B̶r̶o̶k̶e̶n 💔💔💔
26.8K subscribers
7.22K photos
1.7K videos
3 files
218 links
@marakye22
#photo


#Tik_tok😅😅
#scholl_life📝
#sad_mood_picture💞
💓💕💞💗💖💌💘💔

#For any promotion @merii19 inboxme

Any comments 👉 @merii19
Cross @merii19


Join 🙏🙏 @marakye22
Download Telegram
ክብደት መጨመሪያ multivitamins

ለማዘዝ @merii19 inboxme
🙏🏼🙏🏼🙏🏼
ማደግ ማለት መቀባባት ዊግ መትከል መዝናናት ሚመስላችሁ ተሳስታችኋል

ማደግ ማለት ጥሩውን ከመጥፎ መለየት ለይተን ደሞ ከመጥፎ መራቅ

አሁን ላይ ተቀባብተን በጣም ቆንጆ የሆንን ይመስለናል ግን ነገ ላይ ልክ እንዳልነበርን እናውቃለን


ስለዚህ በ ወጣትነታችን በ እግዚአብሔር ቤት እናሳልፍ እሱን ብቻ እናስደስት ሰውች እንዲወዱን ብለን ያልሆነ ነገር ዉስጥ አንግባ

ያረጃል የዓለም ዝና! ጊዜያችንን በ አግባቡ እንጠቀም ነገ የተሻለ ነገር ለማግኘት እላለው

#በጉብዝናህ ግዜ ፈጣሪህ አስብ

ይሄ ማለት በወጣትነታችን ጊዜ እግዚአብሔር ማገልገል በ እግዚአብሔር ቤት መኖር እግዚአብሔር ማውራት ማለት ነው በወጣትነታችን ግዜ የራሳችንን ስሜት ወደ ፶ላ አድርገን እግዚአብሔር እንከተል እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ እንመራ


@marakye22 @marakye22
    🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

                  💙  ፅጌረዳ 🌹🔸


❤️  ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ❤️

አዘጋጅ ማኔ

                       #ክፍል_6️⃣3️⃣


ሆስፒታል ስንደርስ እህቴና ሰራተኛዋ ምሳ ይዘው ሊመጡ ወደቤት ሄደዋል ሌሎቹ ቁጭ ብለው እየጠበቁ ነበር።

አቶ ሳሙኤል ስቅቅ እያሉ ተጨነቄ አስጨነኳችሁ አደል ቤታችሁን ዘግታችሁ እዚህ ሆስፒታል ተቀምጣችሁ ልትውሉ ነው አሏቸው።
እናቴ በዛ ጣፋጭ አንደበቷ  ተው እንጂ እንደዚህ አይባልም አንተ ለኛ ልጃችንን ወልደህ አደል እንዴ የሰጠኸን እኛ አሁን ምን አደረግንልህና ነው ና ይልቁኑ አረፍ በል አለቻቸውና አረፍ አሉ።

ምሳችንን ይዘውልን መጡና በላን ።
ዶክተሩ ቁርጥ ያለውን ነገር እስኪነግረን እየጠበቅን ነበር ።

ማታ ላይ አቶ ሳሙኤልና አባቴ ዶክተሩጋ ገቡና አወሩት ።
ሲመለሱ ምን እንዳላቸው ለመስማት ጓጉተን እየጠበቅን ነበር።
ምናልባት ሆስፒታል ውስጥ አንድ ሳምንት ወይም 15 ቀን ካልሆነም ከዛ በታች ልትቆይ ትችላለች እንዳላቸው ነገሩን።

አቶ ሳሙኤል ሰብሰብ አደረጉንና በቃ አሁን ቁርጡን ስላወቅነው እናንተም ወደቤታችሁ ወደ ሀዋሳ ተመለሱ ናታኔም ከኔጋ ይቆያል አሉ።

አባቴ እኔ ከዚህ ለመሄድ ምንም የሚያስቸኩል ጉዳይ የለኝም እዚሁ ነው ምቆየው አለ።
እናቴም እኔ ቢያንስ አንዳንድ ቀን ሆስፒታል እያደርኩ እንድታርፉ አደርጋችኋለሁ እዚሁ ነው ምሆነው አለች።

እህቴም ቀጠለች ምንም ቢሆን ሚዜዬ ነበረች በደስታዬ ቀን ከጎኔ ቆማለች ሰርጌን አድምቃልኛለች ስለዚህ አሁን እሷ ሆስፒታል ተኝታ ለመሄድ የሚያስቸኩለኝ ጉዳይ የለም አለች።

አቶ ሳሙኤል ፈገግ አሉና መቼስ ልጄ ሆስፒታል ከገባች ጀምሮ የሚመጣውን ሰው አይታችሁታል  እኔ ከተማው ላይ የማላቀው የማያቀኝ ሰው ያለ እስከማይመስለኝ ድረስ ነው ሚሰማኝ ለማሂ ሰርግ አድማቂ የነበሩ ሚዜዎቿ አጃቢዎቿ መቀመጫ እስኪጠፋ የነበሩት እነዛ ሁላ እንግዶች ዛሬ የሉም  የመጡትም የይውጣልኝ ደረስ ብለው ለመመለስ ነው ።
እናንተ ግን በቃ እኔጃ
ፈጣሪ ሰዎችን ደስተኛ ሊያደርግ ሊያከበር ሲፈልግ ሰው ነው ሚሰጣቸው ሁላችሁንም አመሰግናለሁ።

ግን ችግር የለውም  በቃ ሂዱ እዚህ ምንም አንሰራም አሉ ።
እኔ ባይሆን እህቴ አዲስ ሙሽራ ስለሆንሽ ከባልሽጋ ብትመለሽ ባይ ነኝ እናቴና አባቴ ግን በናንተ ፍላጎት ይሁን አልኳቸው።

አዎ ልጄ በቃ እናንተ ሂዱና ባይሆን ትመለሻለሽ ከሆስፒታል ምትወጣ ቀን ቤቱን አሟሙቀሽ ትጠብቂናለሽ አለቻት እናቴ።
በቃ እናንተ እንዳላችሁ ብላ እህቴና ባሏ  በነጋታው ወደሀዋሳ ተመለሱ።

በሶስተኛው ቀን ማሂ መናገር ጀመረች ፖሊሶቹ በምን ፍጥነት እንደመጡ ሳይታወቅ መጡና መረጃ ልንወስድ ነው ብለው ወደ ውስጥ ገቡ ለሷ አንዳንድ ጥያቄዎችን ማቅረብ ጀመሩ ።
ማሂ ብዙ ሳትለፈልፍ የቀድሞ ባለቤቴ ነው እንደዚህ ያደረገኝ ከስራ ቦታ ወጥቼ እየሄድኩ ሲከተለኝ ነበር ።

የማይሆን ቦታ ላይ ስደርስ መኪናዬን ከአስፋልት አስወጥቶ እንዲገለባበጥ ለማድረግ ከኋላ መጥቶ ገጨኝ አለች።

አንቺ እሱ መሆኑን እንዴት አወቅሽ ከኋላ ከገጨሽ አሏት ፖሊሶቹ።

እኔ ከኋላ እየተከተሉኝ እንደሆነ ስላወኩ ተጠንቅቄ ነበር ስነዳ የነበረው እና መጥቶ ከገጨኝ ቡሀላ መስታዎቱን ከፍቶ ምን አይነት ጉዳት እንዳደረሰብኝ ቼክ እያደረገ ነበር ጋቢና አብሮት ጠቆር ያለ ፂማም ልጅ ነበረ አለች። አንዳንድ ጥያቄዎችን ከጠየቋት ቡሀላ ምስጋናቸውን አቅርበው  ለአቶ ሳሙኤል የልጆትን ባል ቤት ልታሳዩን ትችላላችሁ አሏቸው ...

እሺ ብለው አብረዋቸው ሄዱ ግን እሱ ቤት አልነበረም ።
አቶ ሳሙኤል ፊታቸው ጥቁር እንዳለ ተመልሰው መጡ ።

አየህ አደል ልጄ አንዳንድ ሰዎች ወደህይወትህ በግድ ጥላቻን ይጠራሉ።
ማሂ ምን ብትበድለው ምን ብታስቀይመው በትዳር ተጣምረው ሚስቴ ነሽ ብሎ የተቀበላትን ሴት ለመግደል ይሞክራል።

አንዳንድ ሰዎች ጭንቅላታቸው ከምን እንደተሰራ ይገርመኛል

የናቱ ወይ ያባቱ ገዳይ አደለች እንዴት ከመሬት ተነስተው ገና ለገና ተቀያየምን ብሎ እስከመግደል ይደርሳል ለነገሩ አንዳንድ ወንዶች ወንድነታቸውን የሚያረጋግጡት በሴቶች ላይ ነው።

እኔ ግን ፈጣሪ ይጠብቀኝ ብቻውን ካገኘሁት የኔም የሱም ህይወት ነው ሚበላሸው ቸኩዬ እሱ ላይ እርምጃ ብወስድ ከሱ በላይ እኔ እጎዳለሁ እንዴት ካልከኝ እኔ እሱን ሳጠቃው ወንጀለኛ እሆናለሁ እታሰራለሁ ለልጄ አባት መሆን አልችልም እቅፎቼ ውስጥ አትነቃም አብረን ጊዜ አናሳልፍም ብቻዋን እተዋታለሁ አሉኝ።
ይቅርታ አቶ ሳሙኤል በጣም አዝናለሁ ግን የማሂን ልብ እያወቀ ጨክኖ እንደዚህ ለማድረግ ካሰበ ልቡ ውስጥ የተቀመጠ አንዳች ትልቅ ሴጣን አለ ማለት ነው።
ለማንኛውም  ማሂን በስርአት እናውራት እስኪሻላት ፊታችን ባይቀየር ጥሩ ነው የባሰ ተጨንቀን እንዳናስጨንቃት አልኳቸውና ተያይዘን ወደ ውስጥ ገባን እናቴ እጇን ይዟ እያሻሸቻት በጨዋታ ሌላ አለም ውስጥ ወስዳታለች።

አየኋቸውና ፈገግ አልኩኝ እናቴ ባይኗ ጠቀስ አደረገችኝና ጨዋታዋን ቀጠለች ማሂ እንደለመደችው ፍንድቅድቅ እያለች ሳያት የሆነ ከሰማይ የወረደ ታምር ያለ ያህል ነው የተሰማኝ ያ የተሰማኝን ድንጋጤ ተስፋ መቁረጥ ባንዴ በፈገግታዋ ውስጥ ቀበርኩት።

ወደ ማታ ላይ እናቴን ይዣት ወደ ቤተክርስቲያን ሄድንና ስለቴን አስገባሁ።

ማሂ እንደተባለው 15 ቀን መቆየት አላስፈለጋትም በሳምንቱ ወደቤት መሄድ እንድትችል ፍቃድ ተሰጣት።

እንደነገ መውጣት ትችላለች ሲሉን ለእህቴ ደውዬ ነገርኳት ቃሏን ጠብቃ ወደአዲስ አበባ መጣች እናቴም እኛ ከመውጣታችን በፊት ቀድማን ወደቤት  ሄደች ።

11 ሰአት አካባቢ ላይ ማሂን ይዘን ወደቤት ስኔድ በአል አስመስለውት ሞቅ ደመቅ አድርገው ጠበቁን።
አባቴና አቶ ሳሙኤል ሳይታዩ ሹልክ ብለው ወጡና እንደለመዱት እኔን የሚያክል በግ ይዘው መጡ እኔ ወደ ቤተሰቦቼ የተቀላቀልኩ ጊዜ ሀዋሳ ላይ የተከበረው ደስታ አዲሳባ ላይ ተደገመ



ይቀጥላል.....



🔻ክፍል6️⃣4️⃣1️⃣0️⃣0️⃣Vote❤️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን! 😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
 💔 @marakye22
@marakye22
    🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

                  💙  ፅጌረዳ 🌹🔸


❤️  ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ❤️

አዘጋጅ ማኔ

                       #ክፍል_6️⃣4️⃣


ማሂ እንደተባለው ቀኝ እጇ ላይ እና ጎኗ ላይ የደረሰባት አደጋ እጇ መንቀሳቀስ እንዳይችልና በስርአት መራመድ እንዳትችል አድርጓታል ቁጭ ማለትም ብዙም አትችልም ።

እኛ ግቢውን አሟሙቀን እሳት እያነደድን ጥብስ እየጠበስን አንዳችን አንዳችንን ስናስተናግድ እሷ የተዘጋጀላት ፍራሽ ላይ ጋደም ብላ በፈንጠዝያ ታየናለች።

እየሰራሁ አይኔ ከሷ ላይ አይነቀለም አይኗ ከኔ ላይ አይነቀለም እንደልጃገረድ ስታሽኮረምመኝ ሳሽኮረምማት አመሸን።

ቡሀላ ላይ በላልተን ወደ መጠጥ ሲገባ ትላልቆቹም የራሳቸውን ወሬ እኛም የራሳችንን ወሬ ያዘንና ጨዋታውን አደራነው።

እህቴ እኔ ምልሽ ማሂ ግን እዚህ ቤት ውስጥ አንቺና አባትሽ ብቻ ስትኖሩ የመጠፋፋት አደጋ አጋጥሟችሁ አያቅም እእእ መንግስት ግን ይሄን ሁሉ ይዞታ ይዛችሁ እንዴት ዝም አላችሁ የላይኛው ሳሎናችሁ ብቻኮ 3 ቤተሰብ
የታችኛው 5 ቤተሰብ የሚያኖር ቤት ነው አንቺና አባትሽ ብቻችሁን ተሸክማችሁት ኖርር አላችሁ አደል አለቻት።

ማሂ ፈገግ ብላ ይሄ የምታይው ቤት ቤት እንዳይመስልሽ መሰረቱ የተጣለው በናቴ ባባቴ የደም ላብ ነው።
አባቴ ከዚህም በላይ ይገባዋል።

ከናቴጋ ሲጋቡ የኔን መታጠቢያ ቤቴን የምታክል ቤት ተከራይተው ነበር የሚኖሩት።
ያው ምን ዋጋ አለው እናቴ ይሄንን ሳታይ ተንደላቃ ለመኖር ሳትታደል ቀረች የሷን እጣ ፈንታ እኔ ወሰድኩት አለች እንባ እየተናነቃት።
የዛኔ እህቴ ደንገጥ አለችና አረ ማሂ እኔኮ ለቀልድ ነው ጨዋታውን ያነሳሁት ምኑን ከምኑ አገናኘሽው ገና መች ፈጣሪን አመሰግነሽ ጨረሽና ነው ወደለቅሶ የገባሽው ብላ ተቆጣቻት።


የዛሬው አጭር ስለሆነ ክፍል 65 ይለቀቃል like & share እያደረጋችሁ ጠብቁን


ይቀጥላል.....



  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን! 😀
@marakye22 @marakye22
    🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

                  💙  ፅጌረዳ 🌹🔸


❤️  ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ❤️

አዘጋጅ ማኔ

                       #ክፍል_6️⃣5️⃣



ስንሳሳቅ አመሸን ያ ድንጋጤ ሰሞኑን የነበረው ሀሳብ ጭንቀት ሆስፒታል የማደሩ ድካም ባንዴ ለማጥፋት እየሞከርን ያለን ነው ሚመስለው።

ማሂ ፈገግ ብላ ሁላችንንም በየተራ ካየች ቡሀላ አይገርምም ግን እንደቀልድኮ ሰፊ ቤተሰብ ኖረን ።

ያለምክንያት አደለም ገና እንዳየሁህ እንደዛ ያሳዘንከኝ መጥቼ መተኛት ያልቻልኩት።
ለማንኛውም ግን የናትህና ያባትህ ቤታቸውን ዘግተው መምጣታቸው ምን ያህል እንዳስገረመኝ አልገባችሁ አለች።

አረ ማሂ የኛ ወላጆችኮ እንደዚህ ናቸው ሀዋሳ ላይ በደግነታቸው በፍቅራቸው ነው ሚታወቁት ላንቺ ደሞ ይሄ ሲያንስብሽ ነው ምን አደረጉልሽና አልተሸከሙሽ ዋናው ነገር እንኳን ተረፈሽልን አለቻት።

ሰአቱ ወደሌሊቱ ሲቃረብ ሁላችንም ገባንና ቦታ ቦታችንን ያዝን።

ጠዋት ላይ እህቴ የማሂን ልብስ ቀይራላት ለቁርስ ይዛት መጣች።
ቁርሳችንን እየበላን እናቴና አባቴ ዛሬ እንሂድ መባባል ጀመሩ አቶ ሳሙኤልም እሺ መልካም እኔ ነኝ ማደርሳችሁ አሉ።
እነሱ አይሆን አንተ ታማሚ ልጅ ቤት ትተህ እኛን ለማድረስ እዛ ድረስ አትንከራተትም አሉ።

ምግቡን በልተን እስክንጨርስ እየተከራከሩ ማሂ እረጅም ሰአት ቁጭ ማለት ስለማትችል ወደ አልጋዋ ይዣት ሄጄ አስተኛኋትና ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን በመሀል ስልክ ተደወለላት ።
አንስቼ የተደወለላት ቁጥር አሳየኋት አላቀውም አንሳና ስፒከር ላይ አርገው ጆሮዬ ላይ ይዤ ማውራት አልችልም አለች።

እሺ ብዬ አነሳሁና ስፒከር ላይ አደረኩላት።

ሄሎ አለች።
ሄሎ አንቺ በረሮ አላት ከወዳኛው መስመር የሚመጣው የወንድ ድምፅ።

አቤት አቤት ምን አልክ አለች ኮስተር ብላ

ምን አልክ ነው ያልሽው ያልኩትማ መች ነው የጀመርነውን ምንጨርሰው እያልኩሽ አይገርምሽም እንደዛ ተገጭተሽ መትረፍሽ አላት።

የዛኔ ከሷ በላይ የኔ ፊት ቅይር አለ ።
አንተ የቀድሞ ባለቤቷ ነህ እንዴ አልኩት???!
ኦኦኦ ይገርማል ጎረምሳሽ እንዳለ አላወኩም ነበር የጎዳናው ልጅ ነህ አደል አለኝ እያፌዘ።

ስልኩን ይዤ ከተቀመጥኩበት ብድግ አልኩኝ ትሰማኛለህ ከእንዳንተ አይነት ከድንጋይ የባሰ ድንጋይ ከሆነ ሰውጋ በማውራቴ አፍራለሁ ግን አንድ ነገር ልንገርህ ወንድ ልጅ ከሆንክ ጓዳ ጓዳውን እየተደበክ ሴቷጋ ደውለህ አታስፈራራ እኔጋ ደውል ከሷጋ ለቀረህ ለእያንዳንዱ ጉዳይ እኔ አለሁ።
ሌላው የምነግርህ ነገር ምንም የወንድነት መስፈርት የማታሟላ ተራ ሰው መሆንህን ልነግርህ እፈልጋለሁ አልኩት።

ብሮ አፍህን በከፈትክ አደለም
ለማንኛውም የጀመርኩትን እጨርሰዋለሁ በልልኝ አለኝና ስልኩን ዘጋው።

ፈጠን ብዬ ሄጄ ለአቶ ሳሙኤል ስልኩን ሰጠኋቸውና ለፖሊሶቹ እንዲልኩላቸው አደረኩ።

ወደ ማሂጋ ስመለስ በንዴት ፊቷ ቀልቶ እያለቀሰች ነው።
ምኗ ደደብ ነኝ ከዚህ ጋር የሆንኩት
አሁን ላይ ከሱጋ ቆሜ ለታየሁት ሁላ እያፈርኩ ነው።

ቆይ እኔ ሳላስቀይመው ካፌ ክፉ ሳይወጣ ከሌላ ሴትጋ አልጋዬ ላይ ይዤው ።
ገመናው ሸፍኜ እንደፈለገ ይሁን ብዬ ከህይወቱ ስለወጣሁ ለኔ ይሄ ነው ሚገባኝ እእ።
ቆይ ዝም ስላልኩት የፈራሁት መስሎት ነው ወይስ ዘላለሙን እየተጫወተብኝ እንዲኖር ስላልፈቀድኩለት ነው።

ቆይ አባቴ በትንሽ ቀን ውስጥ ልክ ካላስገባዎ ምን አለች በለኝ አለች።

አቅፌ አፅናናኋት የራሴን ንዴት ወደጎን ጥዬ የሷን ማብረድ ጀመርኩ።

በድንገት ጭንቅላቴ ውስጥ አንድ ሀሳብ ተተኮሰ ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁን ማሂ ላይ ትኩር ብዬ እያፈጠጥኩ ለምን ወደ ሀዋሳ አኔድም ለምን ከዚህ አካባቢ ትንሽ እራቅ አንልም በዛውምኮ እናቴ አሪፍ አድርጋ ታስታምምሻለች እህቴም አሁን ስራ እየሰራች ስላልሆነ ቀን ቀን እኛጋ ትውላለች እኔም የቀሩኝን ጉዳዮቼን እጨራርሳለሁ ማሂ በኔ ይሁንብሽ ህክምናሽንም እዛ ሚገርም ሆስፒታል እንድትከታታይ እናደርጋለን በፈጠረሽ እሺ በይኝ አልኳት።

አይኗን ሳታሽ እሺ እኔ ደስ ይለኛል ግን አባቴስ አለች።

ችግር የለም እሳቸውም ስራ ሲኖራቸው እዚህ ሳይኖራቸውም ደሞ ሀዋሳ እያሉ መቆየት ይችላሉ ትንሽ ጊዜኮ ነው አልኳት።

እሺ ግን አባቴን ጠይቀው መጀመሪያ አለችኝ።





ይቀጥላል.....



ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን! 😀



@marakye22 @marakye22 @marakye22
Cats snapshot ለማንሳት ተጨማሪ ሶስተ ቀን ጨምረውል
airdrop ላይ ብቁ ለመሆን
5 ሰው ጋብዙ ወይ ደሞ ton ትራንዛክሽን ፈፅሙ
ለመጀመር 👇👇

http://t.me/catsgang_bot/join?startapp=dTMwdw6w4KunubLU5M-IF
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🥰
    🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

                  💙  ፅጌረዳ 🌹🔸


❤️  ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ❤️

አዘጋጅ ማኔ

                       #ክፍል_6️⃣6️⃣

ከክፍሉ ፈጠን ብዬ ወጣሁና ከሁሉም ፊት ቆሜ ለሁላችሁም ምነግራችሁ ነገር አለኝ በተለይ አቶ ሳሙኤል አልኳቸው።

ሁሉም ግራ ተጋብተው እያዩኝ አይናቸውን ከኔ ላይ ሳይነቅሉ ምንድነው ምንድነው አሉኝ።

ማሂ ከኛጋ ወደ ሀዋሳ ብትሄድ ምን ይመስላችኋል እስኪሻላት እኛጋ ትሁን አልኳቸው።

ሁሉም በጣም ደስ አላቸው።
አቶ ሳሙኤል ብቻ ያልጠበቁት ሀሳብ ስለሆነ ደንገጥ ብለው ዝም አሉ።

አይ ልጄ ተው እዚሁ ብትከታተል ይሻላታል ካይኔ እንድትርቅ አልፈለኩም ልጄ ሳይሻላት ድጋሜ መንገድ ለመሄድ ትቸገራለች አሁን ቁጭ ማለት እራሱ እንደማትችል ታውቅ የለ አሉኝ።

መልስ አጥቼ ዝም አልኩኝ ።
ለማንኛውም ቆይ ማሂን ላውራት ብለው ወደማሂጋ ሄዱ ።
እኛ ቁጭ አልን አውርተው እስኪጨርሱ እየጠበቅን እናቴ ጥሩ ሀሳብ ነው ያመጣኸው ልጄ እኔ እራሱ እስኪሻላት እዚህ ልሁን ወይስ ልሂድ እያልኩ ነበር አለችኝ።

አባቴ ደሞ እንደኔ እንደኔ ይሄ ነገር ለሳሙኤል ከባድ ስለሚሆንበት እዚሁ ብትሆን ባይ ነኝ ።
ምክንያቱም በደህናው ጊዜ እራሱ ለአይኑ አያምናትም ጭራሽ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆና ደሞ ካጠገቡ ስትርቅ መቋቋም ሊያቅተው ይችላል አለ

ለማንኛውም ያውሩና ይንገሩን አልኳቸው።

ትንሽ ቆዩና አቶ ሳሙኤል መጡ ።

እሺ በቃ ልጄ እንደዛ ከሆነ ነገ እንሂድ ዛሬ ልቦሶቸበን አስተካክሉላት ያንተንም አዘጋጅ ኮንትራት ዶልፊን ልያዝላትና ከኋላ በጀርባዋ ተኝታ ትሄዳለች መቀመጥ አትችልም ። ከዛ በፊት ከዶክተሩጋም በደንብ ላውራ ለፖሊሶቹ ምትሰጠው ያልጨረሰችው ቃል መስጠትም ካለ ትጨርስ አሉንና ስልክ መደዋወል ጀመሩ።

እኔና እህቴ ማሂጋ ገባንና ልብሶቿን ማስተካከል ጀመርን ።

አንቺ ምን ብለሽ ነው ያሳመንሻቸው ግን አልኳት አረ ምን ያላልኩት አለ ስንቱን እንደቀባጠርኩ ብታይ አለችኝ እየሳቀች።

የኔንም የሷንም ልብሶች አስተካከልን መዳኒቶቿን ከተትን ።

በነጋታው እንደተባለው እኔ እና እህቴ ከማሂጋ ዶልፊን ውስጥ ገባንና ከጀርባ ተኝታ ጉልበቴ ላይ ተንተራሰች።


አባቴና እናቴ ደሞ የአቶ ሳሙኤል መኪና ውስጥ ገብተው ከፊትና ከኋላ ተከታትለን ጉዞ ወደሀዋሳ ተጀመረ።

እህቴ የሷና የባሏን ከመጀመሪያው  የንግግር አንስቶ እስከትዳር እስከደረሱበት ያለውን ሂደት ፊልም በሚመስል መልኩ ተረከችልን።

ማሂ ሰምታት ስትጨርስ ፈገግ አለችና ታድላችሁ ግን ሁለታችሁም አፍቃሪ ልብ ነው ያላችሁ አለች ቀና ብላ አይኔ እያየች።

እናቴ ደወለችና ልጄ በቃ እኛ እንቅደማችሁ የተዘጋ ቤት ውስጥ ከምንገባ ቢያንስ በሩን ከፍተን  እንጠብቃችሁ ጎረቤት እንኳን ገብቶ እንዳይከፍተው በድንጋጤ ቁልፉን ይዜ ነው የመጣሁት እንጀራ ና ወጥ ደውዬ ስሩ ብያቸዋለሁ አለችኝ።


እሺ በቃ ችግር የለም ዞሮ ዞሮ የኛ መኪና መፍጠን ስለማይችል መቆየታችን አይቀርም አልኳት።
ወዲያው ከኋላችን የነበረው የአቶ ሳሙኤል መኪና እንደነፋስ ባጠገባችን ውልብ አለ።







ይቀጥላል.....



ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን! 😀


@marakye22 @marakye22
    🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻

                  💙  ፅጌረዳ 🌹🔸


❤️  ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ❤️

አዘጋጅ ማኔ

                       #ክፍል_6️⃣7️⃣


እኛም አንዱን ስናነሳ ስንጥል መኪናው ገጭ ባለ ቁጥር ካሁን ካሁን አመማት እያልኩ  እየተሳቀኩ ሀዋሳ ደረስን።

በምን ቅፅበት እንዳሰማመሩት አላቅም ቤቱን ፏፏ አድርገው ጠበቁን።

ጎረቤቶቻችን አንዳቸው እንጀራ አንዳቸው ወጥ አምጥተው ጉድ ጉድ እያሉ ነበር።
ማሂን አቅፌ ከመኪናው አወረድኳትና ወደቤት አስገባኋት ።

አቶ ሳሙኤል እዛ እስክንደርስ ስንቴ እንደደወሉ መቼስ ፈጣሪ ነው ሚያቀው።

ቡና ተፈላ ምግብ በላን ሚጠጣ ነገር ጠጣንና ለማሂ ልብስ ልትቀይርላት ወደ ውስጥ አስገባናት ማሂ የእህቴ ክፍል ልታርፍ ተወሰነና እቃዎቿን ወደሷ ክፍል አስገባንላት በዛውም ልብሷን ቀያይራላት ትንሽ እረፍት አደረገች።

ማታ ላይ የእህቴ ባል ፌስታል ሙሉ እቃ ተሸክሞ መጣ ለናቴ ጠጋ አለና ለማህሌት እንዲጠጋግናት እናንተም እንዳተቸገሩ ብዬ ነው ስጋ እንቁላል ፈሳሽ ነገርም ገዝቻለሁ ሌላ ሚያስፈልጋት ካለም ችግር የለም እንገዛለን  አላት።
እናቴ ግንባሩን ሳምም አደረገችውና አቀፈችው ልጄኮ የምርቃቴን ነው ያገኘችው አለች እንዳቀፈችው።

ማታ ትንሽ ተጫወትንና እህቴን ይዟት ወደቤታቸው ሄዱ እኔ የራሴ ክፍል
አቶ ሳሙኤልና ማሂም የእህቴ ክፍል አባትና እናቴም የራሳቸው ክፍል ቦታ ቦታችንን ይዘን አደርን።

እናቴ ገና ሳይነጋ ተነስታ ጉድ ጉድ ስትል ብዙም እንቅልፍ ስላልወሰደኝ ተነሳሁኝና ማገዝ ጀመርኩ ።

አይ ልጄ የዛን ቀን በድንጋጤ ሌማት ውስጥ ያለውን እንጀራ እንኳን ለሰው ሳልሰጠው ትናት ስከፍተው ጥጥ ሆኖ ጠበቀኝ ሌማቴ እራሱ ተበላሽቷል አለችኝ።
በቃ ሌላ እገዛልሻልሁ ለማሂ ብለሽኮ ነው ይሄ ሁሉ ብዬ ጠቀስ አደረኳት።

አደልል እእ እኔ ምልህ ግን የማሂና ያንተ ነገር ምኑም አልገባሽ አለኝ ያኔ እዚህ እንደመጣችሁ ጓደኛህ መስላኝ ነበር ።

ከዛ ነገሩ ሁላ ሌላ እንደሆነኮ አሁን ነው የተገለጠልኝ
ምኑ የተገለጠልሽ አልኳት።

ያው ሁለታችሁም ትዋደዳላችሁ ግን አብራችሁ አልሆናችሁም ቢሆንም ግን ወደፊት መሆናችሁ አይቀርም እኔ ታይቶኛል አለችኝ።

አይ እናቴ ላንቺኮ ሁሉም ይታይሻል አደል ለማንኛውም ፈጣሪ ያውቃል አሁን ቶሎ ቁርስ ሰርተን እናብላት እያልኩ ካፌ ሳልጨርሰው እህቴ በዛ በሌሊት መጣች።

እናቴ አየቻትና አይ የኔ ልጅ በዚህ በሌሊት ምን አስመጣሽ እረፍት አታደርጊም ነበር አለቻት።

አረ እማ ላግዝሽ ብዬኮ ነው ደሞ በቅርቡ ባሌን ይዤ ወደዚህ ቤት መግባቴ አይቀርም ስሄድ እየናፈቃችሁኝ ነው እዚህ በዝታችኋል እኔ ብቻ ማታ ተነጥዬ ስወጣ ሆድ ስለሚብሰኝ ከሚከራዩት ቤቶች አንዱን ስጭኝ እና እዚህ ልኑር አለቻት።

እናቴ ከት ብላ እየሳቀች አይ የኔ ልጅ አሁንምኮ ያው ነው እዚሁ ጎረቤቴ አደለሽ እንኳንም ከዚህ በላይ አራቅሽብኝ አለቻት እየተሳሳቁ አንዳቸው እንጀራ መጋገር አንዳቸው ደሞ ወጥ መስራት ጀመሩ እኔ በመሀል ቤቴ ለሁለቱም እቃ አቀባይ ሆኜ የሞቀ ጨዋታ ያዝን።

በመሀል ቡና አቀራረብኩላቸውና እህቴ ማፍላት ጀመረች እኔ እነማሂንና አባቴን ቀሰቀስኳቸውና ለቁርስ እንዲነሱ ነገርኳቸው ።

አባቷ አጣጥበው ልብስ ቀያይረው የእጇን ቁስል ቼክ አድርገው  ደግፈው ይዘዋት መጡ ።

ሁላችንም ክብ ሰርተን በአንድ ትሪ ቁርሳችንን በላልተን ስንጨርስ አቶ ሳሙኤል በቃ እኔ አዲሳባ ደርሼ ልምጣ ቢመሽብኝም መምጣቴ አይቀርም አስቸኳይ ጉዳይ ስላለችኝ ነው አሉ።







ይቀጥላል.....



ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️🀄️ሉን! 😀



@marakye22 @marakye22
Cherry game

✔️Tap tap
✔️Task መስራት ብዙ ከሰራችሁ 10$💵 withdraw ማድረግ ትችላላችሁ

Cherry game ደስ ሚለው ነገር
ልክ አንደ fintopio ነገር ነው የተለያየ phase አላቸው ሚቆየውም ለ 2 ሳምንት ነው 10,000 usdt ቶፕ 500 ውስጥ ለገቡ ሰዎች ይሸለማሉ 😳

ቦቱ Viral ስላልወጣ ብትጀምሩት መልካም ነው




Lemጀመር

https://t.me/cherrygame_io_bot/game?startapp=r_5716245371