እንተዋወስ(entewawes)
179 subscribers
53 photos
22 videos
12 files
140 links
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
Download Telegram
ያስለቀሰኝ ታሪክ
.
.
.. ከሼይኮች አንዱ ባለቤቱ ሞተችበት አላህም ለሚስቱ ምህረትን ያብዛላትና ሸይኹ በጣም አዘነ.. ሀዘኑም በእሷ ላይ የበረታ ሆነ, እናም አንድ የባለቤቱ ጓደኛ ትዕግስት (ሰብር) እንዲሰጠው ብላ መልእክት ላከችለት እና ደብዳቤዋ እንዲህ ይላል... "ሰላም ለእናንተ ይሁን ሼክ እኔ ከሚስትህ ጓደኞች አንዷ ነኝ ስለ ውድ ሚስትህ ኡሙ ሙዓዝ ሞት ተነገረኝ። ያለፍክበት ሀዘንህን ሰምቻለሁ.. እና ታሪኬን አንብብ ... ስለ ማጣት እና ህመም የተከሰተ የመጀመሪያው ታሪክ አይደለም. እንደ እኔ በህመም እና በእጦት የሚሰቃዩ በመቶዎች የሚቆጠሩ አሉ።  አንዱ ወላጆቹን አጥቶ፣ ወይም ወንድሞቹንና እህቶቹን፣ ወይም ሁለቱንም አጥቶ የሚኖር አለ። ታሪኬ የጀመረው በረመዷን 27ኛው  በቀኑ የመጨረሻ ሰአት ላይ ነው። በእለቱ ሁላችንም በአንድ መኪና ተሳፍረን ዑምራ ለማድረግ ወደ ተከበረው የአላህ ቤት ልንሄድ ተስማማን።  ወንድሞቼ በየራሳቸው መኪና መምጣትን ትተው ከኛ ጋር በ አንድ መኪና ለመሄድ መፈለጋቸው የ አላህ ውሳኔ ነው ... ስምንት ሰዎች ነበርን... እኔ፣ ወላጆቼ፣ እህቶቼና ወንድሞቼ..
መኪናውን ሚነዳው አባቴ ነበር እና እናቴ ከጎኑ ነበረች። በዚያን ጊዜ እያንዳንዳችን ቁርኣንን ይዘን ሀረም እስክንደርስ ድረስ ሙሉ ቁርዓኑን ቀርተን (አንብበን) ለመጨረስና ዱኣ ለማድረግ ተስማማን ። እናም በዝምታ እና በተመስጦ ማንበብ ቀጠልን ዳግመኛ ማንበብ እንደማንችል ነገር ይመስላል አቀራራችን። እህቴ እያነበበች ታለቅሳለች ሌላኛዋም ወደ እኔ እያየች እያለቀሰች ዱኣ ታደርጋለች... እንባው ለምን እንደሆነ ጠየኳቸው..? ከመካከላቸው አንዷ፡- እያነበብኩ ሳለ የአላህ ድምፅ ወደ እኔ ቅርብ ነው አለችኝ ። በዛን ጊዜ .. ይመስለኛል አባቴ አላህ  ይዘንለትና እንቅልፍ አሸነፈው  .. መኪናው ከ ኮረብታው ጫፍ ላይ ተንሸራተተ.. ይህ ኮረብታ በተራራው አናት ላይ ነበር የነበረው.
መኪናው ከረጅም ርቀት ወደ ሸለቆው ውስጥ ያስገባን ጀመረ.. እና ገለበጠን መኪናው በተንከባለለ ቁጥር አንድ ሰው ከመኪናው ውስጥ ተወርውሮ  ይወድቃል .. እኔ ዛፍ ላይ ወደቅኩኝ የቀሩት በሸለቆው ውስጥ ወደቁ.. አደጋው በደረሰበት ሰአት የመግሪብ ሰላት አዛን እየተጣራ ነበር እና ፆመኞች ነበርን..ከዛ... ራሴን ሳትኩኝ ብዙ ደማሁኝ.. አስታውሳለሁ ከእንቅልፌ እንደነቃሁ እየጮህኩኝ ፈልጌያቸው ነበር። ስብራት እና ጉዳት ቢደርስብኝም አንድ ጊዜ እየተራመድኩ አንዴ ደግሞ ተኝቼ እየተሳብኩ እነሱን መፈለግ ጀመርኩኝ ። መኪናው ሲወድቅ ማንም አላየንም ነበር። እነሱ ጋር እስክደርስ ድረስ መጎተት ጀመርኩ
ከዛም እህቶቼን አገኘውና ልሸፍናቸው ሞከርኩ.. ሞተውም አገኘኋቸው እያንዳንዳቸውም የፊት ጣታቸው ከፋ አድርገው ነበር  ነእና ምስጋና ለ አላህ ይሁን ሸሃዳ ይዘው ነው የሞቱት ። በአንድ ቦታ ሰበሰብኳቸው። ከዛ ጨለመ... የእንስሳት ድምፆችን እና ጨለማን መፍራት ጀመርኩኝ . ወንድሞቼን በጭራሽ ላገኛቸው አልቻልኩም ። እየተሳበኩ ስሄድ እናቴን ሞታ አገኘኋት። እሷም ሸሃዳ ይዛ ነበር ..አባያዋም እንደ ከፈን ተጠቅልሎባት፣ጣቷ ብቻ ከሷ ላይ ይታይ ነበር ፣እናም ሸሃዳ ይዛለች...የተሸፋፈነቺው እንኳን አልወደቀም።በእቅፏ ላይ ሆኜ እሷ እንድትሰማኝ ለማድረግ ሞከርኩ.. ግን ምንም ውጤት የለም .. አባቴ ጋር ደረስኩ፣ እሱ አሁንም በህይወት አለ እና እየደማ ነበር። እኔ ህይወትሽን አደራ እልሻለሁ .. እዚህ ለረጅም ጊዜ እንዳትቆዪ.. ወደ ተራራው ውጪ እና የሚረዳሽን ሰው ጥሪ.. ወንድሞችሽን እና እናትሽን እርጂያቸው አለኝ. ያን ጊዜ የውሻዎችን ድምፅ ፈራሁ፤ በዚህ በድቅድቅ ጨለማ አላህ በዙሪያዬ አቆየክ ብዬ
በአባቴ እቅፍ ላይ ቆየሁ.. ደም እየደማሁ ነው እናም መንቀሳቀስ እንደማልችል ነገርኩት እና ከአንተ ጋር እቆያለሁ አልኩት.. በዚያን ጊዜ ደረቱ ላይ ወሰደኝ.. በገባው ቃል መሰረት እንድሆን መከረኝ .. ዱኣ ያደርግልኝም ነበር.. እሱም እየመከረኝ እያለ በዛው ህይወቱ አለፈች.. እራሴን ስቼ  እስከምወድቅ ድረስ ብቻዬን እያለቀስኩ ዱኣ እያደረኩኝ ቆየሁ..ራሴን አልተሰማኝም, በጣም  ደም ስለፈሰሰኝ እራሴን ሳትኩኝ.. በ ዓይነ ህሊናህ አስበው እስኪ በሁለተኛው ቀን እስከ አስር ድረስ  ማንም አላየንም ነበር አንድ ሙሉ ቀን ማንም አላየንም።ከዛ ቡሃላ አንድ እረኛ አገኘን.. ለአከባቢ ጠባቂዎች አሳወቀ..ከዛ የመከላከያ ቡድኑ ከአውሮፕላን እና ከመኪና ጋር መጡ.. በቡድን ተጎተትን.. ከዚያ በኋላ እስከ አምስት ወር ድረስ  ከኮማ አልነቃሁም ነበር። እና የሆነውን ነገር ገባኝ.. እንደ ቅዠትና ህልም ይመስል ነበር.. ሁለት አመት በካናዳ በህክምና ውስጥ አሳለፍኩ። በጭንቅላት፣ አንገት፣ ጀርባ፣ ዳሌ፣ ብዙ ቦታዎች ላይ ከባድ ስብራት ነበረብኝ።
በደም መፍሰስ ምክንያት እናት የመሆንን ፀጋ አጣሁ። በዶክተሮቹ በኩል ብዙ ሙከራዎች ቢደረጉም  አልተሳካም. ስለዚህ ምርጫው ወይ ሕይወቴ ማጣት ነበር...ወይ ደግሞ የልጆችን የማግኘት በረከት ሊያሳጣኝ የሚችለው ቀዶ ጥገና... ምርጫው ከባድ ነበር ... እና ብዙ አሰቃየኝ ... አሁን ደህና ነኝ እና ጤነኛ ነኝ (አልሃምዱሊላህ) አላህ ይመስገን። ያ ሸይኽ እኔም ሆን ብዬ ታሪኬን የነገርኳቹህ በጣም የምትወዱትንና የምትሳሱለትን ሰው ያጣቹት እናንተ ብቻ እንዳልሆናችሁ እንድታውቁ  ነው። እና አለም ከነሱ አንዳቸውን በማጣት እንደማያበቃ...ነገር ግን የ ኢማን መሟለት ምንክያት በሆነው በአላህ ቅድመ ውሳኔ (በቀደር) መታገስ አለብን። እና አላህ ይመስገን እነሆ ወደ ስራዬ ተመልሻለው ..ወደ ሪያድ ተዘዋውሬ ከአዲሱ ህይወቴ ጋር መኖር እና መኗኗር  ጀምሪያለው.... ስለ ሁሉም ነገር አላህ ይመስገን.. ሳልነግራችሁ ረሳሁት...የእህቶቼ ሰርግ ሁለት ሳምንት ቀርቶት ነበር...ከሰርጋቸው በፊት ዑምራ ለማድረግ ፈልገን ነበር። እስከ አሁን ድረስ የሰርግ ልብሳቸው ከእኔ ጋር ነው እኔም እስክሞት ድረስ እጠብቃቸዋለሁ ።
💡
💡
መልእክት ፡
በዙሪያቸው ካለው ነገር ሁሉ ምኞታቸው ለዘገየባቸው ሁሉ ጥቂት አመታት መታገስ ምንም ችግር የለውም  በዩሱፍ (ዓለይሂ ሰላት ወሰላም) ላይ የሆነው ነገር ሁሉ ታጋሽ በሆኑት ላይ ሁሉ ይፈጠራል ። አላህ የወሰደው ለጥበብ ነው፣ ያስቀረው ለምህረት ነው ... በእርግጥም የሚሰጠን ነገር መጠኑ ሊጨምር ሲል ምኞቶቻችን ይቆያሉ ። ስለዚህ በ አላህ ላይ ያላቹን እምነት አስተካክሉ።
ሶስት ዱኣዎችን ሱጁድ ላይ ስትሆን ማድረግን አትርሳ፡- ጌታዬ ሆይ የ ኻቲማን ማማር እለምንሃለሁ ጌታዬ ሆይ ከሞት በፊት ቅን ንስሐን ስጠኝ አንተ ልቦችን የምትገለባብጥ የሆን አምላኬ ሆይ ልቤን ዲንህ ላይ አፅናት። ይህን መልእክት እንኳን ሼር ለማድረግ ካሰብክ፤ ንያህን በመልካም ነገር አሳምረው ፤ ምናልባት አላህ ከቅርቢቱና ከኋለኛይቱ ዓለም ጭንቀት  ሊገላግልህ ይችላል።
.
አንብበው ከጨረሱ ቡሃላ አልሀምዱሊላህ ብለው ይፃፉ!!

#join us👇 & share
╭┈─────── ೄ🌻ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ
@fafiru_illahi
             
@fafiru_illahi