መዝገበ ቅዱሳን
24.2K subscribers
1.97K photos
9 videos
6 files
26 links
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው! መ/ሳ 1÷7
Bewust mesimer lemanegager
@Yesadkusitota
የሰማነውን እንናገራለን
ያየነውን እንመሰክራለን
Download Telegram
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ሚያዝያ 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=

✞ ሰማዕቱ በብኑዳ ✞

+ቅዱስ በብኑዳ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ በምድረ
ግብፅ ተባሕትዎን መርጦ የሚኖር ገዳማዊ አባት ነው::
በበርሃ
በጾምና በጸሎት ተወስኖ ለእግዚአብሔር የምስጋናን
መስዋዕት እየሠዋ አገልግሏል::

+በዘመነ ሰማዕታት ክርስቲያኖች በግፍ ሲገደሉ ቅዱሱ
ሰው በበርሃ ውስጥ ነበር:: አንድ ቀን የእግዚአብሔር
መልአክ መጥቶ
ሰማዕት እንዲሆን መከረው:: እርሱም ነጭ በነጭ ለብሶ
አምሮበት ወደ ንጉሡ ሔደ:: በፊቱም ቀርቦ በክርስቶስ
ስም ታመነ::
ብዙ ጸዋትወ መከራም ተቀበለ::

+ንጉሡ (መኮንኑ) "አመጣጥህ ወደ ሞት ሳለ ምነው
እንዲህ እንደ ሠርገኛ ማጌጥህ?" ቢለው "እኛ
ክርስቲያኖች ትልቁ
ሠርጋችን ሞታችን ነው:: ልንሔድ ከክርስቶስም ጋር
ልንኖር እንናፍቃለንና" ብሎታል::

+ቅዱስ በብኑዳ ብዙ ተሰቃይቶ: ተአምራትን ሰርቶ በዚሕች
ቀን ተሰይፏል:: የጽድቅን አክሊል ከሰማዕትነት ጋር ደርቦ
አግኝቷል::

❖ቸሩ አምላክ ከሰማዕቱ በረከትን ያካፍለን::

❖ሚያዝያ 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ በብኑዳ (ሰማዕት ወጻድቅ)
2.ቅዱስ ቄርሎስ: ሚስቱና 12 ልጆቹ ሰማዕታት (ከቅዱስ
በብኑዳ ጋር የተገደሉ)

++"+ በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን
ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራን ብትቀበሉ
ብጹዓን ናችሁ::
ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ:: አትናወጡም:: ዳሩ ግን
ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት:: በእናንተ
ስላለ ተስፋ
ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር
የተዘጋጃችሁ ሁኑ:: ነገር ግን በየውሃነትና በፍርሃት
ይሁን:: +"+ (1ዼጥ.3:13-16)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
@yedingelsitota
#ትህትና

በመፅሀፈ መነኮሳት ላይ ታሪካቸው የሚገኝ አንድ አባት የበቁ አባት ነበሩ። ከሰውነታቸው ብርሃን ይወጣ ስለነበር ሰው ፀጋቸውን አወቀ ። እሳቸው ግን በዚ ደስተኛ አልነበሩም ።ስለዚህ ፀጋቸውን ለመደበቅ ሰው እንዳያገኛቸው ቀን ቀን መውጣት አቁመው ማታ ማታ ለመውጣት ወሰኑ ።ከዛ ሰው ሲተኛ እኩለ ለሊት ላይ ሲወጡ ከሳቸው ላይ ከሚወጣው ብርሀን የተነሳ ሰው ነጋ እያለ መውጣት ጀመረ ። እግዚአብሔር እንዲ ነው እኛ ትሁት ስንሆን እሱ ፀጋውን ያበዛልናል ። ዝቅ ስንል ከፍ ያረገናል።

እኔ እንዲ ነኝ እኔ የእከሌ ልጅ ነኝ ፣እከሌ የተባለው ባለስልጣን ወዳጄ ነው ፣ ካዝናዬ ሙሉ ነው ብሬን ይጭነቀው ምናምን እያልን በብር በባለስልጣን እንዲሁም በሌላ ስንመካና ስንታበይ እንወድቃለን። የዲያቢሎስም የውድቀቱ መጀመሪያ ትዕቢት ነበረች ። ነገር ግን መፅሀፍ እንደሚል ማንም የሚመካ ቢኖር በእግዚአብሔር ይመካ ።

አባ ቢሾይ የበቁና ክርስቶስ የሚያናግራቸው አባት ነበሩ። ከእለታት በአንዱ ቀን የገዳሙ መነኮሳት አባ ቢሾይን ክርስቶስ ለኛም ይገለጥልን ዘንድ ንገሩልን ይሏቸዋል ። እሳቸውም እሺ ይላሉ። ማታ ሲፀልዩ ክርስቶስ መጣ ከዛ እሷቸው ጌታ ሆይ ለወንድሞቼ መነኮሳት ተገለጥላቸው አሉት ። ጌታም ቢሾይ ልጄ ነገ በተራራው ላይ በ6 ሰዓት እንደምገለጥላቸው ንገራቸው አላቸውና ተሰወረ ። ቢሾይም ለመነኮሳቱ ነገሯቸው ።

ከቀኑ 6 ሰዓት በሆነ ጊዜም መነኮሳቱ ክርስቶስን ለማየት ወደ ተራራ ሲሮጡ አንድ አቅመ ደካማ ሽማግሌ ተራራው ስር ቁጭ ብለው ፡ልጆቼ እባካቹ ጌታን ላየው እሻለውና እኔንም ውሰዱኝ እያሉ ለመኗቸው ። መነኮሳቱ ግን አንተን ይዘን ታዘገየናለህ ሳናየው ታሳልፈናለህ እኛ ቸኩለናል እያሉ እያለፏቸው ሄዱ ። መጨረሻ ላይ አባ ቢሾይ ሲመጡ እነዛ ሽማግሌ አባ ቢሾይን እባክህ ውሰደኝ አሏቸው ።

አባ ቢሾይም አቅፈዋቸው ጉዞ ጀምሩ ትንሽ ቆይተውም ሽማግሌው ሰውዬ ከበዷቸው ዝቅ ብለው ቢያዩዋቸው ሽማግሌው ወደ ወጣትነት ተቀየሩ እጁና እግሩን ሲያዩት ችንካር አለው ። ደነገጡ ።ክርስቶስ ነው ። ቢሾይ ልጄ እንዳከበርከኝ አከብርሀለው ። ለመነኮሳት ወንድሞችህ ተገልጬ እንደነበርና በንቀታቸው ምክንያት እንዳለፍኳቸው ንገራቸው

አጠገባቹ ያለውን ሳትወዱና ሳታከብሩ እኔን እንወድሃለን እናከብርሀለን ብትሉ ፍቅራቹ ውሸት ነው በላቸው ብሎ ክርስቶሰ ተሰወረ ።ሰውን ስናከብር ፈጣሪ ያከብረናል ሰው የፈጣሪ አምሳል ነውና ። ለዚ ነው መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየው ሰውን መግደል የእግዚአብሔርን ፎቶ መቅደድ ነው የሚሉት ። ፈጣሪን በቀጥታ አናገኘውም በሰው ውስጥ ግን እናገኘዋለንና ሰውን እናክብር ። ለዚ ነው ክርስቶስ ለፍርድ ሲመጣ ከነዚ ከታናናሾች ለአንዱ ያደረጋችሁት ለኔ እንዳደረጋችሁት እቆጥረዋለው ያለው።

@uedingelsitota
[መቅሠፍትን የምታርቂ የኦርና ዐውድማ እመቤታችን ሆይ]
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
❤️ እስራኤል ዘነፍስ ምእመናን በምልጃዋ ከሞተ ነፍስ የሚሠወሩባት ቅድስት ድንግል ማርያም ዳዊትና የእስራኤል ሕዝብ ከቸነፈር (ከተላላፊ በሽታ) መቅሠፍት በዳኑባት መሥዋዕት በተሠዋባት በኦርና ዐውድማ ትመሰላለች (2 ሳሙ 24፥18-25)፡፡

❤️ ይኸውም ክቡር ዳዊት ቢትወደዱ ኢዮአብን ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉትን እስራኤልን ቊጠራቸው አለው፤ ኢዮአብ ግን ሰው ገንዘቡን ቢቈጥሩበት እንደማይወድ ኹሉ እስራኤልም የእግዚአብሔር ገንዘቦች ናቸውና ይኽ ጥሩ አለመኾኑን ቢገልጽለት እንኳ፤ የዳዊት ቃል በመበርታቱ ሕዝበ እስራኤልን ለመቊጠር ኢዮአብና የሰራዊቱ አለቆች በመውጣት በዘጠኝ ወር ከኻያ ቀን ዐሥሩን ነገድ ቈጥረው ቊጥራቸውን አስታወቁት።

❤️ ዳዊት አታድርግ የተባለውን በማድረጉ ምክንያት ጌታም በዳዊት ላይ የሚያመጣበትን ሦስት መከራዎች ለነቢዩ ጋድ ገለጸለት፤ ጋድም ወደ ዳዊት መጥቶ “የሦስት ዓመት ራብ በአገርኽ ላይ ያምጣብኽን? ወይስ ጠላቶችኽን እያሳደዱኽ ሦስት ወር ከእነርሱ ትሸሽን? ወይስ የሦስት ቀን ቸነፈር (ተላላፊ በሽታ) በአገርኽ ላይ ይኹን? አንዱን ምረጥ ብሎኻል” አለው፤ ዳዊትም “ይኄይሰኒ እደቅ ውስተ እደ እግዚአብሔር እስመ ብዙኅ ውእቱ ምሕረቱ ፈድፋደ እምእደቅ ውስተ እደ ዕጓለ እመሕያው” (የእግዚአብሔር ይቅርታው ብዙ ነውና፤ በሰው እጅ ከምወድቅ በእግዚአብሔር እጅ ብወድቅ ይሻለኛል) በማለት ቸነፈሩን (ተላላፊ በሽታን) መረጠ፡፡

❤️ የስንዴም መከር ወራት በሆነ ጊዜ ቸነፈሩ (ተላላፊ በሽታ) በሕዝቡ መካከል ጀመረ፤ ከሕዝቡም ሰባ ሺሕ ሰው ሞተ። የእግዚአብሔርም መልአክ ኢየሩሳሌምን ያጠፋት ዘንድ እጁን በዘረጋ ጊዜ ጌታም ሕዝቡንም የሚያጠፋውን መልአክ፦ እንግዲህ በቃህ እጅህን መልስ አለው።

❤️ ንጉሥ ዳዊትም “እነሆ እኔ በድያለኍ፤ ጠማማም ሥራ እኔ አድርጌአለኍ፤ እነዚኽ በጎች ግን ምን ዐደረጉ? እጅኽ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ እንድትኾን እለምንኻለኊ” ብሎ ተናገረ። ነቢዩ ጋድም በዚኽች ቀን ወደ ዳዊት መጥቶ በኢያቡሳዊዉ በኦርና ዐውድማ ለጌታ መሠዊያ እንዲሠራ ነገረው።

❤️ ዳዊትም እንደታዘዘው ወደ ኦርና ኼደ፤ ኦርናም በዳዊት ፊት ሰግዶ ንጉሡ ለምን ወደእሱ እንደመጣ ጠየቀ።ዳዊትም “መቅሠፍቱ ከሕዝቡ ላይ ይከለከል ዘንድ ዐውድማውን ከአንተ ገዝቼ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ልሠራ ነው” ብሎ፤ ዐውድማውንና ለመሥዋዕት የሚኾኑ በሬዎችን በሃምሳ ሰቅል ብር ገዝቶ በዐውድማዋ ላይ ሕዝቡን ከንጉሡ ጋር ንጉሡን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስማማ መሥዋዕት በዖርና አደባባይ አቀረበ፤ ጌታም የለመነውን ልመና ሰምቶ መቅሠፍቱን ከእስራኤል ከልክሎ ምድርን ይቅር ብሏታል፡፡

❤️ ይኽቺ ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር ያስማማችና መቅሠፍትን ያስቆመች የኦርና ዐውድማ ምሳሌነቷ የቅድስት ድንግል ማርያም ነው፤ ይኸውም ዳዊት በኦርና ዐውድማ ላይ የሠዋውን መሥዋዕት እግዚአብሔር ወዶ እንደተቀበለለት ዛሬም በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አምነን የምናቀርበውን ጸሎትና ልመና ጌታ ወድዶ ይቀበልልናልና (ኢሳ ፩፥፱፤ ዮሐ ፪፥፩-፲፩)።

❤️ ዳግመኛም በኦርና ዐውድማ የተሠዋው መሥዋዕት ዳዊትን ከመቅሠፍት እንደጠበቀ ኹሉ፤ በእመቤታችንም ጸሎትና ቃል ኪዳን ወዳጆቿ ከመቅሠፍት ይጠበቃሉና። በተጨማሪም በዐውደ ኦርና በተሠዋው መሥዋዕት እስራኤል ዘሥጋ ተጠብቀው እንደኖሩ ሰአሊ ለነ ቅድስት የምንል እስራኤል ዘነፍስ የተባልን ምእመናንም በየጊዜው በጸሎቷ ከመቅሠፍት የምንሰወር ኾነናልና የእመቤታችን ጣዕመ ውዳሴዋ እጅጉን የበዛለት ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በእንዚራ ስብሐት መጽሐፉ፡-

✍️ ‹‹አንቲ ውእቱ ገራህተ ኦርና ዘብኪ ሦዓ ዳዊት መሥዋዕተ መድኀኒት ለፈጣሪሁ
መቅሠፍተ ብድብድ ጽኑዕ ኦመ ኮነ ለሕዘቢሁ››

(ብሩቱ የቸነፈር መቅሠፍት በሕዝቡ ላይ በመጣ በበዛ ጊዜ፤ ዳዊት የመድኀኒት መሥዋዕት የሠዋብሽ የኦርና አዝመራ ምድር (እርሻ) አንቺ ነሽ) በማለት አመስግኗታል፡፡

❤️ ዳዊት በበደለ ጊዜ ከአምላኩ የታረቀባት የዖርና መሠዊያ የተባልሽ ቅድስት ድንግል ሆይ የአደራ ልጆችሽ የሆንን እኛም ልጅሽን አምላካችን ክርስቶስን በድለናልና የቃል ኪዳን እጆችሽ በተወደደው ልጅሽ ፊት መዐቱን በምሕረት ቁጣውን በትዕግሥት እንዲመልስልን የተዘረጉ ይሁኑልን።

💚 @yedingelsitota
† እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ብሩታዎስ ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

† ቅዱስ ብሩታዎስ †

† ሐዋርያው ቅዱስ ብሩታዎስ በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያው የውዳሴ ማርያም ደራሲ ነው::
ይህስ እንደምን ነው ቢሉ:-
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ ሙቶ ከተነሳ ከ8 ዓመታት በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ያምናል:: ባመነ በ6 ዓመቱ (ማለትም ከክርስቶስ ዕርገት 14 ዓመታት በኋላ) እየሰበከ ግሪክ አቴና /ATHENS/ ደርሶ ብዙ ፈላስፎችን ወደ ክርስትና ሲያመጣ አንዱ ይህ ቅዱስ ብሩታዎስ ነበር::

ቅዱስ ብሩታዎስ በክርስቶስ አምኖ: ተጠምቆ: ሐዋርያትን ተከትሏቸው: እነሱም ቅስና ሹመውታል:: ጵጵስና እንሹምህ ቢሉት በፊታቸው ተንበርክኮ አልቅሷል:: አይገባኝም ማለቱ ነበር::

ታዲያ ቅዱስ ብሩታዎስ ሐዋርያት ስለ ድንግል እመቤታችን ሲጨዋወቱ እየሰማ "መቼ አይቻት" እያለ በፍቅሯ ይቃጠል ነበር:: አንዴ ግን ወሰነ:: "እመቤቴን ሳላያት እንቅልፍ አላይም" ብሎ በሽማግሌ እግሮቹ ከግሪክ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ::

የሚገርመው እርሱ እሥራኤል (ጽርሐ ጽዮን) የደረሰው በ49 ዓ/ም ጥር 21 ቀን እመቤታችን ልታርፍ ሰዓታት ሲቀራት ነበር:: ቅዱሱ ሽማግሌ እመቤታችንን በአካለ ሥጋ ስላያት በፊቷ እንደ እንቦሳ ዘለለ:: እየሰገደም አመሰገናት:: እመ ብርሃንም በንጹሐት እጆቿ ባረከችውና ዐረፈች::

ይሕን ጊዜ ምሥጢር ተገልጦለት ዜማና ቅኔ ያለውን የመጀመሪያውን ውዳሴ ማርያም ዕለቱኑ ደርሶ ለሐዋርያት ሰጣቸው:: እነርሱም ከምስጋናው ጣዕም የተነሳ ተደነቁ:: ከሐዘናቸውም ተጽናኑ::

ይሕ ድርሰት በዘመነ ሰማዕታት በመጥፋቱ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ አምልቶና አጉልቶ ደርሶታል::

ቅዱስ ብሩታዎስ ግን ብዙ ሃገራትን በሐዋርያነት አዳርሶ በመልካም ሽምግልና አርፏል::

††† ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ብሩታዎስ ላይ ያሳደረውን የድንግል እናቱን ፍቅር በእኛም ላይ ያሳድርብን::

††† ሚያዝያ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ብሩታዎስ ሐዋርያዊ
2.አባ ዕንባቆም ጻድቅ ሰባኬ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ (በትውልድ የመናዊ በጸጋና አገልግሎት ግን ኢትዮጵያዊ አባት ናቸው:: ደራሲ : ሰማዕት : ባሕታዊና ሊቀ ምኔትም ነበሩ::)
3.ቅዱስ አካክሪስ
4.ቅዱስ ይወራስ

††† ወርኀዊ በዓላት
1፡ እግዝእትነ ማርያም
2፡ አበው ጎርጎርዮሳት
3፡ አባ ምዕመነ ድንግል
4፡ አባ ዓምደ ሥላሴ
5፡ አባ አሮን ሶሪያዊ
6፡ አባ መርትያኖስ
7፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል

††† "ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሠጠዋል:: ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና:: ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል . . . ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጐም ይሰጠዋል:: ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድለት እያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል::" †††
(፩ቆሮ. ፲፪፥፯-፲፩)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
#yedingelsitota
"ማንስ ነው ከቅዱሳን ሁሉ በላይ እንደሆነች ያላስተዋለ? እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠና የሚነኩት ሁሉ ከበሽታው ከተፈወሰ፣ ጥላቸው ያረፈበት ተአምር ከተፈፀመለት፣ ጴጥሮስ በጥላው ካዳነ (የሐዋ 5÷15)፣ የጳውሎስ የልብሱ ጨርቅ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ (የሐዋ 19÷11)፤ ለእናቱማ ምን አይነት ስልጣንና ኃይል ተሰጥቷት ይሆን? ለቅዱሳኑ ይኽን ያኽል ድንቅ እንዲያደርጉ ባለሟልነትን ከሰጣቸው ወልዳ ላሳደገችው እናቱማ ምን ያኽል ይሰጣት ይሆን? በምን አይነት ስጦታ አስጊጧት ይሆን? ጴጥሮስ "ክርስቶስ አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ " ስላለው ብፁዕ ከተባለና የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ ከተሰጠው (ማቴ16÷16-19)፤ እርሷ ከሁሉም ይልቅ እንዴት የተባረከች (ብፅዕት) አትሆን? (ሉቃ1÷45)፤ ጳውሎስ ታላቅ ክብር ያለውን የክርስቶስን ስም በመሸለሙ "ምርጥ እቃ " ከተባለ (የሐዋ9÷15)፤ የአምላክ እናትማ የምእመናን ምግብ የኾነ መናውን ሳይሆን የሕይወት ሰማያዊ እንጀራን ያስገኘች እርሷ ምን አይነት ልዩ እቃው ትሆን?
@kegdlat. @kegdlat. @kegdlat
ነገር ግን ስለ እርሷ ብዙ እናገራለሁ ብዬ ስለ ክብሯ ጥቂት በመናገር እራሴን በኅፍረት ውስጥ እንዳልጨምር እፈራለሁ ስለዚህ ካሁን ወዲህ የንግግሬን መልህቅ ስቤ በዝምታ ወደቤ ላይ ማረፍን መርጫለሁ"
@kegdlat. @kegdlat. @kegdlat
(ቅዱስ ባስልዮስ)
@yedingelsitota
ምክረ አበው!

"በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው"
ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ

"ሰዎች አንድ ሰው ተነሥቶ ሌላውን ሲገድል ወንጀለኛ ነህ ይሉታል። አንድ ላይ ተሰባስበው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ግን ውጊያ ይሉትና መግደላቸውን ጀግንነት ይሉታል" ቅዱስ ቆጵሮሳዊ

"የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው"
ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ

"መካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ታላቅ ትዕቢት የለም" ቅዱስ ባስልዮስ

"ክርስቶስ ጴጥሮስን "ሰይፍህን ወደ ሰገባው አስገባ" ሲለው ትጥቅ ያስፈታው ጴጥሮስን ብቻ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ነበር" ሊቁ ጠርጡለስ
ሥርዓተ ማኅሌት ዘሚያዝያ ጊዮርጊስ "ሚያዝያ ፳፫"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ። ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ። ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ። ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ። ወተክለሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዓጽሙ።

ዚቅ
በደመ ሰማዕት መዋዕያን : ወበገድለ ጻድቃን ቡሩካን : ተሣሃለነ እግዚኦ።

ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ። ለወልድኪ አምሳለ ደሙ። መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ። ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ። እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ጻድቃን ይበውኡ ውስቴታ : የዋሃን የዓውዱ መሠረታ : ሰማዕት ይቀውሙ ዓውዳ : በዕለተ #ጊዮርጊስ ስብሐት የዓውዳ ለቅድስት ቤተክርስቲያን።

ነግሥ
ሰላም ለቆምከ ዘአዳም ቆሙ። ወለመልክዕከ በይነ ሰላሙ። ቅዱስ ጊዮርጊስ መክብበ ሰማዕታት ኲሎሙ። ሶበ መተሩ ክሣደከ ምድረ አጥለለት ደሙ። ወጊዜ ሞትከ ብርሃናት ፀልሙ።

ዚቅ
ሶበ መተርዎ ሶበ መተርዎ : ሶበ መተርዎ #ለጊዮርጊስ : ፀሃይ ጸልመ : ወወርኅ ደመ ኮነ : ዬ ዬ ዬ : አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት።

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘሰሌዳ ሞገስ መጽሐፉ። ዘያሜኒ ኲሎ ወዘያስተሴፉ። ጥዑመ ዜና #ጊዮርጊስ ለሀሊበ ዕጎልት ሱታፉ። ሰላምከ ወረድኤትከ በላዕሌየ ያዕርፉ። አኮ ለምዕር ዳዕሙ ለዝሉፉ።

ዚቅ
ከመ ሀሊብ ዘዕጎልት : ወከመ ወይን ዘገነት : ይጥዕም ስምከ #ጊዮርጊስ ሰማዕት።

ወረብ
ከመ ሀሊብ ዘዕጎልት ወከመ ወይን ዘገነት/፪/
ስመከ ይጥዕም "#ጊዮርጊስ"/፪/ ሰማዕት/፪/

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለክሣድከ ዘተመሰለ ምንሐረ። በአንቅዖ ሀሊብ ወማይ አመ በመጥባሕት ተመትረ። #ጊዮርጊስ ዘፆርከ ሥቃየ ኲነኔ መጽእረ። በለኒ በቃለ ብሥራት ከመ ነሃሉ ኅቡረ። ጥቃ ቤተ ነፍስየ ለከ ሐነጽኩ ማኅደረ።

ዚቅ
ቅዱስ #ጊዮርጊስ ሶበ ተከለለ : ደም ወሀሊብ እምነ ክሣዱ ፈልፈለ።

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለሕሊናከ ዘመከረ በልባዌ። በሞቱ ወበተንሥኦቱ ለተሳትፎ መርዓዌ። ዓቃቤ ሥራይ #ጊዮርጊስ መፈውሰ ደዌ። ለወለት ከመ ቤዘውካ እምአፈ ደራጎን አርዌ። ተረፈ ሕይወትየ ቤዙ እምኲሉ ምንሳዌ።

ዚቅ
ጸርሐ #ጊዮርጊስ በዓቢይ ቃል : ወይቤ እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል።
ዓዲ (ወይም)
ሰኪቦ ለወልድ ትንሣኤ ሞቶ : #ጊዮርጊስ ወረሰ ሰማያዊተ መንግሥቶ።
ዓዲ (ወይም)
ቀዊሞ ገሃደ ውስተ ዓውደ ስምዕ : #ጊዮርጊስ ሰበከ ትንሣኤ ሞቱ ለበግዕ።

ወረብ
ወይቤ #ጊዮርጊስ በዓቢይ ቃል ጸርሐ በዓቢይ ቃል ወይቤ/፪/
እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል/፪/
ዓዲ (ወይም)
ጸርሐ ጊዮርጊስ በዓቢይ ቃል ወይቤ በዓቢይ ቃል/፪/
እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል/፪/

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለፀዓተ ነፍስከ ጽዋዓ ደመ ስምዕ ሰሪቦ። እማኅፈደ ሥጋ በገድል መከራ ስቃይ ድኅረ ረከቦ። #ጊዮርጊስ ስመከ ሶበ እጼውእ በአስተርክቦ። ረድኤትከ ኀበ ሀሎኩ በአርአያ ብእሲ ቀሪቦ። ለትካዘ ልብየ ዘልፈ ያሰስል ዕፅቦ።

ዚቅ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት : አጽነነ ርዕሶ #ጊዮርጊስ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ።

ወረብ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት "ጊዜ"/፪/ ፮ቱ ሰዓት/፪/
አጽነነ ርዕሶ #ጊዮርጊስ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ/፪/

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለበድነ ሥጋከ እምርጢነ ገለአድ ዘተኃርየ። በላዕለ ድውያን ፈወሰ እስመ ፈድፋደ አርአየ። #ጊዮርጊስ ለከ ትብለከ ነፍስየ። በበድነ ሥጋከ ተማኅጸንኩ ኢታስተኀፍር ተስፋየ። ስዕለተ ከናፍርየ ስማዕ ወፈጽም ጻህቅየ።

ዚቅ
ፈወሰ ዱያነ ወከሠተ አዕይንት ዕውራን : ወኲሎ ፈጺሞ አዕረፈ #ጊዮርጊስ ሰማዕት።

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለግንዘተ ሥጋከ በዕደ አግብርቲከ ፪ኤ። ድኅረ ሰለጥከ መዊተ እንዘ ብከ ተስፋ ትንሣኤ። #ጊዮርጊስ ዘፆርከ ሥቃየ ዓመታት ሱባኤ። ስመከ በተአምኖ ሶበ አወትር ጽዋዔ። አስራበ ረድኤትከ ያጥልል ዘዚአየ ጒርኤ።

ዚቅ
፯ ዓመተ ዘኮነንዎ : ለቅዱስ #ጊዮርጊስ ኢመሰሎ ከመ አሐቲ ዕለት : ብእሲ ጻድቅ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር።

መልክዐ ጊዮርጊስ
ሰላም ለመቃብሪከ ምክሐ አድያሚሃ ወዓጸዳ። ለምድረ ሙላድከ ልዳ። #ጊዮርጊስ ዘልፈ ሀብተ በረከት ዘእፈቅዳ። ከመ ትጸጊ ሕንባበ ረዳ ለኢያሪኮ በዓውዳ። በዲበ ድማኅየ ትጽጊ እምሰማይ ወሪዳ።

ዚቅ
ወረደ ብርሃን ኀበ መቃብሩ ለብእሴ እግዚአብሔር : ወኮነ መቃብሩ ዘየሐዩ ዱያነ : ጸሎቱ #ለጊዮርጊስ ወበረከቱ የሃሉ ምስሌነ።

ምልጣን
ዮም ተጽሕፈ እምነገሥት ከላሌሁ በመጥባሕት #ለጊዮርጊስ ሰማዕት : ጸለየ ጊዮርጊስ ወአውዓዮሙ በነበልባል : አማን ኃያል ገባሬ ኃይል።

አመላለስ
አማን በአማን/፬/
ኃያል ገባሬ ኃይል/፬/

እስመ ለዓለም
ወሰበረ ኆኃተ ብርት ሞዖ ለሞት : ተንሥእ ወልድ በሣልስት ዕለት : ወአግዓዘ ነፍሰ ጻድቃን እምጽልመት ወጽላሎተ ሞት : ካዕበ ይቤሎሙ ለአርዳኢሁ : ገሊላ እቀድመክሙ።

ዓዲ(ወይም)
እስመ ለዓለም
ንግበር በዓለ በትፍሥሕት : በአስተሐምሞ ቅድስተ ፋሲካ : ተዝካረ ትንሣኤሁ #ለጊዮርጊስ : ነገሮ ኅቡዓተ ኲሎ ሥርዓተ ምሥጢር በደኃሪ ይትገበር ዘሀሎ በንዝኃተ ደሙ ለክርስቶስ : ለመፃጉዕ ዘአሕየዎ በቃሉ : ወለዕውርኒ ዘከሠተ ዓይኖ : ተንሥአ እሙታን : ለአልዓዛር ተንሥእ ዘይቤሎ ወለያዕቆብ ዘአዕተዎ ብሔሮ : ተንሥአ እሙታን : ምዕረ ሦዓ ርእሶ ወተዓውቀ በመንፈሱ : በፈቃዱ ወልድ አቅተለ ርእሶ : ተንሥአ እሙታን : ሲኦለ ወሪዶ ሰበከ ግዕዛነ : በመስቀሉ ወልድ ገብረ መድኃኒተ : ተንሥአ እሙታን: ጸርሐት ሲኦለ ወትቤ ሰማያዊ ዝስኩ ዘለኪፎቶ ኢይክል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @petroswepawulos
እንኩዋን ለጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

አቡነ ተክለ ሃይማኖት

=>ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በዚህች ቀን ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል::

+ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር:: የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል::
+ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በሁዋላ ነው::

+ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር:: ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-
*በቤተ መቅደስ ብስራቱን
*በቤተ ልሔም ልደቱን
*በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
*በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
*በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::

+የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው::

+በዚያም:-
*የብርሃን ዐይን ተቀብለው
*6 ክንፍ አብቅለው
*የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
*ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
*ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
*ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
*"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::

=>የተክለ ሃይማኖት አምላክ ከጻድቁ ትሩፋት: ጸጋና በረከት ይክፈለን::

† አባ ይስሀቅ †

በዚች ቀን ከግብፅ ደቡብ ከእብክ አውራጃ ከሆሪን ከተማ የከበረ አባት ይስሀቅ አረፈ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብርሀም የእናቱም ስም ሶስና ነው ታናሽም ሆኖ ሳለ እናቱ ሙታ ብቻውን ያለእናት አባቱ እያሳደገው ኖረ።

ጥቂት በአደገም ጊዜ የአባቱን በጎች የሚጠብቅ ሆነ አባቱም ሌላ ሚስት አገባ በዚያ ወራትም ታላቅ ረኃብ ሆነ የአባቱም ሚስት ትጠላው ነበረ ከጥቂትም በቀር እንጀራ አትሰጠውም ያንኑም ሁልጊዜ ለእረኞች ሰጥቶ እርሱ ግን እስከምሽት ይፈፀማል።

ምሳውን ለእረኞች እንደሚሰጥና ሁልጊዜ እስከምሽት እንደሚፆም አባቱ ሰምቶ እውነት እንደሆነ ሊያይ ወደርሱ ሄደ። ቅድሱም ህፃን የአባቱን መምጣት አውቆ በልብሱ ሶስት ጭቃ አድበልብሎ አሰረ እንደ ታሰረ በሚያየው ጊዜ ለአባቱ አምባሻ እንዲመስለው ብሎ።

አባቱም በመጣ ጊዜ የልጁን ልብስ ፈትቶ አየ አንባሻም ሆነው አገኛቸው።የነገረውንም ሰው ምግቡን ለእረኞች ከሰጠ በዛሬይቱ ቀን ይህ አምባሻ ከወዴት ተገኘለት ብሎ ጠየቀው እርሱም በእውነት ሰጥቷል አለ ሌሎችም ብዙዎች መጥተው በዚህ ነገር ምስክሮች ሆኑ አባቱም አደነቀ እግዚአብሄርንም አመሰገነ።

ይህም በአደገ ጊዜ አባ ኤልያስ ወደሚባል ሰው ሄዶ መንኩሶ በዚያ እየተጋደለ ብዙ አመታት ኖረ። አባ ኤልያስም በአረፈ ጊዜ በርኑግ ወደሚባል ገዳም ሄደ ስሙ ዘካርያስ ከሚባል አረጋዊ ዘንድ በታላቅ ገድል ተጠምዶ ኖረ።

አባቱም ያገኘው ዘንድ በሀገሮች ሁሉ ይዞር ነበረ በዚህ በበርኑግ ገዳምም በአገኘው ጊዜ ከእርሱ ጋራ እንዲመለስ አባቱ ለመነው አይሆንም አለ አባ ዘካርያስም ከአባቱ ጋራ ይሄድ ዘንድ እስከ ሚአርፍም ከእርሱ ዘንድ እንዲኖር አዘዘው ይህ ቅዱስም ከአባቱ ጋራ ሄዶ እስከሚአርፍ ድረስ ከእርሱ ዘንድ ኖረ።

አባቱም በአረፈ ጊዜ አባቱ የተወውን ገንዘብ ሁሉንም ለድኆችና ለምስኪኖች ሰጠ ከከተማውም ጥቂት ራቅ ብሎ ለራሱ ታናሽ ማደሪያ ሰራ በሰላም እሰከ ሚአርፍባት ቀን ድረስ ያለ ማቋረጥ በበጎ ገድል በፆም በፀሎት በስግደት ኖረ በአረፈ ጊዜም በመልካም ቦታ አኖሩት ከዚያም ተሰወረ።

ከብዙ ዘመናትም በኃላ እግዚአብሄር ሊገልጠው ወዶ በመቃብሩ ላይ መብራት ሲበራ እህል ለሚአጭዱ ሰዎች ሶስት ቀን ያህል ታየ ሊያዩትም ወደቦታው ሲደርሱ ያ መብራት ከእርሳቸው ይሰወራል በሁሉ ዘንድ እስቲሰማም እንዲህ ሆኖ ኖረ።

ከዚህም በኃላ በመቃብሩ ላይ እያበራ ያ መብራት ደግሞ ታያቸው ስጋውም በዚያ እንዳለ ሁለተኛ በህልም ነገራቸው ምእመናንም አክብረው በግመል ጭነው ወደ ሀገሩ መካከል ወደ ሆሪን ወሰዱት ነስሪን ከሚባል ሀገር መካከል ሲደርሱ ግመሉ በዚያ ተንበረከከ እንዲነሳም መቱት መነሳትንም እቢ አለ መኖሪያው በዚያ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሄር ፈቃድ እንደሆነ አወቁ።

በዚያም በስሙ ቤተ ክርስቲያን ሰርተው ስጋውን በውስጥዋ አኖሩ ሰርተው ስጋውን በውስጥዋ አኖሩ ከእርሱም ብዙ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ።

† ቅዱስ እለእስክንድሮስ †

በዚች ቀን የከበረ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳትም አስራ ዘጠነኛ የሆነ እለእስክንድሮስ አረፈ። ስለርሱም ሀዋርያዊ አባት አትናቴዎስ እንዲህ አለ አባቴ እለእስክንድሮስ ተቀምጦ ወንጌልን አያነብም ቁሞ ያነባል እንጂ ከርሱ ጋራም ብርሀን አለ።

ሁለተኛው ስለርሱ ሲናገር ወደርሱ እመምኔቶች መጥተው በእኛ ዘንድ ሰባት ሰባት ቀን የሚሶሙ ደናግል አሉ ።በእጆቻቸውም ምንም ምን ስራ አይሰሩም ብለው ነገሩት።

እርሱም እህቶቼ ሆይ እኔ ሁለት ቀን እንኳን ከቶ አልፆምኩም ፀሀይ እስኪገባው ቆይቼ አልበላሁም በልክ እበላለሁ በልክም እፆማለሁ በልክ በመጠንም እሰራለሁ በልክ ይበሉ ዘንድ በልክም ይፆሙ ዘንድ በልክም ስራ ይሰሩ ዘንድ ነግሯቸው በበጎ ስራ ሁሉ ይሰለፉ አለ።

የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ደጎች ምእመናን ናቸው እርሱም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ሆኖ ከታናሽነቱ ጀምሮ በውስጥዋ አደገ።አባ መክሲሞስ አናጒን ስጢስነት አባ ቴዎናስ ዲቁና ተፍፃሜተ ሰማእት ጴጥሮስም ቅስና ሹመውታልና እርሱም ከታናሽነቱ ጀምሮ ንፅህ ድንግል ነው።

አባ ጴጥሮስ በሰማእትነት የሚሞትበት ጊዜ ሲቀርብ በግዞት ቤት ሳለ ይህ እለእስክንድሮስና አኪላስ ከውግዘቱ ይፈታው ዘንድ ስለ አርዮስ ወደርሱ ገብተው ለመኑት ስለርሱ አባ ጴጥሮስን ይማልዱለት ዘንድ ሁለቱን ለምኖአቸዋልና።

አባት ጴጥሮስ ግን በውግዘት ላይ ውግዘትን ጨመረበት እንዲህም ብሎ ነገራቸው የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀደደ ልብስ ለብሶ ተገለፀልኝ ልብሴን አርዮስ ቀደዳት አለኝ። ይህም የባህርይ አንድነቴን ለያት ማለት ነው ውግዘቱንም እንድጨምርበት እርሱ አዘዘኝ።

ደግሞ እንዲህ ገለጠላቸው አኪላስ ሊቀ ጵጵስና እንዲሾም ከርሱ በኃላም እለእስክንድሮስ እንደሚሾም አርዮስን እንዳይቀበሉት በምንም ስራው እንዳይተባበሩት አዘዛቸው።

አባ ጴጥሮስም ምስክርነቱን በፈፀመ ጊዜ አኪላስ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ የአባት ጴጥሮስንም ትእዛዝ ተላልፎ አርዮስን ከውግዘቱ ፈታው። ቅስናም ሾመው ስለዚህም አኪላስ በመንበረ ሲመቱ ያለ ስድስት ወር አልኖረም በድንገት ሞተ።

ከዚህ በኃላ ይህ አባት እለእስክንድሮስ ሊቀ ጵጵስና ተሹሞ በመንበረ ሲመቱ ላይ ተቀመጠ አርዮስንም ከወገኖቹ ጋራ አውግዞ አሳደደው። የሀገር ታላላቆችም ከህዝቡ መጡ ከውግዘቱ እንዲፈታውም ለመኑት። በውግዘት ላይ ውግዘትን እንዲጨምር እንጂ እንዳይፈታው አባት ጴጥሮስ እንደአዘዘው ነገራቸው።

ከዚህ በኃላ አርዮስ ወደ ንጉስ ቈስጠንጢኖስ ሂዶ በግፍ አወገዘኝ ብሎ እለእስክንድሮስን ከሰሰው። ስለዚህም ንጉሱ ሶስት መቶ አስራ ስምንት የከበሩ አባቶችን በኒቅያ ከተማ ሰበሰበ።
ይህም አባት እለእስክንድሮስ ተመርጦ ለጉባኤው ሊቀ መንበር ሆነ አትናቴዎስ ፀሀፊ ነበር ።አርዮስንም ተከራክረው ክህደቱን ግልፅ አደረጉ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከአባቱ ከአብ ጋራ ከህይወቱ መንፈስ ቅዱስም ጋራ በመለኮቱ ትክክል እንደሆነ አስረዱት።

ከክህደቱ ባልተመለሰ ጊዜ አውግዘው ለይተው ከቤተ ክርስቲያን አሳደዱት። በአንድ ቃልም ፀሎተ ሀይማኖትን ከአባቶች ጋራ ሰሩልን ደግሞ በእርሳቸው ቤተ ክርስቲያን ለዘላለም የምትመራባቸው ሀያ ቀኖናን ሰርተው ወሰኑ።

ከዚህ በኃላም ይህ አባት እለእስክንድሮስ ወደ መንበረ ሲመቱ ከደል ጋራ ተመለሰ። በበጎ አጠባበቅም መንጋውን ጠበቀ በወንጌላዊ ማርቆስ መንበርም አስራ ሰባት አመት ኖሮ በሰላም አረፈ።

† አባ ሚካኤል ዘእስክንድርያ †

በዚችም ቀን የከበረ አባት አባ ሚካኤል የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አረፈ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሀምሳ ሶስተኛ ነው። ይህም ቅዱስ ፃድቅ መንኲሶ በአስቄጥስ በቅዱስ ዮሀንስ ገዳም አበ ምኔት ሆኖ ተሾመ ከዚያም ያለ ፈቃዱ ወስደው በግድ ሊቀ ጵጵስና በእስክንድርያ አገር ላይ ኀዳር ሀያ አራት ቀን ሾሙት።

በሊቀ ጵጵስናውም ስራ ተጠምዶ የሚጋደል ሆነ እንደ ሀዋርያትም አጠባበቅ መንጋውን ጠበቀ። ታላቁ ፆምም በደረሰ ጊዜ ወደ አስቄጥስ በዚያ ሊፆም ወጣ ከመሾሙ በፊት በዚያ ገዳም ውስጥ በብህትውና ሆኖ መጠመዱንና የቀድሞ መጋደሉን አሰበ።

ወደ ጌታችንም እንዲህ ብሎ ለመነ አቤቱ እኔ በብቸኛነት መኖርን እንደምሻ አንተ ታውቃለህ ለዚች ለተሾምኩባትም ሹመት ችሎታ የለኝምና የምትገባኝም አይደለችምና በይቅርታህም ብዛት ነፍሴን ወስደህ ከዚህ ድካም ታሳርፈኝ ዘንድ እለምንሀለሁ ጌታም ልመናውን ተቀበለ ከፋሲካ በአል በኃላም በፍቅር አንድነት አረፈ።የሹመቱም ዘመን ሁለት አመት ከአምስት ወር ነው።

=>ሚያዝያ 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ (አርዮስን ያወገዘ)
3.አባ ይስሐቅ ጻድቅ
4.አባ ማርቆስ ሐዲስ
5.አባ ሚካኤል ዘኢየሩሳሌም
6.አባ ሚካኤል ዘእስክንድርያ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ እንጦንዮስ (አበ መነኮሳት)
5.አባ ዻውሊ የዋህ

=>+"+ ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረዥምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት:: የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር:: ሱራፌል ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር:: ለእያንዳንዱ ስድስት ክንፍ ነበረው:: በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር:: በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር:: በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር:: አንዱም ለአንዱ 'ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች' እያለ ይጮህ ነበር:: +"+ (ኢሳ. 6:1-4)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
@yedingelsitota
እንኩዋን ለታላቁ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ የሰማዕትነት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ዐቢይ ወክቡር: ጊዮርጊስ: ሰርዌ አዕላፍ: ወመክብበ ሰማዕታት

=>መጽሐፈ ገድሉ እንደሚለው የሰማዕታት አለቃቸው: አንድም ሞገሳቸው ታላቅና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ7 ዓመታት ስቃይ በሁዋላ በዚህ ቀን ተሰይፏል:: ይሕስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ:-

+ቅዱሱ የተወለደው ከአባቱ ዘረንቶስ (አንስጣስዮስ) እና ከእናቱ ቴዎብስታ የድሮው ፋርስ ግዛት ፍልስጥኤም (ልዳ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቹ ክርስትናን ጠንቅቀው አስተምረውት አባቱ ይሞታል::

+ቅዱስ ጊዮርጊስ 20 ዓመት ሲሞላው የአባቱን ስልጣን እጅ ለማድረግ ሲሔድ የቢሩት (የአሁኗ ቤይሩት-ሊባኖስ) ሰዎች ዘንዶ (ደራጎን) ሲያመልኩ አገኛቸው:: እርሱ ግን የከተማውን ሕዝብ አስተምሮ: አሳምኖ: ደራጎኑንም በፈጣሪው ኃይል ገድሎ መንገዱን ቀጥሏል::

+ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዱድያኖስና 70 ነገሥታት ዘንድ ሲደርስ ክርስቶስ ተክዶ ለጣዖት ይሠገድ ነበር:: በዚያች ሰዓት ድንግል እመቤታችን ወደ ሰማዕቱ መጥታ መከራውንና ክብሩን ነገረችው:: እርሱም በክርስቶስ ስም መሞት ምርጫው ነበርና ከእመቤታችን ተባርኮ ወደ ምስክርነት አደባባይ (ዐውደ ስምዕ) ደረሰ::

+ከዚያም ለተከታታይ 7 ዓመታት ብዙ ጸዋትወ መከራዎችን ተቀበለ:: 3 ጊዜ ሙቶ ተነሳ:: ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ትዕግስት በላይ የሆነ ስቃይን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በመቀበሉ የሰማዕታት አለቃቸው: ፀሐይና የንጋት ኮከብ በሚል ይጠራል::
"ተውላጠ ጻማሁ ወሕማሙ:
ዘተለዐለ ሞገሰ ስሙ" እንዲል መጽሐፍ::

=>ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዘመናት በብዙ ስቃያት ሲያስጨንቁት ኖረው በጽናቱ አሸነፋቸው:: 70 ነገሥታትን ከነ ሠራዊታቸው ከማሳፈሩ ባሻገርም በርካታ (በመቶ ሺ የሚቆጠሩ) አሕዛብን ማርኮ ለሰማዕትነት አበቃ::

+በዚህ የተበሳጨ ዱድያኖስም ኮከበ ፋርስ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲቆራርጡት አዘዘ:: ወታደሮቹም ቅዱሱን ቆራርጠው: በብረት ምጣድ ላይ ጠበሱት:: ያለ ርሕራሔም አካሉን አሳረሩት:: ቀጥለውም ፈጭተው አመድ አደረጉት::

+በአካባቢው ወደ ነበረው ትልቅ ተራራ ጫፍ (ደብረ ይድራስ) ወጥተውም በነፋስ በተኑት::
"ሐረድዎ ወገመድዎ: ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ዓመድ" እንዲል:: (ምቅናይ)
+እነርሱ ይህንን ፈጽመው ዘወር ሲሉ ግን የቅዱሱ ዓጽም ባረፈባቸው ዛፎች: ቅጠሎችና ድንጋዮች ሁሉ "ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት" የሚል ጽሑፍ ተገኘ::

+ወዲያው ግን ኃያል ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተበተነበት ተነስቶ ወታደሮችን አገኛቸውና "በክርስቶስ እመኑ" ብሎ: አስደንቆ ወደ ሕይወት መራቸው:: 70ው ነገሥታት ግን አፈሩ::
+ከ7 ዓመታት መከራ በሁዋላም በዚሕች ቀን ከብዙ ተዓምራት ጋር ተሰይፎ ደም: ውሃና ወተት ከአንገቱ ፈሷል:: 7 አክሊላትም ወርደውለታል::

=>በ390ዎቹ አካባቢ (ሰማዕት ከሆነ ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ) በዚያው በሃገሩ ደብር አንጸው: አጽሙን አፍልሠው ቀድሰዋታል::
+ቅዱሱ ሰማዕት ከሰማዕትነቱ በፊትም ሆነ በሁዋላ ተአምረኛ ነው:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ሲያፈሱ ከነበሩ አራዊት (ነገሥታት) መካከል አንዱ የሆነው ዲዮቅልጢያኖስ ርጉም የ47 ሚሊየን ክርስቲያኖችን ደም አፍስሶ ነበርና ፈጣሪ ደመ ሰማዕታትን የሚበቀልበት ጊዜ ደረሰ::

+በ305 ዓ/ም አካባቢ አረመኔው ንጉሥ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተአምረኛነት ሰምቶ እንዲያፈርሱት ሠራዊት ላከ:: የሠራዊቱ አለቃም ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ገብቶ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል ላይ ተሳለቀ::

+ከፊቱ የነበረውን ቀንዲል በሰይፍ እመታለሁ ሲል ግን ቀንዲሉ ተገልብጦ መሐል አናቱን መታው:: እንደ እብድ ሆኖ ሞተ:: ሠራዊቱም ሰምቶ ወደ ንጉሡ ሸሸ:: ይሕን ሰምቶ የተበሳጨው ዲዮቅልጢያኖስ ግን ራሱ ሊያፈርሰው ሔደ:: ከቤተ ክርስቲያኑ በር ላይ ሲደርስ ሚካኤልና ገብርኤል ዐይኑን አጠፉት::

+እገባለሁ ሲል ቅዱስ ጊዮርጊስ ከላይ መረዋውን (ደወሉን) ለቀቀበት:: ራሱን ቢመታው ደነዘዘ:: የብዙ ቅዱሳንን ደም የጠጣው ርጉሙ ንጉሥም አብዶ ለ7 ዓመታት ፍርፋሪ ሲለምን ኑሮሰ ይጣን ከገደል ጫፍ ወርውሮ ገድሎታል::

=>አምላካችን እግዚአብሔር ከኃያሉ ሰማዕት ጽናትና ትእግስት: ከበረከቱም ይክፈለን::

=>ሚያዝያ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
2.ቅዱስ ሮቆ ጻድቅ (በስሙ ለተማጸነ ከወባ በሽታ እንዲጠብቀው ጌታ ቃል ኪዳን ገብቶለታል)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እስራኤል
3.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
4.አባ ሳሙኤል
5.አባ ስምዖን
6.አባ ገብርኤል

=>+"+ የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ:: ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ: በመጋዝ ተሰነጠቁ: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ: መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ: በዋሻና በምድር ጉድጉዋድ ተቅበዘበዙ:: +"+ (ዕብ. 11:35-38)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
@petroswepawulos