Mega Tutor
210 subscribers
575 photos
1 video
9 files
98 links
🍭Our channel is committed to help freshman students of Ethiopian universities.
We provide:-
📚 Smart notes
📽️ Video tutorials
🖨️ Freshman exams
🎙️ Voice recording

For registration👇
@megaAMUBOT

For suggestion👇
@Devmulugeta
@Soliana4
📢 Mega tutor
Download Telegram
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው ተሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋን (ፕ/ር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር አድርገው ሾሙ።

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሹመቱን የሰጡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲቋቋም በ1294/23 የራስ ገዝ አዋጅ በረቀቀው መሠረት እና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 23ኛው መደበኛ ስብሰባ የዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቁን ተከትሎ ነው።

በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን በላቀ መልኩ እንዲፈጽሙ እንዲሁም የሰው ሀብት እና የፋይናንስ አስተዳደር ነፃነትን በማረጋገጥ በሀገሪቱ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የላቀ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል ነው።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ ከተሾሙት ቻንስለር በተጨማሪም አዲስ የቦርድ አመራሮች የተሰየሙለት ሲሆን ቦረዱም ዩኒቨርሲቲውን በኃላፊነት ሊመሩ የሚችሉ ፕሬዚዳንት እና ም/ፕሬዚዳንቶችን በቀጣይነት እንደሚሾም ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን Join and share በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ👍
👇👇👇
@ https://t.me/mega_tutor
@ https://t.me/mega_tutor
#Update

ፍሬሕይወት ታምሩ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቦርድ ሊቀመንር ሆነው ተሾሙ

👉(ዶ/ር) ሳሙኤል ክፍሌ የዩንቨርስቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲደራጅ ለተወሰነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሾሙ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቦርድ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑትን ፍሬህይወት ታምሩ የየኒቨርስቲው የቦርድ ሊቀመንበር አድርጎ መሾሙን ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ደግሞ፤ ከነሐሴ 24/2015 ጀምሮ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን ገልጸዋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ2016 ጀምሮ ራስ ገዝ እንዲሆን በአዋጅ የተፈቀደ ቢሆንም፤ ሙሉ በሙሉ ራስ ገዝ ሆኖ ሥራ የሚጀምረው የሚተዳደርበት መመሪያዎች ከተዘጋጁ በኋላ ከ2017 ጀምሮ እንደሚሆን ሚኒስትሩ መናገራቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቻንስለር እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አህመድ ሹመት ማግኘታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን Join and share በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ👍
👇👇👇
@ https://t.me/mega_tutor
@ https://t.me/mega_tutor
👏1
#TVTI_Exit_Exam

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የመውጫ ፈተና ለተመራቂ ተማሪዎቹ መስጠት ጀምሯል፡፡

ፈተናው በስምንት የፈተና ጣቢያዎች በተመሳሳይ ሰዓት በኦንላይን እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም እንደአገር በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ እስከ ደረጃ V ምዘና ሲሠጥ የቆየ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የደረጃ VI እና ከዚያ በላይ ሰልጣኞች የምዘና ፈተና እየሰጠ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ኢንስቲትዩቱ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን ከ3,650 በላይ ተማሪዎች ባለፈው እሁድ ማስመረቁ ይታወሳል፡፡

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን Join and share በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ👍
👇👇👇
@ https://t.me/mega_tutor
@ https://t.me/mega_tutor
#MoE

⚡️የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም አጋማሽ ድረስ ይፋ ይደረጋል።

የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም 2016 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ ይፋ እንደሚደረግ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።

በጥቅምት 2016 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመጀመር ዕቅድ መያዙንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በ2015 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን ሲወስዱ የነበሩት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች፣ የመጨረሻዎቹን ሦስት ፈተናዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት አለመፈተናቸው ይታወቃል። እነዚህ ፈተናውን ያልወሰዱ ተማሪዎች በቅርቡ ፈተናቸውን እንደሚወስዱም አሳውቀዋል።

እነዚህ ተማሪዎች በዚህ ዓመት መጨረሻ ድረስ ፈተናቸውን እንዲያሚያጠናቅቁ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በኦንላይን እንደሚሰጥም ጥቆማቸውን አስቀምጠዋል።

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን Join and share በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ👍
👇👇👇
@ https://t.me/mega_tutor
@ https://t.me/mega_tutor
👍1
#ሪፖርተር

ትምህርት ሚኒስቴር የመማርያ መጻሕፍት ለማሳተም ያወጣውን ጨረታ የጃፓን ኩባንያ አሸንፏል።

ቶፕሀም የተባለ የጃፓን ኩባንያ በሰባት ቢሊዮን ብር ወጪ የኅትመት ሥራውን እያከናወነ ነው ተብሏል።

ኅትመቱ ባለፈው ዓመት የተከሰተውን የመማርያ መጻሕፍት አቅርቦት ችግር ለመፍታት እንደሚያስችል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል።

ድርጅቱ ኢትዮጵያ በመግባት ማምረት እስከሚጀምር ድረስ ለቀጣይ ዓመት የሚሆኑ 40 ሚሊዮን የመማርያ መጻሕፍት እንዲያቀርብ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ጥቂት መጻሕፍት፣ እንዲሁም እስከ ግማሽ ሴሚስተር ድረስ የተቀሩትን ለማስገባት ታቅዷል ብለዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን Join and share በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ👍
👇👇👇
@ https://t.me/mega_tutor
@ https://t.me/mega_tutor
የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር አመራሮች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ በትምህርት፣ በመምህራን ጉዳዮች እና በአጠቃላይ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ትኩረት ማድረጉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

መምህራን የደረጃ ዕድገት፣ የመኖሪያ ቤት እንዲሁም የደመወዝ ጥያቄ ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

ምስል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን Join and share በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ👍
👇👇👇
@ https://t.me/mega_tutor
@ https://t.me/mega_tutor
#WallagaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የመደበኛ እና የተከታታይ (CDEP) መርሐግብር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡

የሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የቅድመ ምረቃ እና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 21 እና 22/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ምዝገባው በዩኒቨርሲቲው ሦስቱም ካምፓሶች (ነቀምቴ፣ ጊምቢ እና ሻምቡ) እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡


ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን Join and share በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ👍
👇👇👇
@ https://t.me/mega_tutor
@ https://t.me/mega_tutor
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ የማካካሻ (ሬሜዲያል) ትምህርት ተከታታዮች ፈተና የሚሰጥበትን አቅጣጫ አስቀምጧል።



ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን Join and share በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ👍
👇👇👇
@ https://t.me/mega_tutor
@ https://t.me/mega_tutor
#Update

የሬሜዲያል ተማሪዎች ፈተና ከመስከረም 07 እስከ 10/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

የሬሜዲያል/ማካካሻ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም የተሰጠውን የማዕከል ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናው እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህም ፈተናው በ30 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 07 እስከ 10/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል።

ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥም ተገልጿል። #MoE

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን Join and share በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ👍
👇👇👇
@ https://t.me/mega_tutor
@ https://t.me/mega_tutor
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም በሬሜዲያል መርሐግብር ትምህርታቸውን በተቋሙ የተከታተሉና የማጠቃለያ የማለፍያ ውጤት ያገኙ ተማሪዎች በ2016 የትምህርት ዘመን አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጋር ጥሪ እንደሚደረግላቸው ገልጿል።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤት ሲገለፅና ጥሪ ሲደረግ፣ ለሬሜዲያል ተማሪዎቹም የምዝገባ ጥሪ ስለሚደረግ በትዕግሥት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን Join and share በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ👍
👇👇👇
@ https://t.me/mega_tutor
@ https://t.me/mega_tutor
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለሁሉም መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

የዩኒቨርሲቲው የ2016 ትምህርት ዘመን የመደበኛ መርሐግብር ነባር ተማሪዎች ምዝገባ 👉

• 3ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ፦ መስከረም 10 እና 11/2016 ዓ.ም

• 1ኛ ዓመት የግብርና ኮሌጅ ሚድ ካሪየር ተማሪዎች፦ ጥቅምት 5 እና 6/2016 ዓ.ም

• የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች፦ ጥቅምት 05 እና 06/2016 ዓ.ም

Note: ማስታወቂያው የሬሜዲያል ተማሪዎችን እንደማይመለከት ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።


ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን Join and share በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ👍
👇👇👇
@ https://t.me/mega_tutor
@ https://t.me/mega_tutor
👍1
🎊ውድ ቤተሰቦቻችን እንኳንአደረሳችሁ።


🌼  Happy Ethiopian New Year! 🌼

May this year bring joy, unity, and prosperity to all! #EthiopianNewYear #NewYear_2016
      
🌼 ይህ ዓመት  የደስታ ፣ የአንድነት እና የፍቅር  ያድርግልን!🙏


ዘንድሮም እንደአምናው ሁሉ አብራቹን እንደምቶኑ ባለ ብሩህ ተስፋ ነን😘

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/mega_tutor
👍1