❖ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን TUBE❖
1.73K subscribers
92 photos
8 videos
5 files
70 links
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሊቃውንት እና በመምህራነ ወንጌል የሚቀርብበት፡፡Watch "ሊቃውንተ ቤተ ክርስትያን ቲዩብ" on YouTube
https://youtube.com/channel/UCwgXhC5VHW17S-TUMuvPZrw
@lkawntabot
Download Telegram
++ ‹‹ ትንሣኤና ሕይወት ›› ++

ሞት ህይወትን ይየዘው ዘንድ አልተቻለውም ነብሳትን ከመቃብር ያግዝ ሲነጥቅ የነበረው ሞት በክርስቶስ ሞት ግን ነብሳትን እንዲነጠቅ ሆነ ። ውስን ያልሆነ ሕይወት ክርስቶስ በፍጥረቱ ብቻ የተወሰነው ወደ ሆነው ሞት ሄደ ውስኑ ሞት ማይወሰነውን ህይወት ክርስቶስን ይይዘው ዘንድ አልቻለውም ። ትንሣኤና ሕይወት እርሱ ነውና ዮሐ 11፥25 ። በታተመች ድንግል ማኅፀን በጠባብ ደረት የተወሰነ ድንግልናዋን ሳያጠፍ የተወለደ በታተመ በተዘጋ መቃብርም ክፈቱልኝ ሳይል ወጣ ። ሞት በኃያሉ ኃይሉን አጣ ። ትንሣኤ ፦ *መነሣት* ማለት ሲሆን ፍሲካ ፦ *ማለፍ* (መሻገር) ማለት ነው ። እስራኤል ስለልጆቻቸው ፍንታ በግ ሰውተው የበጉን ደም በራቻው ላይ በመቀባት ሞት እንዳለፈላቸው የእኛም ሞት በክርስቶስ ሞት እንዲያልፍልን ሆኗል የበጉን ደም ያልቀቡት ግብፃውያን ግን የበኩር ልጆቻቸውን ሞት ወስዶ ነበር ። በክርስቶስ ሞት ግን ሁሉን አጥቷል ። *ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም* ሁሉን የመነጠኩን የማጣቱን ምሬት ሲገልፅ ‹‹ ሞት እንዲህ አለ ፦ ወደ ሙሴ ዘመን ብመለስ ሳይሻለኝ ይሆን ? ሙሴ እኮ በዓልን ደግሶልኝ ነበር ። በግብፅ ፍሲካ የታረደው በግ ከእያንዳንዱ ግብፃዊ ቤት የበኩር ልጅ ሰጥቶኝ ነበር በሙት ላይ ሙት በሲኦል ደጅ ተከምረውልኝ ነበር ይኅኛው የፍሲካ በግ (ክርስቶስ) ግን ሲኦልን በዘበዘው ሲኦልን ከእጄ ነጥቆ አወጣቸው›› ። እያለ ይገልፃል ። ትንሣኤው እኛ ክርሰቲያንኖች ከሞት በኋላ ህይወት እንዳለ ምናምንበት ነው ። ጥቂት የምድር መከራዎቻችንን ሁሉ በትንሣኤው ተስፍ እንታገሳቸዋለን ሮሜ 8፥18 ። የክርስቶስ ትንሣኤ በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኘን ለእኛም ትንሣኤ ማስረጃ ስለሆነ ።
‹‹ ሙታን የማይነሱ ከሆነ ክርስቶስ አልተነሳም ክርስቶስ ካልተነሳ እምነታቹ ከንቱ ናት ›› እንተደተባልን ። (1ኛ ቆሮ 15፥16) የሃይማኖት ፍፃሜው ትንሣኤ ነውና ። ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ ማስረጃ ምንድ ናቸው ከተባልም አስቀድሞ በብሉይ በትንቢት በብዙ የተነገሩ እንዲሁም እራሱ ክርስቶስ ስለራሱ ትንሳኤ የተናገራቸው ይሆናሉ ፦ “እግዚአብሔርም ዮናስን የሚውጥ ታላቅ ዓሣ አሰናዳ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ነበረ።” ዮናስ 2፥1
ዮናስ ሶስት መዓልት እና ሌሊት ህያው ሆኖ በአሳ ሆዱ ውሰጥ መቆየቱ ህያው የሆነ ክርስቶስም በመቃብር ሶስት ቀን የማደሩ ምሳሌ ነው ። ክርስቶስም ፈሪሳውያን ምልክት ሽተው ለጠየቁት ጥያቄ ሲመልስ “ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።” ዮናስ በአሳ አንባሪ ሆድ ውስጥ ሶስት ቀን እና ሌሊት እንደ ቆየ እንዲሁ የሰው ልጅም በምድር ልብ ውስጥ ይኖራል ብሎ ሰው የሆነ እርሱ በመቃብር ሚቆይበትም ተናግሮ ነበር ማቴዎስ 12፥39 ።

ክርስቶስ ለምንድ ነው በመቃብር ሶስት ቀን ብቻ የቆየው ለምንስ ከዛ በላይ ወይም በታች ሁለት አንድ ቀን ብቻ አድሮ ያልተነሳው ሚሉ ጠያቂዎች ይኖራሉ ። ለዚህ ምላሽ ፦ በእፀ መስቀል ላይ ከድካሙ የተነሳ ተጠማሁ ባለ ጊዜ
‹‹ ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፥ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ ›› ። መዝ 69-21 ያለው ቃል ይፈፀም ዘንድ በሰፍነግ ሆምጣጤ አጠጥተውት ነበር ። አይሁድ በአንድ ቀን ከመቃብር ቢነሳ ያጠጣነው አስክሮት አደንዝዞት ነው እንጂ በእውነት ሞቶ አይደለም ይሉ ስለ ነበረ ምክንያት ያሳጣቸው ዘንድ ቶሎ ከመቃብር አልተነሳም ። በሶስተኛውም ቀን በመቃብር ካደረ በኋላ የተነሳው በእርሱ መፍረስ መብስበስ እንደሌለ ያሳውቅ ዘንድ ነበር ‹‹ ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንመበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም ›› ። መዝ 16፥10 ዳዊትም ስለራሱ ሳይሆን ስለ ክርስቶስ ሳይፈር ከመቃብር መነሳት የተናገረው በክርስቶስ ትንሣኤ ተረጋገጠ ። በኋላም አስቀድሞ ተናግሮ የታወቀ የተነገረ በመሆኑ ተናግሮም ታውቆም ብቻ አልቀረ ውሸት ይባላልና በኋላም ሲናሳ በዚህ ታውቋል ። ዓለምን
ሁሉ በሚያድን፡ትንሣኤው፡እማፀናለሁ ። እኔንም ፡ከመውደቅ፡ያነሳኝ፡ዘንድ፡ከመቀጥቀጥ፡ልምሾም፡ከመሆን፡ያድነኝ ፡ዘንድ እፈቅዳለሁ። (አርጋኖን አባጊዮርጊስ ዘጋስጫ)** _ ሙታን እንደ ሚነሱ ተስፍ ለሰጠን መሲህ ምስጋ ይገባል እርሱ ሞትን አጥፍቶ ተነስቷል እና በሞት የበሰበሰው ዳግመኛ እንደሚታደስ ለሰው ልጅ ማረጋገጫ ሰጠ ። (ድርሳነ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ )

መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንላቹሁ 🙏

ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ሚያዝያ 7 2015 ዓ.ም
ኢትዮጵያ
@likawinte_betekiristiyan@likawinte_betekiristiyan
“ወዳጄ ሆይ! የትዕቢት መርዝ ተጠራቅሞ አብጦብሃልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ስለ ወዳጆቹ ሲል አርአያ ገብርን የነሣ ትሑቱ ጌታም ትሕትናን ያስተምርሃል፡፡ የስግብግብነት ትኩሳት አስቸግሮሃልን? ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ደግነትንም ትማራለህ፡፡ የምቀኝነት ብርድ አስቸግሮሃልን? እንኪያስ ወደ ሰማያዊው መዓድ ቅረብ፤ ምህረት ማድረግንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡ ትዕግሥትን የማጣት እከክ ይዞሃልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ራስን መግዛትንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወትህ ልል ዘሊል ብትሆን ይህን መንፈሳዊ መዓድ ተመገብና ብርቱ ትሆናለህ፡፡ ቆሽሸሃልን? እንኪያስ ወደዚሁ መብልና መጠጥ ቅረብ ብዬ እመክርሃለሁ፤ ንጽሕናንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡”

ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ
+ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር+

(ጥር 1 ቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕት የሆነበት ዕለት ነው)

የመጀመሪያው ሰማዕት ዲያቆን እስጢፋኖስን በግፍ ከቤተ ሳይዳ መግቢያ ከአንበሳ በር አውጥተው በድንጋይ ወግረው በግፍ እንዴት እንደገደሉት ዝርዝር ታሪኩ በሐዋርያት ሥራ ላይ ተጽፎአል:: የታሪኩ ማብቂያ ላይ ያለው ዐረፍተ ነገር እስጢፋኖስን በጭካኔ በድንጋይ ከቀጠቀጡት ሰዎች ጋር አብሮ ባይቀጠቅጠውም የሌላ አንድ ተሳታፊ ስም ተጠቅሶአል:: "ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር" (ሐዋ. 7:60)

በዚያች የምታሳዝን ዕለት ራሳቸው ከሳሽ ራሳቸው ፈራጅ የነበሩት ጸሐፍት በጭካኔ ታውረው ሆ ብለው በእስጢፋኖስ ላይ ተነሥተውበት ነበር:: በዚያ ባለ ብዙ ተስፋ ወጣት ላይ የድንጋይ ዶፍ ሲያወርዱ ትንሽ እንኳን አልዘገነናቸውም:: ይቅር በላቸው ከማለት ውጪ ክፉ ያልወጣውን ምስኪን ክርስቲያን ወጣት ያለ ርኅራኄ ቀጥቅጠው ገደሉት::

በዚያች ዕለት ሳውል ተሳትፎው ምን ነበር? እርግጥ ነው በእጁ ድንጋይ አልያዘም:: በእስጢፋኖስ ጭንቅላት ላይ ጉዳት ለማድረስ እጆቹን አላስወነጨፈም:: ነገር ግን አንድ እውነታ መካድ አይቻልም:: ሳውል በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ስለነበር በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ ከእስጢፋኖስ ሞት ጋር ስሙ አብሮ ተነሥቶአል::

የሰው ልጅ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት ፍጹም አዛኝ መልአክ መሆን እንደሚችል ሁሉ ሁኔታው ከተመቻቸለት ፍጹም አውሬ የመሆን እምቅ ችሎታ ያለው ፍጡር ነው:: ጭካኔም ሆነ ርኅራኄ ከየትኛውም ዘር ብትወለድ ሊኖርህ የሚችል ነገር ሲሆን በሕግ በሃይማኖትና በሰብአዊነት መርሆች ካልተገታ በስተቀር የሰው ልጅ የማያደርገው ክፉ ነገር እንደሌለ የዓለም ታሪክ ያስረዳል::

በዘመናችን የምናየው የንጹሐን ግድያ ላይ በቀጥታ የሚሳተፉና ብዙ እስጢፋኖሶችን በግፍ የሚገድሉ ጨካኞች አሉ:: በሕግ የሚጠየቁትም የሚቀጡትም እንደዚህ ያሉት ቀጥተኛ ተሳታፊዎች ናቸው::

ሆኖም በእኛ ሀገር በቁጥር እጅግ የሚበዙት እስጢፋኖስ ላይ ድንጋይ ከወረወሩት አይሁድ ይልቅ በእስጢፋኖስ መገደል የተስማሙት ሰዎች ናቸው:: ከሩቅ ሆኖ "ተነሣ በለው" ማለት ያም ባይሆን "እዚህ ሰፈር ሰው ተገደለ" ሲባል "እዚያ ሰፈርስ ሞቶ የለ ወይ?" እያሉ ለማካካስ መሞከር : ይበለው ይበላት ብሎ መናገርም በእስጢፋኖስ መገደል መስማማት ነው::

ወዳጄ በክፋት ውስጥ በቀጥታ መሳተፍም : ከሩቅ ሆኖ ቃላት መወራወርም : ጥላቻን መዝራትም : ሌላውን እየናቁ ራስን መኮፈስም ዞሮ ዞሮ በፈጣሪ ፊት ስለ ንጹሐን ደም ማስጠየቁ አይቀርም::

እስጢፋኖስን የመሰሉ በግፍ የተገደሉ ሁሉም ሰማዕታት በፈጣሪ ዙፋን ፊት ቆመው "እስከመቼ አትፈርድም?" ማለታቸው ስለማይቀር ሳናውቀው ዕዳ በራሳችን ላይ እንዳናከማች ከየትኛውም የጥላቻ ንትርክ ራሳችንን እናውጣ::

እስጢፋኖስ ሲገደል ሳውል የተስማማ ቢሆንም በመጨረሻ ግን "ይቅር በላቸው" በሚለው የእስጢፋኖስ ጸሎት ምክንያት በክርስቲያኖች መገደል ከመስማማት ወጥቶ በክርስትናው መከራ የተቀበለ ሐዋርያ ሆነ::
በጣም የሚደንቀው የእስጢፋኖስን ቤተሰቦችም ያጠመቀው በልጃቸው መገደል ተስማምቶ የነበረው ሳውል (ጳውሎስ) ነበረ:: የልጃችን ደም አለበት ሳይሉ ይቅር ብለው የተጠመቁት ጥፋትን በጥፋት ማረም እንደማይቻል ተረድተው ነበር:: ክርስትና ዘር ቆጥሮ የእኔን ወገን እንዲህ አድርገሃል ብሎ የመበቀል ሕይወት ሳይሆን
ባለፈ የጥላቻ ቁስል ማነከስን ትቶ በይቅርታ ዛሬና ነገን መኖር ነው:: ለትውልድ ቂም ማውረስ ለልጅ መርዝ ከማጠጣት አይተናነስም : ይቅርታን ማስተማር ግን ለልጅ በሰማይም በምድርም ርስት እንዲያገኝ ማድረግ ነው::

ኢትዮጵያ እግር አውጥታ ከእኛ እንዳትሸሽ እነዚህ ሦስት ነገሮች ከእንግዲህ በሀገራችን አይኑሩ

- በግፍ የሚገደል እስጢፋኖስ
- በግፍ የሚገድሉ ፈሪሳውያን
- በእስጢፋኖስ መገደል የሚስማሙ ሳውሎች

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሐምሌ 9 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
++++ ያልተተከሉ ዛፎች +++
                   ❖

አንድ ሩስያዊ የቴዎሎጂ መምህር የተናገሩትን አዝናኝ ወግ ሐበሻዊ ቀለም ሠጥቼ እንዲህ ልተርከው :-

ባልና ሚስት ከተጋቡ ጥቂት ዓመታት ቢያልፋቸውም ልጅ ግን አልወለዱም ነበር:: ወደ አንድ አባት ይሔዱና እባክዎን ልጅ እንዲሠጠን ይጸልዩልን ይሏቸዋል:: አባም ችግሩን ሰምተው የሚከተለውን ምክር ሠጡ

“እዚያ ተራራ ላይ ያለችው ገዳም ትታያችኁዋለች?" አሉአቸው
"አዎ አየናት" አሉ ባልና ሚስቱ
"ነገ በጠዋት እህል ሳትቀምሱ ሒዱና ገዳሙ ውስጥ የወይራ ዛፍ ተክላችሁ ልጅ ሥጠን ብላችሁ ስእለት ተሳሉ"

ባልና ሚስት በማግሥቱ ወደ ገዳሙ ሔደው የወይራ ዛፉን ተከሉ:: ይህ በሆነ በጥቂት ቀናት ልዩነት ውስጥ አባ ወደ ሌላ ሀገረ ስብከት ተመድበው ከዚያች ትንሽ የገጠር ከተማ ተሰናብተው ሔዱ::

ከሃያ ዓመታት ቆይታ በኁዋላ በአንድ አጋጣሚ አባ ወደዚያች ከተማ ተመልሰው መጡ:: ትንሹ ከተማ ትልቅ ሆኖ ብዙ ነገር ተለውጦ ጠበቃቸው:: የመጡበትን ጉዳይ ከፈጸሙ በኁዋላ የእነዚያ ባልና ሚስት ነገር ትዝ አላቸው:: በከተማው መቀየር ትንሽ ቢቸገሩም ቤቱን ፈልገው አገኙትና በር አንኳኩ::

አንድ የሚያምር ሕፃን የታቀፈች ሴት በሩን ከፈተች:: መካኒቱ ሴት ነበረች:: ከታቀፈችው ልጅ ሌላ እግርዋን ተጠምጥመው የያዙ ሁለት ሕጻናት አባን ሽቅብ እያዩ ይቁለጨለጫሉ:: መስቀል አሳልመው ወደ ውስጥ ሲዘልቁ ሶፋ ላይ ቁጭ ብለው ቴሌቪዥን የሚመለከቱ አራት ሕጻናት ተደርድረዋል::

ታላቆቻቸው የሚሆኑ ሁለት ልጆች ደግሞ ጠረጴዛው ላይ ቁጭ ብለው ያጠናሉ:: ይህ እንግዲህ ቡና የምታፈላውን ሴት ልጅና በሕፃን ልጅ አልጋ ላይ የተኛውን አራስ ልጅ ሳይጨምር ነው::

አባ በደስታም በመደነቅም ፈዝዘው ቀሩ::
"እንኩዋን ለዚህ አበቃችሁ ልጄ" አሏት በደስታ
"በእርስዎ ጸሎት ነው አባታችን" አለች እናት
"ለመሆኑ ባለቤትሽ የት ነው?" አሉ በጉጉት
እናት አንገትዋን ደፋች አባ ደነገጡ
"ምነው ሰላም አይደለም?" አሉ በስጋት
"ኸረ ሰላም ነው ... በጠዋት ወደዛች ተራራ ላይ ወዳለችው ገዳም ሔዶአል" አለች እያፈረች
"ምነው? ለምን ጉዳይ ሔደ?"
"ያኔ የተከልነውን የወይራ ዛፍ ሊቆርጥ"

✍🏽   ✍🏽    ✍🏽.     ✍🏽✍🏽  ✍🏽   ✍🏽

ሊቁ ተርቱሊያን "የሰማዕታት ደም የክርስቲያኖች ዘር ነው" ብሎ ነበር:: "ክርስቲያን መግደል ክርስቲያን እንዲበቅል መዝራት ነው" እንደማለት ነው:: ከዚያ ውጪ ደግሞ ሌላው የክርስቲያን ዘር መውለድ ነው:: ብዙ ምእመናን የመውለድን ጸጋ ተጎናጽፈው ከመውለድ ይሸሻሉ::

ድሆች ሆነው እንኩዋን በፈጣሪ መግቦት አምነው የሚወልዱ እንዳሉ ሁሉ የኢኮኖሚ አቅም እያላቸው የተማሩ በመሆናቸው መውለድን እንደ ኁዋላ ቀርነት ቆጥረው ከመውለድ ወደ ኁዋላ የሚሉም ብዙዎች ናቸው::

ከላይ እንዳየነው ሰው ያህል እንኩዋን ሳይወልዱ ዛፍ ቆረጣ የሚሮጡ ብዙዎች ናቸው:: የሚወልደውን ኸረ በቃህ በቃሽ እያሉ የሚተቹ "ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉ ሲባል ብቻህን ልትሞላ ነው እንዴ?" ብለው በወለዱ የሚዘብቱ አሉ::

መውለድ ጸጋ በረከት ነው:: የልጅን ጣዕምና ጸጋ የወለዱ ሁሉ ያውቃሉ:: ልጅ መውለድ የወላጆችን መንፈሳዊ ሕይወት ሳይቀር ከፍ ያደርጋል:: ልጅ ፊት አይወራም ሲባል ከሚተው ክፉ ወሬ ጀምሮ አርኣያ ለመሆን ሲባል ከሚደረግ ጥረት ድረስ ልጅ መውለድ ትልቅ በረከት ነው::

ለቤተ ክርስቲያን ደግሞ የልጆች መብዛት በረከት ነው:: አንድ አባትም "በሕፃናት የለቅሶ ጩኸት የማትረበሽ ቤተ ክርስቲያን የነገ ተስፋ የሌላት ቤተ ክርስቲያን ናት" ብለዋል:: ሕፃናት የሚበዙባት ቤተ ክርስቲያን ግን ነገ እንደምትኖር ያረጋገጠች ቤተ ክርስቲያን ናት።

       ክርስቲያኖች ሆይ ውለዱ!

       (በመምህር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
https://t.me/likawinte_betekiristiyan
ኦርቶዶክስ ኖት ?

📚 የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ
ይፈልጋሉ? የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት
መፅሐፉን ያግኙ። መልካም ንባብ 📖


🔰 መጽሐፍ ቅዱስ
🔰 ድርሳናት 
🔰 ገድላት  
🔰 ተዓምራት
🔰 መልከዐት
🔰 ውዳሴ ማርያም
🔰 መዝሙረ ዳዊት
🔰 ህማማት
🔰 መፅሀፈ ቅዳሴ                     
🔰 የሰዶም መጨረሻ                      
🔰 ባህረ ሀሳብ         
🔰 የሳጥናኤል ጎል               
🔰 አንድሮሜዳ
🔰 እመጓ ዝጎራ
🔰 መርበብት ሰበዝ
🔰 መጽሐፈ ሄኖክ 
🔰 ውዳሴ ማርያም
🔰 የወጣቶች ህይወት
🔰 ኦርቶዶክስ መልስ አላት
🔰 የዋልድባ ገዳም ታሪክ
🔰 መጽሐፈ አክሲማሮስ
🔰 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት   
🔰 ሐይማኖተ አበው
🔰 ራዕየ ማርያም 
🔰 ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ
🔰 ፍካሬ ኢየሱስ
🔰 መርበብተ ሰሎሞን
🔰 የቶ መስቀል ትርጉም
🔰 ባሕረ ሐሳብ 
🔰 ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ቅድስት ኢየሉጣ እናታችን በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩና በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳት አንዷ ናት:: በወቅቱ ቅዱስ ቂርቆስ የሚባል ደግ ልጅ ወልዳ ባሏ ባለመኖሩ በመበለትነት ትኖር ነበር:: የዚያ ዘመን ክርስቲያኖች ለክርስቶስ የነበራቸው ፍቅር ከመነገር በላይ ነው:: በዛው ልክ ደግሞ መከራው በጸጉራቸው ቁጥር ልክ ነበር::

ከሮም ግዛት በአንዱ ከቅዱስ ልጇ ጋር የምትኖረው ቅድስት ኢየሉጣ የስደቱ ዘመን ሲመጣ እርሷም እንደ ሌሎቹ ክርስቲያኖች ተሰደደች:: እስክንድሮስ የተባለው ከሃዲ ንጉሥ ግን ያለችበት ድረስ ተከትሎ እንድትያዝና እንድትቀርብ አደረገ::

ወዲያውም "ስምሽ ማን ይባላል?" ቢላት "ክርስቲያን እባላለሁ" አለችው:: ንጉሡ ተቆጣ:: "መዋቲ ስሜን ከፈለክ ኢየሉጣ ይባላል" አለችው:: ንጉሡ መልሶ "አሁን ለጣዖት ካልሠዋሽ ሲጀመር ስቃይ: ቀጥሎም ሞት ይጠብቅሻል" ቢላት ቅድስቲቱ መልሳ "በከተማ ውስጥ የሦስት ዓመት ሕፃን አለና እርሱን አምጣው:: ማንን ማምለክ እንዳለብን ይነግረናል" አለችው::

አስፈልጐ ቅዱስ ቂርቆስን አስመጣው:: "ስምህ ማን ይባላል?" አለ ንጉሡ:: "ከማይደፈርስ ከንጹሕ ምንጭ የተቀዳ ጥሩ ምንጭ ስሜ ክርስቲያን ይባላል:: መዋቲ ስሜን ከፈለግህ ግን ቂርቆስ ይባላል" አለው::

ንጉሡ ሊያታልለው "ደስ የተሰኘህ ሕፃን" ቢለው ቅዱሱ ሕፃን "ትክክል ተናገርክ: ለእኔ በሰማያት ደስታ ይጠብቀኛል:: አንተ ግን እውነተኛው አምላክ ይፈርድብሃል" አለው:: በሦስት ዓመት ሕፃን አንደበት ዘለፋ የገጠመው ከሃዲ ተቆጣ::
እናትና ልጅን በብዙ መክፈልተ ኩነኔ አሰቃያቸው::

ሰውነታቸውን ቸነከረ: አካላቸውን ቆራረጠ: ዓይናቸውን አወጣ:: ሌላም ሊናገሩት የሚጨንቅ ስቃይን አሰቃያቸው:: በዚህች ቀን ግን ትልቅ ድስት አሰርቶ ባሩድ: አረር: ስብና የመሳሰሉትን ጨምረውበት በእሳት አፈሉት::

የእሳቱ ወላፈን አካባቢውን በላው:: በድስቱ ውስጥ ያለው ነገር እየፈላ ሲገላበጥ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ይጮህ ነበር:: የስድስት ሰዓት የእግር መንገድ ድረስም ተሰምቷል:: ቅድስት ኢየሉጣ ይሔኔ ነበር ልቧ ድንግጥ ያለው:: ሕፃኑ ቂርቆስ የእናቱን ፍርሃት ሲመለከት ጸለየ::

"ፈጣሪዬ! ፍሬው ያለ ግንዱ አይቆምምና እኔን እንዳጸናሕ እናቴንም አጽናት" ሲል ለመነ:: "እግዚኦ ትፈቅድኑ ለፍሬሁ ተአልዶ: እንዘ በእሳት ታውኢ ጉንዶ" እንዲል:: በዚያች ሰዓት ቅድስት ኢየሉጣ ዓይኖቿ ተከፍተው ሰማያዊ ክብርን ተመለከቱና ልቧ ወደ ድፍረቱ ተመለሰ::

ልጇንም "አንተ አባቴ ነህ: አንተን የተሸከመች ማኅጸኔ የተባረከች ናት" አለችው:: ከዚያም ሁለቱንም ወደ ፈላው ድስት ውስጥ ቢጨምሯቸው ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደላቸው:: በበትረ መስቀሉ ባርኮ የፈላውን አቀዘቀዘው:: የነደደውን ውኃ አደረገው:: ቅዱሳኑ ቂርቆስና ኢየሉጣ ከብዙ መከራ በኋላ በሰማዕትነት አልፈዋል::hዘ

መዝሙር ዘሰንበት
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
በ ፮
ይወድስዋ ኵሎሙ ወይብልዋ እኅትነ ነያ፤ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ በሰማያት ኵሎሙ መላእክት ይኬልልዋ፤ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ ወበምድር ኵሎሙ ቅዱሳን ይቄድስዋ፤ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤እስመ ወለደት ወልደ ዘበኵራ ያፈቀርዋ፤ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ እንዘ ንጽሕት ይዕቲ በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ ማርያምሰ ኃርየት መክፈልተ ሠናይ ዘኢየኃይድዋ፤ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ


አመላለስ፦
ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ/፪/
ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ
+‹‹ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ ››+

ቤት ሲቃጠል ሚወድ ይኖር ይሆን  የብዙ ቀን ልፍትን በቅስፈት ሲያወድም  ላየ አያድርስ ማለቱ እንዴት ይቀራል ስለሌላ ሰው ከልባችን በቁጣ ጭረን ያስቀመጥ ነው የክፍት እሳት የመቀጣጠል ጊዜው በረዘመ መጠን  በብዙ እያሳጣን አያድርስ ሚል ሲታጣ ይበልጥ ክፍት ልቆ ይገኛል ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን መልእክቱ "በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት"። (ኤፌ 4፥27) ይለናል ከወዳጃችን የደረሰብንን ጉዳት ከእኛጋ ከማደሩ በፈት ቆርጠን እንጥለው ዘንድ ። ቀንስ ከወዳጅ ስለደረሰብን ክፍ ቃል በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ተወው ወንድምህ አይደል ስለምትቀራረቡ ነው እንጂ ክፍት አስቦ አይደለም በማለት በተወረወረበት ቃል  ከተጎዳነው ከተጠቃው ባይነት  ክፍ ሐሳብ የሚያስወጡን እና የሚያሰረሱን ብዙዎች ሊኖሩ ይችላሉ ። ሌት ግን ይዞት ሚያድር ከሆነ ብቻውን የቀኑን የእሳት ጭረት እያወጣ እያወረደ ይበልጥ ያነደዋል እና ፀሐይ አይግባብን ብሎ እንድንፈጥን  ይነግረናል ። ይህን ካለማድረግ ዛሬ በወዳጅነት ስንኖር የነበርን  እንደ ሃገር በአጭር ጊዜ ብዙ እኛነታችንን ሚንዱ  ሚያጠፍ አብረን በምናሳድረው ቁጣና ክፍት ወንድሞቻችንን ወዳጆቻችንን እያጠፍን ነው ።

ጠቡቡ በመክብቡ "ቁጣውን የሚያዘገይ ሰው መጥፊያው ይሆንበታል ይለናል "። (መክ 1 ፡ 22)

ጌታችን በስጋዌው ወቅት በሚያስተምርበት ጊዜ “እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ብታቀርብ ጊዜ ፥ በዚያም ሳለህ የተጣላህ  ወንድምህ እንዳለ ብታስብ ፥ መባህን ከዚያ በመሰዊያው ፈት ትተህ ሂድና  አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ ። (ማቴ 5፥24)  ብሎ ያስተምረናል ስለ ወንድማችን ያለን ፍቅር መስዋዕት ከማቅረብ በላይ በመሆኑ ጌታችን ስለእርሱ ያለንን ክፍት እንድናስወግድ ያስተምረናል ። ከበደል ነው ወንድማችን ጋር ሊያስታርቁ ለሚመጡ ሰዎች ጥፍቱ የእኛ ስለሆነ እንዲህ ብዬ አስቀይሜው እሺ ብሎ ይታረቀኝ ይቻላልን አይ ሌላ ነገር ቢያስብብኝ ነው እንጂማ አያደርገውም የምንል ብዞዎች ነን ። ምክንያቱም ለተበደለው በዳዩን  ይቅር ማለቱ   ከባድ ነው ብለን ስለምናምን ። ጌታችን ግን ይህን ከባድ ብለን ምናምነውን ተበዳዩቹን እኛን ሂዱና  የበደሏቹሁን  ይቅርታ  እንድናደርግ ያዘናል “እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን ”። ማቴ 6፥12 ብለን በፀሎት እንለምነው ዘንድ ያስተምረናል  ምክንያቱም  በፍቅር ስለሌችም አቡነ ዘበሰማያት ብለን ስርየተ ሐጥያትን ሰለወዳጃችንም በመለመን እንጀምራለንና ። እርሱን በድለነው ሳለን የበደልነውን እኛን ከዘመናት ሐጥያታችን ያነፃን ዘንድ በይቅርታው ወደሱ የመለሰን ነውና ።

"በዜና አበው " ላይ ጓደኛን ይቅር ሳይሉ ይቅር በለኝ ብሎ መጠየቅ እንደማይገባ የተቀመጠውን ትምህርት ጠቅሼ ልጨርስ "አንድ ባሕታዊ መነኩሴ ነበርና ጥቅም ያለውን ነገርን(ትምህርትን) የሚተይቀው መነኩሴ በመጣ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ በኋለኛይቱ ቀን እንደሚጠይቅህ እኔም እጠይቅሀለው ። ምን ላደርግልህ ትወዳለህ ይቅር በለኝ የምትል ከሆነ አንተ አስቀድመህ ጓደኛህን ይቅር በል እኔም ይቅር እልሀለው ይለዋል ። ማቴ 5-24)

ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ታኅሳስ 26 2015 ዓ.ም
ዲላ ኢትዮጵያ
የወር አበባ  ጊዜ ሴት ልጅ በቤተ ክርስቲያን እይታ።


👉 ሴት ልጅ በወር አበባ ጊዜ መፀለይ ትችላለች ?


በወር አበባ ጊዜ መስቀል
መሳለም፣ መጽሐፍ ቅዱስ እና ሌሎች ጸሎት መጽሀፍትን ማንበብ ይቻላል?
እንዲሁም ወደ ቤተክርስትያን መሄድ ይቻላል ?
የወር አበባ በሴቶች ላይ በየወሩ የሚታይ የደም መፍሰስ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን
አስተምህሮ “ደመ ጽጌ፣ አበባ ደም” በመባል ይጠራል፡፡አሰያየሙም የወንድ ዘር
ካላገኘ ከማህጸን ግድግዳ ፍራሽ ጋር በደም መልክ ስለሚፈስና የኋለኛው
ማንነቱ ደምነት ስለሆነ ነው፡፡ ይህም ማለት አገልግሎቱን የጨረሰ፣ ያረጀ፣ ቆሻሻ
ማለት ነው፡፡ ይህ በየወሩ ዑደትን ተከትሎ የሚሄደው የዘር ፍሳሽ በስነ ህይወት
ትምህርት ኦቫሪ (ከዘር ከረጢት) የሚለቀቅ የወንድ ዘር ካላገኘ ኦቫ (ሴቴ ዘር)
ጋር እየተቀላቀለ የሚወርድ ነው፡፡
የወር አበባ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በሁለት ከፍለን ነው መመልከት
ያለብን፤ በዘመነ ኦሪትና ዘመነ አዲስ ኪዳን በማለት፡፡
በርግጥ በዘመነ ኦሪት የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት ነበር፡፡ ለዚህም
ማስረጃነት በመጽሃፍ ቅዱስ ዘሌ 18÷19፣ 20÷18 ያሉ ጥቅሶች “በመርገምዋ
ርኩሰት ሳለች” እና “ባለ መርገም ሴት” በማለት ሲገልጸው፤ ባንጻሩ ደግሞ
ከወር አበባዋ ነጻ የሆነችውን ሴት “ከርኩሰትዋ ነጽታ” በማለት የወር አበባ
የርኩሰትና የመርገም ምልክት መሆኑን ይጠቁማል፡፡
በዘመነ አዲስ ደግሞ የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት መሆኑ ቀርቷል፡፡
ርኩሰት አይደለም፤ ርኩስም አያሰኝም፡፡ በብሉይ ኪዳን አዳምና ሄዋን በገነት
በነበሩ ጊዜ ዕጸ በለስን በልተው እግዚአብሔርን በደሉ፤ እግዚአብሔርም ሄዋንን
ደመ ዕጸ በለስን አፍስሰሻልና “ወበከመ አድመውኪያ ለእንትኩ ዕጽ ከማሁ
ድምዊ ለለወርኁ፡፡” በማለት ደሟ በየወሩ እንዲፈስ ፈጣሪ ፈረደባት፡፡ ስለዚህ
የሄዋን ደም መፍሰስ መነሻው መርገም ነው፡፡ በአዲስ ኪዳን ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሥቶስ በፈጸመው ቤዛነት መርገምነቱና ርኩስነቱ
ተወግዷል፡፡
የወር አበባ በዚህ ዘመን ርኩሰት ወይም መርገም ባይሆንም እድፍ (ቆሻሻ) ነው፡፡
እድፍና ርኩሰት ልዩነት አላቸው፡፡
ርኩሰት ውስጣዊ ነው፤ በንስሃ እንጂ በውሃ አይጠራም፡፡ እድፍ ደግሞ ግዘፍ
አካል ያለው፣ የሚታይና ውሃ የሚያነጻው ነው፡፡ የወር አበባ በሴቶች ባህሪ ሳለ
እንደ ቆሻሻ አይቆጠርም፣ ከሰውነት ሲወገድ ግን ይቆጠራል፡፡ ይህንን
ለማስረዳት ምሳሌ መሆን ከሚችሉት ውስጥ ዛህል (ንፍጥ)፣ ሽንት፣ ምራቅ፣
ዓይነምድርና ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል፡፡
ወር አበባ ርኩሰት ባለመሆኑ መስቀል ከመሳም፣ ከመጸለይ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን
ከማንበብና ከመድገም አያግድም፡፡ ነገር ግን ከሩካቤ፣ ከመጠመቅ፣
ከመቁረብና ቤተ መቅደስ ከመግባት ይከለክላል፡፡
ከሩካቤ:-
ሩካቤ በወር አበባ ጊዜ ከሚከለከሉ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ በወር አበባ ጊዜ
የሚደረግ ግንኙነት የህክምና ባለሙያዎች ሳይቀር ለአባላዘር፣ ለልዩ ልዩ
በሽታዎችና ለኢንፌክሽን ሊያጋልጥ እንደሚችል በመናገር እንዳይፈጸም
ይመክራሉ፡፡ በመንፈሳዊው አስተምህሮ ስንመለከተው ደግሞ የሰው ልጅ ዘር
ቅዱስ በሆነው በእግዚአብሔር አምሳል በመፈጠሩ፣ ይህንን የተከበረ ዘር፣ እዳሪ
ወይም ቆሻሻ ከሆነ ደም ጋር ማዋሃድ ኃጢያት እንደሆነ ይቆጠራል፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ሴት ልጅ በወር አበባዋ ጊዜ እንዳለች የሚፈጸምን ሩካቤ
“እርሷም በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች ኃፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ ወደ እርሷ
አትቅረብ” ዘሌ 18÷19፣ ዘሌ 20÷18።
በዚህም ምክንያት በወር አበባ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ በኦሪትም ይሁን በአዲስ
ኪዳን ክልክል ነው፡፡
ከመጠመቅ:-
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ “ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ
አሁን ያድነናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፡፡ ለእግዚአብሔር በጎ
ህሊና ልመና ነው እንጂ” 1ኛ ጴጥ 3÷21 በማለት ተናግሯል፡፡ ስለዚህ ጥምቀት
ስጋዊ እድፍን ማስወገጃ ስላልሆነ፣ ከመጠመቅ በፊት ተጣጥበው እንጂ ከእድፍ
ጋር ለመጠመቅ መቅረብ ተገቢ አይደለም፡፡ የወር አበባም ከላይ
እንደተመለከተው ከሰውነት ሲወጣ እድፍ (ቆሻሻ) በመሆኑ፣ ከዚህ የቤተ
ክርስቲያን ስርዓት ውጪ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
ቤተመቅደስ መግባት፡-
ሴት በወር አበባዋ ጊዜ የምትከለከለው ነገር ቤተመቅደስ መግባትን ነው፡፡ይህም
የሆነው በርኩሰት ምክንያት ወይም በኦሪት ሕግ ምክንያት ሳይሆን በቤተመቅደስ
መፍሰስ ያለበት ደም አማናዊ የሆነው የክርስቶስ ደም ብቻ በመሆኑ ነው!ይህ
ስርዓት ለሴቶች ብቻ ሳይሆን ለወንዶችም ነው፡፡ አንድ ወንድ እየነሰረው ወይም
የሆነ ነገር አካሉን ቆርጦት ደም እየፈሰሰው ከሆነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት
የለበትም!ምክንያቱም በቤተ መቅደስ ከ ክርስቶስ ደም ውጪ ሌላ ነገር መፍሰስ
ስለሌለበት ነው፡፡
**በወር አበባ ላይ ሳለች ሴት ወደ ቤተመቅደስ አትግባ ማለት ቤተ ክርስቲያን
አትሂድ ማለት ሳይሆን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዳ የመጀመሪያውን ቅጽር (አጥር)
ከገባች በኋላ በመጠለያ ውስጥ በመሆን ትጸልይ፣ ትማር ወይም ማንኛውንም
አይነት መንፈሳዊ ስራዎችን ሰርታ ትመለስ ማለት ነው፡፡
ከመቁረብ፡-
ሴቶች ከወር አበባ ሳይነጹ ሥጋ ወደሙ መቀበል አይችሉም፡፡ ይህንን ስርዓት
ተላልፈው ወደ ሥጋ ወደሙ እንዲቀርቡ ያደረገ ዲያቆንም ይሁን ቄስ ከክህነቱ
እንዲሻር ፍትሕ ነገስት ይደነግጋል፡፡ “ከግዳጅዋ ያልነጻችውን ሴት በደሟ ወራት
ከቤተ ክርስቲያን አግብቶ ሥጋውን ደሙን ያቀበለ ከክህነቱ ይሻር፡፡” ፍትነገ 6፣
ዘሌ 7፡19
ይህ ሥርዓት በሴቶች ላይ ብቻ ሳይሆን ወንዶችም ህልመ ለሊት
በሚያጋጥማቸው ሰዓት እንዳይገቡ ይከለከላል፡፡
ቤተ ክርስቲያን የገነት ምሳሌ ናት፡፡ ሔዋን ከአዳም ጋር በገነት ለሰባት ዓመታት
ስትኖር የወር አበባ አታይም ነበር፡፡ ቤተ መቅደስ የገነት ምሳሌ መሆኗ የተሟላ
እንዲሆን የወር አበባ የምታይ ሴት ወደ ቤተ መቅደስ አትገባም፡፡


አንቺ ከተረዳሽ ለማያቁ እህቶችሽ ሼር አርጊ ። ወንድሜ ለእህቶችህ ሼር አርግ ።


አዘጋጅ ዲያቆን ፍቅረ አብ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ሥርዓተ ማኅሌት ዘዓውደ ዓመት
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
ስርዓተ ነግሥ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለገበዋቲክሙ እለ ዕሩቃን እምልብሰ ወርቅ፤ ሥሉስ ቅዱስ ሥርግዋነ መፍርህ መብረቅ፤ መንገለ(ኀበ) ፍኖቱ ምጽዋት ለቆርነሌዎስ ጻድቅ፤ ይምርሐኒ ወንጌልክሙ እግዚአ ፍኖት ረቂቅ፤ ዘጸያሔሁ ዮሐንስ መጥምቅ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ፤ እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ።
@EOTCmahlet
ዓዲ
ወንጌል ቅዱስ ዘሰበከ ዮሐንስ፤ ቃለ ወልደ እግዚአብሔር።
@EOTCmahlet
ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም መሠረተ ጽድቅ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ወአዘዘ ደመና በላዕሉ።
@EOTCmahlet
ነግሥ
ምስለ ራጉኤል ስዑል በነበልባል ወዮሐንስ ድንግል፤ ወበርተሎሜዎስ ሐዋርያ ሰባኬ ወንጌል፤ ወኢዮብ ዓዲ ተወካፌ ቊስል፤ ዓውደ ዓመት ለባርኮ እምጽርሐ አርያም ጌልጌል፤ ማርያም ንዒ ለምሕረት ወሣህል።
@EOTCmahlet
ወረብ
ዓውደ ዓመት ለባርኮ ባርኮ ዓውደ ዓመት/፪/
ንዒ ማርያም ለምሕረት ወሣህል/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ዮሐንስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ።
@EOTCmahlet
ዓዲ
በምድረ ጽዮን ኢይኩን ሐከክ፤ ወበገራኅታ ኢይብቊል ሦክ፤ ጸሊ ኀበ አምላክ ራጉኤል መልአከ፤ ዓውደ ዓመት ከመ ይትባረክ።
@EOTCmahlet
መልክዐ ዮሐንስ
በስመ እግዚአብሔር እሳት በሐቅለ ኅሊና ነዳዲ፤ ወበስመ ማርያም ድንግል መጥበቢተ ዓለም አባዲ፤ ማኅቶተ ጸዳል ዮሐንስ ጽልመተ አበሳ ሰዳዲ፤ ከመ እዜኑ ኂሩተከ እደ ኃጣውእየ ይፍዲ፤ በአየረ ሰማይ ይጸርሕ ቃልከ ዓዋዲ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
እገኒ ለከ እግዚኦ በኲሉ ልብየ፤ ወእዜኑ ኂሩተ ዚአከ፤ እትፌሣሕ ወእትሐሠይ በአድኅኖትከ።
@EOTCmahlet
ወረብ
እገኒ ለከ እግዚኦ በኲሉ ልብየ/፪/
እትፌሣሕ ወእትሐሠይ በአድኅኖትከ/፪/
@EOTCmahlet
ዓዲ
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ማኅቶተ ጥበብ ውስተ አልባቢነ አኅቱ፤ ኀበ አዘዝከነ ኑፈር ወንዕቱ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክዐ ዮሐንስ
ሰላም ለሥዕረተ ርእስከ እንተ ደለዎ እኳቴ፤ ወለርእስከ ሰላም ዘተመትረ ከመ ናቡቴ፤ ርእሰ ዓውደ ዓመት ዮሐንስ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ፤ መብልዕ ዜና ፍቅርከ ወነገረ ጽድቅከ ስቴ፤ ያስተፌሥሕ መላእክተ ወሰብአ መዋቴ።
@EOTCmahlet
ወረብ
"ርእሰ ዓውደ ዓመት ዮሐንስ"/፪/ ወላዴ መጥቅዕ/፪/
ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ ወላዴ መጥቅዕ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ውስተ ርእሰ ዓውደ ዓመት ተጽሕፈ ተዝካርከ፤ ባርከኒ እንሣእ በረከተከ።
@EOTCmahlet
መልክዐ ዮሐንስ
ሰላም ለአዕይንቲከ እለ ሠኑየ ይትኌለቁ፤ ወለአእዛኒከ ሰላም እለ ይትላጸቁ፤ ዮሐንስ ከማከ ሶበ ፈተዉ ወጽሕቁ፤ እሳተ ነዳዴ ኢተክህሎሙ ያጥምቁ፤ ራጉኤል በትጋሁ ወኢዮብ በጽድቁ።
@EOTCmahlet
ወረብ
"እሳተ ነዳዴ" ኢተክህሎሙ ያጥምቁ/፪/
ዮሐንስ ከማከ ሶበ ፈተዉ ወጽሕቁ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ሰላማዊ ብእሲሁ፤ ቅዱሳት እደዊሁ  እለ አጥመቃሁ፤ ለመድኃኔዓለም።
@EOTCmahlet
መልክዐ ዮሐንስ
ሰላም ለአማዑቲከ እግዚአብሔር ዘገብሮ፤ ወለንዋየ ውስጥከ ሰላም መንጦላዕተ ሥጋከ እንተ ሰወሮ፤ ዮሐንስ ልብው መዝገበ ጥበብ ወአእምሮ፤ እፎ ኢያጽራከ ለሀቅለ ገዳማት ፃዕሮ፤ ፍጹመ መኒነከ አብያተ ዘውቅሮ።
@EOTCmahlet
ወረብ
"አብያተ ዘውቅሮ"/፪/ መኒነከ/፪/
ፍጹመ መኒነከ ዮሐንስ ልብው/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
አብያተ ዘውቅሮ መኒነከ፤ በተዘከሮ ማኅደር ዘበሰማያት፤ ፀጒረ ገመል ረሰይከ ዓራዘከ።
@EOTCmahlet
መልክዐ ዮሐንስ
አምኃ ስብሐት አቅረብኩ ለመልክዕከ በጽዋዔ፤ እንዘ አስተዋድድ ቃለ መጠነ ራብዕ ሱባኤ፤ ተወክፈኒ ዮሐንስ ምስለ በርተሎሜዎስ ቀርነ ጉባኤ፤ ከመ ተወክፈ እግዚእከ ቅድመ ወንጌላዊት ትንሣኤ፤ እምደ አሐቲ ብእሲት ጸራይቀ ክልዔ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ዮሐንስ እዴከ መጥወኒ፤ ወበርተሎሜዎስ አቡየ ለባርኮ ቅረበኒ።
@EOTCmahlet
ወረብ
ዮሐንስ እዴከ መጥወኒ/፪/
ወበርተሎሜዎስ አቡየ ለባርኮ ቅረበኒ/፪/
@EOTCmahlet
አንገርጋሪ
ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ፤ ዓርኩ ለመርዓዊ ትሰመይ፤ ወአዝማዱ በሥጋ ትሰመይ፤ ተፈኖከ ታርኁ አናቅጸ ጽድቅ።
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
ተፈኖከ ታርኁ/፪/
ታርኁ አናቅጸ ጽድቅ/፬/
@EOTCmahlet
ወረብ
ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ ነቢየ ልዑል/፪/
ዓርኩ ለመርዓዊ ትሰመይ ነቢየ ልዑል/፪/
@EOTCmahlet
እስመ ለዓለም፦
በመንፈስ የሐውር ወበኃይለ ኤልያስ፤ አልቦ፤ዘየዓብዮ ለዮሐንስ
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
አልቦ ዘየዓብዮ/፪/
አልቦ ዘየዓብዮ ለዮሐንስ/፬/

እስመ ለዓለም ዘመጥምቁ ዮሐንስ:-
ነአምን ክርስቶስሃ መድኅነ፤ዘዮሐንስ አጥመቆ በዮርዳኖስ ተጠምቀ፤ነአምን ክርስቶስሃ መድኅነ፤ይቤሎ ኢየሱስ ለዮሐንስ፤አጥምቀኒ በማይ ከመ ይትቀደስ ማይ፤ወይኩን መድኃኒተ ለውሉደ ሰብእ፤ነአምን ክርስቶስሃ መድኅነ፤አበዮ ዮሐንስ ወይቤሎ፤ባዕደ ሶበ አጠምቅ በስምከ አጠምቅ፤ወኪያከ ሶበ አጠምቅ እግዚኦ ምንተ እብል፤ነአምን ክርስቶስሃ መድኅነ፤ወልዱ ለቡሩክ ከሣቴ ብርሃን፤ወልደ እግዚአብሔር ተሠሃለኒ በል፤ነአምን ክርስቶስሃ መድኅነ፤አጥመቆ ዮሐንስ ለኢየሱስ፤በፈለገ ዮርዳኖስ።
🇪🇹🌼🌼🌼🌼🌼🌼🇪🇹
🌼 🌼                
🌼 🌼
🌼🌼
🇪🇹🌼🌼🌼🌼🌼🌼🇪🇹

መልካም አዲስ ዓመት
 
መልካም በዓል❤️🙂
🔔  ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች  🔔

🤔 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ
የብዙ ዘማሪያንን መዝሙሮችን አዘጋጅተናል
በመቀላቀል የፈለጉትን መርጠው ያድምጡ‼️

🔔➯ የይልማ ኃይሉ መዝሙር
🔔➯ የቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙር
🔔➯ የዳግማዊ ደርቤ መዝሙር
🔔➯ የቀዳሜጸጋ መዝሙር
🔔➯ የኪነጥበብ መዝሙር
🔔➯ የቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
🔔➯ የቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
🔔➯ የዘማሪ አቤል መክብብ መዝሙር
🔔➯ የዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
🔔➯ የዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
🔔➯ የዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
🔔➯ የዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
🔔➯ የዘማሪት ለምለም ከበደ መዝሙር
🔔➯ የዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
🔔➯ የዘማሪት አቦነሽ አድነው
🔔➯ የዘማሪት ትንቢት ቦጋለ
🔔➯ የዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ


በቻናላችን ላይ የእነዚህን ድንቅ ዝማሬ እና ሌላ
ብዙ መዝሙሮችን ያገኙበታል ይ🀄️🀄️ሉን።
➲ @Orthodox_mezemur

መዝሙሮቹን ለማግኘት ከስር
OPEN የሚለውን ይጫኑት። 👇

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
█  🔰 ✞  𝑶𝑷𝑬𝑵  ❖  𝑶𝑷𝑬𝑵  ✞ 🔰  █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬