ከውሣኔው እንደምንረዳው ከሟች ጋር ምንም አይነት የስጋ ዝምድና ወይም የጉድፈቻ ውል መሠረት ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች የሟች ያለ ኑዛዜ ወራሽ ነኝ በማለት በሚቀርቡበት ሁኔታ መኖሩን ሲሆን በሌላ በኩል አንድ ተከራካሪን አስመልክቶ ጉዳዩን በስር ያየው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ከሥነ ሥርዓት ሕጉ መሠረት ይግባኝ ወይም መስቀለኛ ይግባኝ ካልቀረበበት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ ስህተት ቢኖርበትም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በራሱ አነሣሽነት የማይሽረው መሆኑን ነው፡፡
በአጠቃላይ የሟች ውርስ አስመልክቶ ከሚነሡት በርካታ አለመግባባቶች የሟች ያለ ኑዛዜ ወራሽ ነኝ በሚሉ ነጥቦች ዙሪያ የሚደረግ በመሆኑ የሕጉን ድንጋጌዎች ዓላማና ይዘት በአግባቡ መረዳትና ሥራ ላይ ማዋል ያስፈልጋል፡፡

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የስነ-ምግባር ጥፋት በፈጸሙ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞችና የፌዴራል ፍርድ ቤት ሬጅስትራር ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
›››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››
የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የዲሲፕሊን ክስ በቀረበባቸው አስራ ሁለት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞችና በአንድ ሬጅስትራር ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
በዚህም መሰረት ጉባኤው በእለቱ በዳኞች ስነ ምግባር ኮሚቴ በቀረቡ የውሳኔ ሃሳቦች ክሶች ዙሪያ ተወያይቶ
አንድ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሬጅስተራር በፈጸሙት ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት ከስራ እንዲሰናበቱ፤
ሁለት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች እና ሶስት የፌደራል ከፍተኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች መልስ እንዲያቀርቡ፤
አንድ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና አንድ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች እንደቅደም ተከተላቸው የጽሁፍና የቃል ማስጠንቀቂያ፤
አንድ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ እና አንድ የፌደራል ከፍተኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ሬጅስትራር ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የቅጣት አስተያየት እንዲያቀርቡ፤
አንድ የፌደራል ከፍተኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ከቀረበባቸው ክስ ነጻ ሲባሉ አንድ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ እና ሁለት የፌደራል ከፍተኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ የቀረበባቸው አቤቱታ አያስጠይቅም ሲል ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በሌላ መልኩ አንድ የመሰየም ጥያቄ ያቀረቡ የፌደራል ከፍተኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ጥፋተኛ ከተባሉበት ጊዜ ጀምሮ ያላቸውን ስነምግባርና የስራ አፈጻጸም መርምሮ መልካም ስማቸው ተመልሶ እንዲሰየሙ ጉባኤው ወስኗል፡፡
#FJAC

👍1
ብርበራ
ብርበራ የወንጀል ድርጊት ለመፈፀም ጥቅም ላይ የዋሉ መሣሪያዎችን ፣ በወንጀል ድርጊት ምክንያት የተገኙ ቁሳቁሶችን ፣ ምርመራ ለሚደረግበት ጉዳይ ጠቀሜታ ያላቸውን ሌሎች ማናቸውም ማስረጃዎች ለመፈለግ እና ለመያዝ በተጠርጣሪዎች መኖሪያ ቤት ውስጥ ወይም የተጠቀሱት ነገሮች ተደብቀውባቸዋል በሚባሉ በሌሎች ሰዎች ቤቶች ውስጥ የሚከናወን የወንጀል ምርመራ ተግባር ነው፡፡ ብርበራ ለማድረግና በሚደረግበት ወቅት የሚከተሉትን መርሆች መከተል አስፈላጊ ነው።
✔ ማንኛውም መርማሪ ፖሊስ ወይም የፖሊስ አባል በፍርድ ቤት የተሰጠ የብርበራ ማዘዣ ካልያዘ በቀር የሰዎችን ቤት መበርበር አይችልም።
✔ ብርበራ የሚደረገው ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ማታ 12፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው። በፍርድ ቤት የተለየ ትእዛዝ ሲሰጥ ብቻ ከዚ ሰአት ውጭ ሊካሄድ ይችላል።
✔ ማንኛውም የብርበራ ማዘዣ የሚበረበረውን እና የሚያዘውን ዕቃ ማመልከት ያለበት ሲሆን መርማሪው ፖሊስ ወይም አብሮት ያለ የፖሊስ አባል በማዘዣው ላይ ከተመለከተው ውጭ ሌላው ዕቃ መያዝ አይችልም።
✔ መርማሪው ፖሊስ ወይም የፖሊስ አባል በማዘዣ ትዕዛዙ የተመለከተውን ዕቃ በሚይዝበት ጊዜ የተያዘውን ዕቃ ዝርዝር መዝግቦ መያዝ ያለበት ሲሆን ከተቻለ ገለልተኛ የሆነ ሰው ሊስቱ ላይ እንዲፈርምበት ይደረጋል።
✔ ብርበራ የሚያደርገው ብርበራ ከሚደረግበት ሰው ጋር ተመሳሳይ ፆታ ባለው ሰው ነው።
✔ ምርመራ በሚደረግበት ጊዜ ፖሊስ አስፈላጊውን ሀይል ብቻ ይጠቀማል።

በዋስ ቢወጡ ሌላ ወንጀል የሚፈጽሙበት ሁኔታ ሰፊ ነው በሚል ዋስትናን ሰለመከልከል *** የሰ.መ.ቁ 245661/ያልታተመ/ #Daniel Fikadu Law Office - አመልካቾች የተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት በተመሳሳይ ማታለል ወንጀሎች ሌሎች መዛግብቶች ያሉባቸው በወንጀሉም የመጠርጠር ሙያ አድርገው የያዙት መሆኑ ሲታይ በዋስ ቢወጡ ሌላ ወንጀል የሚፈጽሙበት ሁኔታ ሰፊ ነው በሚል ነው፡፡ የዚህ ግምት መሠረቱ አመልካቾች በዋስትና ቢወጡ ሌላ ወንጀል የሚፈጽሙበት እድል ሰፊ ነው የሚል እሳቤ የያዘ ስለመሆኑ ግንዛቤ የሚወሰድበት ነው፡፡ ሕጉ ፍ/ቤቱ ይህን ምክንያት ለግምቱ መነሻ እንዳያደርግ እስካልከለከለ እና ሕጉ ለፍ/ቤቱ ስልጣን የሰጠው ለመሆኑ የሚታመን እስከ ሆነ ድረስ የስር ፍ/ቤት የአመልካችን የዋስትና መብት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67(ሀ)(ለ)(ሐ) መሠረት የከለከለው በሕጋዊ ምክንያት ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካቾችን የዋስትና መብት በመንፈግ በሰጡት ትዕዛዝ ላይ የተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት አልተገኘበትም፡፡
👍1
#Ethiopia
የገጠር መሬትን በሸጠ ወይም በገዛ ማንኛውም ሰው ላይ እስከ 5 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት የሚጥል አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጸድቋል።
አዲሱ አዋጅ የግል ፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ ወርሮ ለተገኘ ሰው ተመሳሳይ የእስራት ቅጣት ደንግጓል።
ዛሬ የጸደቀው አዋጅ ከ18 ዓመት በፊት የወጣውን የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅን ያሻሻለ ነው።
አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች በመሬት ላይ ያላቸውን መብቶች አሻሽሏል የተባለ ሲሆን የሴቶች እና ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ያረጋገጡ ድንጋጌዎችንም አካትቷል ተብሏል።
አዋጁ ምን ይዟል ?
- ማንኛውም ሰው መሬት የሸጠ ወይም የገዛ እንደሆነ፤ ከ100 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ወይም ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም በሁለቱም ሊቀጣ ይችላል።
NB. በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረት " መሬት የማይሸጥ፣ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው "። ሕገ መንግስቱ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት የባለቤትነት መብትን የሰጠው " ለመንግስት እና ለህዝብ " ነው።
- የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ የወረረ ማንኛውም ሰው፤ ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አሊያም ከ30 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልበታል።
- የወል ወይም የመንግስት ይዞታ ላይ ጉዳት አድርሶ የተገኘ ማንኛውም ሰው፤ ከ3 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም ከ50 ሺህ እስከ 150 ሺህ ብር ይቀጣል።
- ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ማንኛውንም ግንባታ የሰራ ወይም እንዲሰራ የፈቀደ ሰው ደግሞ በአዲሱ አዋጅ መሰረት ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት አሊያም ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ይቀጣል።
- ከመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ውጪ ይዞታውን ጥቅም ላይ አውሎ የተገኘ ሰው ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት አሊያም ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ይቀጣል።
- ሀሰተኛ የመሬት ይዞታ ማስረጃ ያቀረበ ባለይዞታ እንዲሁም ማስረጃ የሰወረ ወይም የተሳሳተ ማስረጃ የሰጠ ባለሙያ ላይ የሚጣለው እስራት ከላይ እንዳሉት የህግ ጥሰቶች ተመሳሳይ ቢሆንም የገንዘብ ቅጣቱ መነሻ ግን ወደ 20 ሺህ ብር ዝቅ ብሏል።
ምንጭ፦ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@tikvahethiopia

የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 26ኛ መደበኛ ስብሰባው አዲሱን የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አጽድቋል፡፡
የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሰለሞን ላሌ የውሳኔ ሃሳቡን ለምክር ቤቱ በንባብ ያቀረቡ ሲሆን ፥ የረቂቅ አዋጁን መሻሻል አስፈላጊነት እና በምርመራው ሂደት የተከናወኑ ተግባራትንም በዝርዝር ለጉባኤው አስረድተዋል፡፡
አዋጁ የአርሶና አርብቶ አደሩን እና ከፊል አርብቶ አደሩን የኑሮ ደረጃ ሀገሪቱ ከደረሰችበት ዘርፈ ብዙ እድገት ጋር እኩል ለማራመድ የሚያስችል መሆኑ መገለጹን ከምክርቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ረቂቅ አዋጁ የተፈጥሮ ሃብቶችን በዘላቂነት በመጠበቅና በማልማት ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ፣ የሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ማረጋገጥ የሚያግዝ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ረቂቅ አዋጁ በምክርቤት አባላት ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን አዋጅ ቁጥር 1324/2016 አድርጎ አፅድቆታል፡፡ copy

አባትነት የሚረጋገጥባቸው መንገዶች በተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ሕግ
መግቢያ
ልጆች ወላጆቻቸውን የማወቅና ፍቅርና እንክብካቤ አግኝተው የማደግ መብት እንዳላቸው በዓለም አቀፍ የሕፃናት መብቶች ስምምነት አንቀፅ 7 እና በገራችን ሕገ-መንግስት አንቀፅ 36 ላይ በግልፅ ተደንግጎ እናገኘዋለን፡፡ ወላጆችን በተለመከተ በእናትነት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች በጣም አናሳ ቢሆኑም አባትነትን አስመልክቶ ግን ብዙ አከራካሪና እስከ ፍርድ ቤት ድረስ የሚደርሱ ጉዳዮች መኖራቸው የማይካድ ሀቅ ነው፡፡ በዚህ አጭር ፅሑፍ በተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ሕግ አባትነት የሚረጋገጥባቸውን መንገዶች እንዳስሳለን፡፡
የአባትነት ምንነት
የደስታ ተክለወልድ አዲስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት አባትነትን “አባት መሆን” ሲል የተረጎመው ሲሆን “አባት” ማለት ደግሞ ወላጅ፣ አስገኚ፣ አሳዳጊ፣ ሞግዚት፣… የንጀራ አባት፣ የእናት ባል” የሚል ትርጉም ሰጥቷል፡፡ የዚህ ፅሁፍ ዓላማም የተፈጥሮ አባትነትን የሚዳስስ በመሆኑ “ወላጅ” የሚለው ትርጉም የተሻለ ተስማሚ ሲሆን ይኸው መዝገበ ቃላት ወላጅነት የሚለውን ቃል “ወላድነት፣ ወላጅ፣ ወላድ መኾን፣ አባትነት፣ እናትነት፣ ልጅን አስገኝነት” የሚል ትርጉም ሰጥቶት እናገኛለን፡፡
አባትነት የሚረጋገጥባቸው መንገዶች
የልጅ ወላጆች ማንነት መታወቅ ለልጅ አስተዳደግም ሆነ ቀጣይ ህይወት እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ ከላይ በመግቢያው ላይ እንደተገለፀው የአንድ ልጅ እናትን ለማወቅ ሌሎች ልዩ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው ልጁን ፀንሳና አምጣ የወለደችው ተፈጥሯዊ እናቱ እንደሆነች ግልፅ ነው፡፡ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕጋችንም በአንቀፅ 124 ላይ ይህን ያረጋግጣል፡፡ በልጅና በአባት መካከል ግን እንደዚህ ዓይነት ተፈጥሯዊ መስተጋብር ስለማይኖር የልጁን ትክክለኛ አባት መለየት አደጋች የሚሆንባቸው ሁኔታዎች የሚገጥሙ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ሕጉ ሦስት አባትነትን የማረጋገጫ መንገዶችን ደንግጓል፡፡ እነዚህም በሕግ ግምት አባትነትን ማረጋገጥ፣ ልጅነትን በመቀበል አባትነትን ማረጋገጥ እና በፍርድ ቤት ውሳኔ አባትነትን ማወቅ የሚሉ ናቸው (የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 125)፡፡
በሕግ ግምት አባትነትን ስለማረጋገጥ
የሕግ ግምት ማለት አንድ ሕግ በአንድ ጉዳይ ላይ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ የሁኔታዎቹ መሟላት የአንድን ነገር መኖር ወይም አለመኖር ያረጋግጣል ሲል ድምዳሜ ላይ የሚደርስበት መንገድ ነው፡፡ አባትነትን አስመልክቶ ሕጉ መሠረት የሚያደርገው ልጁ በሚፀነስበት ወይም በሚወለድበት ጊዜ በእናትየዋና በአንድ ወንድ መካከል በሕግ የታወቀ ግንኙነት መኖርን በማረጋገጥ ነዉ፡፡ ይህም ልጁ ሲፀነስ ወይም ሲወለድ ከልጁ እናት ጋር በጋብቻ የነበረ ባል ወይም ጋብቻ ሳይፈጽም እንደ ባልና ሚስት አብሯት የነበረው ወንድ የልጁ አባት ነዉ ብሎ ሕጉ ግምት ይወስዳል፡፡ በመሆኑም በልደት ምስክር ወረቀት አባቱ ሌላ ነው ተብሎ ቢፃፍ ወይም አባቱ ሌላ ሰው መሆኑን የሚያመላክት ቢሆንም እንኳን የልደት ምስክር ወረቀቱ እርማት ይደረግበታል እንጂ የህግ ግምቱን አያስቀርም (አንቀፅ 126 እና 130)፡፡
ከጊዜ አቆጣጠር ጋር ተያይዞ ሊነሳ የሚችለውን ክርክር ለማስቀረት ሕጉ ቁርጥ ያለ ጊዜን አስቀምጧል፡፡ በዚህም ልጁ ጋብቻ በተፈፀመ ወይም እንደባልና ሚስት አብሮ መኖር ከጀመሩ በ180 ቀናት በኋላ ወይም ጋብቻው ከፈረሰ ወይም እንደ ባልና ሚስት መኖሩ ካበቃ ከ300 ቀናት ውስጥ የተወለደ ከሆነ ልጁ በጋብቻ ውስጥ ወይም እንደ ባልና ሚስት አብሮ በመኖር ውስጥ እንደተፀነሰ እንደሚቆጠር በአንቀፅ 128 እና 130 ተደንግጓል፡፡
ልጅነትን በመቀበል አባትነትን ማረጋገጥ
ከላይ በተገለፀው አግባብ በሕግ ግምት አባትነትን ማረጋገጥ ያልተቻለ ከሆነ በመቀበል አባትነት ሊረጋገጥ ይችላል፡፡ ይህም አባትየው ልጄ ነው ሲል በመቀበሉ ምክንያት አባትነት ሊረጋገጥ እንደሚችል በአንቀፅ 131 ላይ ተደንግጓል፡፡ እንዲህ ባለ ሁኔታ አንድ ሰው አንድን የተፀነሰ ወይም የተወለደ ልጅ የእርሱ ልጅ መሆኑን አምኖ በመቀበል ቃሉን የሰጠ እንደሆነ በአንቀፅ 132 መሰረት የልጁ አባት ይባላል፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለዉ ልጁ የተፀነሰዉ ወይም የተወለደው እናት ከአንድ ወንድ ጋር ጋብቻ ወይም ያለጋብቻ በአብሮ መኖር ሥርዓት ሳትመሰርት ልጅ ስትወለድ ነው፡፡ ምክንያቱም በመቀበል አባትነት ሊረጋገጥ የሚችለው በሕጉ ግምት መሰረት አባትነትን ማረጋገጥ ሳይቻል ሲቀር ስለመሆኑ በሕጉ የተቀመጠ በመሆኑ ጋብቻ ወይም ጋብቻ ሳይፈፀም እንደባልና ሚስት አብሮ የመኖር ሁኔታ ካለ አባትነትን በተመለከተ የሕጉ ግምት ቅድሚያ ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡
አባትየው መቀበሉን የሚገልጽበት ፎርም ወይም ሥርዓት በክብር መዝገብ ሹም ፊት በመቅረብ በሚሰጠዉ ቃል ወይም በጽሑፍ በሚያደርገዉ ኑዛዜ ወይም በሌላ በማናቸዉም ሥልጣን በተሰጠዉ ባለስልጣን በተረጋገጠ ሠነድ አማካኝነት ነዉ (አንቀጽ 133)፡፡ በመርህ ደረጃ አባትነትን የመቀበል ቃሉን መስጠት ያለበት አካለ መጠን ያልደረሰ ቢሆንም እንኳን አባት ብቻ ነዉ፡፡ ነገር ግን ቃሉን በፍርድ ቤት የፀደቀ ልዩ ዉክልና ስኖር ብቻ ሌላ ሰዉ መስጠት እንደሚችል በአንቀጽ 134 ተደንግጓል፡፡ አባትየዉ ሞቶ ከሆነ ወይም ፈቃዱን ለመስጠት የማይችል በሆነ ጊዜ አንቀጽ 135 መሰረት ከአባትየዉ ወላጆች አንዱ በእርሱ ስም ልጁን ሊቀበል ይችላል፡፡
አባት ነኝ ባዩ ቃሉን በሚገባው ሥርዓት መሰረት ቢሰጥም እንኳን የልጁ እናት የተቀባዩን አባትነት ካላመነች የተሰጠው ቃል በሕግ ፊት ዉጤት የለውም፡፡ ይህን ማረጋገጫ ሳትሰጥ እናት ሞታ ወይም ፈቃድ መስጠት የማትችል ከሆነች ከእናት ወላጆች በአንዱ ሊሰጥ ይችላል፡፡ የእናት ወላጆች የሌሉ ከሆነ ወደላይ የሚቆጠር ሌላ ወላጅ ወይም በፍርድ ቤት በተከለከለው ሰው አሳዳሪ ሊሰጥ እንደሚችል በአንቀጽ136 ተደንግጓል፡፡ አባት ነኝ ባዩ መቀበሉን የሰጠው ልጁ ለአካለ መጠን ከደረሰ በኋላ ከሆነ መቀበሉ ውጤት የሚኖረው ልጁ አባትነቱን ሲቀበል ብቻ ነው (አንቀጽ137)፡፡ በሁለቱም (በእናት ወይም በልጅ) የሚሰጠው ማረጋገጫ አባትነቱን መቀበሉን ካወቁበት ጊዜ ጀምሮ በ1 ወር ጊዜ ወስጥ ክርክር ካላነሱ አባት ነኝ ያለዉን ሰው አምነው እንደተቀበሉ ይቆጠራል (አንቀጽ 138)፡፡
በመርህ ደረጃ ልጅነትን መቀበል የሚቻለው ልጁ በሕይወት እያለ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ልጁ ሌላ ወደ ታች የሚቆጠር ልጅ ተክቶ ከሞተ ብቻ የሞተዉን ልጅ ልጅነትን መቀበል ይቻላል (አንቀጽ 139)፡፡ ይህ የሚያሳየው ሕጉ አባትነት መቀበልን ያመቻቸው ለልጅ ጥቅም ሲባል እንጂ ለወላጅ አባት ጥቅም አለመሆኑን ነው፡፡ በተጨማሪም ለአንድ ልጅ አባት ሊሆን የሚችለው አንድ ሰው ብቻ በመሆኑ ቀደም ብሎ አንድ ሰው ልጅነትን የመቀበል ቃል ሰጥቶ እያለ እና ቃሉም ካልተሻረ ወይም ካልፈረሰ በስተቀር ሌላ ሰው ልጄ ነው ሲል የሚሰጠዉ ቃል ተቀባይነት እንደማይኖረው ከአንቀጽ 142 መረዳት ይቻላል፡፡
ቃልን ስለመሻር እና ስለማፍረስ

አንድ ሰው የልጅ አባት መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ልጄ ነው ሲል የሰጠዉን ቃል መሻር አይችልም፡፡ ነገር ግን ቃሉን የሰጠዉ አካለ መጠን ያልደረሰዉ ልጅ ሲሆንና እሱን ተክቶ አስቀድሞ አሳዳሪዉ ስምምነቱን ካልሰጠ አባት ነኝ ያለው አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ አካለ መጠን ከመድረሱ በፊትእና ለአካለ መጠን ከደረሰ በኋላ እስከ አንድ አመት ጊዜ ድረስ ቃሉን ሊሽር ይችላል፡፡ በዚህም ሁኔታ የመሻር መብቱ አካለ መጠን ያልደረሰው ልጅ ብቻ ስለሆነ የልጁ ሕጋዊ ወኪሎችም ሆኑ ወራሾች ሊሽሩ አይችሉም (አንቀጽ 140)፡፡
በሌላ በኩል ልጅነትን ለመቀበል የተነገረው ቃል በኃይል የተሰጠ መሆኑን ማስረዳት ከቻለ አባትነቱን የተቀበለው ሰው የሰጠው ቃል እንዲፈርስ ማድረግ ይችላል፡፡ እንዲሁም ተቀባዩ ልጁ ከእርሱ ሊፀነስ የማይቻል መሆኑን በማያሻማ አኳኋን ካላረጋገጠ በቀር የመቀበሉ ድርጊት በስህተት ወይም በማታለል የተደረገ ነዉ በማለት ሊፈርስ እንደማችል በአንቀጽ 141 ተመልክቷል፡፡
ፍርድ ቤት ውሳኔ አባትነትን ማረጋገጥ
ከዚህ በላይ በተገለፁት ሁኔታዎች ማለትም በሕግ ግምትና ልጅነትን በመቀበል አባትነት ሊረጋገጥ እንደሚችል አይተናል፡፡ በሕግ የታወቀ ግንኝነት ሳይኖር የሚወለድ ልጅ አባት ነኝ ባይ ሰው በፈቃዱ ካልተቀበለ ልጁ አባት የሚያጣበት ሁኔታ መኖሩ እሙን ነዉ፡፡ በመሆኑም በመካድ ወይም ባለመቀበል አባትነትን ለሚያጡ ልጆች በፍርድ ቤት በሚሠጥ ዉሳኔ አባት እንድያገኙ የሚያስችል ሦስተኛ አማራጭ እንዳለ በሕጉ ተቀምጧል (አንቀፅ 125፣ 143 እና ተከታዮቹ)፡፡
በአንቀፅ 143 መሰረት አባትነትን በፍ/ቤት ዉሳኔ ለማረጋገጥ የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች መኖር አለባቸው ፡-
ልጁ በተፀነሰበት ጊዜ በእናቲቱ ላይ የመደፈር ወይም የመጠለፍ ተግባር የተፈጸመባት ሲሆን፣
ሆነ ተብሎ በተደረገ የተንኮል ድርጊት፣ ሥልጣንን ያለ አግባብ በመጠቀም፣ አገባሻለሁ በማለት የተስፋ ቃል በመስጠት ወይም በሌላ ተመሳሳይ መንገድ ልጁ በተፀነሰበት ጊዜ በእናቲቱ ላይ የማሳት ተግባር የተፈጸመባት ሲሆን፣
አባት ነው በተባለው ሰው የተጻፈና በማያሻማ ሁኔታ አባትነቱን የሚያረጋግጡ ደብዳቤዎች ወይም ሌሎች ጽሑፎች ሲኖሩ፣
በሕግ የታወቀ ግንኙነት ሳይኖራቸዉ የልጁ እናትና አባት የተባለው ሰው በሕግ በተመለከተዉ የእርግዝና ጊዜ ቀጣይነት ባለዉ ሁኔታ በግብረ ሥጋ ግንኙነት አብረው የኖሩ እንደሆነ፣
አባት ነው የተባለው ሰው ልጁን በመንከባከብ፣ በማስተማር ወይም በማሳደጉ ላይ እንደአባት በመሆን የተሳተፈ እንደሆነ ነዉ፡፡
ከእነዚህ ከአምስቱ ሁኔታዎች በእንዱ ምክንያት ልጅ ተፀንሶ ወይም ተወልዶ ከሆነ በድርጊቱ ላይ ተሳታፊ የነበረዉ ወንድ አባት ነው ተብሎ በፍርድ ቤት ይወሰናል፡፡
ማጠቃለያ
ልጆች አባታቸውን አውቀው በአካልም ሆነ በስነ ልቦና በአግባቡ ታንፀው ማደግ እንዲችሉ ሕጉ አባትነትን የማረጋገጫ መንገዶችን ያስቀመጠ ሲሆን ህብረተሰቡ በዚህ ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ ለልጆች መብት መከበር የበኩሉን ሊወጣ ይገባል፡፡
ኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

Forwarded from ETHIO ARSENAL
ስልክ በመንካት ብቻ በ10 ሺዎች ሚቆጠር ገንዘብ በተጨባጭ ተሰርቷል።
ከሳምንታት በፊት Telegram ላይ Notcoin ሚባል ዲጅታል ሳንቲምን ስልካችሁን Tap በማድረግ ብቻ ሰብስሩና ገንዘብ ስሩ ሲባል ብዙ ሰዎች አላግጠዋል። ከOrdinary ሰዎች አንስቶ እዚሁ Facebook ላይ ሚታወቁ የኢኮኖሚክስ ተንታኞች ጭምር "ስልክ በመንካት ብቻ በምንም ተዓምር ገንዘብ አይሰራም ህፃን አትሁኑ!" ብለው አውግዘው ነበር።
ይኀው ዛሬ ግዜው ደርሶ የስልክ ስክሪን በመንካት ብቻ የተሰበሰው ዲጂታሌ ሳንቲም ወደ ብር ተቀይሮ ወጪ መሆን ጀምሯል። ሳንቲሙ ሲለቀቅ በነበረው ተመን 10million የሰራ ሰው 10ሺ ብር አግኝቷል፤ በዚህ መሠረት እኔ እስካሁን ባየሁት ከ5ሺ ብር እስከ 65 ሺ ብር የሰሩ ልጆች አሉ (አስቡት ስልክ በመንካት ብቻ 65 ሺ ብር)። መቼም ከዚህ በኋላ በድጋሚ መሸወድ የላብችሁም።
ለማንኛውም አሁን ሌላ ዕድል አለ፤ ልክ እንደኖትኮይን ያለ ሌላ ተመሳሳይ ዲጂታል ሳንቲም አሁንም አለ ፤ ተሎ ሰብስቡ። ከስር ያለውን ሊንክ በመንካት ተከትላችሁ ግቡና Tap እያደረጋችሁ ገንዘብ ስሩ።
https://t.me/tapswap_mirror_1_bot?start=r_7120758084
🎁 +2.5k Shares as a first-time gift

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥⚡️💥
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከታች በተጠቀሰው መዝገብ ቁጥር የሚከተሉትን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል
👉ፍርድ ቤት እስከ 15 ቀን ድረስ ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 109/1 መሰረት የሰጠዉ ጊዜ ከአለቀ በኋላ በተጠርጣሪዉ ላይ ክስ ሳይመሰርት ተጠርጣሪዉን በእስር ላይ ማቆየት በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 17/2 እና በተባበሩት መንግሥታት የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን አንቀጽ 9/1 የተከለከለዉን በሕግ ከተደነገገዉ ሥርዓት ዉጭ በዘፈቀደ አስሮ እንደማቆየት የሚቆጠር ስለመሆኑ፡፡
👉ተጠርጣሪው የዋስትና መብት እንዲጠበቅለት ጥያቄ አቅርቦ ጥያቄዉ ውድቅ ከሆነ በኋላ የዋስትና ጥያቄ በድጋሚ ለማቅረብ የሚያስችል አዲስ ሁኔታ ሲፈጠር ይህንኑ አዲስ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ለዚያዉ ፍርድ ቤት የዋስትና መብት ጥያቄ በድጋሚ ለማቅረብ ሥነ ሥርዓታዊ መብት የአለዉ ስለመሆኑ፡፡
👉ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርት የተሰጠዉ የ15 ቀን ጊዜ ክስ ሳይመሰርት ያለቀ ከሆነ ተጠርጣሪው በድጋሚ ዋስትና ለመጠየቅ የሚያስችል አዲስ ሁኔታ የተፈጠረ በመሆኑና በድጋሚ የሚያቀርበዉ የዋስትና ጥያቄ አግባብነት ካለዉ ሕግ አንጻር ሳይመረመር በደፈናዉ ጥያቄዉ በድጋሚ የቀረበ ነው በሚል የተያዘዉ ሰዉ ክስ ሳይመሰረትበት ላልተወሰነ ጊዜ ታስሮ እንዲቆይ የሚያደርግ ትእዛዝ/ዉሳኔ መስጠት ስነስርዓታዊ አለመሆኑን አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል።

የስርቆት እና መሸሸግ ወንጀሎች
በተለይም የወንጀል ጎዳዮችን በምንመለከትበት ጊዜ አንደንድ ወንጀሎች ላይ ባለሙያዎችን የሚያከራከሩና በተለያዩ ባለሙያዎች ዘንድም የተለያዬ አቋም የሚወሰድባቸው ወንጀሎችን አስተውላለሁ፡፡ ይህ የሀሳብ ልዩነት በዐቃቢ ሕጎች ዘንድም ያለ በመሆኑ ከክስ አቀራረብ ጀምሮ ልዩነቱ ይንጸባረቃል፡፡ ከሚቀርቡ ክሶች በመነሳትም ሆነ ፍርድ ቤቶች በሕግ በአላቸው ሰልጣን መሠረት ከአንዱ ድንጋጌ ወደሌላ በመለወጥ ጊዜ ይህ ልዩነት በፍርድ ቤቶችም ይስተዋላል፡፡ የሕግ አተረጓጎም ልዩነት የሚደገፍና የሚበረታታ ብሎም ለዳበረ የህግ ሀሳብ መሠረት መሆኑ እንዳለ ሆኖ በአሰራር ረገድ ግን የልዩነት ምንጭ እና ለይግባኝ በር የሚከፍቱ ናቸው፡፡
በአብዛኛው ለክርክር የሚጋብዙና በጽንሰ ሀሳብም ደረጃ የግልጽነት ችግር ከሚስተዋልባቸው ድንጋጌዎች ውስጥ የስርቆት ወንጀል እና የመሸሸግ ወንጀል ይገኙበታል፡፡ በእነዚህ ሁለት ወንጀሎች መካከል ያለው አንድነትና ልዩነት ምንድን ነው? የስርቆት ወንጀል ተቋቋመ ወይም የመሸሸግ ወንጀል ተቋቋመ የሚባለው መቼ ነው? የሚሉ አንኳር ነጥቦችን በማንሳት በተወሰነ መልኩም ቢሆን ብዥታውን ለመቅረፍና በተግባር ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ብሎም ተገልጋይ ከታችኛው ፍርድ ቤት ወደ በላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ ምክንት ከሚደርስበት እንግልትና መጉላላት ለማዳን ይረዳል ብዬ በማመን ይህችን አጭር ጽሑፍ አዘጋጀሁ፡፡
2. ስርቆት ወይስ መሸሸግ?
ስርቆትና መሸሸግ ሁለት የተለያዩ ራሳቸውን የቻሉ ወንጀሎች ሲሆኑ የስርቆት ወንጀል በኢ.ፌ..ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 665 እስከ 669 ስር የተመለከተ ሲሆን የመሸሸግ ወንጀል ደግሞ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 682 እና 683 ስር ተደንግጓል፡፡
ሁለቱም ወንጀሎች በንብረት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች በሚለው ክፍል ስር የሚመደቡ ናቸው፡፡ ይህ አንድ የሚየደርጋቸው ባህርያቸው ሲሆን ልዩነታቸው ደግሞ ስርቆት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ የሚፈጸም ወንጀል በመሆኑ ሆን ተብሎ የሚፈፀምና የቸልተኛነት ጥፋት የሌለበት ነው፡፡ በአንፃሩ የመሸሸግ ወንጀል የግዴታ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት የሚፈጸም ላይሆን ይችላል፡፡ በማወቅ እና ማወቅ እያለበት (እየተገባው) የሚፈፀም በመሆኑ ሆን ተብሎና በቸልተኛነት የሚያስቀጣ ነው፡፡
ማቋቋሚያ ይዘቶች (elements)
ሁለቱ ወንጀሎች ተፈፀሙ ለማለት (ወንጀል ተቋቋመ) ለማለት መሟላት ያለባቸው ይዘቶች (elemnts) የተለያዩ ናቸው፡፡
2.1 የስርቆት ወንጀል
የወንጀል ሕግ አንቀጽ 665(1) “ማንም ሰው የማይገባውን ብልጽግና ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የሌላ ሰው ንብረት የሆነውን ተቀሳቃሽ ዕቃ ወይም ከማይንቀሳቀስ ንብረት የተነጠለን ዕቃ አንስቶ የወሰደ፣ በቀጥታ የራሱ ንብረት ያደረገ፣ ወይም በተዘዋዋሪ ከራሱ ንብረት ጋር እንዲቀላቀል ያደረገ እንደሆነ” በሚል ይደነግጋል፡፡
ስለዚህ የስርቆት ወንጀል ተቋቋመ ለማለት
የሌላ ሰው ንብረት የሆነ የሚቀሳቀስ ወይም ከማይንቀሳቀስ ንብረት የተነጠለ ዕቃ መኖሩ፣
ይህን የሌላ ሰው ዕቃ አንስቶ መውሰዱ፣ በቀጥታ ለራሱ ማድረጉ ወይም በተዘዋዋሪ ከራሱ ንብረት ጋር እንዲቀላቀል ማድረጉ፤
ይህ ተግባር የተፈጸመውም ለራስ ወይም ለሌላ ሰው ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት መሆኑ መረጋገጥ አለባቸው፡፡ እነዚህ የተሟሉ መሆኑን ዐቃቢ ሕግ ካሳዬ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 23(2) መሠረት የስርቆት ወንጀል ተቋቋመ ይባላል፡፡
ይሁን እንጅ በተግባር በብዙ ዳኞች እና ዐቃብያ ሕግ ዘንድ የስርቆት ወንጀል ተፈፀመ ለማለት ድርጊት ፈፃሚው ንብረቱን ሲወስድ ማየት ወይም የደርጊቱን አፈፃፀም ቅደም ተከተላዊ ሂደት የሚያሳይ (ለምሳሌ ዱካ፣ የተንጠባጠበ ነገር ወይም ምልክት) መኖርን እንደተጨማሪ መስፈርት የመፈለግ ዝንባሌ ያለ ሲሆን ሲወስድ ካልታዬ እና መሪ ምልክት ከሌለ ንብረቱ በአንድ ሰው እጅ ቢገኝ መሸሸግ እንጅ ስርቆት አይሆንም የሚል ሀሳብ ይንፀባረቃል፡፡ ብዙ ዐቃብያነ ሕግ በዚህ መልክ የተፈፀመ ድርጊትን በመሸሸግ ወንጀል የመክሰስ ልምዱ ያለ ሲሆን በብዙ ፍርድ ቤቶችም መሰል ተግባርን በመሸሸግ ጥፋተኛ ብሎ ቅጣት የመወሰን ልምድ አለ፡፡
ጉዳዩን ግልጽ ለማድረግ በምሳሌ እንመልከተው
ምሳሌ 1፡- የአቶ ደጉ የእህል ሚዛን በሌሊት ጠፋ፡፡ ሲፈለግ ሚዛኑ ከአቶ ሽብሩ እጅ ተገኘ፡፡ ይህ ሚዛን የግል ተባዳይ (የአቶ ደጉ) መሆኑ እና ከአቶ ደጉ እውቅና እና ፈቃድ ውጪ ከአቶ ሽብሩ እጅ መግባቱ ተረጋገጠ፡፡ በምን አግባብ ከአቶ ሽብሩ እጅ እንደገባ ግን አመላካች ነገር የለም፡፡ ይህ ጉዳይ የስርቆት ወንጀል ነው ወይስ መሸሸግ መሆን ያለበት? ስርቆት ለመባል አቶ ሽብሩ ሰርቆ ሲወስድ መታየት ወይም ዱካ መርቶ ከአቶ ሽብሩ ቤት ማድረስ አለበት?
በእኔ እምነት ከላይ የተገለፀው ነገር በስርቆት ወንጀል የሚያስቀጣ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ንብረቱ የአቶ ደጉ መሆኑ፣ ከአቶ ደጉ እውቅና (ፈቃድ) ውጪ ከአቶ ሽብሩ እጅ የተገኘ መሆኑ ከተረጋገጠ የሀሳብ ክፍሉ ከድርጊት አፈፃፀሙ የምንገነዘበው (infer) የምናደርገው ነው፡፡ ስለሆነም አቶ ሽብሩ ሲወስድ ባይታይም ንብረቱ (ሚዛኑ በእጁ የገባው የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቅ ወይም ማወቅ እየተገባው) የሚያስብል ሁኔታ ከሌለ ሊጠየቅ የሚገባው በስርቆት ወንጀል ነው፡፡ ይህን በመሸሸግ ወንጀል ተጠያቂ ለማድግ አቶ ሽብሩ ሚዛኑ የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቀ የተቀበለ (ያስቀመጠ) መሆኑ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ሚዛኑን ሲወስድ ከታዬ ደግሞ ወንጀሉ ሊሆን የሚችለው ውንብድና (አንቀጽ 670) ነው፡፡
2.2 የመሸሸግ ወንጀል
የወንጀል ሕግ አንቀጽ 682 ስለመሸሸግ ወንጀል የሚደገነግግ ሲሆን ድንጋጌው
ማንም ሰው ዕቃው የተገኘው በአንድ ንብረት ላይ በተፈፀመ ወንጀል ምክንያት መሆኑን እያወቀ ይህንኑ ዕቃ በመግዛትም ሆነ በተውሶ፣ በስጦታ፣ በመያዣነት የተቀበለ ወይም በማናቸውም ይህን በመሳሰመለ አኳኋን የወሰደ፣ የተገለገለ፣ ያስቀመጠ፣ ወይም የደበቀ፣ አሳልፎ የሸጠ ወይም በመሸጥና በመለወጥ ስምምነት ውስጥ አገናኝ ሆኖ የረዳ እንደሆነ
በማለት ይደነግጋል፡፡ ስለዚህ የመሸሸግ ወንጀል ተቋቋመ ለማለት
አንድ በወንጀል ፍሬ የተገኘ ዕቃ መኖር፣
አንድ ሰው ይህ ዕቃ በወንጀል ፍሬ የተገኘ መሆኑን ማወቅ፣
ዕቃው የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቀ የገዛ፣ በመያዣ፣ በትውስት፣ በስጦታ፣ ወይም መሰል መንገድ የተቀበለ፣ የተገለገለ፣ ያስቀመጠ፣ የሸጠ፣ አሳልፎ የሰጠ፣ የደበቀ ወዘተ መሆኑ መረጋገጥ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ የመሸሸግ ወንጀል ተቋቋመ ማለት አይቻልም፡፡
ዕቃው በወንጀል ምክንያት የተገኘ መሆኑን ማወቅ ወይም መገመት ነበረበት የሚያስብል ሁኔታ ሲኖር ደግሞ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 682(3) በቸልተኛነት መሸሸግ ይሆናል፡፡
ስለሆነም የመሸሸግ ወንጀል ሆነ ተብሎም ሆነ በቸልተኛነት የሚያስቀጣ ሲሆን ያልተገባ ጥቅም ማግኘት/ማስገኘት ማቋቋሚያ ሆኖ አልተደነገገም፡፡(copy)

❤1
❗ማንኛውም ሰው #የገጠር መሬት የሸጠ ወይም የገዛ እንደሆነ ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም ከብር 100,000 እስከ ብር 200,000 በሚደርስ መቀጮ ወይም በሁለቱም እንደሚቀጣ አዋጁ ይደነግጋል ::
የተሻሻለው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁ.1324/2016 ይዞት ከመጣው አዲስ ነገር አንዱ የወንጀል ተጠያቂነት ነው። በዚሁ አዋጅ አንቀፅ 62/6/ ላይ ማንኛውም ሰው #የገጠር መሬት የሸጠ ወይም የገዛ እንደሆነ ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም ከብር 100,000 እስከ ብር 200,000 በሚደርስ መቀጮ ወይም በሁለቱም እንደሚቀጣ አዋጁ ይደነግጋል::

በፍትሓብሔር ክርክር የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቀራረብና እልባት አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት
================================
ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በሰጠው መልስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማቅረቡን ማጣራት ይኖርበታል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ቀርቦ ከሆነ ከሳሽ መልስ እንድሰጥበት እድል ይሰጠዋል፡፡ በተቻለ መጠን ፍርድ ቤቱ ለቀረበው መቃወሚያ ወድያውኑ ወይም በአጭር ጊዜ ውስጥ እልባት ልሰጥ ይገባል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ክርክር ላይ የሚቀርቡ መቃወሚያዎች በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 244 (2(ሀ-ረ)) የተዘረዘሩት ሲሆኑ ነገር ግን ሙሉ ዝርዝር አይሆንም፡-
1ኛ/ ፍ/ቤቱ ነገሩን ለመስማት ሥልጣን ከሌለው፤
2ኛ/ ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ከሆነ፤
3ኛ/ ክስ የቀረበበት ጉዳይ በሌላ ፍ/ቤት በመታየት ላይ የሚገኝ ከሆነ፤
4ኛ/ አንደኛው ተከራካሪ በነገሩ ውስጥ አያገበውም የሚል መቃወሚያ፤
5ኛ/ ክሱ በይርጋ የሚታገድ ነው የሚል መቃወሚያ፤
6ኛ/ ክስ የቀረበበት ጉዳይ በዕርቅ አልቆ በስምምነት የተፈጸመ እንደሆነ ወይም ለዕርቅ የተቀጠረ እንደሆነ የሚያስረዳ ነገር ቀርቦ መቃወሚያ የተጠየቀ እንደሆነ ናቸው፡፡
ከዚህ በላይ ከቀረቡት መቃወሚያዎች አንዱ ወይም ከዚያ በላይ የቀረቡ እንደሆነ በቀረቡት መቃወሚያዎች ላይ ከዚህ በታች በተቀመጠው ሁኔታ ብይን ይሰጥባቸዋል፡-
1. ማስረጃ ተቀብሎ ከመመረመሩ ወይም ምስክሮችን ከመስማቱ በፊት ፍርድ ቤቱ አስቀድሞ ማናቸውም ተከራካሪ ወገን ላቀረበው መቃወሚያ ውሳኔ መስጠት አለበት (ቁጥር 244(1)) ፡፡
2. መቃወሚያዎቹ ከአንድ በላይ ከሆኑ ሁለም አንድ ላይ መቅረብ አለባቸው፡፡ ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት የሚያሰናክል ካልሆኑ በቀር መጀመሪያ ያልቀረቡ መቃወሚያዎች በኃላ መቅረብ አይችሉም፡፡ (ቁጥር 244(3))
3. መቃወሚያ መቅረብ ያለበት ከመከላከያ መልስ ጋር ነው እንጂ መጀመሪያ መቃወሚያ ብቻ ቀርቦ ሙለ መልስ በኃላ የሚቀርብበትን አሠራር ፍርድ ቤቱ መፍቀድ የለበትም፡፡ ስለዚህ ሙለ መልስ ተሟልቶ ሳይቀርብ መቃወሚያው ብቻ የቀረበለት ፍርድ ቤት በቁጥር 338 መሠረት የመከላከያ መልሱን ሲመረምር እንድህ አይነቱን ያልተሟላ መልስ አለመቀበል ወይም ተሰተካክል እንድቀርብ ማዘዝ አለበት፡፡
4. ክሱ ትክክለኛውን ፎርም አልተከተለም የሚል ክርክር እንደመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መቅረብ አይችልም (ቁጥር 244)፡፡ (ክሱ ፎርሙን መከተልን የሚያጣራው ሪጅስትራር ስለሆነ ነው፡፡)
5. ፍርድ ቤቱ የቀረበውን መቃወሚያ እንዲሁም የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ በቁጥር 245 መሠረት ተገቢውን ውሳኔ ይሰጣል፡፡
6. የቀረበው መቃወሚያ ክሱ የተነሳበት ጉዳይ በይርጋ የታገደ መሆኑን፣ ወይም አስቀድም በፍርድ የተወሰነ መሆኑን፣ ወይም በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈጸመ መሆኑን፣ ወይም ለዕርቅ የተቀጠረ መሆኑን የሚገልፅ ከሆነና ይህም በማስረጃ ከተረጋገጠ ፍርድ ቤቱ ክሱን ዘግቶ ባለጉዳዮቹን ያሰናብታል (ቁጥር 245(2))፡፡
7. ከላይ በቁጥር 6 ስር ከተገለፀው ውጪ ያለ መቃወሚያ ሲቀርብና በማስረጃ ሲረጋገጥ ግን ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ዘግቶ ተገቢ መስሎ የታየውን ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡
8. ከላይ በቁ. 7 ሥር በተጠቀሰው ሁኔታ መዝገቡ ሲዘጋ ካሳሽ ክሱን አሻሻሎ በዚያው ወይም በሌላ ፍርድ ቤት ክሱን እንደገና ለማቅረብ ይችላል፡፡ ከላይ በቁጥር 6 ሥር በተጠቀሰው ሁኔታ ክሱ ሲዘጋ ግን ከሳሹ በዚያው ጉዲይ ላይ ክስ ለማቅረብ አይችልም (ቁጥር 245 (3))፡፡
9. መዝገቡ የተዘጋው ፍርድ ቤቱ ሥልጣን በማጣቱ ከሆነ ከሳሹ ከከፈለው የዳኝነት ገንዘብ ላይ በደንቡ መሠረት ከሚከፈለው ሂሣብ የቀረው ይመለስለታል (ቁጥር 245 (4)) ፡፡

👍3