መዝገበ እውነት Mezgebe Ewnet
5.42K subscribers
628 photos
127 videos
15 files
54 links
እንኳን ወደ መዝገበ እውነት በደህና መጡ...
በመዝገበ እውነት ላይ ስለ ጥንታዊ የብራና መጽሃፍት፣ ስለ መጽሃፈ ሄኖክ ፣ስለ ኔፍሊሞች ፣ስለ ጥንታዊ ሰዎች ስልጣኔ፣ስለ የረቀቀ ቴክኖሎጂ፣ ስለ ስነ ከዋክብት እና መሬታችን ፣ ስለ ድብቅ ማህበራት ሴራ፣ ስለ ሃገራችን ኢትዮጵያ ታሪክ ፣ ስለ ቤተክርስቲያን እና መጽሃፍ ቅዱስ ወዘተ ያልተነገሩ እና ያልተሰሙ አስገራሚ ድብቅ እውነታዎችን በስፋት እንዳሣለን፡
Download Telegram
ቆርኔሊዎስ አርጤሚስ እና ዜዎስ.... በሌላ ቋንቋ እና ባህል ኒምሮድ ሴምሚራሚስ እና ታሙዝ ተብለው ይጠራሉ... ታሪካቸው ግን አንድ አይነት ነው
ቆርኔሊዎስ ማለት ኒምሮድ ነው

ይህ ቆርኔሊዎስ ምትሃተኛ የአርቴሚስ ባል ኒምሮድ ነበር... ኒምሮድ የኮከብ ቆጠራ እና ፀሐይን አምልኮ በዘመኑ የሚያስተምር... የዓለምን ህዝብ አንድ አድርጎ የባቢሎን ግንብንም የሚያስገነባ ሰው ነበር
ሚስጥራዊው የባቢሎን ሃይማኖት

ይህ ሃይማኖት፣ ዓለም አንድ ሆኖ የባቢሎንን ግንብ በሚሰሩበት ጊዜ የተመሰረት ሲሆን። እግዚአብሔር ለአዳም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለው የሚለውን ቃልኪዳን፣ ገና ጊዜው ሳይደርስ እንደተፈጸመ አድርጎ ማቅረብ ነው ፣ይህንም ዜውስ የአምላክ ልጅ አምላክ ነው እግዚአብሔር ዓለምን እንዲያድን የተላከው መሲህ ይህ ነው እናቱ አርጤሚስ ደግሞ የአምላክ እናት ናት የሚል ሃይማኖት ነበር...
በጥንታዊ ባቢሎን የአርጤሚስ እና የልጇን ሰዕል ስለው፣ ምስላቸውንም ቀርጸው ፣ ቤተመቅደስ ገንብተውላቸው እግዚአብሔር ወደ ዓለም ይላከው የአምላክ ልጅ ዜውስ ነው በማለት ይሰግዱላቸው ነበር ይህም ጣኦት አልምኮ በሃገሪቱ ሁሉ ተስፋፍቶ ነበር ።
በጥንታዊ ባቢሎን የሚገኝ የአርጤሚስ እና የልጇየዜውስ ምስል
እግዚአብሔር የባቢሎንን ግንብ ሳይጨርሱ ቋንቋቸውን በለያየባቸው እና በምድር ሁሉ ገጽ በበታተናቸው ጊዜም ይህንን አምልኮታቸውን ይዘው ነው የተበታተኑት ነገር ግን በተለያየ ቋንቋ እና አገላለጽ ቢሆንም አርጤሚስ እና ልጇን ማምለኩን ኝ አላቋረጡም
በዜና ሐዋርያት ላይም ሮማውያን አርጤሚስን ዲያና ብለዋት ያመልኳት ነበር... ሮማዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎቹም ጥንታዊ ስልጣኔዎች መሲሁን ዜውስ፣ እናቱን አርጤሚስን እና አባቱን ኒምሮድን የተላያየ ስም እየጥሩ ያመልኳቸው ነበር።የጥንታዊ ግብጽ ፣ ህንድ፣ ቻይና፣ ኤሴሪያ፣ ፈሚሻውያን ሁሉ ቋንቋቸው እና ባህላቸው የተለያየ ቢሆንም የመጀመሪያዎቹ ቋንቋቸው ሳይበታተን ያመልኳቸው የነበሩትን የባቢሎን ጣኦታትን ግን ማምለካቸውን አላቋረጡም
የአርጤሚስ እና የልጇየዜውስ ምስል እና ቅርጽ በተለያዩ ጥንታዊ ስልጣኔዎች