ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሀዋሳ እየተከበረ ነው
*******************
ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሀዋሳ እየተከበረ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ ታህሳስ 19 የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በድምቀት ከሚከበርባቸው ደብሮች አንዱ ሀዋሳ ነው።
ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ በሺዎች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች እና ጎብኚዎች በዓሉን ታድመዋል።

“በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ ቋሚ አባል እንድትሆን ፍላጎት አለን”- አምባሳደር ታዬ
አል ዐይን አማርኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ጋር ስላለፉት ሁለት ዓመታት የተመድ ቆይታቸው፣ ስለ ተመድ ማሻሻያ፣ስለየዲፕሎማሲ ጫናዎች እና ሌሎችም ጉዳዮች ቃለመጠይቅ አድርጓል።
ኢትዮጵያ አፍሪካን ወክላ በዚህ መድረክ ላይ ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የተጀመረ ጥረት ይኖር ይሆን? በሚል ጥያቄ የቀረባለቸው አምባሳደር ታዬ፤
“በዚህ የጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ ቋሚ አባል እንድትሆን ፍላጎት አለን፣ ትልቅ ህዝብ እና ታሪክ ያለን ህዝቦች ነን”፤ ይሁንና በዚህ ጉዳይ በአፍሪካ የተለያዩ ውይይቶች በተለያዩ መድረኮች ይካሄዳሉ ብለዋል።
አምባሳደር ታዬ ከአል ዐይን ጋር ያደረጉት ሙሉ ቆይታ፤ https://am.al-ain.com/article/ethio

መቐለ ከተማ የስልክ አገልግሎት አገኘች
****************
በመቐለ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናገሩ።
በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የስልክ አገልግሎት በዛሬው ዕለት መቐለ ላይ የተሳካ ጥሪ ማድረግ መቻሉን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም 981 ኪሎ ሜትር የፋይበር ጥገና ተከናውኖ በ27 ከተሞች የስልክና ሌሎች የቴሌኮም አገልግሎቶችን ማስጀመር ተችሏል ብለዋል።
የቴሌኮም አገልግሎቱ ዳግም መጀመር በመቻሉ 61 የባንክ ቅርንጫፎችም ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግ እንደተቻለ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል።

👍1
የኤርትራ ሰራዊት ከአዲ ዳዕሮ መውጣት ጀመረ
አዲ ዳዕሮ እና አዲ ነብሪት በተባሉ የትግራይ ከተሞች ሰፍሮ የነበረው የኤርትራ ሰራዊት አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ተሰማ ።
ከሰሜን ምዕራባዊቷ የትግራይ ከተማ ከሽረ እንዳ ስላሴ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙት የአዲ ዳዕሮ እና አዲ ነብሪት ከተሞች በተደጋጋሚ የኤርትራ ሰራዊቶች ጥቃት ሰለባ የሆኑ ቦታወች መሆናቸው በስፋት ይነገራል ። ይህንንም ተከትሎ በህውሃት አመራሮች ተደጋግሞ በነዚህ ከተሞች ላይ ያነጣጠረ የአየር ድብደባ እና ጥቃት የኤርትራ ሰራዊት ፈጸመ የሚል ሮሮ ባሳለፍናቸው ወራት በተደጋጋሚ ተደምጦ አልፏል ። አሁን ላይ ታድያ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የውጭ ሃይሎች ከትግራይ መሬት መልቀቃቸው ስምምነቱ ላይ በመስፈሩ ይህንን መሰረት አድርጎ በነዚህ በሁለቱ ከተሞች ሰፍረው የነበሩ የኤርትራ ሰራዊቶች አካባቢውን ለቀው መውጣት መጀመራቸው ተሰምቷል ። ይህም ተግባር መንግስት ስምምነቱን ምን ያህል እያከበረ እና እየተገበረ እንደሚገኝ የሚያረጋግጥ ትልቅ ማሳያ ሁኗል።