ሰው ከቦኛል መሰል ሰሞኑን ፅሁፍ መፅሃፉም ጠፍቶብኛል በእሬን አንስቼ ከወረቀት ጋር ሳገናኘው የያዝኩት ሀሳብ ሁሉ ወና ይሆናል ለእኔ ጽሁፎቼ የብቸኝነት ጓዶቼ ናቸው አንዳዱ በደስታ ሌላው በሀዘን ላይ ሲሆን ይፅፋል
የእኔ ጽሁፎች እኔ እና እኔ ስንገናኝ የተፃፉ ናቸው እኔ በደስታ ስካር አልፅፍም በሀዘን መሸንቆር ላይ ሆኜም አይደል በትውስት እየተነዳሁ ስላለፉት ደስታዎቼ ስላለፉት እንባዎቼ ቁጬ ብዬ ከብእሬ ጋር አወጋለሁ በዚች ከንቱ አለም ምን ያስፈራሃል ቢሉኝ ከወጀቡ ይልቅ ከጀርባው ያለነፋስ የምል ይመስለኛል ወጀቡን በአይኔ አየዋለሁ ነፋሱ ግን መቼና እንዴት እንደሚመጣ ሰለማላውቅ ጠርጎ ወስዶ አንዳች ነገር ላይ እንደሚከተኝ ስለማውቅ ያስፈራኛል።
አብረን አድገን አብረን ተምረን ያሳለፍናቸው ጓደኞቻችን ዛሬ ላይ የሉም አንድ ወንበር ላይ ተቀምጠን የቆጥ የቋጡን ስናወራ ፤ ስናወገ የነበርን ጓዶች አውሎ ነፋስ እንደ ወሰዳት እፉዬ ገላ ከእኛ በብዙ ማይል እርቀዋል ።
ዛሬ ላይ..... እንደቀልድ የተመላለስንባቸው መንገዶች ትዝታ ሆነው ቀርተው ዱካቸውን እንናፍቃለን ከቁም ነገር ያልቆጠርናቸው ንግግሮችን በትውስታ ማእበል ወስደው አጀብ ይሄንንም አውርተን ነበር ያሰኙናል...
ብቻ ግን ከነገ ዛሬ ይሻላል ።
✍S...M(ዘብስራት)

❤18🤝3🫡1
እንደዚህ ጠዋት በደህና አይተነው እንደ ጠዋት በሞት ያጣነው ሰው የለም? ያ ሰው ያን ቀን ከቤቱ ሲወጣ በምድር ላይ የመጨረሻ ቀን እንደሚሆን አልጠረጠረም ነበር።ማለዳ ከእንቅልፋችን ስንነቃ የሚሰማን ልበ ሙሉነት አለ።እንደሌላው እለት የምንኖር እንጂ የምንሞት አይመስለንም ግን ይሄ ቀን እንደ ትላንት ባይሆንስ?
የዲያቆን ኢዩኤል ሀብታሙ የጠዋት ቴክስት ከሁለት አመታት በፊት
የዲያቆን ኢዩኤል ሀብታሙ የጠዋት ቴክስት ከሁለት አመታት በፊት
❤20😢11
መጥፎ ቀን ጥሩ ቀን የሚባል ነገር የለም።ያለው ጸሎት አድርገህ የወጣህበት ቀን እና ጸሎት ሳታደርግ የወጣህበት ቀን ነው። ያልጸለይክባቸው ቀናት በክፉ ምኞትና የሥጋ ፍላጎት የተሞሉ ስለሆኑ ክፉ ቀናት ናቸው።
ቅዱስ ቄርሎስ ሣድሳዊ
ቅዱስ ቄርሎስ ሣድሳዊ
❤31😍6🙏3❤🔥1
ሰላም ተወዳጆች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ✨እንደጠፋን እናውቃለን መስቀልም አይደል ትንሽ ያለንበት አካባቢ ለመስቀል በዓል busy ስለሚያደርግ ነው እግዚአብሔር ከረዳን ሰኞ ምን ይመሰል እንደነበረ በፎቶ እናሳያችኋለን 😊
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን✨
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን✨
❤15🙏10
አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ። አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤
ስለዚህ በድፍረት። ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል? እንላለን።
ዕብራውያን 13:5_6
ስለዚህ በድፍረት። ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል? እንላለን።
ዕብራውያን 13:5_6
❤15❤🔥5🥰2
“ለብቻ መሆን ፈልጋችሁ አታውቁም? ለአንድ ለሁለት አመት ብቻ በር ዘግቶ መቀመጥ በስውር መጨነቅ የተረዳች መስላ ሳታበቃ ችግራችሁን ምትንቅ አለውላችሁ ያለ አፏ ሳይዘጋ ተስፋ የሰጠ ምላሷ ሳይመለስ መልሳ ማናችሁ እናንተ ምትል ይቺ ከንቱ አለም ላይ ጀርባችሁን መስጠት የራስን ችግር ከራስም ከአምላክም ጋር ማውጋት ወረቀት ላይ በብዕር ማፍሰስ አያሻችሁም? ውሃ ዳር ሄደን መተከዝስ አያስፈልገንም? ነፋሳቱ የነፍሳችንን ዕድፍ ይዘው እንዲበኑ ዕድል ልንሰጣቸው አይገባም?”
#eyuelhab_morning_text_two_years.....
#eyuelhab_morning_text_two_years.....
❤20😇5❤🔥4
በዚህ አያበቃም! የተሰበረው ይጠገናል አይሆንም ያልነው ይሆናል ! ለውድቀት አይደለም የተሰራነው........ ጠብቁ😊
#eyuelhab_morning_text_two
#eyuelhab_morning_text_two
❤31
እመኑኝ፤ እግዚአብሔር ለአደጋ የተጋለጥንባቸውንና እርሱም ከእነርሱ የጠበቀንን አደጋዎች ቢገልጥልን ኖሮ፣ ሙሉ ሕይወታችን ለእርሱ ምስጋና ለማቅረብ ባልበቃ ነበር።"
አቡነ ሺኖዳ
አቡነ ሺኖዳ
❤28❤🔥8
“ከልቦቻችን በማይነቀሉ የፍቅሩ ችንካሮች ተቸነከርን:: ያዝነው አንለቀውም እርሱም አቀፈን አልተወንም:: ወደ እርሱ በሃይማኖት አቀረበን:: ከእርሱም ወደ ቀኝ ወደ ግራ አንሸሽም:: እንደ ቀለበት በልባችን እንደ ማኅተም በክንዳችን አኖርነው:: እንደ ዕንቁ በልባችን ሳጥን አስቀመጥነው:: እንደ ወርቅ በሕሊናችን መዝገብ አኖርነው::
እንደ ግምጃ ለበስነው:: እንደ ሐር ግምጃ ተጎናጸፍነው:: እንደ ወታደር ሰይፍ ታጠቅነው:: ለጦር ዕቃ እንደተዘጋጀ የድል ጋሻ ተደገፍነው:: ተከዜና ግዮን በኢሎል ወር እንደሚሞሉ ፍቅሩ በልባችን መልቶአል:: እንደ መከር ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ እንደ ክረምት ጊዜም የጤግሮስ ወንዝ ስንዴ ሲያሹት እንደሚሆን እንደ ኤፍራጥስ ወንዝ ልባችንን በወንጌል ፈሳሽነት አረሰረሰው:: መርከባችንንም በሃይማኖት ወንዝ አስዋኘው"
ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
መጽሐፈ ምሥጢር 24:20

❤11❤🔥6🔥3👍1
በዚህ ሰአት የሆነ ሰው የሆነ ሆስፒታል አልጋ ላይ ሆኖ እንደእናንተ እንዲያደርገው እየጸለየ ነው
ስላለንበት ሁኔታ ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን🙏
#eyuelhab_morning_text_two_years_ago
ስላለንበት ሁኔታ ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን🙏
#eyuelhab_morning_text_two_years_ago
🙏28❤🔥13❤9😢4
“ደህና ነን… ግን ደህና አይደለንም።
ደህና አይደለንም… ግን ደህና ነን።
እየወጋ ይሰፋናል…
እየገደለ ያድነናል።”
ልባችን በክርስቶስ እስኪያርፍ ድረስ፣ በእነዚህ ከፍታና ዝቅታዎች ውስጥ መጓዛችንን እንቀጥል🙏
ደህና አይደለንም… ግን ደህና ነን።
እየወጋ ይሰፋናል…
እየገደለ ያድነናል።”
ልባችን በክርስቶስ እስኪያርፍ ድረስ፣ በእነዚህ ከፍታና ዝቅታዎች ውስጥ መጓዛችንን እንቀጥል🙏
❤32😢4🙏3🤝1
ሰዎች አንተ እኔን በምታውቅበት ልክ ቢያውቁኝ ኖሮ በፊቴ አንድስ እንኳን የሚቆም ባልተገኘ ነበር። አንተ ግን እያወከኝ የፍቅርህ መጠን አልቀነሰብኝም።
ክርስቶስ❤️🩹
#eyuelhab_Morning_text...
ክርስቶስ❤️🩹
#eyuelhab_Morning_text...
❤29😢12❤🔥5
+ እኔ ግን እኔ አይደለሁም +
አውግስጢኖስ ፈጣሪ የለም ባይ እና በዝሙት የተበላሸ ሕይወት ይኖር የነበረ ሰው ነው:: በቅዱስ አምብሮስ ስብከት ከተመለሰ ቡኋላ ግን ይህ ሰው ፍጹም በንስሓ ተለውጦ በምንኩስና መንገድ ሔዶ እስከ ጵጵስና ደረሰ:: ይህንን የንስሐ ሕይወት መኖር ከጀመረ ቡኋላ ቀድሞ በአመንዝራነት ሕይወት ሲኖር ወዳጁ የነበረች አንዲት ሴት መንገድ ላይ ከሩቅ አይታ ተከትላ ጠራችው::
ወደ ቀድሞ ትዝታውና ኃጢአቱ መመለስ ያልፈለገው ይህ አባትም ጥሪዋን
እንዳልሰማ ሆኖ በፍጥነት መሔድ ጀመረ::
ይህች ሴትም እየሳቀች :-
አውግስጢኖስ እኔ እኮ ነኝ! ብላ ጮኸች
እርሱም ወደ እርስዋ ዞሮ :-
''እኔ ግን እኔ አይደለሁም'' አላት።
ከክርስቶስ የምትለየን ኃጢአት ላይ ❝እኔ ግን እኔ አይደለሁም❞ ብለን እናልፋት ዘንድ እርሱ ጸጋውን ያድለን።

❤20😢6🔥5❤🔥1
"እግዚአብሔርን አንዲት ነገር
ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ
በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥
እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።" መዝ 27:4
ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ
በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥
እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።" መዝ 27:4
❤25❤🔥5
ሰው ህይወት ነው። ሰው ነፍስ ነው ሰው ፍቅር ነው ሰው ሰማይም ምድርም ነው። ሰው ብርሃን.... ሰው ጨለማም ነው። ያለ ሰው ትርጉም ያለው ሕይወት የለም። እንዋደድ ልክ እርሱ እንደወደደን 😊
#eyuelhab_Morning_text_twoyears_ago
#eyuelhab_Morning_text_twoyears_ago
❤8❤🔥6