Good-thinkingጥሩ_እናሰብ
19 subscribers
1 video
4 links
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Key board and its key
1. Alphabet key( The key which contain A to Z)
2. Functional key(which is occur at head of key board
that is F1-F12)
3. Symbol key (the key which is occur top of key board
which contains syembol(!,@,#,$,%,^,&,*,(,),_,+,=,>etc).
Symbol is always write by use Shit+symbol)
4. Backspace: This key deletes letters backward.
5. Delete: This key deletes letters forward.
6. Shift: this key, when pressed with another key, will
perform a secondary function, like capitalizing text
7. Spacebar: this key enters a space between words as you
type
8. Tab: this key will force the cursor to indent or jump to
another entry field
9. Caps Lock: This key will present the capitalized version
of each letter key.
10. .Control (Ctrl): This key, when pressed WITH another
key, performs a shortcut.
11. Enter: This key executes a command (pressed in
Microsoft Word, it begins a new line)
12. Number Keypad: this is a redundant keypad existing
only for user preference.
13. Arrow keys: Like the mouse, these keys are used to
navigate through the document upand down ward ,left
and right move.
14. ESC key= used to cancel process of acction in computer
15. Start key =used to start computer with outmouse
16. Home key :Move the curoser at the beginning of line and
17. Ctrl+Home:Move the curose at the beginning of the page
18. End key:move the curoser at the end of line and
Ctrl+end:move the curose at the end of the page
19. Page up:move one page up from the current page
20. page down:move one page down from the current page
21. Mathematical operation(Addtion (+),Subtraction(-),
multipication(*),division(/),power(^),equal(=),greater
than(>),less than(<), etc)
IT2013
ልጅ አባቱን " ፕሬዜዳንት ማለት ምን ማለት ነው? " ብሎ ይጠይቃል።
አባት:- " ፕሬዜዳንት ማለት መሪ ማለት ነው። አሁን ለምሳሌ እኔ የዚህ ቤት ፕሬዜዳንት ነኝ።" ብሎ ይመልስለታል።
ልጅ ጥያቄውን አላቆመም።
ልጅ:- " እናቴስ ምንድን ናት?"
አባት:- " እናትህ ገንዘብ ሚኒስቴር ናት።"
ልጅ:- " አያቴስ?"
አባት:-" አያትህ ሰላይ ናት።"
ልጅ አሁንም ጥያቄውን ቀጠለ " እኔስ ምንድን ነኝ?"
አባት:- " አንተ ህዝብ ነህ።" ብሎ ይመልስለታል።

በሌላ ጊዜ አባት ስራ ሄዶ መኖሪያ ቤታቸው ሌላ ሰው ይመጣል። ከዛም ልጅ ተደብቆ አባቱ መስሪያቤት ይደውልና ምን ቢል ጥሩ ነው?










" ሄሎ አባዬ! ትሰማኛለህ? እቤታችን ሌላ ፕሬዝዳንት መጥቷል፣ ገንዘብ ሚኒስቴር ሽር ጉድ እያለ ነው፣ ሰላይ ያንቀላፋል፣ ህዝብ ግን ተጨንቋል።
THERE ARE 4 VERY IMPORTANT WORDS IN LIFE

Love,Honesty,Truth,Respect

Without these in your life

YOU HAVE NOTHING.

ᴘsʏᴄʜᴏ thoughts
Love is what you do, inspite of what you feel.
Sandwiches "taste better" when they're made by someone else When you make your own, you anticipate its taste, and become less hungry for it
#funfact
ከድሮ ፍቅረኛዬ ጋር በኔትወርክ ምክኒያት እኮ ነው የተጣላነው...

#እሷ፦ "እንዴት አደርክ ውዴ "
#እኔ፦ " እንዴት አደርሽልኝ የኔ ማር (sending failed)
#እሷ፦ "ለምንድነው የማታወራኝ ውዴ "
#እኔ፦ "አረ ኔትዎርኩ እምቢ ብሎኝ ነው (sending failed) "
#እሷ "በቃ ለእኔ ያለክ ፍቅር የውሸት ነው ?"
#እኔ፦ "አረ ሜሪ ቴክስቱ በኔትዎርኩ ምክኒያት አልላክም ብሎኝ ነው (አሁንም እምቢ አለ አልተላከም )
#እሷ "በቃ ስትፈልግ ገደል ግባ አንተ ባታወራኝ ስንቱ የሚያወራኝ መሠለህ ከእንግዲህ ላገኝክ አልፈልግም "
#እኔ፦ "አቦ የራስሽ ጉዳይ ምን ትጨቃጨቂያለሽ የፈለግሽበት ሂጂ (sent successful /ቴክስቱ ተልኳል)
ፌክ አካውንት ከፋቼ ሚስቴን ለ2 ሳምንት ብጀነጅናት
'
'
'
ባሌ ከሞተ 1 ወሩ አለችኝ 😪🤧
ፕሮቴስታንት ቺክ መጀንጀን በጣም ይከብዳል

ውዴ በጣም እኮ ነው ምወድሽ ስላት

አሜን ወንድሜ አንተንም ጌታ ይወድሀል
😊
ከመጠጥ ቤት ተፈንክተህ ሆስፒታል ከገባህ በኃላ ነርሷ ለቁስሉ አልኮል አምጡለት ስትል

ማነሽ እናት ደብል አርጊው🤤🤤🤕
❣️#ስለ_ፍቅር ❣️

" በቦታም ሆነ በጊዜ አውታር የማይለካ፣ በሁሉም ስፍራና ጊዜ የሚኖር፣ የግራቪቲን ሕግ የሚደመስስ ክስተት አለ፣ እሱም" ፍቅር"ብቻ ነው።"
#ኦሾ

"ፍቅር ከሚነደው የነፍስ ጉድጓድ በመመንጨት ምድሪቱን በብርሃን የሚሞላ አስማታዊ ጨረር ነው፡፡ ፍቅር ሰው የአምላኩን ሀይል እንዲያይ የሚያስችለው ሰማያዊ ዕውቀት ነው፡፡"
#ካህሊል_ጂብራን

"በጥበብ ማፍቀርን የመሰለ ነገር የለም፡፡ ይሁን እንጂ ምንም ካለማፍቀር ግን በሞኝነትም ቢሆን ማፍቀሩ ይመረጣል"
#ዊልያም_ኤልቪስ

"በህይወት ውስጥ ካሉ ነገሮች ሞትን በብቸኝነት ሊያሸንፈው የሚችለው ነገር ፍቅር ብቻ ነው፡፡"
#ኦሾ

"ፍቅር የተሟላ ህግ ነው።"
#ቅዱስ_ጳውሎስ

"እርጅና ሁሉ በአንድ ውስጥ ቢታወር ከማፍቀር አያስጥልህም ይሁን እንጂ ብዙውን ጊዜ ፍቅር ከእርጅና ያስጥልሀል።"
#ጂያን_ሞሬታ

"ያልበሰለ ፍቅር ‹አፈቅርሻለሁ ምክንያቱም ታስፈልጊኛለሽ› ይላል የበሰለ ፍቅር ደግሞ ‹ታስፈልጊኛለሽ ምክንያቱም አፈቅርሻለሁ› ይላል"
#ኤሪች_ፍሮም


"በፍቅር ብትወድቁ፣ የመሬት ስበት ተጠያቂ አይደለም፤"
#አልበርት_አንስታይን


"ፍቅር ያዘኝ ማለት በጣም ቀላል ነዉ.. በፍቅር ዉስጥ መቆየት ግን ልዩ መሆንን ይጠይቃል፡፡"
#ፌቡ

"ፍቅር ራሱን እንጂ ሌላ ምንም አይሰጥም፤ ከራሱ እንጂ ከሌላ ከማንም ምንም አይቀበልም፤ ፍቅር ለፍቅር በቂ ነውና!! ፍቅር ምንም ንብረት የለውም፣ የማንም ንብረት ሊሆንም አይችልም።"
#ካህሊል_ጂብራን

"ፍቅር ሲኖር ስራ ሁሉ ቀላል ይሆናል."
#ካህሊል_ጂብራን

"ፍቅር ከጥልቁ ውስጣችን የሚመጣ ነው። በጥያቄ ልናመጣው አንችልም ሲመጣም ዝም ማሰኘት አይቻልም። ፍቅር እኛ የምናደርገው ምርጫ አይደለም።"
#ኦሾ

"እውነተኛ ፍቅር ሁሉንም ያሳያል በእውነት ስታፈቅር መስተዋት ፊት በየዕለቱ እንደመቆም ይቆጠራል"
#ጀኒፈር_አኒስተን

"ለፍቅር የበለጠ ከማፍቀር ውጭ ሌላ ፈውስ የለውም።"
#ሔነሪ_ዴቪድ_ሰሮው

"የማያፈቅር ልብ ከሚኖረኝ የማያዩ አይኖች፣ የማይሰሙ ጆሮዎችና የማይናገር አንደበት ቢኖረኝ ይሻላል!"
#ሮበርት_ቲዞን

"ወሳኙ የምትሰጠው መጠን ትንሽነትና ትልቅነት ሳይሆን በምትሰጠው ነገር ላይ የምትጨምረው ፍቅር ነው።"
#ማዘር_ቴሬዛ

"በአብዛኛው ጊዜ ሴቶች የፍቅር ትርጉም የሚጠፋባቸው በውበታቸው ማምለክ ሲጀምሩ ሲሆን፣ ወንዶች ደግሞ ገንዘባቸውን ማምለክ ሲጀምሩ ነው፡፡"
#ያልታወቀ

"ፍቅር መስማት የተሳነው ሰው ሊያዳምጠውና አይነስውር ሊያነበው የሚችል ቋንቋ ነው።"
#ኮልሬጅ

"የሚያፈቅር ልብ ሁልጊዜ ወጣት ነው"
#ግሪኮች

🎁ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ!🎁
ጀለስ መንጃ ፍቃድ ተፈትኖ ሲመጣ እንዴት ሆንክ ስለው...
.
#የማልፍ_ይመስለኛል ፈታኙን ገጭቼዋለሁ ከሆስፒታል ሲወጣ ነው የሚነግረኝ🚐🚐
ብርዱም ተነሳበት - ያው ዝናቡ መጣ '
ትውስ አለኝ ፍቅርሽ - አንቺን አለኝ አምጣ
'
እርሷ በንዴት:
'
ይሄን ሁላ ጊዜ አንዴም - ትዝ ያላልኩህ !
ክረምቱ ሲገባ አሁን - የታወስኩህ '
ዘርተህ ያበቀልከኝ - በቆሎ መሰልኩህ !!
ልባም ሚስት ባሏ ሸክ ብሎ ሊወጣ ሲዘገጃጅ በነጭ ሽንኩርት ያበደ ፍርፍር ታጎርሰዋለች።
Forwarded from Feker Yashenfal
የደብተርና የወረቀት ዋጋ በዚሁ ከቀጠለ መጪው ትውልድ በቃሉ እየያዘ እንደሚማር ይገመታል
(#ሊብራ_ልጅ)

ከመስከረም 13 እስከ ጥቅምት 12
Best ደስተኛ ቤተሰብ ውስጥ ሚኖሩ ከሆኑ በጣም የተረጋጉ ልጅ ይሆናሉ።

»» በማህበረሰብ ውይይት ወቅት ሁሌም ተሳታፊና አሳታፊ ንግግሮችን ያደርጋሉ፣ ውይይቶች ወደ አንድ ያጋደሉ ከሆነ፣ ድልድይና ሁለቱን ሀሳቦች ሚያስታርቁ ሀሳቦችን ያቀርባሉ። ተግባቢ ቢሆኑም ለብዙ ግዜ፣ አብሯቸው ከቆዩ ሰዎች ጋር መሆንን ይመርጣሉ። ከትልቅ ሰዎች ጋር እንዴት መግባባት እንዳለባቸው በደንብ ያዉቃሉ፣ ጎበዝ ናቸው። ከብዙ ሰዎች ጋ ከመወያየት፣ አንድ በአንድ ቢያወጉ ይመርጣሉ፣ እንዲ አይነት ዉይይቶችም የበለጠ ይጠቅማቸዋል፣ አለምን ሚመለከቱበትን አቅጣጫ የሰላና የበሰለ እንዲሆን ያደርጋዋል።

»» ስሜታዊ ሚሆኑበት አጋጣሚዎች ትንሽ ናቸው፣ በተቻላቸው አቅም ምክንያትና ሁኔታዎችን ባላንስ ለማድረግ ይሞክራሉ። ሊብራዎች በውስጣቸው የቱ ትክክል እንዳልሆነ፣ የቱ ትክክል እንደሆነ ተሰምሮ በውስጣቸው አለ፣ ያውቁታል፣ በዚህ የተነሳም ምርጥ አደራዳሪ ይወጣቸዋል። ኔጌቲቪቲ ሊብራዎችን ያሳምማቸዋል፣ ካልሆነም እንኳን ከሁሉም ነገር ራሳቸውን ያገላሉ። ለሕግጋት እንኳን ተገዢ ሚሆኑት ሕጉ የማያደላ ከሆነ ብቻ ነው። ሊብራ ልጆች ከመጣን በላይ ጣፋጭ ይወዳሉ፣ እንደያበዙ በመጠኑ እንዲበሉ ያድርጓቸው።

(#ሊብራ_ሴት_ልጅ)          

»» የሊብራዎች ገዥ የሆነችው ቬነስ ለሊብራ ልጆች ደስሚል ገፅታ ትሰጣለች፣ በሷ አከባቢ ላይ ላሉት ሰዎች ደስተኛ እንዲሆኑ ታደርጋቸዋለች፣ ሊብራ ሴት ልጅም ትኩረትና ምለሽ ትፈልጋለች፣ በተለይ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ፣ እሷ ምትፈልጋቸው ነገሮች እንደምትፈልጋቸው ካልሆኑ ትደነግጣለች፣ ወደ ቀድሞ ሁኔታ ለመመለስ በምታደርጋው ጥረት ውስጥም፣ ያስሜት መዋዠቅ ይታይባታል።

»» ምርጥ የፈጠራ ብቃት አላት፣ ከጓደኞቿ ጋ መሰብሰብ መዝናናት ትወዳለች፣ ያልተሟላላት ምትፈልጋቸው ነገሮች ካሉ ሰላም አይሰማትም፣ ነፃነት ይፈልጋሉ፣ ዝግጅቶችና ፓርቲዎችን ትወዳላች፣ ውሰዷት፣ ጥሩ አለባበስ፣ ጥሩ ሙዚቃና እንዴት ፓርቲ ማዘጋጀት እንዳለባት ጥሩ ግንዛቤ አላት፣ ለፍትህ ያላት አቋም ጠንካራ ነው፣ በዚ የተነሳም ይሰበራሉ፣ ይጎዳሉም። ስራዎችን መስራት ስትፈልግ ባሰበችበት ግዜ ላይ እንድትሰራ ፍቀዱለት፣ ለስራውም ቅልጥፋና ሆነ፣ የፈጠራ ብቃቷን ለማሳደግ ይጠቅማታል።

»» ከት/ቤ ስትመለስ ለራሷ ብቻ ግዜ ሰታቿት በደንብ አውሯት፣ ስለ ት/ቤት ውሎዋ ሆነ ስለምንም ነገር። ሴቶቹ ሊብራዎች ከወንዶቹ በላይ በስሜት ይነካሉ። ሴቶቹ ብዙ ግዜ ወደ አርትና ሙዚቃ ሲሳቡ፣ ወንዶቹ እንቆቅልሾችን መደርደርና የተለያየ ሞዴል ዲዛይነሮችን መመልከት ይወዳሉ፣ ሁለቱም ለልዕለ አዕምሮ ቅድሚያ ይሰጣሉ።  በት/ቤ ውስጥ ተግባቢ ናቸው፣ ትምህርት ላይ በደንብ ትኩረት ማድረግ እንደለባቸው ያውቃሉ፣ አሪፍ የፈጠራ ችሎታ አላቸው፣ የተለያዩ ክበባት ውስጥም እነሱን መመልከት የተለመደ ነው።

(#ሊብራ_ወንድ_ልጅ)  

»» ሊብራ ወንድ ልጆች ነገሮችን ሲመለከቱ ከአንድ አቅጣጫ ብቻ አይደለም፣ ከሁሉም ጎን ያለውን እውነታ ይመለከታሉ፣ ለሚወዷቸው ሰዎች ደራሽ ናቸው፣ ሁሌም ምርጡን ነው ሚመኙላቸው፣ ችግር ውስጥ ካሉም ከነሱ ቀደሞ ደራሽ የለም። ቪርጎዎች የራሳቸውን ስራ ጠንቅቀው ሲሰሩ፣ ሊብራዎች ሰዎችን እንዴት በጋራ ማሰራት እንዳለባቸው ያውቃሉ፣ ሌሎችን እንዴት ማስተባበርና ማሰራት እንዳለባቸው ቢናገሩም፣ በራሳቸው ሕይወት ውስጥ ግን እንዴት ውሳኔዎችን ማስተናገድ እንዳለባቸው ግራ ሲጋቡ ይታያሉ፣።

»» ሊብራ ልጆች አንድ አንድ ውሳኔዎችን፣ ከራሳቸው ፍራቻ ጋ ያያይዙታል፣ እርዳታ ሲፈልጉ ወላጆች አግዟቸው፣ አርቲስቲክ የሆነ ፍላጎት ነው ያላቸው፣ ንፁ ክፍልና የራሳቸው ማሰቢያ ግዜ ስልሚፈልጉ አክብሩላቸው፣ ያልገባቸውንም እንዲገባቸው በደንብ አብራሩላቸው። በብዙ ሊብራዎች አንደበት ውስጥ its knot fair ሚል ቃል አይጠፋም፣ ያልሆነ ድርጊት ካዩ ከወላጆች ጋርም ይሁን ከሌሎች ሰዎች ጋር ሙግት ይገጥማሉ፣ ለማንኛውም ነገር ምክንያትዮሽን ይፈልጋል።

»» ሊብራ ልጆች መርሳት ላይ ጎበዝ ናቸው፣ የቤት ስራቸውንም፣ ምሳቸውን ወይ መጫዎቻቸውንም ሊሆን ይችላል ይረሳሉ። ሲስቁ ፈገግታቸው አይጠገብም፣ ካሜራ አቀባብሎ መጠበቅ ብቻ ነው። ሊብራ ልጆች ተደጋጋሚ ትኩረት ይፈልጋሉ፣ ከእህትና ወንድሞቻቸውም ጋ ትንሽ ቁርሾም አይጠፋም፣ እኔ አዉቃለው ይላሉ። ሊብራዎች የጥምረት ዞዳይክ ስለሆነ ፍቺም ሆነ ጥል በጣም ይጠላሉ።

»» ቅርብ ለሆኑ ጓደኞቻቸው፣ የኔ ማለት ያንተም ነው ያሚል ብሂል አላቸው፣ የግዜ አጠቃቀም የሊብራዎች ዋንኛ ችግር ነው፣ በጫዎታና ከሰዎች ጋ ባላቸው ግንኙነት ይዘናጋሉ፣ እንዴት ግዜን መጠቀም እንዳለባቸው፣ ሆነ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው አሳዯቸው፣ ተገቢ የሆነም እንክብክቤን ይፈልጋሉ። ለምሳሌ ሊብራ ልጆች ልደታቸው እንዲያልፋቸው አይፈልጉም፣ ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋ ማክበር ይፈልጋሉ፣ እነዚ ልጆች የነገሮች ድምቀት ናቸው።
.
# የአለም__እውነታወች
1. የሚከተልህ ሁሉ አድናቂህና ወዳጅህ አይደለም ፣ አንዳንዱ የሚከተልህ ሊጥልህ ነው

2. ሕይወት ድልድይ ናት፣ አቋርጣት እንጂ
በላይዋ ላይ ቤት አትስራ።

3. ውሀ ቅርፁን ከመያዣው ጋር እንደሚስማማ
ሁሉ ብልህም ራሱን ከሁኔታው ጋር ይስማማል።

4. ምንም ያህል ርቀት በተሳሳተ መንገድ
ብትጓዝም ወደኋላ ተመለስ።

5. ዝቅ ብለህ ብትመለከት ምን ያክል ከፍ
እንዳልክ ታውቀዋለህ።

6. አንድ ሰው ስትተዋወቀው በልብሱ
ልትመዝነው ትችላለህ፣ ስትለየው ግን
በአስተሳሰቡ ትመዝነዋለህ።

7. ሠርግ እና ቀብር አንድ ናቸው። ልዩነቱ
የሠርግ አበባን ባለቤቱ ማሽተት መቻሉ ብቻ
ነው።

8. ማንክያ የሾርባን ጣዕም እንደማያውቅ ሁሉ
ለስሙ የተማረም የጥበብን ጣዕም አያውቅም።

9. ሀገር እንዳትጠፋ ትልቅ ነገርን አታጥፋ።
"ሰው ሆይ በትዕቢትና በንቀት መወጠርህን
አቁም። የውሸት መኖርህን፣ ሰዎችን መበደልህን፣
ፈጣሪህን ማሳዘንህን አቁምና መልካም ነገርን
አድርግ። ልብ በል ሺህ ጊዜ የውሸት ብትኖር
አንድ ጊዜ የእውነት መሞትህ አይቀርም።

#ሼር ያድርጉ
#ፍትሕ

በሀገራችን በተደጋጋሚ ጊዜ ሴቶች ፣ ትንንሽ ህጻናት ሳይቀሩ ይደፈራሉ ፤ ይገደላሉ የሚሰጠው ፍርድ ግን " እውነት ፍርዱ ለማስተማር ነው ? ፍትሕ ለማስፈን ነው ? " የሚል ጥያቄ የሚያስነሳና እጅግ በጣም አስደንጋጭ ጭምር ነው።

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ፥ መቼም ስለ ሚደፈሩ ሴቶች ፤ ደጉን ከክፉ ያለዩ ምንም የማያውቁ ህጻናት ሳይቀሩ ስለሚፈጸምባቸው አሰቃቂ ግፍና ወንጀለኞች ላይ ስለሚተላለፉት ፍርዶች ብዙ ጊዜ መረጃ ስንለዋወጥ መቆየታችን ይታወሳል።

ለአብነት በቅርብ ወራት እንኳን ፦

- " የ11 ዓመቷን ልጅ የደፈረው አባት 16 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት ተቀጣ። "

- " አንገቷን አንቆና አፏ ውስጥ ጨርቅ ጠቅጥቆ የ14 ዓመቷን ልጅ የደፈረው እና ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በ19 ዓመት ተቀጣ። "

- " የ5 ዓመቷን ህፃን የደፈረው የ17 ዓመት ወጣት በ6 ወር እስር ተቀጣ። "

- " የ10 አመቷን ህፃን ልጅ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ። "

- " የ4 አመቷን ህጻን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ17 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ። "

- " የ8 አመት ህፃናትን አስገድዶ የደፈረው የ41 አመት ጎልማሳ በ10 አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ። "

- " እጅግ አረመኔያዊ በሆነ ሁኔታ ሁለት የ16 እና የ17 ዓመት ልጆቹን በአልኮል አደንዝዞ አስገድዶ የደፈረው አባት በ21 አመት ተቀጣ። "


የሚሉ እነዚህን መረጃዎች በቲክቫህ ገጻችሁ ላይ አንብባችኋል።

ይኸው ዛሬ ደግሞ ጆሮን ጭው ፤ ልብን ቀጥ የሚያደርግ የባህር ዳሯን የ7 ዓመት ህጻን ሔቨንን ጉዳይ ሰማን።

ህጻን ሔቨን ላይ እጅግ አሰቃቂ የመድፈር እና የግድያ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ 25 ዓመት እንደተፈረደበት ተሰማ።

ጭራሽ ይህም እንዳይሆነ የግለሰቡ ቤተሰቦች፣ ጎረቤቶች ፣ አንዳንድ የፖሊስ አባላት ፣ ከፍትህ አካላት ጭምር ጥረት ሲያደርጉ ነበር።

በሔቨን ጉዳይ በርካቶች ልባቸው ተሰብሯል ፤ ተቆጥተዋል። የመንግስት አካላትም ስለ ጉዳዩ ፊት ለፊት ወጥተው ተናግረዋል።

እናት የፍትሕ እያለች ነው። ለፍትሕ እያነባች ነው።

የግለሰቡ ቤተሰቦችም #እህቱን ጨምሮ ስራ የምትሰራበት ቦታ ድረስ ተከታትለዋት መቀመጫ መቆሚያ አሳጥተዋት ስራ እንድትልቀ አድርገዋል።

ከፍርዱ በፊትም ብዙ ማስፈራሪያ ሲደረግባት ነበር። ኃላም እንደዛው።

ማስፈራሪያ እና ክትትሉ ብዙ ጊዜ ቤት እንድትለቅ አድርጓታል።

ዛሬም ለቅሶ ላይ ናት። እናት ዛሬም የፍትሕ ያላህ ትላለች።

" የት እንዲህ ? ወይ ሌላ ሀገር የለን ? ለማን እንናገር ? ማንስ ይሰማናል ? የእውነት አምላክ እሱ ይፍረድ ነው " ቃሏ።

የሔቨን ጉዳይ የብዙዎች ነው።

የእናቷ አንባ የብዙዎች ነው።

ስንት እናቶች ናቸው እውነተኛ ፍርድና ፍትሕ አጥተው ቤታቸውን ዘግተው እያለቀሱ ይሆን ?

መሰል ጉዳዮች ሰሞነኛ ጉዳይ እየሆኑ እያለፉ ነው።

አንድ ሰሞን ይወራል ከዛ ይተዋል። በቃ ሊባልና መፍትሄ ሊፈለግ ይገባል።

የወንጀለኞቹ መታሰር የልጆቻችንን  ህይወት እንኳ ባያስመልስም ትክክለኛ ፍርድ ግን ቢያንስ እንባ ያብሳል። ሌላውን ያስተምራል። አሁን እየሆነ ያለው ያ አይደለም።

ፍትሕ ይስፈን !
አስተማሪና ሀቀኛ ፍርድ ይፈረድ !
ፍትሕ ! እውነተኛ ፍትሕ ለተነፈጉ በርካታ ሴቶች፣ እናቶች ፣ ሕጻናት !
➡️ ሚዳቆ 🦌 ጠዋት በተነሳች ቁጥር ሊበላት የተሰናዳን አንበሳ እየሮጠች ማምለጥ እንዳለባት ካሎነም እንደምትሞት እያወቀች ነው ።

➡️ አንበሳውም🐆 ጠዋት በተነሳ ቁጥር ከሚዳቆዋ ፍጥነት በላይ መሮጥ እንዳለበት ካሎነ ግን በርሀብ እንደሚሞት ያውቃል።

ሚዳቆዋንም ሆንክ አንበሳ ጠዋት በተነሳህ ቁጥር ለኑሮ መሮጥ እንዳለብህ አትርሳ።