መንፈሳዊ ትምህርት ዘኦርቶዶክስ
11.1K subscribers
424 photos
2 videos
3 files
231 links
"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16

"ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ

🕯ነፍሳችንን የሚያለመልመውን ቃለ እግዚአብሔር እንማማር።

ምንም አይነት ሀሳብ፣ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካላቹ @hasabebot ላይ መላክ ትችላላችሁ።
@ty1921
Download Telegram
26  ከእናንተ የመጣ ጥያቄ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
            
             ጥያቄ ?
እስኪ ስለ ተክሊል
ጋብቻ  ማለትም በ ተክሊል ለማግባት ከ ሁለቱም ፆታ ማድረግ የሚጠበቁባቸው ነገሮች , እንዲሁም ከ ጋብቻ በዃላ ምን ማድረግ እንዳለባቸው  በጥቅሉ ዘርዘር እንድታደርጉልኝ በ እግዚአብሔር ስም እጠይቃለው🙏🙏

            መልስ
✳️ሥርዓተ ተክሊል

➡️ተክሊል የሚፈጸመው ንጽሕናዋን ጠብቃ ከወንድ እርቃ ለኖረች ጥብቅ ልጃገረድ ወይም በሥጋ ድንግልናዋን ለጠበቀች በተግባር ዝሙት ላልፈጸመች ኦርቶዶክሳዊ ሴት ነው። ሴትን በምንጣፍ ተገናኝቶ የማያውቅ ንጽሕናውን ጠብቆ ልኖር ኦርቶዶክሳዊ ወንድ ብቻ የሚፈጸም የጋብቻ መፈጸሚያ አይነት ነው፡፡ በአጠቃላይ ተክሊል ከሥጋዊ ድንግል ጋር አብሮ የሚሄድ ምሥጢር መሆኑን ቤተ ክርስቲያን የሥርዓት መጽሐፍቶች ሁሉ ተባብረው የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው። ለምሳሌ ፍትሃ ነገስት እንዲህ ይላል ፦ "ይህ ተክሊል በጋብቻ ጊዜ ለድንግል ወንድና ለድንግል ሴት ይገባል።" ፍትሃ ነገስት 24:906

✳️ለተክሊል ጋብቻ መሟላት ያለባቸዉ ዋና ዋና መስፈርቶች ምንድን ናቸው

            ዕድሜ

➡️የሚጋቡት ወጣቶች ዕድሜአቸው ትዳር የሚጠብቀውን ሓላፊነት ለመወጣት ብቁ ሊሆኑ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም አስቀድሞ በፍትሐ ነገሥት እንደተገለጠው ሴቷ 15 ወንዱ ደግሞ 18 ዓመት የሞላቸው መሆን አለባቸው፡፡ እንደዚህም ሆኖ ሌሎች ነገሮች ካልተሟሉ ከዚህ በላይ ቢሆን መልካም ነው፡፡

የአእምሮም ሆነ የአካላዊ ብቃት፡-

➡️የሚጋቡት ወጣቶች በአእምሮም ጤነኛ ቢሆኑ አካላቸውም ከጋብቻ በኋላ ለሚፈጸመው የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወይም ከሥነ ልቡናዊ ችግር የተነሣ የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም ባይችል የቀረውን ወገን ወደ ሌላ ኃጢአት ይገፋፋልና የግድ አካላዊ ብቃት ሊኖር ያስፈልጋል፡፡ የአእምሮ ሁኔታም በትዳር የሚጠበቅበት ሓላፊነት ወይም ቤተሰብ የማስተዳደር ብቃት ሊኖር ያስፈልጋል፡፡

        የኢኮኖሚ አቅም፡-

➡️የሁለቱም ተጋቢዎች ወይም ከሁለት አንደኛው ወገን ራሱን የቻለ ሊሆን ያስፈልጋል፡፡ የኢኮኖሚ ዐቅማቸው ቤተሰቡን ለማስተዳደር በቂ መሆኑ ሊረጋገጥም ይገባል፡፡ በርግጥ ይህ ሁልጊዜ ላይሆን ይችላል፤ ፍቅር ካላቸው ሁለቱም ሠርተው ሊያፈሩ ይችላሉና፡፡

       ስለ ትዳር ማወቅ:-

➡️ተጋቢዎች ከመጋባታቸው በፊት ስለ ትዳር በአጠቃላይም ስለተክሊል ጋብቻ በሚገባ ሊያውቁ ያስፈልጋል፡፡ ትዳር በሌላ በሦስተኛ ሰው ግፊት የሚፈጸም ወይም ሌላው ስላደረገው ብቻ እስቲ ልሞክረው ተብሎ የሚገባበት ሕይወት አይደለም፡፡ ስለዚህ ከገቡበት በኋላ እንዳይቸገሩ ወጣቶች የትዳርን ምንነት አስቀድመው ሊያውቁ ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ስለ ሥርዐተ ተክሊል አስቀድመው በንስሐ አባታቸው ወይም ሰንበት ት/ቤታቸው ሊማሩ ይገባል፡፡

የንስሐ አባት ምስክርነት:-

➡️ሥርዐተ ተክሊል የሚፈጸምላቸው ወጣቶች አስቀደሙው ንስሐ እየገቡ ንጽሕናቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ የግድ የንስሐ አባት ሊይዙ ያስፈልጋል፡፡ ለንስሐ አባታቸውም ስለጋብቻቸውም ሆነ ስለማንኛውም ሕይወታቸው ሊያማክሩ ይገባል፡፡ በዘመናችን አልፎ አልፎ እንደሚታየው ገንዘብ ከፍዬ ወይም ወደማልታወቅበት ቦታ ሔጄ አገባለሁ እያሉ ተደብቆ ሥርዐተ ተክሊልን መፈጸም አይቻልም፡፡ ተጋቢዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማሟላታቸው በንስሐ አባታቸው ሊረጋገጥና ይህም ሊመሰከርላቸው ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም የተጋቢዎቹ መንፈሳዊም ሆነ ሥጋዊ ኑሮ በንስሐ አባታቸው ፊት የተገለጠ ሊሆን ይገባል፡፡

✳️እንግዲህ ተጋቢዎች እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች ካሟሉ የተቀደሰው የሥርዐተ ተክሊል ጋብቻ ሊፈጸምላቸው ይቻላል፡፡ በተረፈ ሥርዐተ ተክሊል ከአጽዋማት ቀናት በስተ ቀር በማንኛውም ቀን ሊፈጸም ይችላል፡፡ ሥርዐተ ተክሊልን ለመፈጸም ወሳኙ ነገር የቀናቱ መለያየት ሳይሆን የተጋቢዎቹ ማንነት ነው፡፡


‹‹መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፡፡ለመኝታውም ርኩሰት የለውም ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል፡፡ ›› ዕብ ም፥፲፫ ቑ፥፬

           @menefesawinet
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
#ሆሳዕና_ማለት_ምን_ማለት_ነው ??
#በሆሳዕና_ለምን_ቀለበት_እናስራለን ?
#በሆሳዕና_ጌታችን_ለምን_በአህያ_ላይ_ተቀመጠ
#በሆሳዕና_ለምን_ዘንባባ_አነጠፉ ?
................................................................

=> ሆሳዕና ማለት ምን ማለት ነው ?

ሆሳዕና ማለት፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::

=> በሆሣዕና ዕለት በእጃችን እደ ቀለበት ማሰራችን የምን ምሳሌ ነው ?

1.ጌታ ለአዳም የሰጠው ቃል ኪዳን ለማስታወስ፡-ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድነሃለሁ ያለውን የተስፋ ቃል ለማስታወስ፡፡
2.ጌታ ለእመቤታችን የገባላትን ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
3.ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
4.ጌታ ለአዳም ከሰይጣን ግዛት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም ከሰይጣን ግዛት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከኃጢአት አውጣን ማረን ለንስኃ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን ስንል ለጌታ ዳግም ላናጠፋ ቃል የምንገባበት ነው፡፡
=> ጌታችን በዕለተ ሆሳዕና ለምን በፈረስ ላይ አልተቀመጠም ?
ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ "
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ
ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።(ትንቢተ ዘካርያስ 9:9)

=> በአህያ መቀመጡ፦
👉 ትህትናን ለማስተማር
👉 የሰላም ዘመን ነው ሲል
👉 ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና በየዋህነት ለሚኖሩ ምዕመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል፡፡
👉 አህያዎች ትሁታን ናቸው ረጋ ብለው ነው
የሚሄዱት፤በቀላሉ ትወጣበታለህ፤በቀላሉ
ትይዘዋለህ፤እንደፈለክም ታዝዋለህ
=> ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ዘባባ የመነጠፉ ሚስጢር የምን ምሳሌ ነው ?
1.ዝንባባ፡- ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ ደስ ብሎት አብርሃም ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔር አመስግነዋል፡፡
2.ዝንባባ ደርቆ እንደገና ሂይወት ይዘራል፡- የደረቀ የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
3.ዝንባባ የሰላም ምልክት ነው፡- የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
4.ዝንባባ የደስታ መግለጫ ነው፡- አንተ ደስ የምታሰኝ ሃዘናችንም የምታርቅልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
5.ዝንባባ እሾሃማ ነው፡- አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
6.ዝንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጂ፡፡ ጌታም አንተ ባህሪህን የማይመረመር ነው ሲሉ ነው፡
ህዝቡ ከልብሳቸው ሌላ ስንት አይነት ቅጠል አነጠፉለት ምን ምን ?
=> ልብሳቸውን ማንጠፋቸው፡-
ለክብሩ መግለጫ ነው፡፡
ሌሎችም ሦስት አይነት ቅጠል አነጠፉለት ዘንባባ፤የቴመር ዛፍ፤የወይራ ዛፍ አነጠፉለት፡
=> ትልቅዋ አህያ በምን ትመሳለለች ውርን ጭለዋስ ?
ትልቅዋ አህያ የኦሪት ምሳሌ ነው።
1.ትልቅዋ አህያ ሸክም የለመደች ናት ህገ ኦሪትም የተለመደች ህግ ናትና፡፡
2.የእስራኤል ምሳሌ ነው፡-ትልቅዋ አህያ ሸክም እንደለመደች ሁሉ እስራኤልም ህግ ለመፈጸም በህግ ለመራመድ የለመዱ ናቸው፡፡
3.የአዳም ምሳሌ ነው፡- አዳም ሸክም የበዛበት ነበርና።

ውርጭላዋ
1.በህገ ወንጌል ትመሰላለች፡-ምክንያቱም ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ የመሰረታት የሰራት አዲስዋ ህግ ናትና፡፡
2.በአህዛብ ትመሰላለች፡-ትንሽዋ አህያ ሸክም የለመደች አይደለችም እንዲሁም አህዛብም ህግህን የመቀበል የመቀበል የለመደ አይደሉም፡፡ ለህግህ አዲስ ናቸውና፡፡
3.የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡- የዓለም ሸክም አቅልላለችና በእመቤታችን ትመሰለላለች፡፡ እመቤታችን ድህነተ ምክንያታችን ጌታን የተሸከመች ንጽህት እንከን የሌላት እናት ናትና
@menefesawinet
🌿🌿🌿🌼🌼🌼🌿🌿🌿🌼🌼🌼
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ. አሜን
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
                            ሰሙነ ሕማማት
        "ሰሙነ" ማለት 'ሰመነ' (ሳምንት) ሳምንት አደረገ ማለት ነው።ይሔውም ከዕለተ ሆሳዕና ሰርክ እስከ ትንሣኤ ሌሊት ያለውን ጊዜ እና ቀናት የሚያመለክት ነው።
       "ሕማማት" የሚለው ቃሉ 'ሐመ፣ታመመ' ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን 'ትኩሳት ፣ንዳድ ፣በሽታዎች ፣ኅዘናት፣ ጭንቀቶች ፣መከራዎች ፣ዋይታዎች' የሚሉ ትርጉሞችን ይሠጣል።
        በመጽሐፍ ቅዱስ የመድኃኔዓለም ክርስቶስን መከራዎች ለመግለጽ 'ሕማማት' የሚለው ቃል ተጠቅሞ የምናገኝው ቅዱስ ሉቃስ ሲሆን 'በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ አሳያቸው።(ሐዋ 6፥3) ሲል እናገኝዋለን። ሕማማት የሚለው ቃል 'በሽታን' የሚገልጽ አሳብ ቢኖረውም መድኃኔዓለም ክርስቶስ ግን የታመመው በስጋ በሽታ ሳይሆን በመከራ ብቻ ነው። ስለዚህ ከትንሣኤ በፊት ያለው ሳምንት "ሰሙነ ሕማማት" ይባላል። ሳምንቱ የጌታችን ሕማሙና ሞቱ ይዘከርበታል።
         ቤተ ክርስቲያናችን በዕለተ ዓርብ 'ነአምን ነአምን ነአምን ሕማሞ ለዘኢየሐምም' 'የማይታመመውን የእርሱን ሕማሙን እናምናለን እናምናለን እናምናለን' እያለች እያዜመች እንደምትሰግደው 'ሕማማት' ስንል መድኃኔዓለም ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ሲል በፈቃዱ የተቀበለውን እንግልት ፣ድብደባ ፣መውደቅ መነሳት ፣የእሾህ አክሊል መድፋት ፣ግርፋት ፣ችንካርና መስቀሉን ማለታችን ነው።
          መከራው ከመከራ የዳንበት ፣ሞቱም ሕይወትን ያገኘንበት በመሆኑ በትንሣኤውና በዕርገቱ ተጽናንተን የምንዘነጋው ፤በምጽአቱ ተስፋ ተሞልተን የምንረሳው አይደለም ። <ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ> የተባልነውን ይዘን "ንዜኑ ሞትከ እግዚኦ"(አቤቱ ሞትህን እናገራለው) እያልን ዘወትር የምቀድሰው ነው።1ቆሮ 11፥26
           በተጨማሪም ከአዳም እስከ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያሉ ነፍሳት በሲኦል የቆዩበት 5500 የመከራ ፣የፍዳና የኩነኔ ዘመን የሚታሰብበት ነው። ይህ ሳምንት ቅዱስ የመጨረሻ ሳምንት ተብሎ ይጠራል። በዚህ ሳምንት ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ አይቀደስም ፣ስብሐት ነግህ አይደረስም ፣ጸሎተ ፍትሐትና አስተሰርዮም አይደረግም ፣ጥምቀተ ክርስትናም አይፈጸምም ፣ክብረ በዓል በዚህ ሳምንት ቢውል ከትንሣኤ በኋላ እንዲውል ይተላለፋል ፣መስቀል እንደማይሳለሙት ሁሉ መጨባበጥ (መሳሳም፣የትከሻ ሰላምታ) መለዋወጥ አይፈጸምም።

                     <<ሰሙነ ህማማት ሰኞ>>
"መርገመ በለስ ወይም አንጽሆተ ቤተ መቅደስ"
ጌታችን በሆሳዕና ዕለት ቢታንያ በምትባል መንደር ያድራል፤ በማግስቱም ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ፡፡ (ማር 11፡11-14) ቅጠል ያላትን በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ‹‹ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ፡፡›› ብሎ ረገማት፡፡ በዚህ ምክንያት ይህ ዕለት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፡፡ ይህ ታሪክ ውስጡ ምስጢር አለው፡፡
"በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፡፡"፦
ጌታችን ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈለገ፤ አላገኘም፡፡ እስራኤልን ሕዝበ እግዚአብሔር መባልን እንጂ፣ ነቢይነት፣ ካህንነት፣ መሥዋዕት አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡ በመርገሙ ምክንያት ትንቢት፣  ክህነት፣ መሥዋዕት ከቤተ እስራኤል ጠፉ፡፡
"በለስ ኦሪት ናት"፦ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ‹‹ኦሪትና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽር አልመጣሁም፡፡›› በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና ፍሬ ባንቺ አይሁን አላት፤ ድኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡ በአዲስ ኪዳን የድኅነት ዘመንም ተተካች፡፡
"በለስ ኃጢአት ናት"፦
የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነ ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ ‹‹በአንቺ ፍሬ አይገኝ›› ማለቱም ‹‹በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር›› ማለት ነው፡፡ በለሷም ስትረገም ፈጥና መድረቋ፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው ፡፡
ከዚህ ቀጥሎ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተመቅደስ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ‹‹ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች… እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት›› ማቴ 21፡13 ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው ፣ ገርፎም አስወጣቸው፣ ይህም የሚያሳየው ማደርያ ቤቱ የነበርን እኛ የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እነዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ አንጽሖተ ቤተመቅደስ የተፈጸመበት ሰኞም ይባላል ።                            
ሥርዓተ ስግደት ዘሰኑይ ነግህ
በነግህ ዲያቆኑ ጥቁር ልብስ ለብሶ መስቀል ይዞ ቃጭል እየመታ ቤተ ክርስቲያኑን ሦስት ጊዜ ዞሮ ሲመለስ መዝሙረ ዳዊት 150ው እና ነቢያት ያደገማል፡፡ መኃልየ መኃልይ ዘሶሎሞን አይደገምም ። ቀጥሎ የሰባቱ ቀን ውዳሴ ማርያም፣ አንቀጸ ብርሃን ይደገማል፡፡ መልክእ አይደገምም አቡነ ዘበሰማያት ይባላል፡፡
🌿🌿🌿🌼🌼🌼🌿🌿🌿🌼🌼🌼
< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

     #መልካም ቀን

  #ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@menefesawinet
+++ ሰሙነ ህማማትና ሚስጢራቱ +++

~ ከትንሳኤ በፊት ያለው ሳምንት ሰሙነ ህማማት ይባላል። ይኸውም በነቢዩ ኢሳይያስ ነሰአ ደዌነ ወፆረ ህማማነ፣ በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ በእርሱ ቁስል ዕኛ ተፈወስን። /ኢሳ 53:34-36/ ተብሎ በመንፈስ ቅዱስ ትንቢት የተነገረው ቃል ተፈጸመ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ሳምንት ውስጥ ለድኅነት ዓለም ሲል በአጭር ቁመት፣ በጠባብ ደረት ተወስኖ የተቀበለውን ጸዋትወ መከራ ለማስታወስ የወጣ ስያሜ ነው።

     1. በዚህ ሳምንት ውስጥ ያሉት ዕለታት ስያሜያቸውና በእያንዳንዳቸው ዕለታት የተፈጸሙትን ድርጊቶች እንደሚከተለው እንመለከታለን።

                             ሰኞ

       * አንጽሖተ ቤተ መቅደስና መርገም በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው። የሆሳዕና ዕለት ቢታንያ ያድራል። በማግስቱም ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ ወበሳኒታ ወፂኦ አምቢታንያ ርኀበ ወርእየ በለስ እምርኁቅ ወባቲ ቌጽለ ወሖረ ይርአይ እመቦ ዘይረክብ ፍሬ በውስቴታ ወበጺሖ ኀቤሃ አልቦ ዘረከበ ዘእንበለ ቁጽል ባህቲቱ እስመ ኢኮነ ጊዜሁ ለበለስ፣ ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ ዓይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳችም ፍሬ አላገኘባትም፤ ወአውሥአ ወይቤላ ለዓለም አልቦ ዘይበልዕ ፍሬ እምኔኪ እንከ፤ ከአሁን ጅምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። / ማር 11:11-12/

       *በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት። ፍሬ የተባለች ሃይማኖት ምግባር ናት። ከእስራኤል ፍቅርን ሃይማኖትን ምግባርን ፈለገ አላገኘም። እስራኤል ህዝበ እስራኤል መባል እንጂ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት። በመርገም ምክኒያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ድግ ሰው ጠፋባት።

    * አንድም በለስ ኦሪት ናት። በዚህ ዓለም ስፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት። እጸ በለስን ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት።

* አንድም በለስ ኃጢአት ናት። የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ኃጢአትም በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት። በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክኒያት ያገኘችን እዳ በደል በእርሱ ካሳነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው።

   * ከዚህ በኋላ ወደ ቤተመቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተጸሎት፣ ቤተመስዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተምስያጥ / የንግድ ቤት/  ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያግኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው።

    * በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምዕመናን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፣ በሰለስት፣በስድስት ሰዓትና በተሰዓቱ ሰዓት መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ። በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ። ምክንያቱም የደረሰበትን መከራ ኅዘኑንና /5500/ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ህይወት ይኖር እንደነበር ለማዘከር ነው።

                            #ማክሰኞ

    * የጥያቄ ቀን በመባል ይታወቃል። ምክንያቱም ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ ስልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና።

   * ጥያቄውም ከምድርልውያን ነገስታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታት በማን ስልጣን ታደርጋለህ ? የሚል ነበር

   ~ ይህንስ ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ። የየሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች ? ከሰማይ ወይስ ከሰው ? አላቸው። እነርሱም ከሰማይ ነው ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ? ይለናል። ከሰው ነው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፤ እንደ መምህርነቱም ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት። እርሱም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ እኔም አልነግራችሁም አላቸው። ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም። ልቦናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነው እንጂ። ከዚህ የምንማረው የእነሱን ክፉ ጠባይና ግብር መከተል እንደማይገባን ነው።

   * በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስም ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል። ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ፣ መክሮ መመለስ እንደሚገባ ሲያስተምር ነው።

                           #ረቡዕ

    * ይህ ዕለት የምክር ቀን ይባላል። ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጻሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር የጀመሩበት ቀን ስለሆነ ነው። በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር። ምክንያቱም ወቅቱ የፈሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት በመሆኑ ብዙውን ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱን የሚያደንቁ ስለነበር ሁከት እንዳይፈጥር ነው። በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል። /  ማቴ 26:1-5   ፤   ማር 14:1-2 /

    * የሐዲስ ኪዳን ካህናት ምእመናን በዚህ ዕለት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው ከእህልና ውኃ ተለይተው፣ መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው፣ የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ፣ ስለዚህ ታሪክ የሚይልወሳውንም በማንበብ እስከ ኮከብ መውጫ በጾም፤ በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ።

        ~ ይሁዳ ማለት ታማኝ ማለት ቢሆንም እንደ ስሙ ግብሩ አልተገናኘም። ስምና ግብሩ አልተባበረለትም። እኛስ እንደ ስማችን ይሆን ግብራችን ?

     * መልካም መዓዛ ያለው ቀንም ይባላል። ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ህይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት ከእንግዲህ በኃጢአት ተጎድቶ ይኖር የነበረውን ህይወቴን እደዚሁ መልካም ሽቶ ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የሞላ ሽቱ ይዞ በመሄድ በጠጉሩ /በራሱ/ ላይ በማርከፍከፍ ስላቀረበች ነው።

     * የእንባ ቀንም ይባላል። ይህም ይህችው ሴት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና።  /ማቴ 26:6-13  ፤  ማር 14:3-9   ፤  ዮሐ 12:1 /  ከዚህም እያንዳንዳችን ልንማር የሚገባን ነገር አለ። ይኸውም የራሳችንን ኃጢአት በማሰብ ማልቀስና የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብ ነው።
ይቀጥላል
@menefesawinet
1. ሕጽበተ እግር ይባላል።
ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው። ይህም የሚያሳየው የዓለምን ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው። ይህንን ለማስታወስ ዛሬ ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝቡን ኃጢአት እጠብ ሲሉ ሲሉ በቤተ ክርስቲያናችን የተገኙትን ምእመናን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ሲያጥቡ ያረፍዳሉ። / ዮሐ. 13:4-15/

       2. የጸሎት ሐሙስ ይባላል።
የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ የሚደክም ሥጋን የተዋሐደ አምላክ ፍፁም ሰው መሆኑን ለመግለጽና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ በጌቴሴማኒ ሲጸልይ በመቆየቱ ነው /ማቴ 26:36  ፤  ዮሐ 17:1/

    3. የምስጢር ቀንም ይባላል።
ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ በዚህ ዕለት ተመስርቷል። ይኸውም ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ስጋዬ ነው፤ እንካችሁ ብሉ ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል ላይ የሚፈስ ደሜ ነው፤ ከእርሱም ጠጡ በማለት እኛ ከእርሱ ጋር አንድ የምንሆንበትን መንገድ ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው።

       ~ በዚህ ዕለት ቅዳሴ ይቀደሳል። የሚቀደሰውን በለሆሳስ /በዝግታ/ ሲሆን እንደ ቃጭል በመሆን የሚያገለግለውም ጽናጽል ነው። ይህም አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ ሲመጡ ድምፃቸውን ዝግ አድርገው በለሆሳስ እየተነጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ ነው።

    ~ በቅዳሴውም ኑዛዜ አይደረግም። ሥርአተ ቁርባን ግን ይፈጸምበታል። ይህም ጌታችን የሰጠውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ለማሰብ ነው። በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሀ ታጥቦ ተዘጋጅቶ ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ይኖርበታል።

    4. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።
ምክንያቱም መስዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንሰሳ ደም የሚቀርበው መስዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኀነቱ ዓለም ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው። /ሉቃ 22:18-20/ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው ደሜ የሚሆን የአዲስ ኪዳን ነው። ከእርሱም ጠጡ በማለቱ ይታወቃል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት መሆኑን በማሰብ የቃል ኪዳኑ ፈጻሚዎች ጠባቂዎች መሆን እንደሚገባን እንማራለን።

       5. የነጻነት ሐሙስ ይባላል።
ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፤ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው። ራሱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ ነፃነት ሲናገር ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆቼ ግን ብያችኋለሁ በማለቱ /ዮሐ 15:15/ ከባርነት ነፃ የወጣንበት ቀን መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል። ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከኃጢአት ባርነት በመራቅ ከእግዚአብሔር ሕይወቱን በቅድስና መምርልት ይኖርበታል። እርሱ ጠላቶቹ ስንሆን ወዳጆቹ አድርጎናል። /ማቴ 26:17-19/

     6. አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአትክልት ቦታ ስለ ጸለየ።

                        #ዕለተ_ዓርብ

     * የስቅለት ቀን ስቅለት፣ መስቀል፣ አሰቃቀል ማለት ነው። መስቀል በቁሙ መስቀያ፣ መመዘኛ፣ መሰቀያ፣ መንጠልጠያ፣ ለሞት የሚያበቃ መከራ በማር 8:34 ወጸውዖሙ ለሕዝብ ምስል አርዳኢሁ ወይቤሎሙ ዘይፈቅድ ይፀመደኒ ይጽልአ ለነፍሱ ወያጥብዕ ወይፁር መስቀለ ሞቱ ወይትለወኒ፤ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ሕዝቡን ጠርቶ እንዲህ አላቸው። ሊከተለኝ የሚወድ ሰው ራሱን ይካድ፤ ጨክኖም የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ ይላል።

    * ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በ /1ኛ ቆሮ. 1:17/  ላይ ወኢኮነ በጥበበ ነገር ከመ ኢንስዐር፤ መስቀሉ ለክርስቶስ የክርስቶስን መስቀሉን ከንቱ እንዳናደርግ ነገርን በማራቀቅ አይደለም ይላል።

    * ጌታችን በተሰቀለ ዕለት ከስድስት ሰዓት ጅምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ። /ፀሐይ ጨለመ/ ፣ እንሆም የቤተ መቅደስ መጋረጃም ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፤ ምድርም ተናወጠች፤ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤ መቃብሮችም ተከፈቱ፤ ተኝተውም ከነበሩት ቅዱሳን ብዙዎች ተነሱ፤ ከትንሳኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ለብዙዎች ታዩ። /ማቴ 27:51/

      * ጌታችን ለዓለሙ ያሰበውን ቤዛነት ሊፈጽም በመስቀል ላይ መሰቀሉ የሚታሰብበት ነውና ለስቅለቱ መታሰቢያ የሚሆን አጎበር ተዘጋጅቶ ከርቤ እየታጠነ ስቅለቱን የሚመለከት ምንባባት ሲነበብና ሲሰገድ ይዋላል። የሰው ልጅ በሙሉ በእግረ አጋንንት ተረግጦ ከፈጣሪው ተጣልቶ ለ5500 ዘመን በጨለማ መኖሩን ለማስታወስም መንበሩ ታቦቱ በዚህ ቀን በጥቁር ልብስ ይሸፈናሉ። ዲያቆኑም በቤተ ክርስቲያን በመዞር የሚያሰማው የቃጭል ድምጽ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለቅሶ አንድም ዋይ ዋይ እያሉ የተከተሉት የኢየሩሳሌም ሴቶችን ሙሾም ምሳሌ ነው። /ሉቃ 23:31/

      * በዕለተ አርብ ነፍሳት ከሲኦል ወጡ። አንቀጸ ገነት ተከፈተልን፣ ርስተ መንግስተ ሰማያት ተመለሰችልን፣ አባታችን አዳምም ከፈጣሪው ጋር ታረቀልን በማለት ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሳኤሁ አግሃዶ እያልን የተድላ፣ የደስታ ምልክት ወይም መገለጫ የሆነ ልምላሜ ያለውን ቆጽለ ሆሳዕና ወይም ቄጤማ ግጫ ይዘን የምስራች እንባባላለን። /ኤፌ. 2:15-15/ ወዘእንበለ ምሳሌሰ ኢተናግሮሙ፣ ያለ ምሳሌ አልተናገረምና እንዳለ /ማቴ 13:34-35/ በኖኀ ጊዜም ርግብ ሐጸ ማየ አይኀ፣ ነትገ ማየ አይኅ፣ የጥፋት ውኃ ጎደለ፣ አለቀ እያለች ቅጠል ዕፅ ዘይት ይዛ ለኖኀ አብስራዋለች። /ዘፍ 8:8-11/

   * ርግብ የካህናት፣ ኖኀ የምእመናን፣  ኖኀ እጁን ዘርግቶ ርግብን እንደተቀበላት ካህናትም በየመንደሩ እየዞሩ ክርስቶስ ተመረመረ ዲያብሎስ ታሰረ በማለት ቄጤማ ሲያድሉ ምእመናንም እጃቸውን ዘርግተው መቀበላቸው የዚህ ምሳሌ ነው። ስለዚህ አሁንም ቢገኝ የወይራ ልምላሜ ቢታጣ ግጫን እየታደልን የምስራች መባባላችን ነፍሳት ከሲኦል ለመውጣታቸው መታሰቢያ ነው። ይህን ቅጠል ልምላሜ ይዞ ተድላ፣ ደስታ መግለጽ ከጥንት ጀምሮ ሲያያዝ የመጣ ነው እንጂ እንግዳ ነገር አይደለም። ለዚህ በመጀመሪያዪቱ ቀን ከበጎ እንጨት ፍሬን የሰሌንና የተምር ዛፍ ልምላሜ ይዛችሁ በየ አመቱ ሰባት ቀን ተድላ፣ ደስታ ታደርጋላችሁ ብሏል /ዘሌ. 23:40-44/።
~~
   

            2. በሰሙነ ሕማማት ጊዜ ቤተክርቲያናችን የምታደርገው ትውፊት/ የሐዋ.ሥራ 1:13/

  * ከሆሳዕና እስከ ቅዳሜ ሥዑር ያሉት ዕለታት የዓመተ ፍዳ መታሰቢያ ናቸው። ጸሎተ ፍትሐት አይደረግም። በዚህ ሳምንት ውስጥ ለሚሞቱ ምዕመናን እግዚኦ ሕያዋን ይደገማልና። በሰሙነ ሕማማት መስቀል የለም። ስምንቱ የዘመነ ኦሪት ምሳሌ ስለሆነ እርስ በእራስ መሳሳም፣ ሰላም መባባልና መልክዐ መልክዕ መድገም የለም። ይኸውም ይሁዳ ክርስቶስን በሰላምታ ስላስያዘው እርሱን ላለመምሰል። /ማቴ 26/
* በዚህ ሳምንት ብሉያትና ሐዲሳት መጻሕፍት ከጠዋት እስከ ማታ ይነበባሉ። የአምላኮ ስግደት ይሰገዳል። ይኸውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ሲል መስቀልን ተሸክሞ ሲወድቅ ሲነሳ የዋለበትን፣ ይልቁንም ሥርዓተ ስግደትን ራሱ ሰግዶ እኛን ያስተማረንን በማሰብ ነው። /ሉቃ. 22:41-45   ፤  ዮሐ. 4:22-24/
.    
      * ስለዚህ በዚህ ሳምንት ወርኃዊ፣ አመታዊ በዓል ቢሆን እንኳ ስግደት አይቋረጥም። የአምልኮት ስግደት ሳምንት ስለሆነ። ዲያቆኑ ጥቁር ለብሶ መስቀል ይዞ ቃጭል እያቃጭለ ቤተክርስቲያንን ሶስት ጊዜ መዞሩ ዲያቆኒ የዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ፣ ቃጭል የእመቤታችን ምሳሌ ሲሆኑ፤ ዮሐንስና እመቤታችን ጌታችን የተሰቀለበትን እግር መስቀሉን እየዞሩ አልቅሰው ነበርና።

    * በዕለተ ዓርብ ሰርህ ሲሆን ምእመናን ወደ ቄሱ እየቀረቡ ስግደት እንዲሰጣቸው ይጠይቃሉ። ቄሱም በወይራ ቅጠል እየጠበጠበ ተጨማሪ ቀን ሲሰግዱ ከዋሉ ሌላ ስግደት ይሰጣቸዋል። ጥብጠባ የጌታችን ግርፋት ምሳሌ ነው። አንድም የተግሳጸ ምሳሌ ነው። /ማቴ 26:27/

                   አክፍሎት
 
    * አክፍሎት ማለት ማካፈል፣ ማጠፍ፣መደረብ፣ ሁለቱን ቀን አንድ አድርጎ መጾም፣ ጌታ ከተያዘበት እስከ ተነሳበት ድረስ ይህ ስርዓት የመጣው በቤተክርስቲያናችን ልማድ እመቤታችን፣ ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤ በመቆየታቸው ምክንያት ነው። በሀገታችን ብዙ ስዎች ሐሙስ ማታ የቀመሱ እሑድ የትንሳኤ እለት ብቻ እህልና ውኃን የሚቀምሱት፣ ያልተቻላቸው ግን ዓርብ ማታ የቀመሱ እስከ ትንሳኤ ይሰነብታሉ። የሁለት ቀን ማክፈሉ እንኳ ቢከብድ ቅዳሜ ማክፈል ሥርዓት ነው ቅዳሴው በመንፈቀ ሌሊት ስለሆነ በልቶ መቁረብ እንዳይሆን።
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++

   3. በሕማማት ለምን መስቀል አንሳለምም ወይም አናማትብም ?

    * የመስቀል ክብር እና ኃይል የታወቀው ጌታ በመስቀል ከተሰቀለ በኃላ ነው በሰሙነ ህማማት ከ ሰኞ እስከ ዓርብ ያሉ ቅናት የዓመት ፍዳ መታሰቢያ ናቸው በዚህ ዘመናት ሰዎች የመስቀልን አገልግሎት እንዳልጀመሩ ለማሳየት በሰሙነ ህማማት በቤተክርስቲያን ስርዓት መሰረት መስቀል ማሳለምም ሆነ የማማተብ ስርዓት የለም
~~

  
     4. በሰሙነ ህማማት ለምን አንሳሳምም ?

* ይሁዳ ጌታውን በመሳም አሳልፎ ሰጥቷል እኛም እንደ ይሁዳ ክፋት ካለው መሳሳም መለየታችንን ለማስረዳት ከዚህ በተጨማሪ ፍፁም ሰላም በዘመነ ፍዳ እንዳልነበረ ለማሳየት በሰሙነ ህማማት እስከ መሳሳም የደረሰ ጥብቅ ሰላምታ የለም
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++

       5. ስለ ሰሙነ ህማማት በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈ አለን?

* ነብዩ ኢሳይያስ " በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ ሕማማችንንም ተሸክሞአል" /ኢሳ. 53:4/ ይላል ህማማት የሚለው ቃል በቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ የወሰደ ሲሆን የጌታን መከራ የምናስብበት ሳምንት ነው የጌታችንን ሞቱን ህማሙን ማሰብ መዘከር እንደሚገባ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል / ጌታ እስኪ መጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና / (1ኛ ቆሮ 11: 26)

      * ይህ ሳምንት ለአይሁድና ለመሰሎቻቸው የደስታ ወቅት ቢሆንም ለክርስትያኖች በጥልቅ ኅዘን ውስጥ የሚገቡበት ሳምንት ነው እንዲሁ ተብሎ እንደተጻፈ / እናንተ ታለቅሳላችሁ ሙሾም ታወጣላችሁ ዓለም ግን ደስ ይለዋል እናንተም ታዝናላችሁ ነገር ግን ኃዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል/  (ዮሐ 16:20)
በእርግጥ ኅልዘናችን ትንሳኤውን እስንናይ ለጥቂት ጊዜ ቢሆንም ግን እናዝናለን በትንሳኤው ደግሞ ደስታውን እንካፈላለን
~~

 
6. በሰሙነ ህማማት የማይፈቀዱ ሌሎች ነገሮች ምን ምን ናቸው ?

* ማንኛውም ለስጋ የሚያደሉ ተግባሮች መቀነስ እና ቢቻለን አብዛኛውን ጊዜአችንን በቤተ እግዚአብሔር የጌታን መከራ ሕማም በማሰብ በጾም በስግደት በጸሎት ማሳለፍ
    በትዳር ያሉ በመኝታ ከመተዋወቅ መታቀብ
     ቢቻል አመጋገባችንን ከወትሮው መቀነስ

ከህማሙ ከመከራው በረከት ይክፈለን
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን
ወስበሀት ለእግዚአብሔር
@menefesawinet
Audio
ሞትን ይሽረው ዘንድ የማይሞተው ሞተ ከሰሙንነ ህማማት ጀምሮ እስከ ትንሳኤ የጌታችን የመድሃኒታች የእየሱስ ክርስቶስ ትረካ💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ
ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ
ያብጽሕክመ ለብርሃን ትንሣኤሁ
እግዚአብሔር  በፍስሓ ወሰላም
አሜን፫ 🕊 እናዳምጥ 🕊
††† እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† መድኃኔ ዓለም †††

††† ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ በዚሕ ዕለት ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት::
ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::

*ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::

በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት:: በሠለስት (ሦስት ሰዓት ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት::

ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት:: ሰባት ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ::
ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ::

ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በባሕርይ ሥልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ:: በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: አሥራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት::

በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ:: (ማቴ. 27:1, ማር. 15:1, ሉቃ. 23:1, ዮሐ. 19:1)

††† ለእኛ ለኀጥአን ፍጡሮቹ ሲል ይህንን ሁሉ መከራ የታገሰ አምላክ ስለ አሥራ ሦስቱ ኅማማቱ: አምስቱ ቅንዋቱ: ስለ ቅዱስ መስቀሉ: ስለ ድንግል እናቱ ለቅሶና ስለ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስ ብሎ ይማረን::

††† መድኃኔ ዓለም ከወዳጆቹም ጸጋ ክብርን ያድለን:: 

††† "የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ::" †††
(፩ጴጥ. ፪፥፳፩-፳፭)
@menefesawinet
“አንዱ ስለሁሉ ሞተ” (2ቆሮ 5÷14)
የስሞነ ሕማማት ዕለተ ዓርብ በቤተክርስቲያናችን ልዩ ቀን ነው።
፩- የስቅለት ዓርብ ይባላል
የዓለም ሁሉ መድኀኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ለዓለም ድኅነት መስዋዕት ሆኖ የዋለበት ዕለት በመሆኑ የስቅለት ዓርብ ተብሏል (ማቴ 27፡35)

፪- መልካሙ ዓርብ (GOOD FRIDAY) ይባላል
ይህም የሚያስገነዝበን ከስቅለተ ክርስቶስ በፊት ማንም ሰው ስያጠፋ በመስቀል ተሰቅሎ እንዲሞት ይደረግ ነበር፡፡ በተለይ በሮማውያንና በፈሪሳውያን ሕግ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ነበረ፣ በዚህ ዕለት ግን ታሪክን የሚቀይረው፣ ነገርን የሚገለብጠው አምላክ የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል በደሙ ቀድሶ የምህረት ምልክት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያብሎስ ድል መንሻ ፣ የቤተክርስቲያን ጌጥ፣ የገዳማት ዘውድ፣ ስለአደረገውና በዕለተ ዓርብም በሞቱ ሕይወትን ስለአገኘን መልካሙ ዓርብ ተብሏል፡፡
የልደትሽ ቀን ልደታችን ልጅሽ ደሞ ህይወታችን ነው🙏🙏🙏

እንኳን አደረሳችው ግንቦት 1
✦✧<< ከልጅ ልጅህ ተወልጄ >>✦✧

ክቡራን የእግዚአብሔር አገልጋዮች ካህናትና እግዚአብሔርን የምትወዱ ምእመናን


ሕያውና ዘላለማዊ የሆነው ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤውና ለቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በዓለ ልደት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ።

◦ ቅዱሳን የቤተ-ክርስቲያን አባቶች እንደሚያስተምሩን አዳምና ሔዋን እግዚአብሔር አትብሉ ያላቸውን የዕፀ በለስን ፍሬ በሰይጣን ምክር ተታለው በበሉ ጊዜ- ከተድላ ገነት ወጡ- በፈጣሪ ፍርድም ተቀጡ። እግዚአብሔር አዳምና ሔዋንን ከገነት አስወጥቶ በገነት አንጻር (ትይዮ)በደብር ቅዱስ አኖራቸው ስለምን ቢሉ ገነትን እያስታወሱና በሩቅ እያዩ ኀዘን እንዲጸናባቸው። በዚያውም ላይ << ወደ ቀደመው ቤታችን ወደ ገነት ይመልሰን ይሆን>> እያሉ እንዲጸጸቱ ብሎ ነው።

አደም እና ሔዋን በደብረ ቅዱስ ሲኖሩ ሳለ ከዕለታት በአንዱ ቀን አዳም << እግዚአብሔርን ያህል ጌታ ገነትን ያህል ቦታ ያጣውት በአንቺ ምክንያት እኮ ነው>> ሲል ተቆጣትና ፊት ነሣት።

በዚያን ጊዜ ሔዋን ደንግጣ ከአዳም ሸሽታ ሄደች። አዳምም ብቻውን እያዘነና እየጸለየ ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አዳም መጥቶ << ከሚስትህ ጋር ተጣልተህ እርስዋን አባረክ እንዴት ትጸልያለህ ሂድና ታረቃት >> አለው።

አዳምም << እግዚአብሔርን ያህል ጌታ ገነትን ያህል ቦታ ያጣሁት በእርስዋ ምክንያት ስለሆነ አልታረቅም>> ብሎ መለሰ።

መልአኩም በእርስዋ ምክንያት ያጣኸውን ብታጣ ከፈጣሪህ ጋር መታረቂያህም እርስዋ ናትና ታረቃት አለው።

አዳም ግን አይሆንም አለና ጸሎቱን ቀጠለ።

መልአኩም እንደ ገና ወደ አዳም መጥቶ እግዚአብሔር የመስተቀይምን (የቂመኛን) ጸሎት አይቀበልም እና በመጀመሪያ ከሚስትህ ታረቅ አለው።

አዳምም ለመልአኩ መልሶ ጌታዬ አንተው ሂደህ ብታመጣልኝሳ አለው።

መልአኩም ለአዳም መልሶ ጌታዬ አንተው ሂድና አምጣት እንጂ እኔ ምን ባይ ነኝ ሲል መለሰለት።

በዚያን ጊዜ አዳም ሄዶ ከሔዋን ጋር ታረቀ መለሳትም።

ከዚያን ጊዜ በኋላ ሁለቱም ሲጫወቱ ሔዋን ለአዳም እግዚአብሔር አምላካችን እንደ ተጣላን ይቀር ይሆን አይታረቀንም ብለህ ስትል ጠየቀችው።

አዳምም እግዚአብሔር መሐሪ ነውና ይታረቀን ነበር። ዳሩ ግን አንቺ አለሽና ምን ይሆናል አላት።

በዚያን ጊዜ ሔዋን ከእንግዲ ወዲህ ካንተ ፍቃድ አልወጣም አለችው።

ከዚያን ጊዜ በኋላ ሁለቱም እግዚአብሔርን ለመለመን ሱባኤ ገቡ።

አዳምና ሔዋን ሱባኤያቸውን ሲፈጽሙ እግዚአብሔር ተገለጠላቸውና አዳም ሆይ ከሰማየ ሰማያት ወርጄ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ እኔ አድንሃለሁ አለው።

አዳም እግዚአብሔር ሆይ መቼ ነው የምታድነኝ? ብሎ ጠየቀ።

በሐሙስ ዕለት ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ: ወእድሕክ ውስተ መርኅብከ ወእትቤዘወከ በመስቀልየ ወበሞትየ (አምስት ቀን ተኩል ሲፈጸም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ: በመንደርህ ተመላልሼ: ተሰቅዬ ሞቼ አድንሃለሁ) ብሎ ተስፋ ሰጠው: ቃል ኪዳን ገባለት።

ይህ የታሪክ ጥቅስ የተገኘው መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ዘሮም: ገድለ አቡነ አዳም: አክሲማሮስ (ሄክሳሜሮን) ዘኢጲፋንዮስ ከተባሉ የትውፊት መጻሕፍት ነው። በመሆኑም አምስት ቀን ተኩል ሲፈጸም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ማለቱም በእግዚአብሔር አቆጣጠር ማለት ነው። ይህም በሰው አቆጣጠር አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ማለት ነው። (5500)

አዳምም እግዚአብሔር በነገረው ተስፋ ተጽናና እግዚአብሔር ያድነኛል ወደገነትም ይመልሰኛል ብሎ ጽኑ ተስፋ አደረገ። እግዚአብሔር ከልጅ ልጅ ከአብርሃም ዘር: ከልጅ ልጁ ከዳዊት ዘር ከምትወለደው ልጅ ተወልዶ አንደሚያድነው ተስፋ አድርጎ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ከኖረ በኃላ አንቀላፋ (ሞተ) (ዘፍጥ.፭÷፩_፭ [ዘፍጥ 5÷1-5] እንዲህ ይላል:-
1የአዳም፡የትውልዱ፡መጽሐፍ፡ይህ፡ነው።እግዚአብሔር፡አዳምን፡በፈጠረ፡ቀን፡በእግዚአብሔር፡ ምሳሌ፡አደረገው፤
2፤ወንድና፡ሴት፡አድርጎ፡ፈጠራቸው፥ባረካቸውም።ስማቸውንም፡በፈጠረበት፡ቀን፡አዳም፡ብሎ፡ጠራ ቸው።
3፤አዳምም፡ኹለት፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ኖረ፥ልጅንም፡በምሳሌው፡እንደ፡መልኩ፡ወለደ፤ስሙንም፡ሴ ት፡ብሎ፡ጠራው።
4፤አዳምም፡ሴትን፡ከወለደ፡በዃላ፡የኖረው፡ሰባት፡መቶ፡ዓመት፡ኾነ፤ወንዶችንም፡ሴቶችንም፡ወለ ደ።
5፤አዳምም፡የኖረበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ዘጠኝ፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ኾነ፤ሞተም።

◦ በዚህ ምክንያት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ ሲወርድ ሲዋረድ ቴክታና በጥሪቃ ከተባሉ የዳዊት ዘር ከሆኑት ከድንግል ማርያም አያቶች ደረሰ። በዮሴፍ ሐረገ ትውልድ በኩል በአጭሩ ሲቆጠር ◦አኪንም ኤልዮድን ወለደ፤ ማትያስም ያቆብን ወለደ፤ ያቆብም ዮሴፍን ወለደ፤ ዮሴፍም በእድሜ ሽምግልና እያለ አምላክን ለመውለድ ትንቢት የተነገረለትን ድንግል እንዲጠብቃት (እንዲያጫት) በእግዚአብሔር መልአክ ታዘዘ (ትርጓሜ ሜቴ.፩÷፲፬ )።

ከዳዊት ዘር ሐረገ ትውልድ የተወለዱ የቅድስት ድንግል ማርያም ቅድም አያቶች ቴክታና በጥሪቃ እጅግ በጣም የበዛ ሀብት ነበራቸው። ነገር ግን ልጅ ስላልወለዱ በሀብታቸው ብዛት እምብዛም አይደሰቱም ነበረ። እንዲያውም ብዙ ጌዜ እግዚአብሔር ፍሬ እንዲሰጣቸው ሱባኤ እየገቡ ይጸልዩ ነበረ።

በአንድ ወቅት ቴክታና በጥሪቃ ሱባኤ ገብተው ሳለ ራእይ ያያሉ፤ ራእዩም አንዲት ነጭ እንበሳ (ጥጃ) ከበረታቸው ስትወጣ: ይህቺም እንቦሳ ሌላይቱን እንበሳ ስትወልድ: እየወለደች እንዲሁ እየተዋለዱ እስከ አምስተኛይቱ እንቦሳ ይደርሳሉ፤ አምስተኛዋ እንቦሳ ግን ጨረቃ መሰል እንቦሳ ትወልዳለች፤ ጨረቃይቱም ፀሐይን ትወልዳለች።

ይህንን ራእይ በዘመናቸው ለነበረው መፈክረ ሕልም (ሕልም ፈቺ) ሄደው ነገሩት። እርሱም: <<ደጋግ ልጆች ትወልዳለችሁ። የጨረቃው ራእይም አሰው በላይ የሆነች ልጅ ትወለዳለች። የፀሐዩ ነገር በርቶ አልተገለጸልኝም። እንደ ነቢይና እንደ ንጉሥ የመሰለ ልጅ ከቤታችሁ ይወለዳል>> ብሎ ነገራቸው።

ከዚህ በኋላ ቴክታ ፀነሰች፤ ወለደችም። ስምዋንም ሄኤማን ብላ ጠራቻት። ሄኤማን ማለት: << ስለቴ ደረሰ፤ እንደ ስዕለቴ ሆነልኝ>> ማለት ነው።

◦ ከዚያም ሄኤማን ዴርዴን: ዴርዴን: ቶናን: ቶና ሲካርን ወለደች፤ ሲካር ሄርሜላን: ሄርሜላም ሐናን ወለደች።

◦ኢያቄምና ሐና እንደ ሳሙኤል ወላጆች እንደ ሐናና እንደ ሕልቃና በእግዚአብሔር ፊት ደጎች ነበሩ። ሁለቱም ጻድቃን ነበሩ። ነገር ግን ልጅ ስላልወለዱ ልጅ እንዲያገኙ ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ፤ <<ሴት ልጅ ብንወልድ በቤተ-መቅደስ እየኖረች እግዚአብሔር እንድታገለግል: ለእግዚአብሔር ስዕለት አድርገን እናቀርባታለን፤ ወንድ ልጅም ቢወለድ እንደ ነብዩ ሳሙኤል የእግዚአብሔር ካህን ሆኖ ዕድሜ ልኩን እንዲያገለግል ለእግዚአብሔር እናቀርባለን >> ብለው ብዕዓት ገቡ ማለት ስዕለት ተሳሉ።

በዚያን ጊዜ ሐናና ኢያቄም በሱባኤ ቆይተውና ስዕለታቸውን ተናግረው ሐምሌ ፳፱ ቀን ወደ ቤታቸው ተመለሱ። ሐምሌ፴ ቀን ሁለቱም ሕልም አዩ።
@menfesawinet
ሐና ለኢያቄም÷ << ዐምር (ግምጃ ) ሲያስታጥቁህ አየሁ። የእጅህ መቋሚያም ለምልማ: አብባና አፍርታ ፍሬዋን ሰው ሁሉ ሲመገብ አየሁ>> ብላ ነገረችው።

ኢያቄም በበኩሉ: <<ርግብ ጸዐዳ (ነጭ ርግብ) ሰባቱን ሰማያት ሰንጥቃ ወርዳ በራስሽ ላይ ስታርፍ: በቀኝ ጆሮሽም ገብታ በማሕፀንሽ ስታድር አየሁ>> ብሎ ነገራት።

ስለዚህ በዚህ እግዚአብሔር በገለጸላቸው ራእይ መሠረት: ነሐሴ ሰባት ቀን ሐና ፀነሰች። ሐና ድንግል ማርያም በፀነሰች ጊዜ የመውለጃዋ ቀን እስኪደርስ ድረስ የታዘዘ መልአክ ሕፃንዋን ከማንኛውም ክፉ ነገር ይጠብቃት ነበር፤ << ዐቀባ መልአክ እምከርሠ እማ ወኢረኲሰት እምዘፈጠራ: ድንግል በሕሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ(በእናትዋ በሐና ማኅፀን ሳለች የእግዚአብሔር መልአክ ጠበቃት፤ ከማንኛውም ርኵስ ነገር ሁሉ ጠበቃት። ከፀነሰችበት ቀን ጀምሮም ምንም ርኩሰት እንዳይነካት መልአኩ ጠበቃት፤ በሐሳብም: በሥጋም ድንግል ሆና ለዘላለም እንደምትኖር የተነገረላት ናትና።)>>

◦ ሐና: ቅዱስት ድንግልን በፀነሰችበት ወራት ታላቅ ደስታ ተደረገ። ብዙ በሽተኞችም የሐናን ልብስ እየዳሰሱ ተፈወሱ። ብዙ ዕውሮችም የሐናን ልብስ እየነኩ ዓይኖቻቸው በሩላቸው። ተአምራቱን ያዩ ምቀኞች ሰዎች ግን ቀንተው ሐናን ሊጣሏት ወሰኑ። በድንጋይም ሊወግሯት ተስማሙ።
በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ለኢያቄም ተገልጾ: <<ወደ አድባረ ሊባኖስ:ወደ ሊባኖስ ተራሮች ይዘሃት ውጣ>> አለው።

ኢያቄምም መልአኩ እንዳዘዘው ወደ ሊባኖስ ተራሮች ይዞት ወጣ። በዚያም በአንድ ዋሻ ውስጥ ሳለች ወለደች። ድንግል ማርያም በተወለደችበት ሰዓት: ዋሻው በረቂቅ ሰማያዊ ብርሃን ተሞላ፤ የሰማይ መላእክትም እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ተሰሙ። በሊባኖስ ተራሮች ጫፍ ብርሃናት እንደ ችቦ ሲበሩ ከሩቅ ታዩ።

◦በዚህም ምክንያት በድንግል መወለድ የአዳም ተስፋው ሊፈጸም ዋዜማው ተጀመረ፤ <<ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ>> ተብሎ የተነገረለት ተስፋ ሊፈጸም መሠረት ተጣለ። ሊቃውንትም ይህንን አስመልክተው፤ <<አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ አምገነት>> ብለው የሚያመሰግኑበት ዘመን <<ዘመነ ሐዲስ>> ሊጀምር አዋጅ ተነገረ፤ <<አዳም ከገነት በተሰደደ ጊዜ: የመዳን ተስፋው ባንቺ በኩል ይሆናል>> ተብሎ የሚነገርበትም ጊዜው ደረሰ።

<<ድንግል ሆይ: ንጹሕና ቡሩክ ጋብቻን ፈጽመው በጽድቅ መንገድ ከሚጓዙ: ከሐናና ከኢያቄም በንጽሕና ተወለድሽ>>ተብላ የምትመሰገን የምስጋና ባለቤት እናት ድንግል በተወለደች ጊዜ: አበው ነቢያት የተናገሩት መሠረት ትንቢት ተፈጸመ። ነቢዩ ዳዊት: <<መሠረቶቿ በቅዱሳን ተራሮች ናቸው>> ሲል የተናገረው ድንግል ማርያም ከአብርሃምና ከዳዊት ዘር መወለዷን ለመግለጽ ነው። (መዝ.፹፮÷፩)።

ቅዱስ ያሬድም: <<ወመሰረቱ ለዓለም አንቲ፤ እጓለ አንበሳ በከርሥኪ ፆርኪ: እመአንስት ቡሩክት አንቲ፤ የምስጢረ ሥጋዌና የምስጢረ ድኅነት መሠረት አንቺ ነሽ፤ የአንበሳልጅ የሆነውን አንበሳ በማሕፀንሽ የተሸከምሽ: ከሴቶች ሁሉ ቡሩክት አንቺ ነሽ>> ሲል አመሰግኗታል።

◦አማን በአማን ተወልደት እመ ብርሃን◦

የብርሃናት ንጉሥ: ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመውለድ ዛሬ የብርሃን እናት ቅዱስት ድንግል በእውነት ተወለደች፤ የአዳም የተስፋው መፈጸሚያ ዛሬ ተወለደች። የድኅነታችን መሠረትና የክብር ዘውዳችን የሆነወሰን ክርስቶስን ለመውለድ ዛሬ አስቀድማ እርሷ ተወለደች። ከሊባኖስ ተራሮች ርግብ ጸዐዳ ተወለደች። በቅዱስ ያሬድ:<<እምሊባኖስ ትውጽእ መርዓት>> ተብላ እንድትወደስ ከሊባኖስ ተራሮች ውስጥ ተወለደች። በሔዋን ምክንያት የተዘጋው የሕይወት መንገድ ይከፈትልን ዘንድ◦የሕይወት እናት ዛሬ ተወለደች። ኢያቄም ሐና: ዳግሚት ሰማይ ተብላ የተጠራችውን ድንግልን ወለደች። እውነተኛው ፀሐይ እየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ይወለድ ዘንድ: እመ ፀሐይ (የፀሐይ እናት) ቅድስት ድንግል ዛሬ ተወለደች።...በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ። በምድርም ሁሉ ስምሽን ያስባሉ>> ተብሎ ትንቢት የተነገረላት ንጽሕተ ንጹሐን ቅዱስተ ቅዱሳን እመ ብርሃን ዛሬ ተወልዳልናለችና ደስ ይበለን፤ እልልም እንበል (መዝ፵፬÷፲፪_፲፯)።

◦ብርሃንን ለማስገኘት መወለድ መታደል ነው። አሰው ልጆችም መካከል መመረጥ ዕፁብ ድንቅ ነው። የመድኃኔ ዓለም እናት ለመሆን መወለድም ሰማያዊ ጸጋ ነው፤ የሴቶች ሁሉ መመኪያ ለመሆን መወለድ እጅግ የሚያስደስት ነው፤ መታደል። የተዘጋውን የገነት በር ለማስከፈት መወለድ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። በእውነት እመ ብርሃን ቅዱስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ስጦታ ናት።

◦ከ፴፫ቱ የእመ ብርሃን በዓላት ሁሉ የልደት በዓሏ የበለጠ መሆኑን ራሷ ቅዱስት ድንግል ማርያም: በቀን ሺህ ጊዜ <<ሰአሊ ለነ ቅድስት >>እያለ ለሚጸልይ ለአድ ባህታዊ እንደነገረችው የቤተ-ክርስትያን አባቶች ይተርካሉ (ትርጓሜ ቅዳሴ ማርያም ምዕራፍ አንድ)።

◦ለመላው ህዝበክርስቲያን ይድረስ መልክቴ ሼር አርጉ አይቶ ዝም ምንምጥቅም የለው በመላው አለም ለምት ገኙ ለመላው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኮን ለእመቤታችን በአለልደት በሰለም በጤና አደረሰን አደረሳቹ እላለው።

አቤቱ እኔ ባርያህን አስበኝ በድያለውና ይቅር በለኝ ብለን ሁላችን በለቅሶ በሀዘን ወደሱ እንቅረብ አምላከ ቅዱስ እስጢፋኖስ የእኛ አምላክ የእመቤታችን የድንግል ማርያም ልጅ የአባታችን የአቡነ ተክለሀይማኖት አምላክ ከሀጥያታችን ያንፅን ሀገራችንን በምህረት አይኑ ይጎብኛት ይቅርም ይበለን። 🙏ፊቱን ይመልስልን🙏 በምህረት አይኖቹ ይመልከተን

"፤ቍጣው፡ለጥቂት፡ጊዜ፡ነው፥ሞገሱ፡ግን፡ለሕይወት፡ዘመን፤ልቅሶ፡ማታ፡ይመጣል፥ጧት፡ግን፡ደስታ፡ይኾናል።"

መዝሙረ ዳዊት 29:(30)÷5

በፀሎታችሁ አስብኝ አትርሱኝ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን

ለመቀላቀል 👇
      @menefesawinet
ዳግም ትንሣኤ፦
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በዚህች ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሤኤው ሳምንት ለሐዋርያው ቶማስ ተገለጠለት::

የዛሬው ቀን እንደ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት አጠራር ዳግም ትንሣኤ ይባላል።

በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

በዛሬው ዕለት የክርስቶስን ዳግም ትንሣኤ በማየታችን የእግዚአብሔር ልጅ የመባልን ክብር ያገኘንበት ቀን ነውና በቤተ ክርስቲያን ተገኝተን ልንከብር ያስፈልጋል።

አባት ሆይ! ከአባቶቻችን ምስጋናን እንደ ተማርን ስለ ምሥጢረ ሥላሴ በዳግም ትንሣኤ አወቅን ተረዳን፤ እንዲሁም እናምናለን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ሒዱ አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው እንዳለ የምናምንባት ሃይማኖት ይህች ናት ከእርስዋ በቀር ለዘላለሙ ሌላ አንሻም።

ካህናት ሆይ እንኳን ደስ አለችሁ! በዛሬው ዕለት አምላካችሁ እኛን የማጥመቅ፣ የማሰርና የመፍታት ሥልጣን፣ ክህነት የመስጠትን ሥልጣን፣ የመባረክን ሥልጣን፣ የመሾም የመሻር ሥልጣን፣ የመቀደስ የመፈወስ ሥልጣን የተሰጣችሁ ቀን በዛሬዋ ዳግም ትንሣኤ ናት እና ኑ በቤተ መቅደስ ተሰባስበን ደስታ እናድርግባት።

ምእመናን ሆይ! ሀብተ ወልድ እና ስመ ክርስትና የምናገኝበትን የምሥራች ጌታ ለሐዋርያት የሰጠበት ቀን በዳግም ትንሣኤ ነውና ኑ በመቅደሱ ተሰባስበን በደስታ በሐሴት እናመስግን።

ሌላም በዛሬው ዕለት ለሐዋርያው ቶማስ በእጆቹና በእግሮቹ ውስጥ የችንካሮቹን ምልክት አሳየው የቶማስንም እጅ ይዞ በመለኮታዊ ጎኑ ውስጥ አኖረውና በጦር የተወጋበትን ቦታ አሳየው ቶማስም ጌታዬና ፈጣሪዬ መነሣትህን አመነኩ አለ::

ጌታችንም ብታየኝ አመንክብኝ የሚመሰገንስ ሳያየኝ የሚአምንብኝ ነው ብሎ መለሰለት::

በትርጓሜ ወንጌል እንዲህ ይላል ቶማስ በመድኃኒታችን ጎን ውስጥ እጁን በአስገባ ጊዜ እጁ በመለኮት እሳት ተቃጠለ በመለኮቱም ደግሞ በታመነ ጊዜ እጁ ከመቃጠል ዳነች::

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በሐዋርያቶች ጸሎት በታጋዮች ጻድቃንም በድል አድራጊዎች ሰማዕታት ጸሎት ይልቁንም አምላክን በወለደች  በክብርት ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ ይምረን ዘንድ ወደርሱ እንለምን ለዘላለሙ አሜን:: መልካም ዕለተ ሰንበት።
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸

      🌸 የምሥራች 🌸

⛪️ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
🙏በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
⛪️አሰሮ ለሰይጣን
🙏አግኣዞ ለአዳም
⛪️ሰላም
🙏እምይእዜሰ
⛪️ኮነ
🙏ፍሥሐ ወሰላም
🇪🇹@menefesawinet
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ከቅዱሳን_ባሕታውያ_ጋር

በአንድ ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡-ከዕለታት አንድ ቀን በሀገረ ስብከቴ ሥር በነበሩ በሜዲትራኒያን ባሕር በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ምእመናንን ለመጎብኘት አሰብሁ፡፡ ከእኔ ጋር ቀሳውስትንና ዲያቆናትን አስከትዬ በጀልባ ተሳፍሬ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዝሁ፡፡ በደሴቱ ውስጥ ስንዘዋወር የሰው ዱካ ብንመለከትም ምንም ሰው ማየት አልቻልንም ነበር፡፡ በአሸዋው ላይ ታትሞ የነበረውን የሰው ዱካ ተከትለን ስንጓዝ ካልተፈለፈሉ ዐለቶች የተሠራ ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ዋሻ ላይ ደረስን፡፡

ዋሻው በርም ሆነ መስኮት የለውም፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ ልክ እንደ ሰባቱ ደማቅ ከዋክብት እጅግ በጣም አንጸባራቂ ብርሃን ቆመው ከሚጸልዩ ሰባት አባቶች ዘንድ ሲወጣ ተመለከትን፡፡ እኛም ከእነርሱ ጋር ለመጸለይ ባለንበት ቆምን። አባቶች ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ እኛ ዞሩና በፊቴ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ። በመቀጠልም ሰላምታ ሰጡን፡፡ እኔ ዮሐንስም ‘እኔ አባታችሁና ፓትርያርካችሁ ዮሐንስ ነኝ’ አልኳቸው፡፡ ቅዱሳኑ እንደገና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በፊቴ ሰገዱ እና እኔን ደካማውን እንዲህ አሉኝ፡- “የምንወደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትባርከንና እኛም አንተን በማየት እንድንበረታ ወደዚህ አመጣህ” አሉ። እኔም “እባካችሁ ታሪካችሁን ንገሩኝ” አልኋቸው፡፡

ሰባቱ አባቶችም “ከብዙ ዓመታት በፊት ሰባታችንም ከቍስጥንጥንያ ወጥተን በአንድነት ተሰባስበን ሕይወታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና በአምልኮ ብቻ ለማሳለፍ ወደዚህ ደሴት መጣን፡፡ ከዚህ ደሴት በደረስንበት ዕለት ከባሕሩ ከሚመጣው አስቸጋሪ ነፋስ ራሳችንን ለመከላከል ዋሻዎችን ለመገንባት ዐለቶችን ሰበሰብን፤ በሁለተኛው ቀን ደግሞ ይህን ቤተ ክርስቲያን መሥራት ጀመርን፡፡ በዐለቶች መካከል ከሚበቅለው ሣር እንበላለን፤ ውኃም ከባሕሩ እንጠጣለን፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን የከበቡትን እነዚህን የአሸዋ ክምሮች ለማስወገድ ፈልገን ነበር፤ ግን አእምሯችንና አሳባችን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ስለተያዘ ጊዜ አጣን” በማለት ታሪካቸውን ነገሩኝ።

እኔም “መንፈሳዊ አባታችሁ የት ነው?” ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ ይህን ጥያቄ ከመጠየቄ ወዲያውኑ አንድ ሽማግሌ በትሩን ተደግፎ ወደ እኔ ቀረብ አለና “እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ” አለኝ፡፡ አረጋዊው ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ራቁቱን ነበረና “ሰውነትህን የምትሸፍንበት ትንሽ ልብስ ትፈልጋለህ?” ስለው እሱም “ጌታ ከክረምቱ ቅዝቃዜ፣ ከበጋው ሙቀት ይከላከልልናል፤ ይጠብቀናልም” በማለት መለሰልኝ፡፡ “ምግብ ያስፈልጋችኋል?” ብዬ ስጠይቀው እርሱም “የሚበቃንን ያህል ከእነዚህ ዕፅዋት እንመገባለን ከዓለም የሆነ ምንም ነገር አያስፈልገንም” በማለት መለሰልኝ፡፡

እኔም “አባቶቼ እባካችሁ ለእኔ እና ስለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ጸልዩ” አልሁት። የእነዚያን ቅዱሳን ባሕታውያን አባቶች በረከት ከተቀበልን በኋላ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም ምሥጋና የሚገባውን የምንወደውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገንን ወደ መጣንበት ተመለስን” ይለናል ቅዱሱ አባታችን ዮሐንስ አፈ ወርቅ።

ምንጭ፦ ግሑሣን አበው
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፡-

ዮሐንስን በቤተ መቅደስ ፊት የእመቤታችን የማርያም ስእል ነበረችና አፈወርቅ ብላ ጠራችው፤ ስለዚህም ዮሐንስ አፈወርቅ ተባለ፡፡ ያእቆብ በእግዚአብሔር አንደበት እስራኤል እንደተባለ እንዲሁ ዮሐንስ በማርያም ስእል አንደበት አፈወርቅ ተባለ፡፡

እኔም ስለርሱ እላለሁ፦
በእውነት አፈወርቅ አፈ እንቁ ስለ አምላክ ከድንግል መወለድ ፍቅር የወር አበባ ያላትን ሴት አንቀፀ ስጋ ለመሳም ያላፈረ በእውነት አፈ ጳዚዮን ነው፡፡

በድርሰቶቹ ቤተክርስቲያንን የሚያስጌጣት አፈ ባሕርይ በእውነት አፈ መአር በቃሉ ጣፋጭነት ምእመናንን የሚያለመልማቸው አፈ ሶከር (ስኳር) በእውነት በትምህርቱ መአዛ የምስጢር በጎችን ደስ የሚያሰኛቸው አፈ ሽቱ አፈ ርሄ ነው፡፡

በእውነት በውግዘቱ ስልጣን ከሃዲወችን የሚቆርጥ አፈ ሰይፍ አፈ መጥባህት ነው፡፡

በእውነት የማይነዋወጥ አምድ የማይፈርስ መሰረት በእውነት ከሞገዶች መነሳት የተነሳ የማይሰበር መርከብ በሃይማኖት ባሕር ውስጥ የሚዋኝ ዋናተኛ ነው፡፡

በእውነት የማይፈርስ ግንብ በጠላት ፊት የሚፀና አዳራሽ ነው፡፡