መዝገበ እውነት Mezgebe Ewnet
5.42K subscribers
628 photos
127 videos
15 files
54 links
እንኳን ወደ መዝገበ እውነት በደህና መጡ...
በመዝገበ እውነት ላይ ስለ ጥንታዊ የብራና መጽሃፍት፣ ስለ መጽሃፈ ሄኖክ ፣ስለ ኔፍሊሞች ፣ስለ ጥንታዊ ሰዎች ስልጣኔ፣ስለ የረቀቀ ቴክኖሎጂ፣ ስለ ስነ ከዋክብት እና መሬታችን ፣ ስለ ድብቅ ማህበራት ሴራ፣ ስለ ሃገራችን ኢትዮጵያ ታሪክ ፣ ስለ ቤተክርስቲያን እና መጽሃፍ ቅዱስ ወዘተ ያልተነገሩ እና ያልተሰሙ አስገራሚ ድብቅ እውነታዎችን በስፋት እንዳሣለን፡
Download Telegram
በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የምስለ ፍቁር ወልዳን ስዕል የምትስልበት እና ሚስጥሩን የምትገልጽበት የራሷ አገላለጽ አላት፣ ይህም ለመረዳት በሃገሪቱ የተለያዩ የጌዜ ዘመን ልዩነት የተሳሉ፣ በተለያዩ ቦታዎች ከሚገኙ ቤተክርስቲያኖች ፣ የብራና መጻህፍት፣ የገበታ ስዕላትን ስንመለከት በስዕሉ አሳሳል ላይ አንድ ወጥ የሆነ አስተምህሮ እንደነበረ እንረዳለን

1. እመቤታችን ጌታችንን በግራ እጇ ታቅፈዋለች
2. ቅዱስ ሚካኤል እና ቅዱስ ገብርኤል በግራ እና በቀኝ ይሳለሉ
3 . እመቤታችን ከላይ ሰማያዊ ልብስ፣ ከውስጥ ቀይ ልብስ ትለብሳለች
4. ጌታችን ቢጫ ወይም ቡርትካናማ ልብስ ይለብሳል
5. የእመቤታችን እራስ ላይ መስቀል እና ትከሻዋ ላይ ኮከብ ይሳላል
6. የእመቤታችን በቀኝ እጇ ሁለት ጣት(የሥጋ እና የነፍስ ድንግልና) እንዲወክል ይሳላል
7. የእመቤታችን በግራ እጇ ጨርቅ(ሰበን) ትይዛለች
8. ጌታችን በቀኝ እጁ ሁለት ጣት (ሁለቱን ልደት እንዲወክል) ተደጎ ይሳላል
9. ጌታችን በግራ እጁ መጽሐፍ (ወንጌልን) ይይዛል
10. እመቤታችን እና የጌታችን ራስ ላይ አክሊለ ብርሃን ተደርጎ ይሳላል
11.ሁለቱም እመቤታችን እና የጌታችን ዘውድ አያደርጉም

ተደርገው የማይሳሉ ነገሮች
1. እመቤታችን ከላይ ቀይ ልብስ ለብሳ
2. እመቤታችን እና የጌታችን እጃቸው ተያይዘው
3. የጌታችን ፊቱ አዙሮ
4. እመቤታችን እና የጌታችን ዘውድ አድርገው መሳል
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማለትም ከ 50፣ 60 ዓመት ወዲህ ስዕሎች ከውጪ አገር ሲገቡ፣የድሮዎቹ አባቶቻችን የሳሏቸው ስእሎች እየተርሱ በአዳዲሶቹ የፈረንጅ ስዕሎች እየተተኩ መጥተዋል፣


ዋናው ነጥብ ግን... እነዚህን የውጪዎቹን ስእሎች የሚስሉት ሰዎች፣ የአምላክን እናት ድንግል ማርያምን እና የመድኃኒአለም የኢየሱስ ክርስቶስን ስዕል ለመሳል ፈልገው ግን እንደ ቤተክርስቲያናችን አባቶች ሚስጥሩን መግለጽ እና ማስተላለፍ አቅቷቸው ነው ወይስ...

ሆን ብለው ሌላ ነገርን ነው እየሳሉ ያሉት...
† እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላምና በፍቅር አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †

† ብርሃነ ትንሣኤ †

† የዓለማት ሁሉ ፈጣሪ : የዘለዓለም አምላክ ወልድ ዋሕድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ዕለት መግነዝ ፍቱልኝ : መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በባሕርይ ኃይሉና ሥልጣኑ ተነስቷልና እንኳን ደስ አለን::

††† አምላካችን ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው በረከት አይለየን:: በዓሉንም የሰላም : የፍቅርና የበረከት ያድርግልን::
የውጪዎቹ ሰአሊያን እመቤታችን ብለው የሚስሉት የእውነት ማንን ነው?

ከጥፋት ውሃ ቡሃላ ከኖህ ልጆች አንዱ በሆነው በያፌት ዘር ከኤፌሶን ልጅ የሆነችው አርጤሚስ ትወለዳለች... አርጤሚስ መልክ ከደም ግባት አስተባብራ የያዘች ነበረች ሰይጣን ኝ በልቦናዋ ትእቢትን አሳድሮባት ነበር።ብዙ ባሎች ቢመጡላትም በሃብት በውበት እና ጥበብ የላችሁም እያለች ትመልሳቸው ነበር...

ከዛም ቆርኔሊዎስ የተባለ ጠንቋይ አንቺ እንድትከበሪ ላድርግሽ እና ላግባሽ ብሎ... በምትሃት አጋንንቶችን በመሳብ አርጤሚስ አምላከ እንደሆነች የሚመሰክር ጽሁፍ በሰዎች መካከል እንዲጥሉለት አጋንንቶቹን አዛዛቸው.... ያም አርጤሚስ አምላክ ነች የሚለው ጽሁፍ አጋንንቶቹ አምጥተው በሰዎች መካከል በሚያስተምርበት ሰዓት ጣሉለት እሱም ለሰዎቹ አነበበላቸው... ከዛም አርጤሚስ አምላክ ናት ብሎ ሰገደላት ሰዎቹም ሰገዱላት...

ከዛም ቆርኔሊዎስ አርጤሚስን አገባት ዜውስንም ወለደ... ዜውስም የአምላክ ልጅ አምላክ ነው ብለው ሰገዱለት... ከሞቱም ቡሃላ በሰዎቹ ዘንድ እንደተነሱ እንዳረጉ ታምኖባቸዋል... ስእልም ተስሎላቸው ምስልም ተቀርጾላቸው እየተመለኩ የሚኖሩ ሆነዋል... ከነሱም ተጨማሪ በፀሐይ በጨረቃ እና በከዋክብትም እየተመሰሉ ይመለኩ ነበር

ከራእየ ዮሐንስ አንድምታ መቅድም ላይ ያለ ታሪክ ነው ሙሉውን ከስር ካለው PDF ያንብቡ