#ማጀቴ
አዲስ የሙዚቃ አልበም!
በ #ኒና_ግርማ
የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ገበያ ላይ ይውላል።
ልብ እና ጆሮአችንን ለአዲስ ሙዚቃዊ ድምጽ እናዘጋጅ!
በግል ጥረቷ ጥቂት ነጠላ ዜማዎችን የለቀቀችው ኒና ግርማ፥ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በምትለቃቸው አጫጭር የዘፈን ቪዲዮዎች ትታወቃለች። እነዚህን ቪዲዮዎች የተመለከተው የሙዚቃ አቀናባሪ #ካሙዙ_ካሳ የሙሉ አልበም ፕሮጀክትን አስጀመራት።
እንደ ማሟሻም #የታል_አለቃ የተሰኘ ነጠላ ዜማዋ ላይ በዜማ ድርሰት እና በቅንብር አንድ አለ። በዚያ የጀመረው የካሙዙ ተሳትፎ፥ እነሆ "ማጀቴ" የተሰኘውን የሙዚቃ አልበም ወልዷል፡፡
የ"ማጀቴ" አልበም ግጥም እና ዜማ ሙሉ በሙሉ በራሷ በኒና ግርማ የተሰራ ሲሆን፣ ካሙዙ ካሳ ደግሞ የሙሉ ዘፈኖቹ አቀናባሪ ነው፡፡
ከራፕ በተጨማሪ የአር ኤንድ ቢ፣ የዳንስሆል፣ አፍሮቢት እና ሌሎች ቅይጥ ስልተ-ምቶችን ያካተተው "ማጀቴ" አልበም፣ በዜማ እና በግጥም ስብጥራቸው የተመረጡ 14 ስራዎችን ይዟል፡፡
አልበሙን አስቀድሞ እንዳደመጠ ሰው ይህን እላለሁ። ደርዝ ባላቸው ግጥሞች አማካኝነት በፍቅር፣ በቤተሰብ፣ በአገር እና ሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩት ስራዎች የኒናን ተሰጥኦ አጉልተው የሚያሳዩ ናቸው። በአጠቃላይ "ማጀቴ"፣ ኒና የራሷን ቀለም ይዛ የመጣችበት አዲስ የሙዚቃ አልበም ነው፡፡
#Nina_Girma #Majete #New_Album #Kamuzu_Kassa #Shakura_Records #Ethiopian_Music #Awtar_Music #Awtar #Get_It_On_Awtar #Ethiopia #Awtar_App #MusicForEveryMood #Ethiopia #Musician #በአውታር