Mame profile photo
1.01K subscribers
197 photos
51 videos
3 links
ለአላህ ብዬ እወዳቸዋለሁ 😍😘😘😍
Download Telegram
ዲን ስታገለግል ሁሌም ከአላህ ብቻ ምንዳን በመጠበቅ ብቻ አገለግል። እውቅና "አዋርድ" ከሚሉት ቲርኪሚርኪ በብዙ መራቅ ነው ያለብህ። ነገ አላህ ፊት በባዶ ያስቀራሃልና!!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنَّ أخوَفَ ما أخافُ عليكم الشِّركُ الأصغرُ، قالوا: وما الشِّركُ الأصغرُ؟ قال الرِّياءُ، يقولُ اللهُ عزَّ وجلَّ لأصحابِ ذلك يومَ القيامةِ إذا جازى النّاسَ: اذهبوا إلى الَّذين كنتم تُرائون في الدُّنيا فانظُروا هل تجِدون عندهم جزاءً؟!﴾

“ከምፈራላችሁ ሁሉ እጅግ የሚያስፈራው ትንሹ ሺርክ ነው። ‘ትንሹ ሺርክ ደግሞ ምንድን ነው?’ ሲባሉ እንዲህ አሉ፦ ለመታየት ተብሎ አምልኮትን መፈፀም ነው። አሸናፊና የላቀው አላህ በቂያማ ቀን ሰዎችን የስራቸውን ዋጋ ሲሰጥ መታየትን አስበው ይሰሩ ለነበሩ ሰዎች እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘ዱንያ ላይ ለመታየት ትሰሩ ነበር። እነዚያ እንዲያዩዋችሁ ትፈልጓቸው የነበሩ ሰዎች ሽልማት ካላቸው ተመልከቱ (ፈልጉ)።’”

📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ፡ 951

Share 🥰
12🙏2
ተጠንቀቅ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿اتَّقوا دعوةَ المظلومِ، فإنها تَصعدُ إلى السماءِ كأنها شرارةٌ﴾

“የተበዳይን ዱዓእ (እርግማን) ተጠንቀቁ። ምከንያቱም ልክ እንደ ነበልባል ሆና ወደ አላህ ትወጣለችና።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 118

Share
4🥰4
በደማስቆ አንድ ደሀ የታክሲ ሹፌር ነበር አንድ ህክምናን የሚማር ተማሪ ገጭቶ በሚያሳዝን ሁኔታ ለሞት ዳርጓል። ሸይኽ ሙሐመድ አየዋድ እና ሌሎች ኡለማዎች ወደ ልጁ አባት ሽምግልና ሄደው ልጁን የገደለውን የታክሲ ሹፌር ይቅርታ እንዲያደርግላቸው ጠየቁት እና ካሳ ብለው የደም ገንዘብ አቀረቡለት። አባትየውም በሚያስገርም ሁኔታ ‹በአላህ እምላለሁ፣ ይቅርታ አድርጌለታሁ እና ከእሱ አንድ ሳንቲም አልፈልግም።  እንደውም ነገ  ወደ ወህኒ ቤት ሄጄ ራሴ አስፈታዋለሁ አለ።  ከዚያም አባትየው፡- ሼክ አይዋድ ወደ ቤቴ መጥተሃልና ቅር እንድትሄድ አልፈልግም! በዚህ ምክንያት የታክሲ ሹፌሩ ይቅርታ አደረጉለት።

ከዓመታት በኋላ እኚህ አባት ሽባ ሆነው በመታመማቸው ቤተሰቦቻቸው ወደ መካ ሀራም የመጨረሻ ጉብኝት አድርገው ወሰዱት። ስትረቸር ላይ አስተኘተው ጠዋፍን ያስደርጉት ነበር። በዚህ ወቅት እያለቀሰ፡- “አላህ ሆይ ሸይኽ አየውድ ልጄን ለገደለ ሰው ይቅርታ ሊጠይቀኝ ሲመጣ ‹እኔን ቅር ብሎህ ከቤቴ እንድትወጣ አልፈቅድልህም› አልኩት። ዛሬ ሽባ ሆኜ ወደ ቤትህ መጥቼ ሳትፈውሰኘ አዝኘብህ እንድሄድ እትፍቀድ!'ብሎ ዱዓውን አልጨረሰውም አላህ ጤንነቱን መልሶለት ተነስቶ በእግሩ መራመድ ቻለ በስትሬቸር ላይሆኖ የጀመረውን ጠዋፍ በእግሩ እየተራመደ አጠናቆ  ሙሉ በሙሉ ፈውስ ይዞ ከመሄድ በቀር  አላጠናቀቀም! የበደላችሁን ይቅር በላቸው አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ተአምራትን ያሳያችኋል! የአላህ በረከቶች ወሰን የለሽ ናቸው...
🥰107
መከራን በትዕግስት ማሳለፍ ያለው ትሩፋት!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إنَّ اللهَ تعالى يقول: إذا ابتلَيتُ عبدًا من عبادي مؤمنًا، فحمدَني وصبَر على ما ابتليتُه به، فإنه يقوم من مضجَعِه ذلك كيومِ ولدَتْه أمُّه من الخطايا﴾

“የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦ አማኝ ከሆኑ ባሮቼ አንዱን ባሪያ በፈተንኩት ጊዜ፤ ያመሰገነኝ እና በፈተናው ላይ የታገሰ ከሆነ፤ ከበሽታው ድኖ ሲነሳ ከእናቱ ሆድ አንደወጣ ህፃን ከወንጀሉ ይፀዳል።”
7🥰5
Ramadan ረመዳን:
የፆም ደረጃ እና ምንነት

#ፆም ወይም በአረብኛው "ሰውም" ማለት መታቀብ የሚል ትርጓሜን የሚሰጥ ቃል ነው።

በሸሪዓዊው ትርጓሜው ደግሞ #ፆም
ማለት ኒያን ነይቶ ከፈጅር አንስቶ እስከ መግሪብ ድረስ ከምግብ፣ከመጠጥ፣ እነሱን ከሚተካም ነገር እና ከተቃራኒ ፆታ ጋር ግንኙነት ከመፈፀም ታቅቦ መቆየት ማለት ነው።

#ፆም በርካታ ጠቀሜታዎችና ትሩፋቶች ያሉት የአምልኮ አይነት ነው።

የአላህ መልእክተኛ  (ﷺ) #የፆምን ጥቅም ሲነግሩን እንዲህ ብለዋል

" #ፆም ጋሻ ነው" (ቲርሚዚ)

ጋሻነቱ በዱንያ ከአላስፈላጊ ስሜቶች ዝንባሌዎችና መጠበቂያ ሲሆን በአኼራ ደግሞ የፆመውን ሰው ከጀሀነም እሳት ነው የሚከላከለው። የአላህ መልእክተኛ (ﷺ)እንደተናገሩት

"በአላህ መንገድ ላይ ማንም ሰው አንድ ቀን #አይፆምም አላህ በእሱና በእሷት መካከል 70 አመት ቢያራርቃቸው እንጂ"ብለው እንደተናገሩት (ቡኻሪና ሙስሊም)

እንዲሁም #ፆም አቻ የሌለው ዒባዳ መሆኑን አስመልክቶ የአላህ መልእከተኛ  (ﷺ)  እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል

" #በፆም ላይ አደራህን እሱኮ
ፆም አቻ የለውም" (ሙስነድ ኢማም አህመድ)

የውመል ቂያማ አማላጅ ሆኖ እንደሚመጣ የአላህ መልእክተኛ (ﷺ)  ነግረውናል። #የፆምን ደረጃ ከገለፁባቸው ሀዲሶች መካከልም ነቢይ (ﷺ) "3 ሰዎች ዱዓቸው አይመለስም #ፆመኛ እስኪያፈጥር፣ ፍትሀዊ መሪ እና የተበደለ ሰው"  ብለው ነግረውናል (ሱነኑ ቲርሚዚይ)

ነብዩ ﷺ እንዲህ አሉ               
በአላህ ለይ ምንም ነገር #አታጋራ  ብትቆራረጥም ብትቃጠልም እንኳን. ፈርድ የሆኑ ሰላቶችን እንዳትተው,  የተዋት ከአላህ ጥበቃ ዉጭ ነው. አልኮል አትጠጣ የመጥፎ ነገሮች  መክፈቻ ነውና.
 ሱነኑ ኢብን ማጀህ 40:34


إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَىٰ إِثْمًا عَظِيمًا

አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ፡፡ 4:48

የፆም መስፈርቶች
በዲናችን የተደነገጉ የአምልኮ አይነቶች የራሳቸው መስፈርት ያላቸው ናቸው። እነዚህ መስፈርቶች በሌሉበት  ዒባዳ (አምልኮ) ትክክል ሊሆን እንዲሁም ተቀባይነት ሊያገኝ አይችልም።
ፆምም ልክ እንደዚሁ የራሱ መስፈርቶች አሉት። እነዚህን መስፈርቶች ያላሟላ ሰው ላይ ፆም ግዴታ አይሆንም እነሱም፦

1⃣ ሙስሊም መሆን፦ የሁሉም ዒባዳዎች መስፈርት ነው። ሙስሊም ያልሆነ ሰው ሙስሊም እስኪሆን ድረስ ፆምም ይሁን ሌላ ዒባዳው ተቀባይነት አያገኝም። መሰረትና ቋሚ ሳይኖር ጣራን ለማቆም እንደማይቻለው። ካፊር የሆነ ሰው ሲሰልም ያለፈህን በሙሉ ቀዷእ አውጣ አይባልም

2⃣ ለአካለ መጠን መድረስ፦ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ህፃን ላይ ፆም ግዴታ አይሆንም ነገር ግን ለማለማመድ ያክል ያልደረሱ ህፃናት እንዲፆሙ ቢደረግ (አቅማቸውን ባማከለ መልኩ) ጥሩና የሚበረታታ ነው። ለአካለ መጠን ከደረሱ በሗላ ፆም እንዳይከብዳቸው ያግዛልና።

3⃣ የአእምሮ ጤነኛ መሆነ፦ ከፆም መስፈርቶች አንዱ የአእምሮ ጤነኛ መሆን ነው። አእምሮው ጤነኛ ያልሆነ ሰው ፆም በሱ ላይ ግዴታ አይሆንበትም በሚድን ጊዜም ቀዷእ ማውጣት አይጠበቅበትም የአላህ መልእክተኛ (ﷺ)

"ከ3 ሰዎች ላይ ብዕር ተነስቷል (መልካምም መጥፎም ስራቸው አይፃፍም) እብድ ወደ ጤናው እስኪመለስ፣ የተኛ ሰው እስኪነቃ እና ህፃን እስኪያድግ (ለአካለ መጠን እስኪደርስ)" ብለዋል (አቡዳውድ)

4⃣ መፆም መቻል፦ በበሽታ ወይም በመሰል ነገራት መፆም ያልቻለ ሰው በሱ ላይ የፆም ግዴታ የለበትም። አለመቻሉ ጊዜያዊ ከሆነ በቻለ ጊዜ ቀዷእ ማውጣት ይጠበቅበታል። አለመቻሉ ግን ጊዜያዊ ካልሆነ እድሜ ልክ አብሮ እንደሚዘልቅ ከተረጋገጠ ለየ አንዳንዱ ላልፆመበት ቀን አንድ ሚስኪን አጥግቦ ይመግባል።

5⃣ ሀገሩ ውስጥ ነዋሪ መሆን፦ በስደት ወይም በጉዞ ላይ ያለ ሰው ፆም የመፆም ግዴታ የለበትም። ወደ ሀገሩ ሲመለስ ግን ቀዷእ የማወወጣት ግዴታ አለበት። ይህ ከመሆኑ ጋር (አለመፆሙ ከመፈቀዱ ጋር) በጉዞ ላይ ሆኖ ቢፆም ፆሙ ትክክል ይሆናል

6⃣ ሴቶች ከወር አበባና ከወሊድ ደም መፅዳት፦ ይህ በሴቶች ላይ የሚቀመጥ መስፈርት ሲሆን የትኛዋም ሙስሊም ሴት ይህ ደም እየፈሰሰ ባለበት ወቅት ፆም መፆምን ትከለከላለች። በደሙ መፍሰስ ሳቢያ ያልፆመቻቸውን ቀናትም ከዚያ በሗላ ቀዷእ ታወጣለች።

⚠️ ማሳሰቢያ
የባለፈው  ረመዳን   ቀዳ  ያለብን   ካለን  ቀጣይ ረመዳን 10  ቀን ገደማ ስለሚቀረው    ከዛ  በፊት  ማውጣት አለብን  

ረመዷንን ከሌሎች ወራት የሚለይበት

አላህ ረመዷንን ከሌሎች  ወራት በብዙ ነገር ለይቶታል ።  ረመዷን ከሌሎች ወራት ከሚለይባቸው በርካታ ነጥቦች መካከል፦

1⃣ አላህ ቁርዓንን ያወረደበት ወር:- በመሆኑ ከሌሎች ወራት ይለያል ቁርዓን በተከበረው በረመዷን ነው የወረደው።
በመጨረሻዎቹ የረመዷን አስር ቀናት ውስጥ አላህ ቁርዓንን አውርዷል። ቁርዓንን ብቻ ሳይሆንም ሌሎችን መፅሀፍ በነብያት ላይ ሲያወርድ በዚሁ በተከበረው በረመዷን ወር ነበር አላህ ያወረደው ይህንንም አስመልክቶ የአላህ መልእክተኛ  (ﷺ)   ላይ  በረመዷን  ጂብሪል (የመላኢካዎች አለቃ)  አላህ ዘንድ የሰው ልጆች መመሪያ የሆነው ቁርዓንን አውርዶላቸዋል አላህም እንዲህ ይላል

"መፆሙ ግዴታ የተደረገባቹህ የረመዷን ወር ማለት ያ በእርሱ ውስጥ ለሰው
ልጆች በሙሉ መሪና መመሪያ፣ እውነትና ሀሰትን የሚለዩ ገላጭ አንቀፆችን የያዘው ቁርዓን የወረደበት ወር ነው..." (አል በቀራህ)


የአላህ መልእክተኛ  (ﷺ)   በሀዲሳቸው እንዲህ ብለዋል

"💎የኢብራሂም መፅሀፍ የረመዷን የመጀመሪያ ሌሊት ላይ ነው የወረደው፣
💎ተውራት (የሙሳ መፅሀፍ) ከረመዷን 6 ቀናት ካለፉ በሗላ ነው የወረደው
💎 ኢንጂል (የዒሳ መፅሀፍ) ከረመዷን 13 ቀናት ካለፉ በሗላ ነው የወረደው
💎 ቁርዓን ከረመዷን 24 ቀናት ካለፉ በሗላ ነው የወረደው" ብለዋል (ሙስነድ ኢማም አህመድ)


2⃣ረመዷን ላይ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፣ የጀሀነም በሮች ይዘጋሉ፣ አመፀኛ ሸይጣኖችም ይጠፈራሉ በየሌሊቱም አላህ ብዙ ሰዎችን ከጀሀነም ነፃ ያወጣል።

3⃣ረመዷንን አምኖና ከጌታው መልካም ምንዳን ተሳስቦ የፆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉን በሙሉ አላህ ይምርለታል።

4⃣በረመዷን ውስጥ ለይለቱል ቀድር አለች በውስጧ ሚሰራባት መልካም ስራ 83 አመት ከሚሰራ መልካም ስራ የበለጠ ምንዳ ምታስገኝ ናት።

5⃣ ረመዷን በኢስላም ታሪክ ብዙ ድሎች የተመዘገቡበት ወር ነው በነቢይ (ﷺ) ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ራሳቸው የተሳተፉበት የበድር ዘመቻ፣
በ15ኛ አመተ ሂጅራ በሰአድ ኢብኑ
አቢ ወቃስ የተመራው የቃሲዲያ ዘመቻ፣
በ92 አመተ ሂጅራ በጧሪቅ ኢብኑ ዚያድ የተመራው የአንደሉስ (ስፔን) ድል፣
በ583  አመተ ሂጅራ በሰላሀዲን አል አዩቢ የተመራ መስጂደል አቅሳን

ረመዳን ሳያገኘ የሞት እድለቢስ ነው ፃሙን እንደጨረሰ የሞተ እድለኛ ነው

ረመዳን #በታሪክ
2
ነብዩ  ና ተከታዮቻቸው   በእምነታቸው ምክንያት በርካታ በደል ስላደረሱባቸው ወደ መዲና  ተሰደዱ የመካ ሙሽሪኮች መካ ላይ ያደረሱት ግፍ  አልበቃ ብሏቸው  ነበዩንና ተከታዮቻቸውን ለማጥፋት  ጦር አዘመቱ  ነብዩም 300 የሚሆኑ ተከታዮቻቸው ፆምኛ ሆነው የተከፈተባቸውን ጦርነት  ከነሱ በሰው ሀይልም ሆነ በመሳሪያ በብዙ እጥፍ የሚበልጣቸውን ሀይል ድል ያደረጉት  በረመዷን  ላይ ነበር.

ከዚህ ድል ስድስት አመት በኃላ የተባረሩበት መካን ያለምን ጦርነት 10,000 ተከታዮቻቸውን ይዘው  በዚሁ በረመ ዷን  ወር ነበር መካን የተቆጣጠሩት.

ሙስሊሞች አንዶሉስን (ስፔን) በአፍሪካዊ ኮማንደር እየተመሩ በዚሁ በረመዳን ነበር ድል አድርገው ለ800 አመት በፍትህ ያስተዳደሩት

በአንድ  ወቅት ሀያል የነበረው የሞንጎሊያን ሀይል ያገኘውን ሁሉ እየደመስሰ ግዛቱን እያስፋፋ  እስልምና ከባድ አደጋ ውስጥ ገብቶ ከግብፅ የተነሳው በጃሉት የሚመራው የሙስሊሞች ጦር ከእልህ አስጨራሽ ውጊያ ቡሀላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞንጎሎች ሀይል ሸንፈት  እንዲቀመሰ አደረገ በዚህም እስልምናን ብቻ ሳይሆን አለምን ከጥፋት የታደጉት በዚህ በረመዳን ወር ነበር

ሳላሀዲን አልአዩቢም  በዚህ በረመዷን ወር ነበር  ጀሩሳሌም ነፃ  ያወጣው

ቀደምቶች በፆም አንጀታቸው ነበር እነዚህን ወሳኘ ድሎች ያስመዘገቡት እኛስ ነብስያችንን እንኳን በማሸነፍ ወሩን በሚገባ ለመጠቀም ምን ያህል  ተዘጋጅተናል .......⁉️⁉️⁉️⁉️⁉️

የረመዷንን ወር  አቀባበላችን
1⃣አንዳንዶች ልክ ይህ ወር የምግብ ወር እስኪመስል ድረስ ወደ ገበያ ተሸቀዳድመው በመውጣት የተለያዩ የምግብ አይነቶችን በመግዛት አቀባበል የሚያደርጉ አሉ፡፡ ጻም ሳይሆን መብላት የገባ ይመስል አብዛኛዉንም ግዚያቸዉን በምግብ ዝግጅት

2⃣ሌሎች ደግሞ የረመዷን ወር ሊገባ ሲል ቀድመው የጊዜ ማሳለፊያ መጫዎቻ ጌሞችን እና የመሳሰሉ መዝናኛ እቃወችን ገዝተው (ፊልሞችን አዘጋጅተው) የሚያስቀምጡ አሉ፡፡ እንዲሁም ለሊቱን ጫት ሲቅሙ ቀኑን በእንቅልፍ በማሳለፍ ይህን በርካታ ጥቅሞች ያሉበትን የተከበረ የረመዷን ወር በማይረቡና በማይጠቅሙ ነገሮች ያሳልፋሉ፡፡

3⃣ሌሎች አላህ የመረጣቸው ፣ በእዝነቱ በእንክብካቤው ያገዛቸው ሰዎች ደግሞ ነፍሳቸውን ከወዲሁ ለዚህ የተከበረ ወር የሚያዘጋጁ ናቸው፡፡ በርካታ መልካም ነገሮችን ከወዲሁ ለመስራት በአዕምሯቸው ያንሰላስላሉ፡፡ ለቁርኣን ፣ ለዚክር ፣ ለሌሊት ሶላት ፣ ሰዎችን ለመርዳት ፣ ለምስኪኖች ለመሶደቅ እና ለዒልም ፕሮግራሞችን ያወጣሉ፡፡ የረመዷንን ወር በእነዚህ መልካም ተግባራት ተጠምደው ያሳልፋሉ፡፡

4⃣አንዳንድ ሰዎች ደግሞ በአላህ ትዕዛዛት ላይ ለመቆም የተለያዩ የመልካም ስራ ፕሮጀክቶችን ቀርጸው ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ሰፊ የሆኑ የመልካም ስራዎችን በመስራት ወቅት ጠቧቸው የጀመሩትን ስራ ሳያጠናቅቁ ወሩ የሚያልቅባቸው ሰዎች ናቸው፡፡

5⃣አንዳንዶቹ ደግሞ የረመዷን ወር ልክ እንደሌላው ወር እኩል የሚሆንባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ሌሎች ወሮች እንደሚያልፉት የረመዷን ወር እንዲሁ በቀላሉ ያልፋል፡፡ ደረጃው ከአንድ ሽ ወር ዒባዳ ይበልጣል የተባለለት ሌሊት እንኳ ልክ ከሌሎች ሌሊቶች ጋር በተመሳሳይ የሚያሳልፉ ሰዎች አሉ፡፡
ይህን የተከበረ ወር በደንብ ልንቀበል ፣ ደረጃውን አውቀን እንግድነቱን ልናሳምር ፤ ነፍስን ለዒባዳ ፣ በውስጡ ለሚገኙ በርካታ ጠቃሚ ነገሮች ልንሽቀዳደምና ልንዘጋጅ ፤ በአጠቃላይ የዚህ ወር እውነተኛ ቤተሰብ ልንሆን ይገባል እንጂ ይህን ወርቃማ አጋጣሚ በከነቱ ልሳልፈዉ በፍጹም አይገባም.
8🥰2
🌙 በሳውዲ አረቢያ ጨረቃ መታየቷን ተከተሎ የታላቁ የረመዳን ፆም ነገ ይጀመራል።

ለመላው ሙስሊሞች ከወዲሁ መልካም የረመዳን ፆም እንዲሆንላችሁ እንመኛለን 🙏🏽

ረመዳን ሙባረክ 🌙

Share share
9🥰5
ረመዳንና ዘርፈ ብዙ ጥቅሞቹ #1

በህይወትህ ውስጥ ካጎደልከው የአላህ ትዕዛዝና ከምትፈፅመው ክልከላው ለመታቀብ ብዙ እየሞከርክ ወደ መስመር መግባት ከብዶህ ይሆናል ረመዳን ግን ለዚህ ምቹ አጋጣሚ ነው። ሰዎችን በማጥመም የሚያታወቁ ዋና ዋና ሰይጣናት የሚታሰሩበት የጀሀነም በሮች ተዘግተው የጀነት በሮች የሚከፈቱበት ለመልካም ስራ ከመቼውም ግዜ በላይ ምቹ አጋጣሚ ነውና የነፍሲያ ተንኮልንና ሌሎች ነገሮችን በማሸነፍ ትኩረት ሰጥተህ ተጠቀምበት።

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إذا كانَت أوَّلُ ليلةٍ من رمَضانَ صُفِّدتِ الشَّياطينُ ومَردةُ الجِنِّ وغلِّقت أبَوابُ النّارِ فلم يُفتَحْ منها بابٌ وفُتِحت أبوابُ الجنَّةِ فلم يُغلَقْ منها بابٌ ونادى منادٍ يا باغيَ الخيرِ أقبِلْ ويا باغيَ الشَّرِّ أقصِر وللَّهِ عتقاءُ منَ النّارِ وذلِك في كلِّ ليلةٍ﴾

“የመጀመሪያው የረመዳን ሌሊት በሆነ ግዜ ጂኒና ሸይጣናት ይታሰራሉ። የጀሀነም በሮች ላይከፈቱ ይዘጋሉ። የጀነት በሮች ላይዘጉ ይከፈታሉ። ተጣሪው ይጣራል፡- መልካም ፈላጊ ሆይ ና፤ ተሰብሰብ ጠጋ በል። ሸር ፈላጊ ሆይ ተመለስ (ሸርህን አቁም) ይላል፡፡ ረመዳን እስኪያልቅ ድረስ በየቀኑ አላህ ከእሳት ነፃ የሚያወጣቸው ባሮች አሉት፡፡”

📚 ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል፡ 1339
4🥰1
ረመዳንና ዘርፈ ብዙ ጥቅሞቹ #2

በረመዳን ወር ፆም ውስጥ ከዚህ ቀደም ይፈቀድልህ የነበሩ ሀላል ነገሮች ተቆጠብ ተብለህ ተከልክለህ እሱን ተቀብለህ እየፈፀምክ፤ እንዴት ታዲያ በሀራም ነገሮች በሀሜት፣ በውሸት፣ በማጭበርበር፣ ሰው በመደል ፆምህን ታውልዋለህ? ፆምህን ከሚፈለግብህ የአላህ ፍራቻ ጋር አስታርቀው።

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَنْ لَمْ يَدَعْ قَوْلَ الزُّورِ وَالْعَمَلَ بِهِ فَلَيْسَ لِلَّهِ حَاجَةٌ فِي أَنْ يَدَعَ طَعَامَهُ وَشَرَابَهُ﴾

“የሐሰት ንግግርን በሐሰት መስራትን እንዲሁም መሀይምነትን (የመሐይማንን ተግባር) ያልተወ ሰው ምግቡንና መጠጡን ከመተዉ አላህ ጉዳይ የለውም።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 1903
1🥰1
ረመዳንና ዘርፈ ብዙ ጥቅሞቹ #3

ረመዳን ታላቅ ወር ነው። ቀደምት ደጋግ ባሮች በውስጡ የሚገኘውን ጥቅም (ትሩፋት) በመረዳት ከ6 ወር ቀድመው አላህ እንዲያደርሳቸው ይማፀኑት ነበር። ደርሰውም በአግባቡ ተጠቅመውበት የቀጣይ የተቃና ሕይወታቸውን መስመር አበጅተውበት ያልፋሉና እኛም ይሄን እድል ልንጠቀመበት ተገቢ ነው…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿رغِمَ أنفُ مَن دخَل عليه رمضانُ ثمَّ لم يُغْفَرْ له﴾

“እጁ አመድ አፋሽ ይሁን ረመዳንን አገኝቶ ወንጀሉ ሳይማርለት ያለፈው።”

📚 ቲርሚዚ ዘግበውታል፡ 3445
3🥰2
በኢስላም ስራዎች የሚለኩት በስተመጨረሻ በሚሰሩ ተግባራት ነው። ታዲያ የታላቁ ወር ረመዳን መጨረሻ አካባቢ እንገኛለን። ረመዳን ሲገባ ስንጀምር እንደነበረው የኢባዳ ነሻጣ ላይ ነን ያለነው? ወይስ ተቀዛቅዘናል? በነዚህ ቀናቶች ግን የታላቁ ነቢይ ባህሪ ይለይ ነበር…

ከእናታችን አዒሻ (رضي ﷲ عنها) ተይዞ፡ እንዲህ ትላለች፦

﴿كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَجْتَهِدُ فِي الْعَشْرِ الْأَوَاخِرِ مَا لَا يَجْتَهِدُ فِي غَيْرِهِ.﴾

“ረሱል (ﷺ) ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት ከሌላ ጊዜ በተለየ መልኩ (በዒባዳ) ላይ ይተጉ ነበር።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 1175
6
ዱዓእ ታላቁ አምልኮ ነው። በዚህ በረመዳን ደግሞ በተለይ በመጨረሻው ሌሊቶች አብዝቶ ማድረግ ወሳኝ ነው። ካደረክ አይቀር ደግሞ…

ከአኢሻ (رضي ﷲ عنها) ተይዞ፡ እንዲህ ትላለች፦ የአላህ መልእክተኛን (ﷺ) ለይለተል ቀድር እንደሆነ ከተሰማኝ ምን እንደምል አሳውቁኝ ስላቸው እንዲህ በይ አሉኝ፦

﴿اللَّهمَّ إنَّكَ عفوٌّ تحبُّ العفوَ فاعفُ عنِّي﴾

“አላህ ሆይ! አንተ በርግጥም ይቅር ባይ ነህ ይቅር ማለትን ትወዳለህ ስለሆነም ለኔ ይቅር በለኝ።”

📚 ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል: 3119
4🥰2
የሸዋል ወር አዲስ ጨረቃ ዛሬ ረቡዕ አመሻሹን ባለመታየቱ የ1447 ዓ.ሂ የዒድ አልፊጥር በዓል ጁመዓ መጋቢት 11/2018 እንደሚውል ተረጋግጧል።
2🥰1
የሸዋል ወር አዲስ ጨረቃ ዛሬ ረቡዕ አመሻሹን ባለመታየቱ የ1447 ዓ.ሂ የዒድ አልፊጥር በዓል ጁመዓ መጋቢት 11/2018 እንደሚውል ተረጋግጧል።

ረመዳን በአመቱ  ተመልሶ  ይመጣአል  ከሌለን የመጨረሻ ረመዳናችንም ሊሆን ስለሚችል የቀረውንም ጊዜ እንጠቀምበት 30  ለሊት ለይለተል ቀድር  እንደምትሆንም ተነግሯል

«ለይለተ-ል-ቀድርን በረመዿን የመጨረሻዋ ሌሊት ላይ ፈልጓት»

[ሐዲሱን አል-ኢማም አል-አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል]
Share 🥰
🥰21
تقبل الله منا ومنكم،
‏وجعل عيدكم مباركا،
‏وذنبكم مغفورا،
‏وسعيكم مشكورا.

Eid Mubarak



عيد_الفطر ١٤٤٧هـ
6🥰5
ፆሙን   ጀምረን በስኬት ለማጠናቀቅ ላበቃን አላህ ምስጋና ይገባው,  ዱንያ የስራ ቦታ እንደመሆኗ መጠን አንዱ ስራ ሲያልቅ ወደሌላ እንቀጥላለን,  ቀጣይ አገራችንን ለመገባት በርካታ ግብአቶች ስለሚያስፈልግ ይህም የሚሟላው በምንተገብረው ስራ ስለሆነ የምድር ቆይታችን እስኪጠናቀቅ ድረስ ኸይር ስራ መላካችን ይቀጥላል

وَٱعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ ٱلْيَقِينُ

እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ.  Al-Hijr 15:99

🌟አማኘ መልካም ስራ የሚፈፅመው #በኢማኑ መጠን ነው ይህ #ኢማን መልካም  ተግባር በማከናወን ሲጠናከር መጥፎ ተግባራት በመስራት ይዳከማል

⭐️ጥሩ ስራ እንዳናከናውን #እቅፋት የሚሆኑት ነብስያና ስይጣን በቀዳሚነት  ይጠቀሳሉ  #ሰይጣንን በማሰር #ነብስያን በፆም በማድከም ለምንሰራው መልካም ስራ እጥፍ ድርብ ምንዳ በመክፈል ጥሩ ስራ እንድንሰራ ከሃጢያት እንድንርቅ በማድረግ #ኢማናችንን እንድናጠናክር ሲያበረታታን ለአንድ ወር ቆይቶል

🌏ሱብሂ መነሳት እንድንችል ለሱሁር ከሱብሂ በፊት እንድንነሳ በማድረግ አለማምዶናል
☀️ሰላት እንዳይከብደን በተራዊ አለማምዶናል
ከሃጢያትና ከሱስ እንድንርቅ በፆም አለማምዶናል

🌼በፆሙ የነበረንን ጥሩ ሙድ እንደያዝን ሰይጣን  በተፈታበት ትንሽ #እንድንለማመድ ከኢድ ቡሃላ ለአንድ ሳምንት (ለ6 ቀን) እንድንፆም ይፍለጋል ለዚህም ረመዷንን ፁመን ከሸዋል ወር 6ቀን የፆመ አመት እንደፆመ በመቁጠር ትልቅ ምንዳ በመስጠት ያበረታታናል.(ከኢድ ቡሃላ ያሉትን 6 ቀናት ብንፆም አላማውን ለማሳካት ይመረጣል)

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَن صامَ رَمَضانَ ثُمَّ أتْبَعَهُ سِتًّا مِن شَوّالٍ، كانَ كَصِيامِ الدَّهْرِ.﴾

“ረመዳንን ፆሞ የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆምን ያስከተለ አመቱን ሙሉ እንደፆመ ይቆጠራል።”  ሙስሊም : 1164
6🥰2
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የአሹራ ቀን ፆም!

ለመልካም ስራ አስተዋሽ እንሁን

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿فَإِذَا كَانَ الْعَامُ الْمُقْبِلُ - إِنْ شَاءَ اللَّهُ - صُمْنَا الْيَوْمَ التَّاسِعَ﴾

“የሚቀጥለው ዓመት ከደረስኩ በአላህ ፍቃድ የአሹራን ቀን ፆም ዘጠነኛውን ጨምሬ እፆማለሁ።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1134


በሌላ ሀዲሳቸው (ﷺ)፦

﴿صيامُ يومِ عاشوراءَ، إنِّي أحتَسِبُ على اللَّهِ أن يُكَفِّرَ السَّنةَ الَّتي قبلَهُ﴾

“የአሹራ ቀን ፆም ያለፈውን አመት ኃጢአት እንደሚያብስ ከአላህ እጠብቃለሁ።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1162
  
ዘጠነኛው እሮብ 17/10/2018
አስረኛው ሐሙስ 18/10/2018
Share share
9🥰1