||ማራኪ ♡ ልቦች||
29.4K subscribers
7 photos
24 videos
19 links
Cr; owner Mr✌🏻


Thanks everyone 😊
Download Telegram
~እጅግ በጣም የምወዳቸውና የምሳሳላቸው ሰዎች በሆነ ጊዜ ላይ ብፈልግም ባልፈልግም እለያቸዋለሁ። አብረን እስካለን ድረስ ግን ለነሱ ማድረግ የሚጠበቅብኝን በምችለው መልኩ ለማድረግ እሞክራለሁ።መለያየት ስሜቱ ቢከብድም ሕይወትን አያበላሽም። ይልቅ እኛ ነን መለያየትን ባለመቀበልና ባለማመን ሕይወታችንን የምናበላሸው። ወደድንም ጠላን እንደምንለያይ ማወቅ ይኖርብናል።

አብረን እስካለን እንዋደድ፣ እንፋቀር፣ እንተሳሰብ ግና መለያየት አይቀሬ መሆኑ እርግጥ ነው። የቱንም ያህል ብንዋደድ፣ ብንፋቀር፣ ብንፈላለግ፣ ብንተዋወስ ምንም ይሁን ምን አንድ ቀን ደስ በሚልም ይሁን በሚያስከፋ መልኩ እንሰነባበታለን። ወይ ስንሔድ እንታያለን አሊያም ሲሔዱ እናያለን።
በቁርዓን ውስጥ የዝሆን ምዕራፍ ተብላ የምትታወቀው ?
Anonymous Quiz
79%
ሱረቱል-ፊል
16%
ሱረቱል-ሁመዛ
5%
ሱረቱል-መሰድ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህ በቪዲዮ ላይ የምታዩት ግለሰብ የደምብ ልብስ ለብሶ በህግ ስር ሆኖ የፈጸመው ወንጀል እና ግልጽ የሆነ የእስልምና ጥላቻን የሚያሳይም ጭምር ነው..! በካሜራ እይታ ዉስጥ ሆኖ ሴትን ልጅ ሲደብድብ እንኳን ተዉ የሚለዉ እና የሚያስቆመዉ ህግ እነደሌለም ማሳያ ነው ።😡😡😡

ይህ ሰዉ ለእኛ ለሙስሊሞች ብቻም ሳይሆን ለሁሉም መማሪያ እንዲሆን በአደባባይ መቀጣት አለበት❗️❗️❗️


ከዋከብቶቹ 💫



            🀄🀄
​​​​​​​​╔══✩⋆✩˚⋆★⋆˚✩⋆✩★✩══╗
 ˚⋆ t.me/Islamic_Star_Team ⋆˚
╚══✩⋆✩˚⋆★⋆˚✩⋆✩★✩══╝
እኔ እና እንቁጣጣሽ
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ዕለቱ መስከረም 1 እንደመሆኑ በእንቁጣጣሽ ዝግጅት ጎረቤቶቻችን ሽር ጉድ ብለዋል የሰፈር ልጆች አዳዲስ ልብስ ለብሰዋል  አበባ ቆርጠው ይዘዋል ፤ የእኛ ቤት ግን ከወትሮ በተለየ ተቀዛቅዟል 😔 የተለየ ድምቀት አይታይም ቢሆንም ግን ከልጆች ጋር በጠዋት ዞረን የሳልናቸውን ስዕሎች ሽጠን የተወሰነች ሳንቲም ሰብስበናል አንድ ብር ስለመሙላቱ ግን እርግጠኛ አይደለሁም 😂 ጠዋት ተነስተን ገላችንን በታጠብን ጊዜ ግን እናታችን ለእኔና ለወንድሜ 1ነገር ብላናለች 🗣️ ''ዛሬ የሚመጣ እንግዳ ስላለ ልብሳችሁ እንዳይቆሽሽ ከቤትም እንዳትርቁ '' ይህች ቀጭን ትዕዛዝ መሆኗ ነው

እዛው ቤት ፊትለፊት እየተጫወትን ከረፋፈደ በኋላ አንድ ዶልፊን መኪና ከበራችን ደርሳ ቆመች እና እንግዶች እየወረዱ ወደ ቤታችን መግባት ጀመሩ በቁጥር 5-7 እንደሆኑ እገምታለሁ ግን ያልተለመዱ አይነት ናቸው ፤ ጀለቢያ የለበሱ አይነት ሰዎች አብሯቸው አሉ እነሱ ቤት እንደገቡ ተከትለን ገባን ከዚያም ትንሽ ከተጨዋወቱ በኋላ (የተነጋገሩትን በወል አላስታውሰውም) ከመሀከላቸው አንዱ ጀለቢያ ለባሽ እኔ የምለውን ተከትላችሁኝ በሉ አለ እሺ አልን ቀጥሎም

🗣️ ''አሽሀዱ አላ ኢላሀ ኢለላህ..... '' አለ እኛም ተከተልነው ፤ ከዚያም ከጎሮቤት የመጡ ወዳጆች እናቴን አባቴን ተነስተው እንደ አዲስ ሲያቅፏቸው አስተዋልኩ። በስጦታም ሁለት መስገጃዎች አንድ ለእናቴ አንድ ለአባቴ ተበረከተ ከዚያም ሸይኹ ቀጠሉ ስማችንን ጠየቁ እኔጋ ሲደርሱ ''አዱኛ''  አልኳቸው እሳቸውም ''ሰዒድ ብዬሃለው '' አሉ እኔ ሌላ ምፈልገው አለ አልኳቸው ማን አሉኝ ''አድናን'' አልኳቸው ፀደቀልኝ 💪

⁰◦በዚያ ዕለት ከመጡ ሰዎች በደምብ የማስታውሰው ሸይኹን ነበር ሸይኽ አብዱልሃሚድ (አሁን የመጅሊስ ባለስልጣን በወቅቱ የአጋሮ አላዛር መስጂድ ኢማም የነበሩ) ::◦⁰🥀

👉በጣም የሚገርመኝ እንግዶቹ ከመምጣታቸው በፊት ለምሳ የጠሩን ጎሮቤት ጋር ከመጀመሪያው ዙሁር ሰላት በኋላ ሄድን ግን በአንድ ድምፅ ስጋ አንበላም እናም ወይዘሮዋ ''ምነው እንግዶቹ ከምሳ በኋላ በመጡ ዛሬን ብቻ አብረን ምሳ በበላን '' (ማለታቸውን አስታውሳለሁ :: ◦⁰🥀

🥀⁰◦ከቤተሰብ መገፋት እና ብቸኛ መሆን ለተወሰነ ጊዜ ቢኖርም በኢስላም ያገኘናቸው ወንድሞች ከሁሉ በላይ ናቸው ◦⁰🥀

⁰◦ከመስከረም 1 በፊት በጣም ሲበዛ ሙዚቀኛ የመሆን ፍላጎት ነበረኝ ብዙም እሞክር ነበር ከዚያ በኋላ ግን እስከ ወዲያኛው አላህ በመረጠው መንገድ መራኝ አልሃምዱሊላህ ◦⁰🥀

👉 ዛሬ ዓመታትን ወደ ኋላ ተመልሼ ያን ቀን አስታወስኩት አለህ ምን ያክል መርጦ እስልምናን 🕌 እንደ ሰጠን አሰብኩት በተቃራኒውም ባይሆንስ ዛሬ ላይ የት ልሆን እንደምችል አሰብኩ 🤔 አለማሰብ ይሻላል

⁰◦መስከረም 1 ፦ አላህ እስልምናን የወፈቀን ቀን ለኛ አዲስ ዓመት አዲስ ውልደት አዲስ ህይወት ◦⁰🥀💚💚

ኻታማችንንም ያሳምርልን ዘንድ በዱዓችሁ አስታውሰን 🤲🙏

ይለናል አዲስ አመታችን
#አዱኛ ኩምሳ [Adnan Ahmed Al-Fewz]

    ➡️ الحمدلله على نعمة الإسلام⬅️ 

እኔም #ፋፊ 💫የከዋክብት ቡድን አባል አንዲህ አልኩ

ሙስሊም የመሆንን ፀጋ ለወፈቀኝ ረበልአለም አልሃምዱሊላህ🤲🤲🤲

#Al-Fewzን የመሰለ ሙስሊም ወንድም ስለሰጠኝ ኩራት ይሰማኛል 👳‍♀🧕


               ይ🀄🀄ሉን
​​​​​​​​╔═══✩⋆✩˚⋆★⋆˚✩⋆✩★══╗
 ⋆ t.me/Islamic_Star_Team
╚═══✩⋆✩˚⋆★⋆˚✩⋆✩★══╝
||ማራኪ ♡ ልቦች|| pinned «እኔ እና እንቁጣጣሽ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 ዕለቱ መስከረም 1 እንደመሆኑ በእንቁጣጣሽ ዝግጅት ጎረቤቶቻችን ሽር ጉድ ብለዋል የሰፈር ልጆች አዳዲስ ልብስ ለብሰዋል  አበባ ቆርጠው ይዘዋል ፤ የእኛ ቤት ግን ከወትሮ በተለየ ተቀዛቅዟል 😔 የተለየ ድምቀት አይታይም ቢሆንም ግን ከልጆች ጋር በጠዋት ዞረን የሳልናቸውን ስዕሎች ሽጠን የተወሰነች ሳንቲም ሰብስበናል አንድ ብር ስለመሙላቱ ግን እርግጠኛ አይደለሁም 😂 ጠዋት ተነስተን…»
• መልካም የሆነ አስተሳሰብ ለህይወት ወሳኝ ነገር ነዉ፡፡ ዛሬም ይሁን ነገ መልካም የሆነ አስተሳሰብ ካዳበርክ መጥፎ የሆኑትን ገፅታዎች ለማለፍ አይከብድህም

• የስራ አለቃህ ሁሌ ትክክል ነዉ፡፡ ፀሃይ በደቡብ ትጠልቃለች ብሎ ቢያወራልህ ትክክል ነህ በለዉ ምክንያቱም 'እድገት' ሲመጣ አይንህን ቁልጭ ቁልጭ ከማድረግ ታድናለህ

• ብር ካለህ የአስተሳሰብ ሁኔታህ በሆነ ደረጃ ይለወጣል እንዲሁም ልትደሰትበት የምትችላቸዉን ነገሮች በቀላሉ መግዛት ትችላለህ ነገር ግን ብር በራሱ ደስታን ሊፈጥርልህ አይችልም...አስታዉስ ብር ላወቀበት 'መልካም ባሪያ' ላላወቀበት ደግሞ 'መጥፎ አለቃ' ነዉ

• ካሁን በኋላ ባለዉ አስር አመት ዉስጥ ያለህን ጊዜ ሁሉ ተጠቅመህ ስራ ትሰራ ይሆናል፡፡ በጣም ታታሪ ከመሆንህ የተነሳ ጤንነትህን ሙሉ ለሙሉ እርግፍ አድርገህ ትተኸዋል፡፡

ከ 10 አመት በኋላ ያሰብከዉ ሚሊየን እጅህ ላይ ገብቶ ታየዋለህ፡፡ ሚሊየነር ሆነህ የምትፈልገዉን በቀላሉ ለመግዛት አቅም ይኖርህ ይሆናል...

ግን ያንን ሁሉ ብር ከያዝክ በኋላ ለሚመጣዉ ሌላ 'የመከራ አመታት' ምክንያቱ ጤናህ መቃወሱ መሆኑ ይገባሀል፡፡ የደከምክበትን ብር በሙሉ ጤናህን ለመመለስ ታፈሳለህ...መጨረሻዉ ኪሳራ ብቻ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡ ስለዚህ ጤናህን ከጎንህ አድርገህ ስራ!

• 99 ፐርሰንት የሚሆነዉ የፍቅር ግንኙነት መስጠትና መቀበል ነዉ፡፡ የምትሰጠዉ ነገር ከሌለህ የሚሰጥህን ሰዉ ማግኘት ሞኝነት ነዉ

• ነገሮች እንዳልነበሩ ሲሆኑብህ “አንተ ሰዉ ደህና ነህ?” ብሎ ሊጠይቅህ የሚችለዉ ብቸኛ የሰዉ ፍጥረት እናትህ ሆና ታገኛታለህ

• የፌስቡክ ጓደኞችህ አቅምህን ጊዜህንና ወጣትነትህን በባዶዉ ይበዘብዙታል ስለዚህ ሰዉ ምረጥ

• ሰዉ በተሰበሰበበት ንግግር አዋቂ ከሆንክ አለምን ልታሸንፍ ትችላለህ

• ኤ...ቲ...ኤም ካርድ ማለት ገንዘብህን የሚጨርስ መርዝ ስለሆነ ቢቻልህ ባይኖርህ አሪፍ ነዉ፡፡ ካለህ ደግሞ ቤት አስቀምጠዉ(ብርህ ምን ያህል እንደሚመናመን ለማወቅ ከፈለክ ይዘኸዉ ዙርና ታየዋለህ...ለዚህ መቼም ልምልልህ አይገባም!)

• 'አላማህን አሳድ' ብሎ ብዙ ሚሊየን ሰዉ ለራሱም ለሌላዉም ሲያወራ ትሰማዋለህ...ግን የሚያሳዝነዉ ወደተግባር ለመለወጥ ከባድ ነዉ!

⭐️መልካም ቀን ይሁንላቹ⭐️

┊  ┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ┊  ✯
┊  ┊  ┊  ☆
┊  ┊  ✯
┊  ☆
✯                   
@islamic_star_team
ፍቅራቹ ውስጣዊ ከሆነ

በዱኒያ ጉዳይ አትለያዩም
ዋናው በ#حب መተሳሰር ነው
ዛሬ በፈረጆቹ ኦክቶበር  7 ነዉ ይህ ቀን 1948 በፍልስጤም ታሪክ ውስጥ "አል-ናክባ" (አደጋው) በመባል ይታወቃል።🇸🇩

እስራኤል ነፃነቷን ያወጀችበት ቀን ሲሆን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ከመኖሪያ ቤታቸውና ከመሬታቸው የተፈናቀሉበት ቀን ነው።


የጨለማ ቀን ተብሎ የሚወሰደው ለዚህ ነው።


• የጅምላ መፈናቀል፡ የነጻነት አዋጁ ከጎረቤት አረብ ሀገራት ጋር ጦርነት ፈጠረ።
ይህም 700,000 የሚገመቱ ፍልስጤማውያን ከመኖሪያ ቤታቸውና ከመሬታቸው ተፈናቅለዋል።
ብዙ ፍልስጤማውያን ስደተኞች በመሆን ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰደዱ።

• የትውልድ አገር ማጣት፡ የእስራኤል መፈጠር የትውልድ አገራቸውን በብቃት ወሰደ።
የተባበሩት መንግስታት የመመለስ መብታቸውን ቢጠይቅም ብዙ ፍልስጤማውያን ወደ ቤታቸው መመለስ አልቻሉም።

• ቀጣይነት ያለው ትግል፡- በ1948 የተከሰቱት ክስተቶች ለቀጠለው የእስራኤል እና የፍልስጤም ግጭት፣ በአመጽ፣ መፈናቀል እና በፖለቲካዊ ውዝግብ ለታየው።
ይህ ግጭት በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ህይወት ላይ ተጽእኖ
ማሳደሩን ቀጥሏል።

🇸🇩🇸🇩🇸🇩🇸🇩🇸🇩🇸🇩🇸🇩🇸🇩🇸🇩🇸🇩

• ኦክቶበር 7 ለፍልስጤማውያን ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ቀን ቢሆንም፣ የ1948ቱ ክስተቶች ውስብስብ ናቸው እና በተፈጠረው ነገር ላይ የተለያዩ አመለካከቶች አሉ።

• ለበለጠ መረጃ የፍልስጤምን ትረካ ወይም ገድል እናንብብ ።

ድል ለፍልስጤማውያን

🇸🇩🇸🇩🇸🇩😭😭😭💪💪💪


              ይ🀄🀄ሉን
​​​​​​​​╔═══✩⋆✩˚⋆★⋆˚✩⋆✩★══╗
 ⋆ t.me/Islamic_Star_Team
╚═══✩⋆✩˚⋆★⋆˚✩⋆✩★══╝
ፊርዓውን  በሺህ የሚቆጠሩ ህፃናትን አረደ። ዓላማው በርሱ ዘመን ሙሳ የሚባል ፍጡር እንዳይኖር ነበር። ግን በሚደንቅ ተዓምር ሙሳን በቤቱ አሳደገው።

“የአላህ ውሳኔ ተፈፃሚ ነው። አትጠራጠር!”


"وَاللَّهُ غَالِبٌ عَلَىٰ أَمْرِهِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ"

"አላህም በነገሩ ላይ አሸናፊ ነው፤ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡"( ሱረቱል ዩሱፍ: 21)