SMI G-1 2020
78 subscribers
392 photos
8 videos
142 files
27 links
Download Telegram
Forwarded from SCHOOL OF MARVEL- ASELLA
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
For more information
0951022931
Teacher Abel English language class @Schoolofmarvel
Forwarded from SCHOOL OF MARVEL- ASELLA
Manni Barumsaa Maarvil galmee kutaa 9ffaa 17/11/2018 irraa kaasee eegale jiraa

ማርቭል ት/ቤት የ 9ኛ ክፍል ምዝገባ ከ 17/11/2018 ጀምሮ እያካሄደ መሆኑን እንገልፃለን
Forwarded from SCHOOL OF MARVEL- ASELLA
Forwarded from SCHOOL OF MARVEL- ASELLA
Forwarded from SCHOOL OF MARVEL- ASELLA
Forwarded from SCHOOL OF MARVEL- ASELLA
Barattoota kutaa 11ffaa fi 12ffaaf

Barnoonnii idilee bara 2019 wiixata 04/12/2017 kan eegallu ta'aa.
Barattoonni hanga ammaa hingalmoofne har'a jimaata hanga sa'aattii 10:30 qofa galmaa'uu ni dandeessu.

Koochoon keessan sa'aattii booda(07:00)

ለ 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ

የ 2019 መደበኛ ትምህርት ሰኞ 04/12/2018 የሚጀምር ሲሆን ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎች እስከ ዛሬ አርብ 10:30 ብቻ መመዝገብ የምትችሉ ይሆናል

ፈረቃቹ ከሰዓት ብኃላ 07:00 ነው
Forwarded from SCHOOL OF MARVEL- ASELLA
Forwarded from SCHOOL OF MARVEL- ASELLA
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ
===============================
በአገራችን እየተመዘገበ ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠልና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የአገሪቱን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት ለማሟላት በመንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡

ይህንንም እውን ለማድረግ ልዩ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የተደራጁትን የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራት ማዕከላት በማድረግ በዘርፉ ብቃት ያላቸውን ሙያተኞችን እያፈሩ ይገኛሉ፡፡

በመሆኑም በ2019 ዓ.ም የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 50% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና ኦንላይን (Online) በመስጠት መቀበል ይፈልጋሉ፡፡

የትምህርት መስኮች፡-

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
ኢንጂነሪንግ
- አርክቴክቸር
- ሲቪል ኢንጂነሪንግ
- ወተር ሪሶርስ ኢንጂነሪንግ
- ኬሚካል ኢንጂነሪንግ
- ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ማቴሪያል ሳይንስና ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሪካል ፓወር እና ኮንትሮል ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሮኒክስ እና ኮሚኒኬሽን ኢንጂነሪንግ
- ኮምፒዩተር ሳይንስና ኢንጂነሪንግ
- ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ

አፕላይድ ሳይንስ
- አፕላይድ ባዮሎጂ
- አፕላይድ ኬሚስትሪ
- ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ
- ፋርማሲ
- አፕላይድ ፊዚክስ
- አፕላይድ ጂኦሎጂ
- አፕላይድ ማቲማቲክስ

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

ኢንጂነሪንግ
- አርክቴክቸር
- ሲቪል ኢንጂነሪንግ
- ኬሚካል ኢንጂነሪንግ
- ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሪካል እና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ
- ኤሌክትሮሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
- ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ
- ኢንቫይሮሜንታል ኢንጂነሪንግ

አፕላይድ ሳይንስ
- ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ
- ፉድ ሳይንስና አፕላይድ ኒዩትሪሽን
- ጂኦሎጂ
- ባዮቴክኖሎጂ

የምዝገባ ጊዜ፡-
- ከነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ለሊቱ 6 ሰዓት ይሆናል፡፡

የምዝገባ ቦታ፡
- የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ https://stuoexam.astu.edu.et ወይም www.aastu.edu.et; www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፡- በድህረ ገፃችን የምዝገባው ቀን ካበቃበት በኋላ እናሳውቃለን ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡-
- በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-
· የፈተና ጣቢያዎቹ ያላቸው የመፈተኛ ቦታ ውስን በመሆኑ ይህንኑ አውቃችሁ ቅድሚያ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
· በቂ አመላካቾች የሌሉባቻው የፈተና ጣቢያዎች በቅርበት ወደሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ሊታጠፉ እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡
· ለፈተና የሚቀርቡት የአመልካቾች ስም ዝርዝራቸው እና የፈተና ጣቢያዎች በሚከተሉት ድረ-ገፆች፡- www.aastu.edu.et ; www.astu.edu.et እንደአመቺነቱም በe-mail የሚገለፅ ይሆናል፡፡
· አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፣ ማለትም (ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል፡፡
· ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል፡፡

· አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
· የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም፡፡
· በውጤታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከላይ በተጠቀሱት ድህረ-ገፆች ይገለፃል፡፡
· በመስፈርቱ መሰረት ያልተመረጡ አመልካቾች ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ይሆናል፡፡
· በፈተናው ዕለት ማንኛውንም የሞባይል ስልኮችን ይዞ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
· በፈተና ወቅት ያልተገባ ተግባር መፈፀም በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ከታች የተጠቀሱትን ድረ-ገፆች እና ቴሌግራም ቻናላችንን መጎብኘት ይቻላል፡፡

www.astu.edu.et; www.aastu.edu.et
Telegram:https://t.me/AdamaSTU_ASTU

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩ
ኒቨርሲቲ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ማስታወቂያ
የ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና  ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-
 
Ø የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን ከነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም ምርጫችሁን ት/ቤት መሄድ ሳይጠበቅባችሁ ባላችሁበት ቦታ እራሳችሁ በመሙላት እንድታሳውቁ እንገልጻለን።
Ø  ማስፈንጠሪያ (Link)  https://student.ethernet.edu.et/
ማሳሰቢያ፡-
v የህክምና፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች እና ከ6 ወር በታች ህፃን የሚያጠቡ እናቶች አስፈላጊውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባችኋል።
 
የትምህርት ሚኒስቴር