታቸው አውርዶ ቍስላቸውንም ፈውሶ ደማቸውን ጠረገላቸው፡፡ አባ ኖብም ጸልየው የታወሩትን ሰዎች የዐይናቸውን ብርሃን መልሰውላቸው አስተምረው ወደ ሃይማኖት መለሷቸው፡፡ እነርሱም መስክረው ሰማዕት ሆነው ተሰይፈዋል፡፡ ወደ አትሪብም ከደረሱ በኋላ አባ ኖብን ክፉዎች ይዘው በብረት ችንካሮች ቸንክረዋቸው በብረት አልጋ ላይ አድርገው እሳት አነደዱባቸው፣ በመጋዝም ሰነጠቋቸው፣ ሰውነታቸውን ቆራርጠው ጣሉት፡፡ ነገር ግን የዘወትር ጠባቂያቸውና በመከራ ጊዜ የሚያጸናቸው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል አሁንም መጥቶ አዳናቸው፡፡ አባ ኖብ በተአምራታቸውና በትምህርታቸው ካሳመኗቸው ከ190 ሺህ ማኅበርተኞቻቸው ጋር አንገታቸውን ተሰይፈው ሰማዕትነታቸውን በድል ፈጽመው የክብርን አክሊል እስከተቀበሉ ድረስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ሁልጊዜ ከቍስላቸው እየፈወሰ መከራውን ያስታግሣቸው ነበር፡፡
የአቡነ ዘዮሐንስ እና የሰማዕቱ የቅዱስ አባ ኖብ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
@petroswepawulos
††† እንኳን ለቅዱስ መርቆሬዎስ እና ለቅዱሳኑ ቴክላ: አበከረዙን: ዱማድዮስ እና ኄኖክ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕተ ሮሜ †††

††† ቅዱሱ ከቀደምት ሰማዕታት አንዱ ሲሆን በ200 ዓ/ም አካባቢ እንደ ተወለደ ይታመናል:: ወላጆቹ ከጣዖት አምልኮ ወደ ክርስትና የመጡት በተአምር ነው:: ስማቸውም #ታቦትና_ኖኅ ይባላሉ:: ቅዱሱ መጀመሪያ " #ፒሉፓዴር" ይባል ነበር:: ትርጉሙ "የአብ ወዳጅ" እንደ ማለት ነው::

ቀጥሎም " #መርቆሬዎስ" ተብሏል:: ይኸውም " #የኢየሱስ_ክርስቶስ_አገል ጋይ" እንደ ማለት ነው:: በጦርነት ኃይለኛ: በመልኩ ደመ ግቡና ተወዳጅ የነበረው ቅዱስ መርቆሬዎስ ስለ ክርስትናው መከራን የተቀበለው በ20 ዓመቱ ነው:: ዘመኑም በዳኬዎስ ቀዳማዊ ነው::

ስለ ሃይማኖቱም ለ5 ዓመታት መከራን ታግሦ በ25 ዓመቱ (ማለትም በ225 ዓ/ም) ሕዳር 25 ቀን አንገቱን ተከልሏል:: በዓለማቀፍ ደረጃም ቅዱስ መርቆሬዎስ ክብሩ ከሊቀ ሰማዕታት ቀጥሎ የሚገኝ ነው::

በተለይ ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን ቅዳሴ ቤቱ ሲሆን ቤቱ በታነጸበት ሁሉ ተአምራትን ያደርጋል:: ስለዚህ ነገር ታሪክ ብቻ ሳይሆን እኛ ኃጥአንም ምስክሮች ነን:: ጋሹ አምባን ጨምሮ ዛሬም ቅዱሱ ድንቆችን ይሠራል::

††† ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ †††

††† ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኄኖክ ከአባታችን አዳም 7ኛው ደግ ሰው ሲሆን አባቱ #ያሬድ ይባላል:: በእርግጥ ቅዱሱ ሚስት አግብቶ #ማቱሳላና ሌሎች ልጆችን ወልዷል:: አካሔዱ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ነበርና ሞትን አላየም::

#ነቢዩ_ኄኖክ በ1486 ዓ/ዓ የመጀመሪያውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ( #መጽሐፈ_ኄኖክን) ጽፏል:: የዚሕ መጽሐፍ ባለቤት ደግሞ ሃገራችን ናት:: ቅዱሱ ብዙ ሰማያዊ ምሥጢሮችን ተመልክቷል::

የእርሱ ሞትን አለመቅመስ #በአቤል ሞት የፈሩትን #ውሉደ_አዳም በተስፋ አነቃቅቷቸዋል::
"በአቤል አፍርሆሙ:
ወበኄኖክ አንቅሆሙ" እንዳለው ሊቁ:: (ዘፍ. 5:24, ኄኖክ. 4:1)

††† ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት †††

††† እናታችን ቅድስት ቴክላ በኒቆምድያ ተወልዳ ያደገች: ከአሕዛባዊ እምነት ወደ ክርስትና በሐዋርያው #ቅዱስ_ዻውሎስ አማካኝነት የመጣች እናት ናት:: እርሷ ክርስትናን ከልብ ለሚሹ ሴቶች ሁሉ መሪና ትልቅ ት/ቤት ናት:: ወንጌልን ከሐዋርያው ስትማር ምሥጢሩ እየመሰጣት አንዳንዴ ለ3 ቀናት ምግብ አትቀምስም ነበር::

እጅግ ቆንጆ ወጣትና የሃብታሞች ልጅ ብትሆንም ስለ ክርስቶስ ሁሉን ለመናቅና መስቀሉን ለመሸከም አልተቸገረችም:: ከኒቆምድያ እስከ አንጾኪያ ወንጌልን ሰብካለች:: ወላጆቿን ጨምሮ ብዙ ነፍሳትን አድናለች:: በፈንታውም ብዙ መከራን ተቀብላ በዚህ ቀን ዐርፋለች:: ቤተ ክርስትያን " #ሐዋርያዊት" ብላ ታከብራታለች::

††† ቅዱስ አበከረዙን ጻድቅ ወሰማዕት †††

††† ስም አጠራሩ የከበረ ታላቁ #አባ_አበከረዙን ወደ ክርስትና የተጠራው ከሽፍታነት (ስርቆት) ሕይወት ነው:: ከአጋሮቹ ጋር ገዳም ለመዝረፍ ሒደው አንድ ባሕታዊ ከማታ 12:00 እስከ ጧት 12:00 ሲጸልይ አይተው ተጸጽተው ንስሃ ገብተዋል::

አበከረዙን ግን ዓለምን ንቆ በምናኔ ለ7 ዓመታት ተጋድሏል:: ነገር ግን ሰማዕት ለመሆን ከነበረው ፍቅር የተነሳ ከገዳም ወደ ከሃድያን ነገሥታት ሃገር ሔዶ ስመ ክርስቶስን ሰብኩዋል:: በእርሱ ላይ ከደረሱ ስቃዮች ብዛት የተነሳ ከሥጋው: ከአጥንቱና ከደሙ የተረፈለት የለም::

እንዲያውም አንዴ በዓየር ላይ ዘቅዝቀው ሰቅለው ደሙ በአፍና በአፍንጫው እየጐረፈ ለ10 ቀናት ቆይቷል:: በወቅቱ የመኮንኑ ሴት ልጅ እየመጣች ያለ ርሕሪሔ ታሰቃየው ነበርና እርሷን መልአክ ወርዶ ቀሥፎ ገደላት::

እርሱ በተሰቀለ በ22ኛው ቀን: እርሷ በተቀበረች በደግሞ በ12ኛው ቀን ከተሰቀለበት አውርደውት ከሞት አስነስቷታል:: ታላቁ አበከረዙንን በዚህች ቀን ብዙ አሰቃይተው: ወገቡን ሰብረው: አንገቱንም ሰይፈው ገድለውታል::

††† ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ †††

††† ለቤተ ክርስቲያን በንጹሕ ሕይወታቸው ካበሩላት ዐበይት ቅዱሳን አንዱ #ቅዱስ_ዱማድዮስ ነው:: እርሱ ወደ ክርስትና የመጣው ከባዕድ አምልኮ ሲሆን መሪው #መንፈስ_ቅዱስ ነው:: ጣዕመ ሕይወቱን ሲሰሙት ዕዝነ ልቡናን ደስ ያሰኛል::

ገና በወጣትነቱ እንደ #ሐዋርያት ሰብኮ አሕዛብን አሳምኗል:: እንደ #ጻድቃን አካሉ አልቆ አጥንቶቹ እስኪታዩ ተጋድሏል:: እርሱ #ድንግል: #ንጹሕ: #መነኮስ: #ባሕታዊና #ካህን ነው:: ግን ውዳሴ ከንቱን አምርሮ ይጠላል:: በዚህ ምክንያት ካደረበት አይውልም: ከዋለበትም አያድርም::

እርሱ በጸሎቱ የተዘጉ ማሕጸኖችን ከፍቷል:: ዕውራንን አብርቷል:: ለምጻሞችን አንጽቷል:: አንካሶችን አርትቷል:: በፈጣሪው ኃይል ፈሳሽ ወንዝን አቁሟል:: እንደ ገናም እንደ ነበረው መልሶታል::

የቅዱስ ዱማድዮስ መጨረሻው ደግሞ #ሰማዕትነት ነው:: በበዓቱ ውስጥ ሳለ ከደቀ መዝሙሩ ጋር ክፉዎች በድንጋይ ወግረው ገድለውታል:: ድንጋዩም የኮረብታ ያህል ነበር:: ልክ በዓመቱ በዚህች ዕለት ምዕመናን ሥጋውን አፍልሠዋል::

††† ቸር አምላክ ከነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃንና ሰማዕታት ክብርን ያሳትፈን::

††† ሐምሌ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ)
2.ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ (ዕርገቱ)
3.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
4.ቅዱስ አበከረዙን ታላቁ (ጻድቅና ሰማዕት)
5.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ (ጻድቅና ሰማዕት)
6.ቅድስት ኢላርያ ሰማዕት
7.ቅዱሳት ቴክላ ወሙጊ ሰማዕታት
8.ቅዱስ እንዲኒና ሰማዕት
9.አባ ይስሐቅ ሰማዕት
10.አባ ሕጻን ሞዐ ዘደብረ ሊባኖስ
11."25,000" ሰማዕታት (የአትሪብ /ግብፅ/ ሰዎች)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
3.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ

††† "እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::" †††
(ዕብ. 6:10-13)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
@petroswepawulos
🌨🌨🌨🌨🌨🌨🌨🌨🌨🌨🌨🌨
@EotcLibilery
​ሐምሌ 26/11/2012 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

መልእክታት
1ይ ጢሞ. 6፡1-12
1ይዮሐ. 2፡1-11
ግብ. ሐዋ. 5፡26-33
ምስባክ፦
ውስተ ኩሉ ምድር ወጽአ ነገሮሙ
ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ
ወእስከ ፀሐይ ሤመ ጽላሎቶ

ትርጉም ፦
" ምድርም ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም፥ የተራሮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ እግዚአብሔርም ተቈጥቶአልና ተንቀጠቀጡ።"
(መዝሙረ ዳዊት 18:7)

ወንጌል ፦ማቴ 10፥1-15
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ(የእመቤታችን ቅዳሴ)
#ይቀላቀሉ
@petroswepawulos