መዝገበ እውነት Mezgebe Ewnet
5.59K subscribers
645 photos
136 videos
16 files
54 links
እንኳን ወደ መዝገበ እውነት በደህና መጡ...
በመዝገበ እውነት ላይ ስለ ጥንታዊ የብራና መጽሃፍት፣ ስለ መጽሃፈ ሄኖክ ፣ስለ ኔፍሊሞች ፣ስለ ጥንታዊ ሰዎች ስልጣኔ፣ስለ የረቀቀ ቴክኖሎጂ፣ ስለ ስነ ከዋክብት እና መሬታችን ፣ ስለ ድብቅ ማህበራት ሴራ፣ ስለ ሃገራችን ኢትዮጵያ ታሪክ ፣ ስለ ቤተክርስቲያን እና መጽሃፍ ቅዱስ ወዘተ ያልተነገሩ እና ያልተሰሙ አስገራሚ ድብቅ እውነታዎችን በስፋት እንዳሣለን፡
Download Telegram
በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የምስለ ፍቁር ወልዳን ስዕል የምትስልበት እና ሚስጥሩን የምትገልጽበት የራሷ አገላለጽ አላት፣ ይህም ለመረዳት በሃገሪቱ የተለያዩ የጌዜ ዘመን ልዩነት የተሳሉ፣ በተለያዩ ቦታዎች ከሚገኙ ቤተክርስቲያኖች ፣ የብራና መጻህፍት፣ የገበታ ስዕላትን ስንመለከት በስዕሉ አሳሳል ላይ አንድ ወጥ የሆነ አስተምህሮ እንደነበረ እንረዳለን

1. እመቤታችን ጌታችንን በግራ እጇ ታቅፈዋለች
2. ቅዱስ ሚካኤል እና ቅዱስ ገብርኤል በግራ እና በቀኝ ይሳለሉ
3 . እመቤታችን ከላይ ሰማያዊ ልብስ፣ ከውስጥ ቀይ ልብስ ትለብሳለች
4. ጌታችን ቢጫ ወይም ቡርትካናማ ልብስ ይለብሳል
5. የእመቤታችን እራስ ላይ መስቀል እና ትከሻዋ ላይ ኮከብ ይሳላል
6. የእመቤታችን በቀኝ እጇ ሁለት ጣት(የሥጋ እና የነፍስ ድንግልና) እንዲወክል ይሳላል
7. የእመቤታችን በግራ እጇ ጨርቅ(ሰበን) ትይዛለች
8. ጌታችን በቀኝ እጁ ሁለት ጣት (ሁለቱን ልደት እንዲወክል) ተደጎ ይሳላል
9. ጌታችን በግራ እጁ መጽሐፍ (ወንጌልን) ይይዛል
10. እመቤታችን እና የጌታችን ራስ ላይ አክሊለ ብርሃን ተደርጎ ይሳላል
11.ሁለቱም እመቤታችን እና የጌታችን ዘውድ አያደርጉም

ተደርገው የማይሳሉ ነገሮች
1. እመቤታችን ከላይ ቀይ ልብስ ለብሳ
2. እመቤታችን እና የጌታችን እጃቸው ተያይዘው
3. የጌታችን ፊቱ አዙሮ
4. እመቤታችን እና የጌታችን ዘውድ አድርገው መሳል
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማለትም ከ 50፣ 60 ዓመት ወዲህ ስዕሎች ከውጪ አገር ሲገቡ፣የድሮዎቹ አባቶቻችን የሳሏቸው ስእሎች እየተርሱ በአዳዲሶቹ የፈረንጅ ስዕሎች እየተተኩ መጥተዋል፣


ዋናው ነጥብ ግን... እነዚህን የውጪዎቹን ስእሎች የሚስሉት ሰዎች፣ የአምላክን እናት ድንግል ማርያምን እና የመድኃኒአለም የኢየሱስ ክርስቶስን ስዕል ለመሳል ፈልገው ግን እንደ ቤተክርስቲያናችን አባቶች ሚስጥሩን መግለጽ እና ማስተላለፍ አቅቷቸው ነው ወይስ...

ሆን ብለው ሌላ ነገርን ነው እየሳሉ ያሉት...