በአማራ ክልል ከ30 በላይ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የፀጥታ አባላት በፋኖ ሀይሎች በተረሸኑበት ጥቃት ምን ተከሰተ?
(መሠረት ሚድያ)- በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ባለፈው ሳምንት ከ30 በላይ የአካባቢው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የፀጥታ አባላት በፋኖ ሀይሎች መገደላቸውን ነዋሪዎችን እና የአካባቢው አስተዳደርን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።
በዞኑ ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ ኅዳር 26/2017 ዓ.ም. ለሁለት ወራት ለመንግሥት "መረጃ እና ድጋፍ ሰጪ" በሚል ተጠርጥረው በፋኖ ሀይሎች ተይዘው የነበሩ በርካታ የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች፣ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት "መረሸናቸው" ታውቋል።
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ዋለ አለማየሁ 20 ከሚሆኑ የወረዳው ካቢኔዎቻቸው ጋር የግድያው ሰለባ መሆናቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።
መስከረም መጨረሻ በአካባቢው "ከባድ ውጊያ" መደረጉን ተከትሎ መስከረም 29/2017 ዓ.ም. ወረዳው በፋኖ ሀይሎች ቁጥጥር ስር መግባቱን እና የመንግሥት ኃይሎች ወረዳውን ለቀው መውጣታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ይህንንም ተከትሎ "[መከላከያ] የሚሊሻ፣ የፖሊስ አባላትን እንዲሁም ካቢኔዎችን በሙሉ መስመር ላይ ነው ጥሏቸው የሄደው" ሲሉ አንድ ነዋሪ፤ 'ባልተለመደ ሁኔታ' የወረዳው አስተዳደር ከተማዋ ውስጥ መቅረቱን ገልጸዋል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ዓለም 20 የሚሆኑ የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች መከላከያ ሠራዊት "ለስምሪት" አካባቢውን ለቆ ሲወጣ "ተቆርጠው" መቅረታቸውን ተናግረዋል።
በፋኖ ሀይሎች ቁጥጥር ስር የነበሩት የአካባቢ አመራሮች "ፈረስ ቤት ሚካኤል" በተባለ የከተማው መውጫ ላይ ተወስደው መረሸናቸውን ሦስት ነዋሪዎች እና የዓይን እማኝ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
Via BBC Amharic

"ኢትዮጵያ እና ሱማልያ ሁለቱንም በሚያግባባ መልኩ ስምምነት ላይ ደርሰዋል"--- የተርኪዪ መሪ ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን
(መሠረት ሚድያ)- የሶማልያ እና የኢትዮጵያ መሪዎችን በተርኪዪ እያስተናገዱ የሚገኙት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ኢትዮጵያ እና ሱማልያ ሀለቱንም ሀገራት በሚያግባባ መልኩ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ብለው ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርገዋል።
ኤርዶጋን ሁለቱ ሀገራት በጋራ ይፋ የሚያደርጉት የስምምነት ዶክመንት እንደተዘጋጀ ጠቅሰው ዶክመንቱ ሀገራቱ የበፊቱን ሳይሆን መጪውን ግዜ እንዴት በጋራ አብረው ተከባብረው እና በመልካም ጉርብትና እንደሚወጡት የሚያሳይ ነው ብለዋል፣ ለዚህም ሁለቱን ሀገራት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ በምሽቱ ፕሮግራም ላይ የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጉዳይ ከህልውናዋ ጋር የተያያዘ መሆኑን አንስተው የዛሬው ውይይት ወደ ጓደኝነት መልሶናል ብለዋል።
የሶማልያው ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በበኩላቸው ዛሬ ምሽት የተደረገው ውይይት በቅርብ ግዜ በሀገራቸው እና ኢትዮጵያ መሀል የነበረውን አለመግባባት ያስቆመ ነው ብለዋል። ሱማልያ የኢትዮጵያ "እውነተኛ ጓደኛ" ሆና ትቀጥላለችም ብለዋል። የኢትዮጵያ ጦር በሶማልያ ለአመታት የከፈለውን መስዋዕትነትም ፕሬዝደንቱ አንስተዋል።
የዛሬ አመት ገደማ በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መሀል የባህር በር አጠቃቀምን በተመለከተ የመግባብያ ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ እሰጥ አገባ ውስጥ ገብተው የሚገኙት ኢትዮጵያ እና ሶማልያ ከስምንት ወር በፊት ጀምሮ በተርኪዪ አመቻችነት ንግግር ቢጀምሩም ውጤት ሳያመጣ ቆይቷል።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia

ኢትዮጵያ እና ሶማልያ ዛሬ ምን ተስማሙ?
(መሠረት ሚድያ)- ዛሬ ምሽት ላይ የኢትዮጵያ እና ሶማልያ መሪዎች ተርኪዪ፣ አንካራ ላይ ስምምነት መድረሳቸው ታውቋል።
'የአንካራ ስምምነት' ዝርዝሩ ምን ይሆን?
መሠረት ሚድያ የስምምነት ነጥቦቹን የያዘውን ዶክመንት የተመለከተ ሲሆን ዋናው ነጥብ ይህ እንደሆነ ተመልክቷል:
"በሶማልያ መንግስት ባለመብትነት ስር በሚከናወን የንግድ ውል፣ ሊዝ እና ሌላ አሰራር ሁለቱም ሀገራትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ይከናወናል፣ ይህም ኢትዮጵያ ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር የመጠቀም እድል ይኖራታል። ይህን ጉዳይ ለማስፈፀም ከመጋቢት 2017 ዓ/ም በፊት የቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሙ የማመቻቸት ስራ ይሰራል፣ በአራት ወር ውስጥ ደግሞ ስምምነት ይፈረማል።"

ሰላም የመሠረት ሚድያ ተከታታዮች፣
ከዜና ቻናላችን በተጨማሪ ቃለ መጠይቆችን እና ልዩ ልዩ ወቅታዊ ትንታኔዎችን የምናቀርብበት 'Meseret Media Plus' የተባለ የዩትዩብ ቻናል ከፍተናል። በቅርቡ ቃለ መጠይቅ እንዲደረጉ የጠቆማችኋቸውን ግለሰቦች ጨምሮ አዳዲስ ትንታኔዎች ስለምናቀርብ ዛሬውኑ ይቀላቀሉ ⤵️
https://youtube.com/@meseretmediaplus?si=bjpL0x3W01hj5HS7

YouTube
Meseret Media Plus
መሠረት ሚድያ በኢትዮጵያ ለበርካታ አመታት በጋዜጠኝነት ሙያ ላይ የሰሩ ባለሙያዎች ወቅታዊ መረጃዎችን ለህዝብ ለማድረስ በማለም ያቋቋሙት ዲጂታል ሚድያ ነው።
ፖለቲከኛ አቶ ጃዋር መሐመድ ከመሠረት ሚድያ ጋር ቃለ መጠይቅ በቅርቡ በ 'Meseret Media Plus' ዩትዩብ ቻናላችን ይቀርባል፣ ይህን እና ሌሎች ቃለ መጠይቆችን ለመከታተል ቻናሉን አሁኑኑ ይቀላቀሉ ⤵️
https://youtube.com/@meseretmediaplus?si=N1apn9TWwDT4pAC3

ኦሮሚያ ባንክ ከአውሮፓ አገኘሁ ያለው ሽልማት እና የሸላሚው አካል ማንነት
(መሠረት ሚድያ)- ኦሮሚያ ባንክ እያስመዘገበ ባለው የማይዋዥቅ የላቀ አገልግሎት ምክንያት ከአውሮፓ ሶሳይቲ ፎር ኳሊቲ ሪሰርች (ESQR) ህዳር 30/2017 ዓ.ም በኦስቲሪያ፣ ቪየና በተካሄድ ፕሮግራም ላይ ሽልማት መቀበሉን አስታውቆ ነበር።
በዚህ ወቅት የባንኩ ሀላፊዎች "ባንካችን ወደ ዓለም አደባባይ በስፋት በመውጣት ተወዳጅ ዓለም-አቀፍ ብራንድ እየሆነ መጥቷል" ብለው ተናግረው ነበር።
በዚህ ሽልማት ዙርያ መሠረት ሚድያ ባደረገው ማጣራት የአውሮፓ ሶሳይቲ ፎር ኳሊቲ ሪሰርች (ESQR) የተባለው ሸላሚ ተቋም ከ4 ሺህ ዩሮ ጀምሮ ክፍያ ለሚፈፅሙ ተቋማት ሽልማት በማከፋፈል ከዚህ በፊት የሚታወቅ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።
የዛሬ ሁለት አመት ናሚቢያ ውስጥ የሚገኙ ሁለት ተቋማት እያንዳንዳቸው 4,200 ዩሮ ከፍለው ይህን ተመሳሳይ ሽልማት ተቀብለው እንደነበር አንድ የሀገሪቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት አጋልጦ ነበር (ሊንክ: https://www.facebook.com/share/v/19pn9HpsZS/)
በተጨማሪም አለም አቀፉ የተደራጁ ወንጀሎች እና የሙስና ተግባሮችን አጣሪ እና ሪፖርት አቅራቢ ተቋም (OCCRP) የዛሬ አስር አመት ባወጣው ሪፖርቱ የአውሮፓ ሶሳይቲ ፎር ኳሊቲ ሪሰርች (ESQR) እና ሌሎች ተመሳሳይ በሽልማት ስም የሚያጭበረብሩ ድርጅቶች ምንም አይነት ውድድር ሳይደረግ እና የማሸነፊያ መመዘኛዎችን ሳያስቀምጡ ገንዘብ ለከፈሉ ሁሉ ሽልማት እንደሚሰጡ ጠቅሶ ነበር (ሊንክ: https://www.occrp.org/en/investigation/what-price-honor)
አሁን አሁን ብዙ የሽልማት ፍላጎት እየበዛ የመጣው ከታዳጊ ሀገራት እንደሆነ ሪፖርቱ ገልፆ ማንኛውም ገንዘብ መክፈል የቻለ ተቋም ከ ESQR እና መሰል ድርጅቶች ሽልማት ማጋበስ እንደሚችሉ ጠቅሟል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ከኦሮሚያ ባንክ በተጨማሪ የንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስትር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን እንዲሁም ሌሎች ሽልማት እየተበረከተላቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ መረጃዎችን ሲያጋሩ ቆይተዋል።
እነዚህ African Leadership Magazine፣ African Governance Award፣ The African Women Awards፣ Africa Respected Professionals Award ወዘተ የተባሉ ሽልማቶች በተለይ ጋና እና ናይጄርያ መቀመጫቸውን ባደረጉ ጋዜጠኞች እየተዘጋጁ የሽልማት ፍላጎት ላለባቸው ሀገራት ገንዘብ በማስከፈል እንደሚሰጡ ታውቋል።

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
#ልዩሪፖርት በኢትዮጵያ እና ሶማልያ መሀል በአንካራ በተፈረመው ስምምነት ዙርያ የቀድሞው የጠ/ሚር ልዩ ጽ/ቤት ባልደረባ የነበሩት አቶ ቢንያም እሸቱ በተለይ ለመሠረት ሚድያ ያጋሩትን ልዩ መረጃ ይከታተሉ ⤵️
https://youtu.be/1QyzBP2x_S8?si=-e4VESALN7Mmu8h3
https://youtu.be/1QyzBP2x_S8?si=-e4VESALN7Mmu8h3
YouTube
በመርህ አልባ ስምምነቶች እና ውጤቶቻቸው ዙርያ የቀድሞው የጠ/ሚር ልዩ ጽ/ቤት ባልደረባ አቶ ቢንያም እሸቱ እይታቸውን ለመሠረት ሚድያ አጋርተዋል፣ ይከታተሉት
የቀድሞው የጠ/ሚር ልዩ ጽ/ቤት ባልደረባ አቶ ቢንያም እሸቱ በኢትዮጵያ እና ሶማልያ አዲስ ስምምነት ዙርያ እንዲሁም መርህ አልባ የሆኑ የቅርብ አመታት ስምምነቶችን የዳሰሱበትን ፅሁፋቸውን ለመሠረት ሚድያ አጋርተዋል፣ ይከታተሉት።
ዛሬ ታህሳስ 6/2017 ዓ/ም 'መሠረት ሚድያ ፕላስ' ምሽት 1 ሰዐት ላይ በዩትዩብ ቻናሉ የሚያቀርባቸው ዜናዎች አርዕስተ ዜናዎች:
1. የቴሌ ሰራተኞች ጩኸት በመጨረሻ ሰሚ አገኘ
2. የባለሀብቶቹ የባንክ አካውንት መታገድ ጀመረ
3. መምህራኑ ብሄራቸውን በአስገዳጅነት ሙሉ ተባሉ
4. በጉቦ አስቸኳይ ፓስፖርት ለማውጣት የሚጠየቀው የገንዘብ መጠን
5. የቤተ ክህነት ስራ አስኪያጁን ጨምሮ 40 ሰዎች ታግተው ተወሰዱ
6. ለኮሪደል ልማት 2 ሚልየን ብር አላዋጣችሁም የተባሉ የግል ባንኮች ታሸጉ
7. እንዲሁም፣ ከኤርፖርት የተሰማው አሳሳቢ የሙስና ወንጀል፣ የሚሉ ዜናዎችን ይዘናል፣ ምሽት 1 ሰአት ላይ በዚህ የ 'Meseret Media Plus' ዩትዩብ ቻናላችን ይጠብቁን ⤵️
https://youtube.com/@meseretmediaplus?si=3OlIt3B4WRztAM6w

የዛሬ የታህሳስ 7/2017 ዓ/ም የመሠረት ሚድያ የምሽት 1 ሰአት አርዕስተ ዜናዎች:
1. የአዲስ አበባ ከንቲባ ከስራቸው ያሰናበቷቸው ሀላፊ እና አነጋጋሪ ምክንያቱ
2. ኢትዮጵያውያንን ከሚያንማር ለማስወጣት እንቅስቃሴ ተጀመረ
3. ግዙፉ የሪል እስቴት ኩባንያ ከህዝብ ከፍተኛ አቤቱታ ቀረበበት
4. በግፍ ተባረርን ያሉ 300 ሰራተኞች ችግር ላይ ነን አሉ
5. በአርባ ምንጭ በርካታ ወጣቶች እየታፈሱ ነው ተባለ
6. እንዲሁም፣ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ከፍተኛ ረሀብ ተከስቶ የሰው ህይወት እያለፈ መሆኑ ተሰማ፣ የሚሉ ዜናዎችን ይዘናል በዚህ ዩትዩብ ቻናላችን ምሽት 1 ሰአት ላይ ይጠብቁን ⤵️
https://youtube.com/@meseretmediaplus?si=Hix_Vj_o6yUc5zHk

#አስተያየት "ኢትዮጵያ ተለዋዋጭ የሆነውን የቀጠናውን እና ዓለማቀፋዊ ሁኔታውን የዋጀ በሳል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መመስረት ከምን ጊዜውም በላይ ያሻታል"--- አቶ ቢንያም እሸቱ
(መሠረት ሚድያ)- አገራት ከፍተኛ ውጥረት እና ፉክክር በተሞላበት ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ ውስጥ ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችንና አጋርነቶችን መመስረት የግድ ይላቸዋል። ማንኛውም አገር ከዓለም አቀፉ ስርዓት ተነጥሎ ሊኖር አይችልምና!
ዲፕሎማሲ በአብዛኛው ሕግ-ተኮር (rule-based ) ሲሆን በዓለም አቀፍ ሕግጋት (International Law) እና በተለምዷዊ አሰራሮች (Norms and principles) ይመራል። የሁለትዮሽ (Bilateral) እና ባለብዙ ወገን (Multilateral) ስምምነቶች ደግሞ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ዋነኞቹ መልህቆች ናቸው።
አገራችን ኢትዮጵያ ከውጫሌ ስምምነት አንስቶ እስከ አሁን በርካታ ባለብዙ ወገን እና የሁለትዯሽ ስምምነቶችን ተፈራርማ የውጪ ግንኙነቷን ስታከናውን ቆይታለች። የውጫሌን ስምምነት በተለየ ሁኔታ ያነሳሁት የመጀመሪያው መደበኛ ዓለማቀፍ ስምምነት ስለሆነ እንጂ ኢትዮጵያ ከሌሎች ዓለማት ጋር ታደርግ የነበረውን ዘመን ጠገብ ግንኙነት ለማሳነስ እንዳልሆነ ልብ ይሏል።
እነዚህ ስምምነቶች በአገር ውስጥ ያሉ መንግስታት በተቀያየሩ ቁጥር የሚለዋወጡ ሳይሆን ዘመን ተሻጋሪ ናቸው። ስለዚህ የትኛውም መንግስት የሚፈራረመው ስምምነት ብሔራዊ ጥቅምን ያስከበረ እና ለመጪው ትውልድ እዳን ትቶ የሚያልፍ አለመሆኑን በአግባቡ መፈተሽ ይኖርበታል።
እዚህ ጋር በኢሕአዴግ መንግስት ወቅት የፋይናንስ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ሱፊያን አህመድ የደርግ መንግስት ከሰሜን ኮሪያ መንግስት ጋር የተፈራረመውን የብድር ስምምነት እዳ አከፋፋል አስመልክቶ ለውይይት ወደ ፒዩንግ ያንግ (Pyongyang ) ባቀኑበት ወቅት የገጠማቸውን ሁኔታ ያጫወቱኝ ትዝ ይለኛል። ልብ በሉ የደርግ መንግስት የገባውን እዳ የኢሕአዴግ መንግስት ሲከፍል ማለት ነው።
ሰሞንኛው የአንካራ ስምምነት የመንግስትን የውጪ ግንኙነቱን አካሄድ ድክመቶች እና አደገኛ መዘዞች በግልጽ ያሳየ ሆኗል። ባለፉት 6 ዓመታት የኢትዮጵያ መንግስት ለቀጣዩ ትውልድ ጭምር ሊተላለፉ የሚችሉ በርካታ ዲፕሎማሲያዊ ስህተቶችን እንደሰራ በርካታ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። ለዚህ ጽሑፍ ሲባል ሶስቱን አበይት ስህተቶች ብቻ እንመልከት:
- የኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት:
የብልጽግና መንግስት አስተዳደር ገና ከጅምሩ ከኤርትራ ጋር ለዘመናት የቆየውን አለመግባባት ለማርገብ ጥረት ማድረጉ በምልዓተ ህዝቡ ተወዶለት ነበር ። ሆኖም ከኤርትራ መንግስት ጋር እንደ አዲስ የመሰረተው ግንኙነት የሚመራበት ይህ ነው የሚባል ስምምነት ወይም መርሆ አልነበረም። ሌላው ቢቀር የአልጀርስን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ አፈፃፀም አስመልክቶ እንኳን የተደረሰበት ስምምነት በግልጽ አይታወቅም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ ተቀብለናል ሲሉ ከዚህ በፊትም የሁለቱ አገራት ውጥረት ዋና እምብርት የነበረው የአልጀርስ ስምምነቱ የአረዳድ እና የአፈፃፀም ልዩነቶች ተለይተው አልተፈቱም። ስምምነቱ ይተግበር ቢባል እንኳ እነዚህ ልዩነቶች ስላሉ ወደፊትም ሌላ ውጥረት እንደሚነግስ እሙን ነው። አለባብሰው ቢያርሱ በአርም ይመለሱ ነውና ነገሩ ብዙም ሳይቆይ እየተቀየረ መጥቷል። ዛሬም ድረስ የአንድ ወቅት ዋነኛ የቀጠናው አጀንዳ የነበረው የኤርትራና የኢትዮጵያ መንግስት ግንኙነት መሰረት በተለምዶ የጂዳው መግለጫ ከተሰኘው ሰነድ በቀር ይህ ነው የሚባል ስምምነት አልነበረም። ይሁን እንጂ የግንኙነታቸው አድማስ በጣም ጥብቅ የሆነ ወታደራዊ ትብብርንም ይጨምር እንደ ነበር የትግራዩ ጦርነት አሳይቷ አልፏል። ግንኙነቱ ግልጽ በሆነ መንገድ ባለመመራቱም በአንድ ወቅት ተሟሙቆ የነበረው ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ተቋርጧል። በአሁኑ ወቅት የሁለቱ አገራት የተካረረ ግንኙነት ወደ ግጭት እንዳይገባ ከፍተኛ ስጋት ተፈጥሯል።
- የኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ግንኙነት:
ሌላኛው አወዛጋቢ ግንኙነት በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኢምሬትሶች ጋር ያለው መርህ አልባ ግንኙነት ነው። የኢትዮጵያ እና ኢሚሬቶች አሁናዊ ግንኙነት የሚመራበት ይህ ነው የሚባል ግልጽ ስምምነት ማቅረብ አዳጋች ነው። ከቤተ መንግስት ማስዋብ አንስቶ በርካታ ሜጋ የአስተዳደሩ ፕሮጀክቶች ከኢሚሬትሶች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እየተከናወኑ እንደሆነ በተደጋጋሚ ቢገለጽም ድጋፉ በምን ስምምነት እንደተገኘ ማስረጃ ማቅረብ የሚቻል አይመስለኝም። ችግሩ የሚመነጨው መሪው አገሪቱን የጋራችን ሳትሆን የግል ንብረታቸው አድርገው ከመቁጠራቸው የተነሳ ይመስላል። አለበለዚያማ ማንኛውም የብድር ወይም የእርዳታ ስምምነት ሲፈጸም የህዝብ እንደራሴዎች ፊት ቀርቦ በይፋ እንዲጸድቅ ይደረግ ነበር (የኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55 (12)። ፓርላማውም በስምምነቱ መሰረት አፈፃፀሙን ሊከታተልም ይገባ ነበር። ሆኖም በአንድ ወቅት ጠ/ሚኒስትሩ አራሳቸው ለምነው በሚያመጡት ገንዘብ ማንም ሊጠይቃቸው እንደማይችል የፓርላማ አባላት ፊት ሲናገሩ ታዝበናል። ለመሆኑ ኢትዮጵያ እስካሁን ከኢሚሬቶች መንግስት ምን ያህል ገንዘብ አገኘች? ገንዘቡ በእርዳታ ነው ወይስ በብድር የተገኘው? ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግሌ ነው የለመንኩት ሲሉ በግላቸው ማን ናቸው? እነዚህ ጥያቄዎች መልስ ያሻቸዋል።
- የኢትዮ-ሶማሊላንድ ስምምነት:
ከቀይ ባህር 60 ኪሜ (37 miles) ርቀት ላይ ብቻ የምትገኘው አገራችን ኢትዮጵያ ከወደብ አልባ አገራት ተርታ መሰለፏ የሁሉም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ቁጭት ነው። በተለይም ታሪካዊውን የአሰብ ወደብ ያለአግባብ እንድታጣ የተደረገበት መንገድ ብዙዎችን አንገት አስደፍቷል። ይህንን ጠንቅቀው የሚያውቁት የአገሪቱ መሪ በሕዝብ ያጡትን ቅቡልነት መልሶ ለማግኘት ይሁን ለአጀንዳ ለማስቀየር ይህንኑ የውሃ አጀንዳ ወደ ፊት ያመጡት የዛሬ ዓመት ገደማ ነበር። ነገር ግን ማንም ኢትዮጵያዊ ባልገመተው መንገድ እንደ አገር እውቅናን ለማግኘት ከምትውተረተረው የሱማሌላንድ ግዛት ጋር በተፈረመ ስምምነት አገራችን የወደብ ባለቤት መሆኗን የሚያበስር ዜና በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት አሰራጩ። በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት አንዲት እንደ አገር እውቅና ያላገኘች አገር የሁለትዮሽ ስምምነት ለመፈረም የሚያስችል ችሎታ (international legal personality ) ስለሌላት ከማንም ልኡዋላዊ አገር ጋር የምታደርገው ማንኛውም ስምምነት ከመነሻው እንዳልተደረገ ይቆጠራል /void ab initio /(የVienna Convention on the Law of Treaties አንቀጽ 46) ። ሱማሌላንድም በዚህ ረገድ ሲታይ እንደ አገር የምትቆጠር ስላልሆነ ይህ የህግ ድንጋጌ ተፈፃሚ የማይሆንባት ምክንያት አይኖርም። ስምምነቱ አስገዳጅ ሳይሆን የመግባቢያ ሰነድ ብቻ ነው ቢባል እንኳን የአፈፃፀም ልዩነት ካልሆነ በቀር በችሎታ ደረጃ ውጤቱ ተመሳሳይ ነው።
የስምምነቱ ህጋዊነት አጠያያቂነት እንዳለ ሆኖ በውጤትም ደረጃ የኢትዮጵያ መንግስት ያሰበውን ያሳካ አይመስልም። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ቢያስገድድ እና ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠት ቢያስፈልግ እንኳ ጊዜ እና ሁኔታን ጠብቆ በጥልቀት የሁኔታዎችን ግምግማ ጥናት ላይ ተመስርቶና አስፈላጊውን ሁሉ ቅድመ ዝግጅት አድርጎ የሚገባበት እንጂ ተዘሎ የሚገባበት አልነበረም።

በተለይም አሁን አገራችን በምትገኝበት እጅግ የተመሰቃቀለ ውስጣዊ ሁኔታ ይህንን ውሳኔ መወሰን እንዝላልንት ነው::
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምም አደጋ ላይ የሚጥል እንጂ የሚያስከብር እንደማይሆን እሙን ነበር:: ሄዶ ሄዶ እንዳየነው የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም የGCC እና የአረብ ሊግ አባላት ስምምነቱን ከመነሻው ነበር የተቃወሙት። መንግስት ከሱማሊያም ጋር የተካረረ አለመግባባት ውስጥ ገባ።
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ውግዘትን አስተናገደ ። በመጨረሻም በቱርክ አንካራ በብዙ ጫና የሱማሊያን ግዛታዊ አንድነት ለማክበርና አጨቃጫቂ ጉዳዮችን ላለማንሳት ተስማማ። ይህም ሱማሌላንድን እንደ አገር ለመቆጠር ከተፈራረመው የቀድሞ መግባቢያ ሰንድ ጋር በቀጥታ ስለሚቃረን የቀድሞውን ስምምነት ዋጋ አልባ ያደርገዋል።
(በነገራችን ላይ ቱርክ በሶማልያ የአገር ውስጥ ፖለቲካም የሶማልያን የማዕከላዊ መንግስት በመደገፍ የምትታወቅ እና ከሶማሊላንድ ጋርም በጥርጣሬ የተሞላ ግንኙነት ያላት አገር ናት)።
እነዚህ ከላይ ለማሳያነት ያነሳዃቸው አበይት ጉዳዮች የዲፕሎማሲያችን አሁናዊ ቁመና በትንሹም ቢሆን ያሳያሉ የሚል እምነት አለኝ። ትንሽ የዲፕሎማሲ ስህተት ትልቅ ብሔራዊ ጥቅም ያሳጣል። የብሔራዊ ጥቅም መነካት ደግሞ ወደ ለየለት ጦርነት ያስገባል።
በመሆኑም ኢትዮጵያ ተለዋዋጭ የሆነውን የቀጠናውን እና ዓለማቀፋዊ ሁኔታውን የዋጀ በሳል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መመስረት ከምን ጊዜውም በላይ ያሻታል። ተቋማት ከአደርባይ ካድሬዎች ይልቅ በሙያተኞች ይጠናከሩ ። መሪዎችም ቢያንስ ለአገርና ለስማቸው ሲሉ ሙያተኛን ይስሙ። ጉዳዩ የአገር ልኡዋላዊነትና ህልውና ነውና!
*** የፅሁፉ ባለቤት አቶ ቢንያም እሸቱ ናቸው። አቶ ቢንያም የቀድሞው የጠ/ሚር ልዩ ጽ/ቤት ባልደረባ የነበሩ ናቸው። ለአስተያየታቸው መሠረት ሚድያ ከፍ ያለ ምስጋና ያቀርባል።
በዚህ አጋጣሚ ለአቶ ቢንያም እሸቱ ምላሽ የሚሆን ወይም የተቃርኖ ሀሳብ ያለው የመንግስት ተቋምም ሆነ አመራር ካለ ፅሁፉን ለማስተናገድ በራችን ክፍት መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

አሁን ድረስ የቀጠለው በቦሌ አየር ማረፊያ መንገደኞች ላይ የሚፈፀሙ እንግልቶች እና የሙስና ተግባሮች
(መሠረት ሚድያ)- በቦሌ አየር ማረፊያ በኩል የሚገቡ እና የሚወጡ መንገደኞች ላይ የሚደርሱ እንግልቶች እና የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች እንደቀጠሉ ናቸው።
ለማሳያነት ለመሠረት ሚድያ የደረሰው የአንዲት መንገደኛ አዲስ አቤቱታ እንደሚያሳየው ህዳር 16/2017 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን በነበረ በረራ ተሳፋሪ የነበረች አንዲት መንገደኛ 400 ዶላር በግዴታ እንድትከፍል ተደርጋለች።
መንገደኛዋ የማታ በረራውን ለማድረግ በአየር ማረፊያው በተገኘችበት ወቅት የበረራ አስተባባሪዎቹ በግልፅ አራት መቶ ዶላር ካላመጣች መብረር እንደማትችል እንደነገሯት እና እሷን ከጉዞዋ ላለመስተጓጎል ክፍያውን እንደፈፀመች ታውቋል።
መንገደኛዋን ዶላሩን ካልከፈለች ልትታሰር እንደምትችል ሲነግሯት እርሷም "ምን አጥፍቼ ነው የምታሰረው?" ብላ ስትሞግት ምንም ሳይፈሩ "እናስርሻለን፣ ማንም አያድንሽም" እንዳሏት ታውቋል።
በመጨረሻም በረራው እንዳያመልጣት በመፍራትና ከህገወጥ እስር ለመዳን ስትል ከፍላ ወደ አሜሪካ መመለሷ ታውቋል።
በተመሳሳይ መልኩ የዛሬ አመት አንዲት ተጓዥ ወደ አየር ማረፊያ ለአሜሪካ ጉዞ በሄደችበት ወቅት "የያዝሽውን ብር እና ወርቅ አካፍዩን" ተብላ እንደነበር ማህበራዊ ሚድያ ላይ መረጃ መውጣቱን ተከትሎ በካሜራ የታገዘ ማጣራት ተደርጎ ሁለት የኤርፖርት ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም የመንገደኞች የቅሬታ ማቅረቢያ ስርዐት ተዘርግቶ ለችግሩ ተገቢው ትኩረት እንደተሰጠው ተገልጾ ነበር።
ጉዳዩ የውጭ ተጓዦችን ብቻ ሳይሆን አሁን አሁን የሀገር ውስጥ መንገደኞችንም እያጉላላ እንደሆነ መሠረት ሚድያ በቅርቡ ተመሳሳይ መረጃ ማቅረቡ ይታወሳል።
በቅርቡ በሰራነው አንድ ዘገባችን ከጎንደር የመጣ አንድ ተጓዥ አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ ተይዞ የጉቦ ገንዘብ አምጣ ተብሎ አልከፍልም በማለቱ ሁለት ቀን ኤርፖርት ግቢ ውስጥ ባለ አንድ ፖሊስ ጣብያ ታስሮ እንደተለቀቀ መረጃ አቅርበን ነበር።
በተያያዘ ዜና የኤርፖርት እና ድንበር አስተዳደር ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ስርዓት የትብብር ስምምነት ከአራት ቀን በፊት መፈረሙ ታውቋል። ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለውን ታላቅ ስምና ዝና ለማስቀጠል እንዲሁም የድንበር ደህንነትን ይበልጥ ለማሳደግ ያስችላል ተብሏል።
የስምምነቱ ዋነኛው ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ክብርና ዝና ማስቀጠል መሆኑ የተለፀ ሲሆን ይህም በቅርብ ጊዜያት አየር ማረፊያው ላይ የሚፈፀሙ የህገወጥ ድርጊቶች መበራከት አንዱ ምክንያት እንደሆነ ታውቋል።

የበርካታ ባለሐብቶች የባንክ ሂሳብ እየታገደ እንደሆነ ታወቀ
(መሠረት ሚድያ)- በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተሻለ ቢዝነስ ያንቀሳቅሳሉ የሚመባሉ የበርካታ ባለሐብቶች የባንክ ሂሳብ እየታገደ እንደሆነ ታውቋል።
እነዚህ በአብዛኛው የአማራ ተወላጅ የሆኑ ባለሀብቶች እየተመረጡ ተንቀሳቃሽ ሒሳባቸው በህግ እየታገደ ወይም Legal Restriction እየተደረገባቸው እንደሆነ የባንኮች ምንጮቻችን ተናግረዋል።
መሠረት ሚድያ ባደረገው ማጣራት በአማራ ክልል ከቀጠለው ግጭት ጋር በተያያዘ ለታጣቂዎች ድጋፍ ሊያደርጉ ይችላሉ የተባሉ ሁሉ 'ከላይ በመጣ ትእዛዝ) በሚል በጥርጣሬ ባንካቸው እየታገደባቸው ይገኛል።
ንግድ ባንክ ላይ ብቻ ቢያንስ 200 የሚሆኑ የእነዚህ ባለሀብቶች አካውንቶች እንደታገዱ ታውቋል፣ የግል ባንኮች ላይ በተመሳሳይ ቁጥራቸው ያልታወቀ እገዳዎች መደረጋቸው ታውቋል።
"አብዛኞቹ የፍርድ ቤት እግድ እንኳን የሌለባቸው ናቸው፣ በጥርጣሬ በሚል በርካታ አካውንቶች ተዘግተዋል" ያሉት ምንጫችን ሁኔታው የዛሬ ሶስት እና አራት አመት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት የትግራይ ባለሀብቶች ላይ ከተደረገው ጋር ተመሳሳይነት አለው ብለዋል።
ሚድያችን በዚህ ዙርያ አካውንታቸው የታገደባቸውን አንድ ነጋዴ እነጋግሯል።
"አካውንቱ መታገዱን የሰማሁት ከቢሮዬ ተደውሎ ክፍያ መፈፀም አልቻልንም ሲሉኝ ነው" የሚሉት እኚህ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ነጋዴ ወደ ንግድ ባንክ ሄደው ሲያጣሩ "ለግዜው እንቅስቃሴ እንዳያደርግ እግድ ተጥሎበታል ተባልኩ፣ ሌላው ቀርቶ በወረቀት ላይ የተፃፈ ማብራርያ ወይም ለእግዱ ማረጋገጫ አልሰጡኝም" በማለት አስረድተዋል።
በተመሳሳይ እርሳቸው የሚያውቋቸው የአራት የአማራ ተወላጅ የቢዝነስ ባለቤቶች አካውንታቸው እንደታገደባቸው እንደሰሙ ጠቅሰው ወንጀል ባልፈፀሙበት እና ክስ እንኳን ባልቀረበበት ጉዳይ ለ40 አመት የሰሩበትን የንግድ ስራ እንዲያቆሙ እንደተገደዱ ተናግረዋል።
በጉዳዩ ዙርያ ከብሄራዊ ባንክም ሆነ ከሌላ የመንግስት አካል የተሰጠ መግለጫም ሆነ ማብራርያ የለም።

"ብሄራችንን የሚጠይቅ ፎርም እንድንሞላ እየተገደድን ነው"--- የጂንካ ዩኒቨርስቲ መምህራኑ
(መሠረት ሚድያ)- የጂንካ ዩኒቨርስቲ መምህራኑ ብሔራቸውን የሚጠይቅ ፎርም እንዲሞሉ እያስገደደ መሆኑ ታወቀ።
መምህራኑ "አላማዉ ምነድን ነው?" ብለው ቢጠይቁም የሚነግራቸው አካል እንዳላገኙ ጠቁመው ፎርሙን መሙላት ደግሞ ግዴታ ነዉ መባሉን ተናግረዋል።
"እንደዚህ ሰዎችን በማንነት መለየት እጅግ አደገኛ ነገር ነው፣ አብዛኛው መምህርም ስጋት ገብቶታል" ብለው ለመሠረት ሚድያ አስተያየት የሰጡ አንድ የዩኒቨርስቲው መምህር ናቸው።
ዩኒቨርስቲው መምህራንን በብሄር መለየቱ በአካባቢው አልፎ አልፎ ግጭት ስለሚከሰት ለጥቃት ሊያጋልጣቸው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል።
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ የሠራተኞች ድልድል ያረገ ሲሆን በአዲሱ የዩኒቨርስቲ አደረጃጀት ከፍተኛ ደረጃ ከያዙት መሀል ከዚህ በፊት በስፋት በሚድያዎች በተጋለጠው የተቋሙ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የነበሩ እንደሚገኙበት ታውቋል።