ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media
4.73K subscribers
454 photos
10 videos
20 files
413 links
ገብተህ የማትወጣ ከሆነ ብቻ JOIN አድርግ! እርግጠኛ ነኝ ትወዱታላችኹ ተቀላቀሉን!
ጥቅሙን ተቀላቅላችኹ ዕዩት፥ በተለይ አጫጭር አነቃቂ ጽሑፎች ይ ማ ር ካ ሉ!
ወቅታዊ ጉዳይ አይታጣበትም... ከገባችኹ ትርፍ አላችኹ!

TIKTok
http://tiktok.com/@mekuriya19
ለሐሳብና አስተያየት
https://t.me/Proud24
Download Telegram
🌿 #ንነጽር_፹፯

ለመጀመርያ ጊዜ ስልክ በያዝኩ ሰዓት ለታናናሽ እህቶቼ ስልኩን
#እንደፈለጉ_እንዲያደርጉት_እሰጣቸው_ነበር
ትንሽ ቆየኹና
#ባትሪው_ይፎርጃል_በቃ_በቃ_ማለት_ጀመርኩ
ትንሽ ቆየኹና ደግሞ
#አያይ_አልሰጥም_ስልኩ_ይበላሻል_ብዬ_መከልከል_ጀመርኩ
...
አየህ ወዳጄ! ሰለ አንድ ነገር በጥልቀት ማወቅ ስንጀምር፤ ለነገሩ የነበረን ቦታ ይቀየራል። ሕይወት ደረጃ እንዳላት ሁሉ ውስጠ ሕሊናችንንም እንዲሁ ጀረጃ አላት።
...
ወዳጄ! ትላንት የነበርክበት ደረጃ ላይ ዛሬም አለህ? ወይስ ፈቀቅ ለማለት ተዘጋጅተሃል?


◦◦●●Join us on telegram
@MekuriyaM
🌿 #ንነጽር_

"ይሰቀል ይሰቀል" ሲሉ ሳንሠማቸው፣
"ይገደል ይገደል" ሲሉም ሳናያቸው፤
         ግና
"አማላጅ አማላጅ" ብለው ሲናገሩ ይኸው አየናቸው፤
       እኛም
ወልደ አብ፣ ወልደ ማርያም አምላክ ነው አልናቸው።

◦◦●●Join us on telegram
      
@MekuriyaM
Forwarded from ማርመድሕ ሚዲያ - Marmedh Media (፩ Mekuriya Murashe)
#ንነጽር_፹፪

ከልቡ አዝኖብኛል፤ ግን አኹንም ይወደኛል። ለእኔ የተለየ ቦታ ያለው ያህል እስኪሰማኝ ድረስ በብርቱ ፍቅር ያፈቅረኛል። ይህም እያወቅኹ እጅግ አስከፋሁት። ለእኔ እየኖረ መሆኑን እያወቅኹ እንኳ ብዙ ጊዜ መኖሩን እዘነጋለኹ። እንደ እኔ እንደ እኔ ቢሆን እመቀ እመቃት መጣል በተገባኝ፤ እንደ እሱ እንደ እሱ ሲሆን ደግሞ ሁሌም በምሕረቱ ውስጥ ነኝ።
እንደ እኔ እንደ እኔ ቢሆን እንጦሮጦስ መጣል በተገባኝ፤ እንደ እሱ እንደ እሱ ሲሆን ደግሞ ከገደል አወጣኝ።

ደግሞ እንደ እሱ እንደ እሱ ቢሆን ይህን ዓለም ትቼ ስለ እሱ በተሰደድኹ፤ እንደ እኔ እኔ ሲሆን ግን ይኸው ለዓለም አዘነበልኹ።

ለእኔ ለብኩኑ ብሎ አቀርቅሯል፣ ደምቷል፣ ቆስሏልም። እኔ ግኔ አኹንም ያው እኔ ነኝ(በደለኛ) ግን አኹንም ይወደኛል።
      ❤️መድኃኔዓለም❤️


◦◦●●Join us on telegram
@MekuriyaM