Mella Tutorials
4.35K subscribers
89 photos
1 video
18 files
266 links
A hub of wisdom.

Subscribe on Youtube | www.youtube.com/@mella_tutorials

Buy ads https://telega.io/c/mella_tutorials
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExam

" ፈተናው የሚሰጠው ከሰኔ 2-10/2017 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን " - ትምህርት ሚኒስቴር

በ2017 ዓ.ም በሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና መመዝገቢያ ጊዜ እስከ ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ብቻ የተራዘመ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

እስከ አሁን ያልተመዘገቡ የድጋሚ ተፈታኞች (resitters) ከዚህን በፊት ለምዝገባ በተከፈተውና በተገለጸው መመዝገቢያ ፕላትፎረም (registration link) በኩል ገብተው ምዝገባቸውን እንዲያጠናቅቁ ተብሏል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ለመውጫ ፈተና የሚቀመጡ ተፈታኞችም በተቋሞቻቸው በኩል መመዝገባቸውን እንዲያረጋግጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

ፈተናው ከሰኔ 2-10/2017 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል።

ለፈተናው የሚያመለክቱ አመልካቾች ለመመዝገብ የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ሊኖራቸው እንደሚገባና ፤ ከግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ቦኋላ ምዝገባ እንደማያስተናግድ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

#MoE

@tikvahethiopia
👍25🔥42