ማንነት/ IDENTITY
452 subscribers
44 photos
3 videos
18 files
14 links
ራስን ማወቅ ጥበብ ነው… የማንዳስሰው ነገር አይኖርም

ከመጽሃፍት አለም
ሃይማኖታችን
ፍልስፍና
የኑሮ ዘይቤያችን
ፖለቲክስ
የፍቅር ህይወታችን…ሁሉም ሁሉንም ማንነታችን ይዳሰሳል

ለየትኛውም ጥያቄ ወይም አስተያየት እና cross @betsiroyal ይጻፉልን…
@maninet1
@maninet1
Download Telegram
የጊዜ_አጠቃቀም_ጥበብ_በዶክተር_ኢዮብ_ማሞ_@only_amharic_books_on_telegram.pdf
16.8 MB
የመፀሀፉ ስም ፦ የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ
ፀሐፊ ፦ በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ገፅ ፦ 149
መጠን ፦ 16.8MB
@maninet1
👍1
ሰላም እንዴት ናችሁ የኛ 558 ታማኝ ቤተሰቦች?
የተለያዩ ሐሳብ ያልችሁ እዚህ ግሩፕ ላይ አድሚን መሆን የምትፈልጉ @betsiroyal ላይ አውሩኝ።
ማንነት/ IDENTITY pinned «ሰላም እንዴት ናችሁ የኛ 558 ታማኝ ቤተሰቦች? የተለያዩ ሐሳብ ያልችሁ እዚህ ግሩፕ ላይ አድሚን መሆን የምትፈልጉ @betsiroyal ላይ አውሩኝ።»
ኔግሮ የሚባል ፍሬንድ ነበረኝ ፀባይኛ ነው፣ ሌባ ነው፥ እናቱን ይወዳታል፥ ትምህርት አይገባውም፤ ተንኮል፣ ኳስ ፣ጆተኒ ፣ ትረባ ጎበዝ ነበር።

በአንድ ሴሚስተር መቶ እና ሁለት መቶ መፅሃፍ ይሰርቃል መቼ? ...እንዴት?...ከማን?... አላውቅም!

መጨረሻ ላይ ውጤቱን እየሳቀ ይነግረኛል።
አንድ ቀን እንኳን ሲሰርቅ ተይዞ አያውቅም !

የሰረቀውን መፅሐፍ ሲሸጥ አብሬው ሄጄ አውቃለሁ። ከሚገዙት ጋር ደምበኛ እንደሆነ ሰላምታ አለዋወጣቸው ያስታውቃል። አሻሻጡ የሰረቀ ፣ ሳይለፋበት ያመጣ አይመስልም፤ በቸልታ አይደለም። በርጋታ እንደትልቅ ሰው... "አይሆንም...፣ ይቅር...፣በቃ፣ ጨምር " እያለ ነው ።

እናቱን "ሸቅዬ... እዛ ማዶ ያሉት ሃብታም ሰዎች፤ ለእናትህ ስጣት ብለው ብር ሰጡኝ" እያለ እንደሚሰጣት ነገሮኝ ያውቃል ።

ሰባተኛ ክፍል ፣ ስምንተኛ ክፍል እያለን እናቱን ያግዛት ነበር ። ይወዳታል፤ አወዳደዱ እንደትልቅ ሰው ነው። "ማሚዋ ደብሯታል ...አሟታል. . . ገበያ ቀዝቅዞባታል" እያለ ያስብላታል።

ከጓደኛው አይሰርቅም። ለጓደኛው ለኔ ለሚለው ሰው ይሳሳል።

አይኖቹ ትናንሽ ናቸው፣ አካባቢውን በትኩረት ያያል፣ ከወሬ ሁኔታን ያያል። ሌባ መሆኑን ብዙ የሩቅ ሰዎች አያውቁም።

ኔግሮ ቁርንጫጭ ፀጉር ያለው፣ ድቅቅ ያለ ገላ ያለው፣ ሲስቅ ቀጭን ድምፅ የሚያወጣ ልጅ ነበር ።

አንዳንድ ቀን ይፎርፍና ሜዳ ጥግ ውኃ ልኩ ጋር ብቻውን ይሆናል ። ዝም ይላል ኳስ አይጫወትም። ቀጭን ድምፅ እያወጣ የሚስቃት ሳቅ አትኖርም። ለመኮረጅ ብዙ አይሰቃይም።

...ጨዋታ ያበዛል...።

ስለ አባቱ አላውቅም፤ እናቱ ግን ትምህርት ቤታችን በር ጎን ላይ ቃርያ ፣ ቲማቲም፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ድምብላል፣ ኮሰረት፣ ስኳር ድንች ...ምናምን ይሸጣሉ። ብዙ ደንበኛ ያላቸው አይመስለኝም። ስንወጣ ስንገባ የደራ ገበያ አንድም ቀን አይቼ አላውቅም ።

ኔግሮ የትምርት ቤት ስሙ መቆያ ነው። እኛ ነን ኔግሮ የምንለው።

እኛ ትምህርት ቤት የሚማሩ የሰፈሩ ልጆች ሲጠሩት ሰምተን መሰለኝ መቆያን ትተን ኔግሮ የምንለው።

መቆያ የሚባለው ክላስ ስም ሲጠራ ብቻ ነው። ኔግሮ ሲባል ነው እሱም ደስ የሚለው።

የሆነ ቀን ሃይሚ ግርማ መፅሃፍ ጠፍቶብኝ ኔግሮ ሰጠኝ አለችኝ። ጠየኩት "ከራሷ ቦክመህ ለራሷ ገጫሃት ኣ?" ስለው ፤ ሲስቅ የሚያወጣትን ቀጭን ድምፅ አውጥቶ ሳቀ "ባክህ እኔ እንደኔ ችስታ እናት ካለው ቤተሰብ አልሰርቅም "አለ ።

ከስምንት ወደ ዘጠኝ ስንዘዋወር ኔግሮ ታስሯል አሉን። ስሰማ "ዕድሜው ለእስር ደርሷል ወይ?" ብዬ ያኔ አልጠየኩም።

የመንግስት ትምህርት ቤት ስለተማርን ለብዙ ነገር ከዕድሜያችን በላይ ነበርን። የሚታሰሩት በግሩፕ የሚጣሉ ልጆች ስለነበሩ ብዙ አልገረመኝም።

መስከረም አስራ ሰባት ቀን ኔግሮ ሞተ አሉን። እናቱን ስናያቸው ጥቁር ለብሰዋል፥ ጉስቁልናው ብሶባቸዋል። ጉሊት የደረደሩት ከዚህ ቀደም ለመሸጥ ከሚደረድሩት በዐይነትም በመጠንም ቀንሶ አየሁ ።

ሞትን ያኔ ነበር በቅርብ ያወኩት ....በቅርብ የማውቀው፣ ሲያወራ የሰማሁት፣ አብሬው የተጫወትኩት ጓደኛዬ ሞተ ሲባል። ያኔ ነው ለመጀመሪያ ግዜ ያመንኩት።

የታሰሩበት ክፍል የነበረው ካቦ መቶት ነው ይላሉ፤ አንዴ ፖሊስ መቶት ነው ይላሉ፤ አንዴ ታሞ ነው ይላሉ ....
ኔግሮ ሞተ። እውነት ነበር!

"ልጅ ይሞታል እንዴ?!" አልኩኝ
ለምን መቆያ አሉት ግን እናቱ??
በዛ ዕድሜው እንዴት በዛ ልክ አሰበላቸው??
በምን ይሆን የሚፅናኑት??
ለምን ሌባ ሆኖ ለጓደኞቹ ታመነ??

እንዴት የሰረቀውን እንደትልቅ ሰው አስቦ ተከራክሮ ሸጠ?? ላለፋበት ነገር እንዴት ዋጋ ሰጠ?? ለምን ምንም ከሌላቸው ሰዎች አልሰርቅም አለ??

በዛ ዕድሜው እንዴት አረጀ ?
እሺ ይሁን መርህ እና ሌብነት እንዴት አብሮ ሄደለት!!

እኔንጃ ኔግሮ ግን ሞተ አሉ !!!

By Adhanom Mitiku

@maninet1
4👍1
ዕድሜዋ ወደ አርባዎቹ እየገሰገሰ ነው....በህይወት ውጣውረድ የዛለ ፊቷ አሁንም ድረስ ድንቡሽቡሽነቱን አላጣም። ዘውትር ለብሳት በምትዞረው አንድ ሺቲ ሙሉ ከተማውን ከጫፍ እስከ ጫፍ ታካልለዋለች። ካልነኳት ማትነካ ብቸኝነትንና ባይተዋርነትን የመረጠች ብቸኛ ነፍስ ናት። ፀጉሯን ማንጨብረር ወይም እንደ 90ዎቹ አፍሮ አርጎ ማቆየት ያስደስታታል። በዛ ድንቡሽቡሽ ገጿ እና ሺ ሀሳብ ቢያጠቃውም ፍንክች ባላለ ሰውነቷ እዚህም እዛም ትባዝናለች።
.
" ሰሚራ " ማህበረሰቡ እብድ የሚል ቅፅላ ሰጥቶ ቢያገላትም ፤ ለኔ ግን የተነጠቀችው ወጣትነት ፤ የተነጠቀችው ህልሟ ጎልቶ ይታየኛል። እደርስበታለሁ ካለችበት ፤ እኖረዋለሁ ካለችው ህይወት ተብትቦ ያደናቀፋት ማህበረሰብ ቀፅላ ሰጥቶ ቁስሏ ላይ ሌላ ቁስል የጨመረላት ምስኪን ነፍስ። የዛሬን አያርገውና አይምሮዋ ከመታወኩ በፊት እንደማንም ጤነኛና ለፍቶ አዳሪ ነበረች። በአንድ ወቅት ለምርመራ በሄድችበት ጊዜ የአባላዘር በሽታ እንዳለባት በሀኪሞች ይነገራታል። ከህይወት ጋ ግብግብ በገጠመችበት ወቅት ፤ አጋዥ ደጋፊ በሌላት ወቅት ይሄን መስማቱ ለእሷ የሞት ታህል ነበር።
.
ዐቅመ ቢስነቷ የእጇ ማጠር ፈውስን ነፍጎ በሽታዋን አበረታባት። ዕለት ተዕለት እየፀናባት ማህበረሰቡ የሚያስተውለው ደረጃ ሲደርስ ሁሉም አገለላት። ተፀይፎ በቃሽኝ ከማለት አልፎ ቅስምን የሚሰብሩ ቃላት እያቀበለ ጨርቋን አስጣላት። ከምላሳቸው ያወጧት ስንዝር ቃል ህልምና ውስጥኗን የቀረቻትን ጥቂት ተስፋ ይዞት ገደል ገባ። ጣት ጠቆሙባት መታመሟ ሳያንስ እብድ ነሽ ብለው የእብደት አክሊል አላበሷት....አሜን ብላ መኖር ቀጠለች።
.
ሳያት ታሳዝነኛለች ፤ እንዲህ ካረጋት ማህበረሰብ ጋር አሁንም ድረስ ተቻችላ ትኖራለች። ከሁሉ ከሁሉ ስታረገው ሳይ የሚያስደስተኝ አንድ ነገር አለ ። ብር እጇ ላይ ከሌለ መሃል አስፓልት ላይ ወጥታ መንገድ ትዘጋለች። ሚያውቋት ሹፌሮችም ባህሪዋን ስለሚያውቁ ገንዘብ ይሰጧታል።
.
ይሄን ስታረግ ሳይ ውስጤ ይረካል። ከመንገዷ ያደናቀፏትን ለደቂቃዎችም ቢሆን መንገዳቸውን አደናቅፋለች። ምትቀበለው ገንዘብ ለሞራሏ ካሳ ባይሆናትም ከኑሮ ወጪ ግን ይታደጋታል። ፖሊስ ቢመጣ ሰማይ ቢገለበጥ ከተቀመጠችበት ፍንክች አትልም።  ታድያ በተቀበለችው ገንዘብ ቡና ልትጠጣ የጀበና ቡና ሻጮች ጋር ትሄዳለች። ማያውቋት ፈርተው የከለከሏት እንደው ትንሽ ግርግር መፍጠሯ አይቀርም። አምነው ለሰጧት ግን ሂሳበቸውን ሰጥታ ሲኒ በስርዓት መልሳ ካገኘች ጫት ካላገኘች ገረባ ሸክፋ ጥጓን ይዛ እየቃመች አልያም ተኝታ ቀኗን ታሳልፋለች።
.
ሚግባቧት ፍቅር ይሏታል ለሌቹ ደሞ በስሟ ይጠሯታል። ከወደደችህ በፍቅር ከጠላችህ ደሞ በስድብ አቀባበል ማድረጓ የተለመደ ነው። አንድ ጊዜ በመንገድ ሳልፍ ምን አበሳጭቷት እንደሆነ ባላውቅም ውሃ ደፍታ አጥምቃኛለች። ብቻ የአንደበታችን ኃይል እንደምናስበው ቀላል አይደለም። መጠገን ከሚችለው በላይ መስበር ይችልበታል። ይች ሴት ምን አልባትም አለውልሽ ሚላት ቢኖር መጨረሻዋ እንዲህ ባልሆነ ነበር። ለኛ ተራ እና ፌዝ መስለው ሚታዩን ቃላት በለሌላው ህይወት ላይ እንደ ደውል ቀን በቀን ያቃጭላሉ።

[ ጥሩቤል ]

@maninet1
4👍1
የጥቁር ልብስ ልክፍት

« ለቅሶ አለብኝ... ልብስ ምረጥልኝ» ብላ የተከፈተ ቁምሳጥኗ ፊት ለፊት አቆመችኝ። የተጠቀጠቀ የጥቁር ልብስ መአአአአአት።

'ይጥቆር እንጂ ደግሞ ለለቅሶ ልብስ መረጣ የምን ቅብጠት ነው። ' አልኩ በሆዴ ... ታዝቤያት። እጄን በግዴለሽነት ሰድጄ አንዱን ጥቁር ጎተትኩትና ፊቷ ዘረጋሁት። ቀሚስ ነበር።

“ ውይ ... ይሄንን ቀሚስማ ሰዓሊው ወዳጄ ሲሞት ለቅሶ ደርሼበታለሁ ፤ አልለብስም።»

«ለለቅሶ የለበስሽውን ቀሚስ አትደግሚም? »

«ሀዘን ይደገማል? » ጥያቄዬን በጥያቄ። «በል ሌላ ምረጥ!»

ምን አከራከረኝ፤ ያነሳሁትን ወለል ላይ ጥዬ ሌላ ጥቁር መዘዝኩ። ባለአንገት ሹራብ።

«ዘፋኙ ጓደኛዬን ቀብሬበታለሁ እሱን። ቀይር»

ሆሆ... ጥዬ ሌላ መዘዝኩ። ሸሚዝ

« የጋዜጠኛ እህቴን አስከሬን በሱ ነበር የሸኘሁት። »

ጣልኩ። አነሳሁ። አንዱን ቀብራበታለች።
ጣልኩ.. አነሳሁ። ለአንዷ አንብታበታለች።
ወለሉ በጥቁር ልብስ፣ ጆሮዬ በሙታን ፕሮፋይል ተሞላ።

እንደ ድንገት አንዷን ሳብኳት። የምታምር ጥቁር ሱሪ። አማረችኝ።

«አታምርም? »

«በጣም ታምራለች። ለምን ይህቺን አትለብሻትም? »

«ቆጥቤያት ነውኮ። በጣም የምወደው ሰው ሲሞት ነው የምለብሳት። »

«ማን ሲሞት?»

«አንተ ነሃ የኔ ፍቅር!»

« ያድኅነነ ከመዓቱ ይሰውረነ ! ምነው በናትሽ»

«ከልቤ ነውኮ። የዛሬ ወር ሾፒንግ ወጥቼ ተሰቅላ ሳያት ትዝ ያልከኝ አንተ ነህ። እንዴት እንደምወድህም ያወቅኩት ያኔ ነው። »

« እርፍ!»

« እርፍ ስትል ነውኮ እለብሳታለሁ ያልኩህ! በዛ ላይ ሰሞኑን እያሳለህ ነው... »

«ምን በወጣኝ ነው የምትወጂኝ በማርያም? ካልጠፋ ሰው እኔን ለምን ወደድሽኝ በሩፋኤል?! »

« ኧረ አንተ ብቻ አይደለህም ውዴ። ያንተን እንደውም ከገዛሁት ቆየሁ። ቁም ሳጥን ውስጥ አልከተትኳቸውም እንጂ... አባቴ... መምህሬ... ክርስትና እናቴ ፣ የእህቴ ባል ፣ ያ ደሞ አቀናባሪው... በየተራቸው ሲታመሙ ጊዜ... “ድንገት ከሞቱ ብዬ” የምለብሰው ገዝቼ አስቀምጫለሁ። እኛ የኪዳነምሕረቱ ቄስ... እኚያ ሰባኪው አወቅካቸው? የምወዳቸው ? ቄሱ... ? ከሰሞኑ ታመዋል ሲሉ ሰምቻለሁ። ከዛሬው ቀብር መልስ... ለሳቸው ለቅሶ የሚሆን ነገር ታጋዛኛለህ »

አሃ... !
ለካ አልቃሾች አዲስ ጥቁር ሲሸምቱ..፣ አዲስ ድንኳን ሲጎትቱ፣ አዲስ ሙሾ ሲሸመድዱ፣ አዲስ አለቃቀስ ሲለማመዱ... መደንገጥ ነበረብን?

ለካ የሞት መላዕኮቻችንን ከምንጠብቅ ፣ አልቃሾቻችን አዲስ ጥቁር ልብስ እስኪገዙ ብንጠብቅ፣ መች እንደምንሞት ይገለጥልን ኖሯል !?

አሳዘነችኝ።
ቁም ሳጥን ሙሉ ልብስ አገላብጣም፣ ለዛሬው ለቅሶ የምትለብሰው ጥቁር አላገኘችም። በርግጥ... እኔ ጋር ገና ያልለበስኩት ጥቁር ካፖርት አለ። «ልስጥሽ?» አልላት ነገር ፈራኋት።

«ሲያምር! እኔ ስሞት ለብሰኸው ትቀብረኛለህ!»
ብትለኝስ?
©ERMI

@maninet1
👍21😨1
“ሰባቱ ማሕበራዊ ኃጢያቶች”

በፈረንጆቹ አቆጣጠር በOctober 22, 1925 ጋንዲ (Mohandas Gandhi) በየሳምንቱ በሚያሳትመው Young India በተሰኘው የዜና መጽሔቱ ላይ “ሰባቱ ማሕበራዊ ኃጢያቶች” (The Seven Social Sins) የተሰኘን ጽሑፍ አስፍሮ ነበር፡፡

እነዚህ ዘመን-ዘለል እውነታዎች የግላችንንና የሕብረተሰባችንን ወቅታዊ ልምምድ በመገምገም ለማስተካከል ድጋፍ እንደሚያደርጉልን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

1. ስራ የሌለው ብልጽግና (Wealth without work)

2. ሕሊና የሌለው ደስታ (Pleasure without conscience)

3. ባህሪይ የሌለው እውቀት (Knowledge without character)

4. ግብረ-ገብ የሌለው ንግድ (Commerce without morality)

5. ሰብዓዊ ርህራሄ የሌለው ሳይንስ (Science without humanity)

6. መስዋእትነት የሌለው ኃይማኖት (Religion without sacrifice)

7. መርህ የሌለው ፖለቲካ (Politics without principles)

EYOB MAMO
4
ከታላቅ ወንድሜ ጋር ነው የምኖረው።
የቤት ኪራይ እና የአስቤዛ ወጪ በእርሱ ነው። የእኔ ኃላፊነት የራሴ ወጪዎች ብቻ ነበሩ። ደሞዝ እንደተጨመረልኝ ያወቅኩ ቀን በቃ ማን ይቻለኝ...'አንተ ማን ስለሆንክ ነው ይኼን ሁሉ ወጪ የምታወጣው? እኔ ለማን ሆነና ቀን ከሌት የምሮጠው?' ተይ ግድ የለሽም ቢለኝም...የማንም ልቅምቅም የሰው ልክ አያውቅም ..ዘራፍዬዬዬ ምናምን ብዬ ወጪህን የምጋራ ነኝ አልኩ....ማን ይቻለኝ የዛን ቀን አካሄዴ ሁሉ ተቀየረ ...የቤቱን ቁልፍ ጣቴ ላይ እያሽከረከርኩ መሄድ ጀመርኩ(የባለቤትነት ስሜት ተሰማኛ)
በአንተ የአስቤዛ ዘመን እኮ የተመጣጠነ ምግብ በልተን አናውቅም...አመዳችን ቡን ብሎ የሚያየን ሁሉ ወላጅ አልባ እየመሰልነው ምፅ እያለ ከንፈሩን እየመጠጠ አይደል እንዴ የሚያልፈው...በቃ አሁን ታናሽህ ደርሳልሃለች አልኩት...ትዕዛዞቼም በዙ..ድምፅህን ከፍ አድርገህ አትሳቅ ጆሮዬ እስከዛሬ የተጎዳው ይበቃል..የማስበው ሳላወራ ይግባህ ለከርስህ ስለፋ ውዬ ደክሞኝ ነው የመጣሁት ምናምን..ኧረ ምን ያላልኩት አለ
በቃ ነገ ቅዳሜ ስለሆነ ወጥቼ አስቤዛ አደርጋለሁ ብዬ ተኛን። አልነጋ ሁላ አለኝ ነው የምላችሁ..አይነጋ የለ ነጋ.."ደግሞ ተጋድመህ ጠብቀኝ አሉህ..ተነስተህ ቤቱን አፀዳዳ" ብዬ ወጣሁ። ከቤት አወጣጤ እንደ ቶሚ(የጄሪ) ሲያሸንፍ አይነት አካሄድ ነበር። ራይድ ይዤ ሄድኩ። (ለወትሮው ከወንድሜ ጋር ነበር የምሄደው ...እኔ እገዛዛለሁ...እሱ በስልኩ transfer ያደርጋል ...ስንመለስ ሸከማውንም ያግዘኛል)
የምገዛዛቸውን ነገሮች ገዛዝቼ ከፋፍዬ የቀረኝን ብር ሳይ ጠላታችሁ ይሟሽሽ ሟሸሽኩላችሁ። ደግሞ ገና ዘይት እገዛለሁ..የቤት ኪራዩንም አለሁበት ብዬዋለሁ እኮ🙆‍♀...እንደምንም ሀይሌን ሰብስቤ ዘይቴን ልግዛና ከዚህ ልጥፋ ብዬ ..ስንት ነው እለዋለሁ 1650 ነው አለኝ...አመተ ምህረት ነው በለኝ ወንድሜ👀 ..ምን ያልኩ መስሎህ ነው? የዘይት ዋጋ ነው እኮ የጠየቅኩህ..ደገመው አንዳች ይደገምበትና..ማለት በቃ አልቻልኩም አጥወለወለኝ...ወደላይ ሊለኝም አሰበ...ዘይት መች ነው እዚህ የደረሰው...እንኳን በራይድ ልመለስ ለኩሊም አልከፍልም ብዬ በአናቴ ተሸክሜ ላብ በላብ እየሆንኩ ጉዞዬን ቀጠልኩ..የሚያልበኝ የወጪው ነው እንጂ የእቃው ክብደት አይደለም..ያን ሁሉ አፌን ከፍቼበት አሁን ምን ልለው ነው የሚለውም ሀሳብ ሰቅዞ ይዞኛል...ለካ እስከዛሬ የቻለኝ መቻል🥹..ቤት ደርሼ አገባቤ እንደ ጄሪ(የቶሚ) ሲሸነፍ አይነት ነበር...ኩምሽሽ ብዬ ገባሁ። "እስኪ የፎከርሽዋ ልጅ...ላመጣጥንልህ ነው ምናምን ያልሽዋ የገዛዛሽውን እንይ" ብሎ ሲያይ ከሱ ዘመን አስቤዛ ያነሰ እንጂ የጨመረ ነገር አልነበረም። "የታለ ዘይት?" አለኝ "ወንድሜ እኔ አስቤዛ ነው እችላለሁ ያልኩት"
"እና ዘይት ምንድነው?"
"እንዴ ዘይትማ 18 ሞልቶት ከአስቤዛ ወጥቶ ራሱን እንደቻለ ነገሩኝ እኮ..ምነው እስከዛሬ ብትነግረኝ.. በሽታ ላይ ወድቄልህ ነበር...እንዲህ አይነቱን ነገር ከስር ከስር ንገረኝ እንጂ" ሳቀብኝ ለጉድ "ሳቅህ እኮ የዚህ ቤት ውበት ድምቀት ነው ወንድሜ ሳቅ...እኔ ልሳቀቅልህ አንተ ሳቅ"
ሳቁ ሲያባራ "የቤት ኪራዩ ስንት እንደሆነ ልንገርሻ ከእንግዲህ ከፋይ ነኝ ብለሽ አልነበር?"
"ማ እኔ?...ተው እንዲሁም ቋፍ ላይ ነኝ ቀጥ እንዳልልብህ እንዳትነግረኝ...ሲጀመር ጋንጃ በሉባንጃ አስጭሰውኝ ነው ..የደሞዝ ጭማሪውን ወረቀት ሲሰጡኝ የሆነ ነገር ቀባብተውበት ነው..እኔ እኔን አልነበርኩም..ትላንት ያወራሁትን ሁሉ እርሳልኝ🤲" ብዬ ስሜው ወደ ቀደመው ኑሮዬ ተመለስኩ።

☑️ል.you

@maninet1
9
ዝንብን ያስናቃት አፈጣጠሯ ሳይሆን አዋዋሏ ነው::

አዋዋል እንምረጥ🙌
4🥰2
📗" ማንበብን የሚያውቅ ተራራን እንደሚወጣ ሰው ነው።

በወጣበት ልክ የሚያየው ነገር እየሰፋለት ይሄዳል።
እማራለሁ ብሎ ዘወትር ማንበብ ዕለት ዕለት ወደ ከፍታ እንደ መውጣት ያህል ነውና ብዙዎችን ነገሮች እንደ ማየት ነው።"

👉ክቡር ዶክተር ከበደ ሚካኤል👈
ከንጹህ ቆዳ የተሰሩ ወብ ቦርሳዎች

$ 2500 birr

🛵 ነጻ ዴሊቨሪ

በብዛት ለሚረከቡ ቅናሽ ይደረጋል።

ሌሎች ቦርሳዎችን እርስዎ በሚፈልጉት ዲዛይን እንሰራለን።

አድራሻ ቦሌ
ይደውሉልን 0944354184
🥰2
ያንድ ምሽት አሳብ
(በእውቀቱ ስዩም)

በሺህ ፈረስ ጉልበት፥ በሺህ ግመል አቅም
ሺህ ጊዜ ቢራመድ፥ ሰው ከቤቱ አይርቅም::

ስጥል ዋልኩኝና፥ ስወድቅ አመሸሁ
ትግሉ ሲበረታ ፥ ወደ ቤቴ ሸሸሁ ፥
ሌቱ ጣራየ ላይ ፥ እንደ እንጀራ ሰፋ
እፍ አልኩት ኮከቡን ፥ እንደ ኩራዝ ጠፋ::

እንግዲህ ምን ቀረኝ?
ምንድነው ያማረኝ?
ወገግ
ፈገግ -ልበል?
ፊትሽን አስቤ?
አልጋ ላይ ልንበልበል
እንቅልፍን ከጎሬው ፥ እንደ ጋኔን ስቤ?

ወዲህ ውብ ትውስታ፤ ወዲያ ንጹህ አልጋ
የቱ ይመረጣል? ያም ተድላ፥ ያም ጸጋ
ገላ ሲስለመለም፤ ልብ ይቀሰቀሳል
ለጊዜውም ቢሆን
እንቅልፍ እና ፍቅር መከራን ያስረሳል።፨
3
😉 ስሚ man ያች diaspora'ራዋ ወሰደችኝ እኮ, ቁንጅናዬን ይንሳኝ! ኤሄን ጭዌ ለራሱ ከdenver colorado ሆኜ ነው ምፅፍልሽ

እንዴዴዴዴ አላስታወስካትም ልጅቱዋን? እንዲያውም የሆነ ክብሮ hotel ቀጥራኝ lobster ካልጋበዝኩህ ብላኝ በuria ማዳበሪያ ይሁን በdape ማዳበሪያ ይሁን, በምን እንደፋፋ የማይታወቅ ግድንግድ በረሮ ካልበላህ ብላኝ ደንግጬ ያመለጥኩዋት ቸከስስስ? እኔ ልብላው እሱ ይብላኝ ማይታወቅ ምግብ አቅርባቡኝ!!!? ......እንዴዴዴዴ እሺ በሌላ ቀን ቀለል ያለ ምግብ ልጋብዝህ ብላ ሩዝ በ chopestick አቅርባልኝ ልበላ እንደምንም የያዝኩትን ሩዝ ልጎርስ ስል እንጨቱ አዶልጦኝ እንጥሌን ያስቦጠጠችኝ??? አዎዎዎ እሱሱሱዋ ወሰደችኝ አኮ እናታ አገር America, ታዲያስ ማንዬ ገባሁልሽ እኮ ምርጡዋ

ግን man አሁን አሁን የኔ ቅሌት መቼም normal ሆኑዋል አ?, ገና america ከመግባቴ በሳምንቱ ቀልኩልህ እኮ

ምን ገጠመኝ መሰለህ, ልንሄድ አከባቢ ምን አለችኝ

እሱዋ : ቢኒዬ አሁን አንተ State ሄደህ የአገሩ system እስኪገባህ ትንሽ ጊዜ ይወስዳል plus መንጃ ፍቃድ እስክታወጣ ምናም for a while ቤት ነው ምታሳልፈው እሺ, እስከዛ የውጭውን ስራ እኔ እሰራለው"..... አለችኝ

እኔም : normallll ነው! ምንም እንዳታስቢ, my femin side ቦታው ላይ ነው, የቤቱን ስራ እኔው ጉድ ጉድ እላለው "...... አልኩልህ

.... እና man እቺ ልጅ አመጋገብዋ ወጣ ወጣ ያለ ስለሆነ እነ motherን በርበሪ, ሽሮ, ተልባ አዘጋጁልኝ ብዬ አዘጋጅቻለው,

ከዛማማ አማሪካዬ ገባሁልሽ, manዬ እዚ የCBE ፎቅ ምናምን እያልን እንገረማለን እዛ ግን የCBE'ን የሚያክል ህንፃ ጎጆ ቤት በለውውው, እዚ ኮሪደር ምናምን እንላለና እዛ man ኮሪደር normal ነውእእእ በስማም

ታዲያ የሆነ ቀን እሱዋ ስራ ሄዳ ቤት ብቻዬን አዛ ሆንኩልህ, እና ሰሙኑን ደረቅ ምግብ ነገር ስንበላ ስለነበር ለምን ተልባ አልጠጣም አልኩልሽ, ሆዴን ላለሰልስ

motherሩዋ የቁዋጠረችውን ስፈታው ጥሬ ተልባ ነበር የቁዋጠረችልኝ....... "ቲሽ ምን ሁና ነው?" ብዬ ተናድጄ ተልባዬን ልቆላ ትልቅ ድስት ውስጥ አስገባሁልሽ, እሰከዛ sofa ላይ ደቅ ብዬ "ተይ ደማም ተይ ደማም
የበሽታን ነገር ለሃኪም ይሰጡታል
የአጋንንትን ነገር ለፀበል ይሰጡታል
የሃገርን ናፍቆት ለማን ይሰጡታል
ተይ ደማም ተይደማም".....እልልሃለው በሳምንቴ

እናማማማማ ተልባው ሞቅ ሱል ቀውጢ አረገው "ጦ ጦ ጦ ጦ ጦሽሽሽ ጦ ጦ ጦ ጦ " ይልልሻል, እኔም ጨርቄን ይዜ ድስቱን እንደ ፋንዲሻ አነቃንቅልሻለው

ልጨራርስ ስል በራችን በሃይል ተንኩዋኩዋ ጉዋ ጉዋ ጉዋ

"this is the police open the door!!!! open the fucking door!!!"

እንዴ የምን policeeee ነው? ምንድነውውው....እልልሃለው, በመስኮት ወጣ ብዬ ሳይልህ እሳት አደጋ መኪና ቆመዋል, አባዲና የለበሱ ምናምን አሉ, የs.w.a.t መኪና ምናምን ሰፈሩን ከበውታል ከታች

ምን ተፈጥሮነው ብዬ በሩን ከፈት አርጌ አንገቴን ሳጮልቅ አንገቴን ስበው እንደ የItalian restaurant chef የ pizza ቂጣ ወደላይ እንደሚወረውረው ወርውረው አንደ Randy Orton RKO መሬት ላይ ፈጠፈጡኝ, ሁለት እጄን ይዘው እያዳፉ police መኪና ውስጥ አስገብኝ...ትልቅ ወንጀል እንደሰራ እንደ O. J. Simpson በመኪና ታጂቤ ጣቢያ ወሰዱኝ.....

ለካ በተልባ ሆዴን ላለስልስ ብዬ የጣድኩዋት ተልባ ስትንጫጫ apartement ውስጥ ያሉ ሰዎች ደንግጠው 911 ደውለው አሸባሪ ህንፃ ውስጥ አለ ብለው ጠቁመዋል.....አይ ተልብነት ተንጫጭተሽ አሳሰርሽኝ ማላቀው አገር

መጨረሻ ላይ ቸከሱዋ ወታ ነው calturale food ምናምን ብላ በዋስ ያስፈታችኝ

ደሞ ምንድነው fam? ፍቅር ቀንሰናል🤔 ሚደረገውን እናርግ እንጂ! share, like, comment ምናምን እ? መቼም በ video መጥቼ አልጠይቅ እ 🤭 ለሰፊው ህዝብ እንድረስ እንጂ, ሰው ልሁንበት እኔም 😉 ጭዌአችንም ኑሮ ላንገላታው ደርሳለት ይፍታታ....
አንድ ጓድኛዬ የሁለት አመት ፍቅረኛው ታማበት ፀበል ነገር ይዟት ይሄዳል ወደ ገዳም!

እንደወሰዳትም "አንተ የseyጣን ነገር ነው  መለፍለፍ  ጀመረች ሳምንት እንቆያለን" ብሎ ደወሎ አሳወቀኝ!

በመጨረሻም በሳምንቱ ከፀበል መመለሱን ነገሮኝ  እንገናኝ ብሎኝ ተገናኝን...

ያው እኔም እንዳገኘውት እንዴት ሆነች ተሻላት ወይ ምናምን ብየ ጠየኩት!

"አዎ!...ግን  የሷን ነገር አታውራብኝ " ምናምን አለኝ

ነገሩ ግራ ሲገባኝ ምን ተፈጥረ? ምናምን ስለው ...መለያየታቸውን ነገረኝ!

ግራ ገብቶኝ የታመመች ልጅ ወስደህ ፀበል  አስጠምቀሃት (seytan ኬዙ ሲሻላት ) ለምን ተለያያችሁ?... ስለው

እሱም ቀጠለና "ባክህ ከፀበል ስንወጣ 'ይቅርታ መለያየት አለብን አለችኝ! ራሷ...'  እኔም ደንግጨ ለምን ? ስላት ...'አንተን የሚያፍቅርህ እኔ አልነበርኩም ሰይጣኑ ነበረ " አትለኝም መሰለህ"....ብሎ ነገረኝ ....

By Jah mac

@maninet1
🤣21
ሁሌም የሴቶች ዶርም ድረስ መጥቶ ሸኝቶኝ ሲመለስ ባለማመን ያዩታል።
«ሔለን ግን ሙድ እየያዝሽብን ነዋ! ያን ሁሉ ወንድ ያባረርሽው ይሔ ፉንጋ ጋር ለመሆን ነው?» ትላለች አንደኛዋ።
«እስኪ ተያት ምን ታውቂያለሽ? ራቁቱን ያዬችው እሷ!» ብላ ሌላኛዋ ታሽካካለች።
እኔም አስከፋናት ብለው እንዳይደብራቸው እስቅላቸዋለሁ። ዋና ምክኒያቴን ከሚያውቁብኝ የጠረጠሩት እውነት እንደሆነ እንዲሰማቸው ባደርግ ይሻለኛል።

ለሰው ባይመስልም ፉንጋው የፀሎቴ መልስ ብቻ ሳይሆን ጨለማ ክፍል ውስጥ ያገኘሁት ሻማዬ ነው።
«ሔሉዬ ሌላ ቅፅል ስም ጠፍቶ ነው 'ሻማዬ' የምትይኝ?» ይለኛል።
«ሻማዬ ካላልኩህ ችቦዬ ነው የምልህ...የቱ ይሻልሀል?»
«አይ ሻማው ይሁን በቃ!» ይላል እየተቅለሰለሰ።

አንዲት ፀበል ለፀበል የምትመላለስ ታላቅ እህት አለችኝ። ሰዎች መንፈስ ይዟት ነው እያሉ ያወራሉ። እኔ ግን ባሏን ፈትታ ከመጣች ቡኃላ የዘመድ አዝማዱን ወሬ አትችለው ብላ እንዳበደች አውቃለሁ። ከዛ ጊዜ ጀምሮ ፀሎቴ አንድና አንድ ብቻ ነው። «ጌታ ሆይ የምወደውን ሳይሆን የሚወደኝን ስጠኝ!»

ለዛ ነው ሻማዬ የፀሎቴ መልስ ነው የምለው። የመጀመሪያ ቀን ሰውነቱ በላብ ተጠምቆ፣ እጁ እየተንቀጠቀጠ፣ መተንፈስ አቅቶት እየቃተተ ሲጠይቀኝ እንደማገባው ወስኜ ነበር። የግቢውን ወንዶች ሁሉ መልሼ እሱን የጠበስኩት እነሱ እንደሚሉት የተለዬ ነገር አግኝቼበት አይደለም። ሪስክ መውሰድ ስለማልችል ነው።

የፈሪ ሰው ጥቅም?...ቀድሞ አያጠቃም!

ግቢ ውስጥ በኔ ምክኒያት ያልደረሰበት ግፍ የለም። ለሁሉም ታዋቂ ካፕሎች ቅፅል ስም ሲሰጡ እኛን ማን ቢሉን ጥሩ ነው? "Beauty And The Beast" ሆሆ!
ተረባውን ችሎ አለፍ ሲል ደግሞ መምህራኖች ግሬድ ያበላሹበታል። ጉልበተኞች ዱላ የቀላቀለበት ማስፈራሪያ ያዘንቡበታል። ዘበኞች እንኳን ባቅማቸው ያዋክቡታል። ሁሉም እንደየስልጣኑ ይበድለዋል።
«ሻማዬ ከዚህ በላይ እንድትጎዳ አልፈልግም» ስለው
«ቀላል ነው ብዬ አልዋሸሽም። ሽልማቴ አንቺ እንደሆንሽ ሳስበው ግን 'ኧረ ያንሰኛል ጨምራችሁ ምቱኝ' ልላቸው ሁላ ያምረኛል!»

እያሳዘነ ያስቀኛል።

ገፍተው ገፍተው ለራሱ ያለውን አመለካከት እንዳወረዱበት የገባኝ የአመቱ መጨረሻ ላይ ነው። እሱ ተመራቂ ስለነበር ቀጣይ አመት እንደማንገናኝ ገብቶት እያለቀሰ መጣ።
«አንተም ስራ ልታገኝ የምትችለው እዚሁ አዲሳባ ነው። እኔም እዚሁ ነው የምማረው! ምን የተለዬ ነገር ተፈጠረና ነው የምታለቅሰው?»
«አንድ ነገር ብቻ ቃል ግቢልኝ!» አለ አሁንም እያለቀሰ!
«እሺ ምንድን ነው?»
«እስክትመረቂ ድረስ የፈለግሽው ወንድ ጋር ሁኚ! ከዛ ቡኃላ ግን ተመልሰሽ ወደኔ ልትመጭ ቃል ግቢልኝ!»

ምንም አላልኩትም። በቆመበት ጥዬው ሔድኩ። ምን ባደርገው ነው ሊተማመንብኝ የሚችለው? እኔስ በዚህ ደረጃ ከሚወደኝ ወንድ ውጭ ሌላ ምን እፈልጋለሁ? ከሶስት ቀን ቡኃላ የሻማዬን ልብ ያረጋል ብዬ ያሰብኩትን ትልቅ ውሳኔ ወሰንኩ።

ሲያዬው አዲስ እንደተወለደ ህፃን ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ። ለነገሩ እኔም ከዛ ያነሰ ግብረመልስ አልጠበኩም። ይሔንን ፊት ለዘላለም እንዳይጠፋ አድርጌ ጀርባዬ ላይ ተነቅሼለት ለቅሶ ሊበዛብኝ ነው?

የሚያስቀው እንራራቃለን ብዬ ፊቱን ተነቅሼለት ሌክቸረር ሁኖ እዛው ግቢ ቀረ። የሚያሳዝነው ደግሞ ተማሪዎች በገቡ በመጀመሪያው ሳምንት ሁሉም ስለታቱዬ አወቁ።

የፈሪ ትልቁ ችግር?....ምርኮኛ አያያዝ አይችልም!

«ለማን ተናግረህ ነው?» ብዬ ሳፈጥበት...አብሮት ሌክቸረር ለሆነ ሰቃይ ጓደኛው ብቻ መናገሩን ነግሮ ይቅርታ ጠየቀኝ። እኔም ከተያዙ ቡኃላ መንፈራገጥ ጥቅም የለውም ብዬ ተውኩት።

የግቢው አየር ባንድ ጊዜ ተገለበጠ። ሻማዬ የግቢው ቁጥር አንድ ተፈላጊ ወንድ ሆኖ ቁጭ አለ። እኔ ደግሞ ስወጣ ስገባ የተረባ መለማመጃ ሆንኩ። አንዴ ወጣቶች ተወራርደው አስገድደው ልብሴን ገልጠው፣ ታቱዬን ካዩብኝ ቡኃላ ከሀዘን የወጣሁበት ቀን ትዝ አይለኝም።

ሻማዬ ሊጠብቀኝ ቀርቶ ቶሎ ቶሎ ሊያገኘኝ ራሱ ጥረት አያደርግም። እኔ ነኝ የምደውልለት። እንዲያውም አልናገርም ብዬ እንጂ አልፎ አልፎ የግቢው ታዋቂ ሴቶች ከቢሮው ሲወጡ አያለሁ። በአንድ ወቅት ሊነካኝ ከብዶት ሲንቀጠቀጥ የነበረ ሰው፤ ዛሬ መዳፉ ላይ ሲያገኘኝ ጨብጦ ሊያፈርጠኝ ሲዳዳ ባዬው...ለመረዳት ከበደኝ።

የሆነ ቀን ጉዳዩን ጨራርሰን እንደተቀመጥን «ሰሞኑን መድሀኒት ስትጠቀሚ አላይሽም! ሌክቸረር ሆነ ብለሽ ልታረግዥብኝ ነውዴ?» አለኝ። በዚች ንግግሩ ታሪኬን ቀዬረው።

ትምህርቴን አቋርጨ አዲስ ህይወት ጀመርኩ። ስሜንም ቀየርኩ። ታቱዬን ሙሉ ጥቁር አድርጌ "ብላክ ሆል" ነው እያልኩ መንገር ጀመርኩ። ሰላም ያለው ህይወት ለመኖር የነበረኝ አንድ አማራጭ ነበር። ሁሉንም ሰው ከህይወቴ አስወጥቼ ልጄን ማሳደግ። የዚያኔ እንደዛ ባለኝ ሰዓት ፀባዩ ሲስተካከል እነግረዋለሁ እያልኩ ያረፈድኩባት ፅንስ ነበረችኝ።

አሁን አሁን ሳስበው ታሪኬ ረጅም ይመስላል እንጂ አጭር ነው። ይቺው ናት ውጣ ውረዴ! ልጄን እስካሳድግ ድረስ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው ከቤተሰቦቼ ጋር የተገናኘሁት። እነሱም እምብዛም ሊያዩኝ አይፈልጉም። መላቀቅ ነው! ይቅሩብኝ ከነምላሳቸው! ምላስ ሽሽት ነው ነው ኑሮዬ!

አልፎ አልፎ ስር እንዳይሰድ አድርጌ የወሲብ ግኑኝነት እጀምራለሁ። እነሱም ስለኔ ትንሽ ማወቅ ሲጀምሩ ጥያቸው ዲዲዲዲዲዲ! በዚህ ርዕስ ላይ ከማወራ ይሻለኛል።

ልጄ በኔ መልክ ባባቷ ጭንቅላት በመውጣቷ ያገኛት ሁሉ ይወዳታል። እኔም በሷ እየተፅናናሁ እኖራለሁ። በቃ።

ይሔን ሁሉ ቁጭ ብዬ የማስበው ዛሬ «አባቴ ማነው?» ብላ ጠይቃኝ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ሩጨ የማላመልጣት ሰው ገጠመችኝ። የመመለስ ግዴታ እንዳለብኝ አውቃለሁ። ግን እንዴት ነው የአ'ምሮ በሽተኛ ሳላደርጋት ስለአባቷ ልነግራት የምችለው? ተረት ላድርገው ይሆን? እምብዛም የማይንቁት...እምብዛም የማያደንቁት የ'ንደኔ አይነቷ ኖርማል ሰው ህይወት እንዴት ነው የሚተረተው?

«ተረት ተረት!»
«የመሰረት!»
«በድድሮሮሮሮ ጊዜ አንዲት ሔለን የምትባል፤ ከብርጭቆዋ ጋር ጨለማ ክፍል ውስጥ የምትኖር ልዕልት ነበረች።»
«እእእሽ»
«ሁሌም ሌቦች ብርጭቆዬን ይሰርቁብኛል ብላ ስለምትሰጋ ጨለማው ያስፈራት ነበር። ከዛ አንድ ቀን ምን ብታገኝ ጥሩ ነው?»
«ምን?»
«ሻማ!...በጣም ደስ አላት። ሻማዋን አብርታ እያዬች ደስ አላት። 'ይቺ ሻማ እስካለች አልሰጋም' ስትል አሰበች። ሻማዋ ግን 'እጠፋለሁ' ብላ ትሰጋ ነበር። ንፋስ በመጣ ቁጥር ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል። ልዕልቷም ሻማዋን ከንፋስ ለማስጣል ብላ አንድ የሞኝ ውሳኔ ወሰነች!»
«ምን አደረገች?»
«በብርጭቆዋ ሸፈነቻት።»
«ከዛስ?»
«ከዛማ ሌባ ይገባል ብላ በር በሩን እያዬች ከኋላዋ ቃቃቃቃቃቃ የሚል ድምፅ ተሰማት። ደንግጣ ስትዞር የምትሳሳላት ብርጭቋዋ ናት። ንፋስ መቋቋም አቅቷት ልትጠፋ የነበረችው ሻማ በሙቀቷ ብርጭቆዋን ሰንጥቃባታለች። ልዕልቲቱ አዘነች። ውሀ አጣጯ ቢመጣም ውሀ መጠጫ እንደሌላት እያሰበች አለቀሰች! አለቀሰች!..» እያለ የሚቀጥል ተረት!

፨፨፨
March 19 2022
Michael Azmeraw
1😢1