#በእንተ_ጸሎት_ሐሙስ
"ተራሮችን በኃይሉ የሚያስታጥቃቸው ለማገልገል ማበሻ ጨርቅ ታጠቀ፡፡ የባሕርን ውኃ እንደ አቁማዳ የሚሰበስበው በቀላያትም መዝገቦች የሚሾማቸው ርሱ ከወዳጁ ከአልዓዛር ቤት የውኃ ማድጋ አንሥቶ እግሮችን ለማጠብ ያገለግልባት ዘንድ ወደ ኩስኩስት አፈሰሰ፡፡ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በሚታጠቡበት ገንዘብ የናስ ኩስኩስት ሠርቶ በደብተራ ኦሪት ደጃፍ እንዲያኖራት ሙሴን ያዘዘው ውኃውን በኩስኩስት ሞልቶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ዠመረ፡፡ የተረከዞቻቸውንም እድፍ በታጠቀው ማበሻ ጨርቅ አሸ፡፡" (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)
"በወገቡ የታጠቀውን ማድረቂያ አይተው መላእክት አደነቁ፤ ስሙ ከፀሓይና ከጨረቃ በፊት የነበረ ርሱ አገልጋይ ኾነ፤ ሕያው ጌታን ሱራፌል ያመሰግኑታል፤ ቦታውን ግን አያውቁም፤ ሱራፌልን የፈጠረ ርሱ በራት ጊዜ ወገቡን ዘርፍ ባለው ዝናር ታጠቀ፤ እንዳያቃጥል በመፍራት የማይታይ እሳት ለሐዋርያት አገልጋይ ኾኖ አብነት ይኾናቸው ዘንድ የትሕትና ሥራን የሚሠራበትን ውሃ በኩስኩስት ቀዳ የደቀ መዛሙርቱን አለቃ ጴጥሮስንም እግሩን ሊያጥበው ጠራው"
(ሃይማኖተ አበው ዘያዕቆብ ዘሥሩግ)
@mehereni_dengl