ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media
6.9K subscribers
463 photos
10 videos
22 files
453 links
ገብተህ የማትወጣ ከሆነ ብቻ JOIN አድርግ! እርግጠኛ ነኝ ትወዱታላችኹ ተቀላቀሉን!
ጥቅሙን ተቀላቅላችኹ ዕዩት፥ በተለይ አጫጭር አነቃቂ ጽሑፎች ይ ማ ር ካ ሉ!
ወቅታዊ ጉዳይ አይታጣበትም... ከገባችኹ ትርፍ አላችኹ!

TIKTok
http://tiktok.com/@mekuriya19
ለሐሳብና አስተያየት
https://t.me/Proud24
Download Telegram
ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media
ሽልማት አለው የእውነት ተሳተፉ A) "የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" እና B) " #የማያውቁትን_ያደርጋሉና_ይቅር_በላቸው" ልዩነት አላቸው ወይስ የላቸውም?
የሚያደርጉት አያውቁምና...
ምን እያደረጉ እንደሆነ አያውቁም። ሊመቱት፣ ሊያዳፉት፣ ሊዘባበቱበት ... ይችላሉ ግን እያደረጉ ያለው ምን እንደሆነ አያውቁም።

የማያውቁትን ያደርጋሉ ሲል ሌላ የሚያውቁት ነገር አለ፤ ነገር ግን አኹን እየሠሩት ያለው የሚያውቁትን አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ መሆኑን አያውቁም።

በደንብ ደጋግማችኹ በሉት ትንሽ ልዩነት አለው።

Tsionawit 👏👏👏
. ትንሣኤም፣ መልአክም፣ መንፈስም የለም ብለው የሚሉት እነማን ናቸው?
Anonymous Poll
40%
ሰዱቃውያን
19%
ፈሪሳውያን
13%
ሁለቱም
28%
ሁሉም
ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media
. ትንሣኤም፣ መልአክም፣ መንፈስም የለም ብለው የሚሉት እነማን ናቸው?
“ሰዱቃውያን፦ ትንሣኤም መልአክም መንፈስም የለም የሚሉ ናቸውና፤ ፈሪሳውያን ግን ሁለቱን ያምናሉ።”
  — ሐዋርያት 23፥8
#ክርስቶስ_ተንሥአ_እሙታን (ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ) (Christ is risen from the dead!)
ስለ ኃጥያቴ ታመምክ፣ሞትክ፣ሞትንም ድል አድርገህ የተነሣህ ጌታ ሆይ በመንግሥትህ በመጣው ጊዜ አስበኝ።

#በዐቢይ_ኃይል_ወሥልጣን (በገናና ኃይልና ሥልጣን) (By the highest power and authority!)
ትንሣኤህን ሳስብ እጅግ ይደንቀኛል ነገር ግን በዳግም ምጽአት፡ እኔ እንደማዉቀህ ሰውኛ ገፅህ ተለውጦ በአምላካዊ ብርሃን እጅግ በሚያስፈራ በሚያስደነግጥ ግርማህ እንደምትመጣ ሳስብ ልቤ በፍራት ይርዳል።

#አሰሮ_ለሰይጣን (ሰይጣንን አሰረው) (He chained Satan!)
ቀን ከሌሊት ያለ ዕረፍት ሊያስት የሚጥረዉ ጠላቴን በትሩፋት አስተክዘዉ ዘንድ ልቤን በፍቅርህ እሰረዉ።

#አግአዞ_ለአዳም (አዳምን ነጻ አወጣው) (Freed Adam!)
አዳምን ለማዳን ከክብርህ ዝቅ ብለህ በፈጠርካቸዉ እጆች የተገፋህ ነህና ዛሬም ነፍሴ ከስንፍና እስር ትፈታ ዘንድ በትንሣኤህም ትበረታ ዘንድ ፍቃድህ ይሁን።

#ሰላም (ፍቅር አንድነት) (Peace!)
ሰማይ መቀመጫዉ ምድር መረገጫዉ አልፋና ኦሜጋ የጌታዬ፥ የጌታሽ እናት ድንግል ማርያም ሆይ ቅዱስ ገብርኤል ብሥራቱን ይዞ በመጣ ጊዜ በሰጠሽ ሰላምታ ሰላም እልሻለዉ።

#እም_ይዕዜሰ (ከእንግዲህስ) (Henceforth)
ስፍር በሌለዉ መውደድ ወደኸኝ ልክ በሌለው ሕማም ታመህልኛልና የልቤን መቅበዝበዝ አርግተህ ልቤንም እንደ እግሬ ወደ ቤትህ ጥራው።

#ኮነ (ሆነ) (Is!)
ያለና የነበረ ያለ ፍጻሜ የሚኖር ማብቂያ በሌለው ዘለዓለማዊ መንግሥትህ በፍቅር እቅፍ እየሞቅኩ መኖር እናፍቃለው።

#ፍሥሐ_ወሰላም (ደስታና ሰላም) (Joy and Peace!)
ጌታዬ ከአንተ ዘንድ ያለው የውስጥ ሰላሜን በእንቁም የማልሸምተው ነውና በስስት የሚያዩኝ አይኖችህን ፣ በደስታዬ የሚፈነድቀው ልብህን ሌት ተቀን እኔን በመጠበቅ የማትደክም በመልካም ምግባሬ ደስታህን እውን አደርገው ዘንድ ፤ እኔም አንተን በማግኘት እቦርቅ ዘንድ ፤ በትንሣኤህ እኔም ተሰነካክዬ ከወደቅኩበት ኃጢአት መግነዜን ፈተህ ይዘኸኝ ተነሥ፤ ዘመኔም በፍሥሐ በቤትህ ሰላም ይለቅ!

ረድኤት አሊ / Rediet Ali.

◦◦◉◉Join us on telegram
t.me/MekuriyaM
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
"ኢየሱስ ክርስቶስ " ሞቶ በስንት ቀን ተነሳ?
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ተወለደችልኝ

🌹🌹🌹🌹🌹🌹

ከዘላለም ህይወት በኃጥያት ተለይቼ
በመከራ ስኖር እውነትን ጠልቼ
ጌታዬ አምላኬን ዘወትር ሳሳዝነው
ሰላምን አጥቼ ነፍሴን አንገላታው
ድክመቴን ያወቀ የፈጠረኝ እሱ
ሊያድነኝ ወደደ መሀሪ ቅዱሱ
ከሴቶች መሀከል በንጽህና መርጧት
በፍጹሙ ፍቅሩ በልዕልና ወዷት
ዳግም ሰው ሊያደርገኝ በቃል አደረባት

ታድያ እቺ ልዕልት እርሷ የኔ ጸሀይ
ሰንሰለት ሆነችኝ ከእርሱ እንዳልለያይ
ከቅድስት እናቷ ከቅዱስ አባቷ
ለአለም አብርቶ ውበት ደምግባቷ
ወላዲተ አምላክ ድንግል እመቤቴ
ተወለደችልኝ ሆነችኝ ህይወቴ

እናቴ ይህ የአንቺ ብቻ አይደለም የኔም የልደት ቀኔ ነው። ከአንቺ ተለይቶ የሚቆጠር ዘመን የለኝም። አንቺ ባትኖሪልኝ እኔ ምንም ነበርኩ። ሰው የሆንኩት፣ አምላኬን ያወቅኩትና ነፍሴን ያሳረፍኳት በአንቺ ነው።

ዛሬ ነፍሴ ልደቷ ነው። ከአንቺ ተወልዳለችና። ያደረግሽልኝን ለመናገር ቃል አጥቻለሁ። ደግሞስ ከየት ጀምሬ የት አቆመዋለሁ። ብቻ በምድር አብሬሽ መኖሬ አይደለም በሰማይም ከእግርሽ ስር መኖሬ እጅጉን ደስተኛ ያደርገኛል።

ደስተኛይቲ ሆይ ደስ ይበልሽ

◦◉◉Join us on telegram
@MekuriyaM
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
የተወለዱበትን ቀን በመምረጥ ፣ ስለራሶ እና ስለቤተሰቦ እንዲሁም ስለ ሀይማኖቶ ይወቁ ፣
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
💁‍♂ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል።  ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል ቻናሉን ለመቀላቀል

     🔐ከስር ክፈት የሚለውን
     በመጫን ይቀላቀሉ👇👇👇
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
የተወለዱበትን ቀን በመምረጥ ፣ ስለራሶ እና ስለቤተሰቦ እንዲሁም ስለ ሀይማኖቶ ይወቁ ፣
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
"እድሜዎ ስንት ነው" ፣ ምን ማረግ አለብኝ በዚ እድሜ?
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
የተወለዱበትን ቀን በመምረጥ ፣ ስለራሶ እና ስለቤተሰቦ እንዲሁም ስለ ሀይማኖቶ ይወቁ ፣
ይወዳት ነበር። በደንብ አድርጎ ያፈቅራት ነበር። ቀን በቀን እቤቷ ሲመላለስ አየው ስለነበር እቀናበት ነበር። እኔም እጅግ አድርጌ አፈቅራት ነበር። ግን አንድም ቀን እቤቷ ሄጄ አላውቅም። በቃ ይጨንቀኝ ነበር። የእርሱ ብቻ የሚያደርጋት እየመሰለኝ ሌላ ሌላ ነገር ማሰብ ጀምሬ ነበር።

እሚገርማችሁ ነገር፥ ገና ጩጬ እያለኹ ነበር ከእሷ ጋር ፍቅር የያዘኝ። ጓደኛዬም እንደ እኔው ገና ፈላ እያለ ነበር እቤቷ መመላለስ የጀመረው። ይመላለስ እንጂ አንድም ቀን በአካል አይቷት አያውቅም። እንዲሁ በተስፋ ይመላለስ ነበር።

ከዕለታት አንድ ቀን ጓደኛዬ ይዞን ወደ ቤቷ ይወስደኛል። ገና የውጭ መግቢያው ጋር ስደርስ የእርሷ ቤት መሆኑን እንዲሁ ታወቀኝ። ደስ የሚል መዓዛ ይሸትተኝ ጀመር፤ ሰዎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የእርሷን ስም ሲጠሩ ሰማኹ። ለካ ወዳጇ እኔ ብቻ አልነበርኩም። ከእኔም በላይ አብልጠው የሚሿት ሰዎችም እንደ ነበሩ ገባኝ።

ከዚያማ እኔም ወደ ቤቷ መገስገስ ጀመርኳ! ማን ሊያስቆመኝ? ስለ እርሷ ማወቅ(መማር) ተያያዝኩት። ቀን በቀን ስሟን መጥራት ጀመርኵ። ከትንሽ ዓመታት በኋላ በሌላ አነጋገር ስለ እሷ አወሳ ዘንድ አንደኛው ሰውዬ ነገረኝ። "ምን ብሎ?" አትሉኝም?

"ምን ብሎ?" "ስለ እርሷ መማር በዚህ ብቻ አይደለም። በዜማም ተቀኝተዉላታልና በዜማም ስሟን ጥራት አለኝ።" ጀመርኳ!

ለዚያም ነው... "ማርያም መሠረተ ሕይወት" ብዬ ያዜምኩላት!
ቅኔ ይቀኛሉ መላእክት ከራማ
ተሰጥቶሻልና የመወደድ ግርማ
በእግዚአብሔር ቀኝ የምትቆሚ
ዕጸ ጳጦስ ልመናችንን ስሚ

◦◎● Join us on telegram
@MekuriyaM

Dn Mekuriya Murashe
ዘማሪት ማርያማዊት
ክራር፥ ዲ/ን መኩሪያ

◉◎●Join us on telegram
t.me/MekuriyaM
ዘማሪት ምሕረት
ክራር፥ ዲ/ን መኩሪያ

◉◎●Join us on telegram
t.me/MekuriyaM
ዘማሪት ማርያማዊት

የአንቺስ ጸጋ የጉድ ነው😍

◉◎●Join us on telegram
    
t.me/MekuriyaM