የ2017 ትምህርት ዘመን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት መርሃ ግብር ተገለጸ፡፡
ፈተናው ከሰኔ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም የሚሰጥ ሲሆን በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 21 እና 22/2017 ዓ/ም እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 29 እና 30/2017 ዓ/ም ወደሚፈተኑበት ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ይሆናል፡፡ በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተፈታኞች ከመኖሪያ ቤታቸው በየቀኑ እየተመላለሱ በተመደቡበት መፈተኛ ማዕከል የሚፈተኑ ሲሆን ዝርዝር መርሃ ግብሩ በሚከተለው ሠንጠረዥ ተገልጿል፡፡
የፈተናው ይዘት በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያተኮረ በመሆኑ እያንዳንዱ ተፈታኝ በትምህርት ቤቱ የተማረበትን የተማሪ መጽሐፍ መሠረት አድርጎ ተገቢ የሆኑ አጋዥ መጽሐፍትን ለበለጠ እውቀትና መረዳት በመጠቀም እንዲዘጋጅ እናበረታታለን፡፡ በፈተና ወቅት ለፈተና ስርቆትና ኩረጃ የሚውሉ ማንኛውንም ቁሳቁሶች መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ዝርዝሩ በቀጣይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ግንቦት 01/2017 ዓ/ም

የመቱ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ስራ አስፈጻሚዎችፕሬዝደንት ምርጫ ተካሄደ።
ግምቦት 4/2017 ዓ.ም (ህዓአግ)
===========+==========
በኢትዮጲያ ዩኒቨርሲቲዎች መ/ራን ማህበር የመቱ ዩኒቨርሲቲ መ/ራን ማህበር ስራ አስፈጻሚዎችና ፕሬዝዳንት ምርጫ የመቱ ዩኒቨርሲቲ አካ/ቴክ/ሽግ/ማ/አገ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር በድሉ ተካ በተገኙበት ተካሂዷል።
በመቱ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው የምርጫ ሂደቱን ያስተባበሩት በጂማ ዩኒቨርሲቲ የጆርናሊዝም ት/ት ክፍል መምህር እና የኢትዮጲያ ዩኒቨርሲቲዎች መ/ራን ማህበር ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ደመላሽ መንግስቱ ሲሆኑ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር እንቅስቃሴን በተመለከተ ባቀረቡት አጭር ሪፖርት በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ከተቋቋመ ረጅም የሚባል ጊዜ የሆነው ቢሆንም የዩዩኒቨርስቲ መምህራን እስካሁን የተደራጀና ጠንካራ ማህበር እንደሌላቸው ገልጸው ለወደ ፊት ግን የዩኒቨርስቲ መምህራን ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር በህብረት ሆነው ሀገራዊ ግዴታቸውን መወጣት እና መብታቸውን ማስከበር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
የማህበሩ ዓላማ መምህራንን እንደ ማህበር ከየትኛውም የፖለትካ፤ የዕምነት፤ የብሔር ወዘተ አመለካከት ወገንተኝነት ነጻ ሆኖ ለጋራ ግብ በማሰለፍ ግዴታቸውን እንዲወጡና መብታቸውን እንዲያስከብሩ ማስቻል ነው ብለዋል።
በማህበሩ አደረጃጀት ላይ ውይይት ከተደረገ በኃላ በየት/ት ክፍሉ፤ በኮሌጆች እና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ መምህራንን የሚወክሉ ስራ አስፈጻሚዎች የተመረጡ ሲሆን መ/ር ጥላሁን ነጋሽ በኢትዮጵያ ዩኒቨርርሲቲዎች መ/ራን ማህበር የመቱ ዩኒቨርሲቲ መ/ራን ማህበር ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል። ፕሬዝዳንቱ እና ስራ አስፈጻሚዎቹ በትጋትና በታማኝነት ለመስራትም ቃለ- መሃላ ፈጽሟል።
We're dedicated to serve the community!