እንተዋወስ(entewawes)
181 subscribers
52 photos
22 videos
12 files
140 links
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
Download Telegram
🌹የነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአመጋገብ ሱና🌹

#1ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) መብላት ከመጀመራቸው በፊት እጃቸውን ይታጠብ ነበር ።የሚበሉት በቀኝ እጃቸው ሲሆን ከፊታቸው ካለው ምግብ ነበር የሚበሉት
#2የነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ተደግፈው በልተው አያውቁም፣ምግብ ሲበሉ የተለያየ ዓይነት አቀማመጥ ነበራቸው ።
ሀ,ልክ ተሽሁድ ላይ እንደሚቀመጡት አይነት ይቀመጡ ነበር ።
ለ,ልክ እንደዚሁ ይቀመጡና የአንድ እግራቸው ጉልበት ደረታቸው ጋር ይደርስ ነበር።
ሐ,የውስጥ እግራቸው መሬት ላይ ተለጥፎ ቁጢጥ ይሉ ነበር።
#3ነቢያችን(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በጠረጼዛ ተደግፈውም ሆነ ወንበር ላይ ተቀምጠው በልተውም አያውቁም ።ደስታርኸዋን (ቆዳ ወይም ጨርቅ) መሬት ላይ አንጥፈውአንጥፈው ይመገቡ ነበር።
#4አብዛኛውን ጊዜ ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲመገቡ በሶስት ጣታቸው (በአውራ ጣት፣ጠቋሚ ጣት እና መሀል ጣታቸው )በመጠቀም ነው።ምግቡ ቀጠን ያለ ከሆነ ግን የቀለበት ጣታቸውንም ጨምረው ይመገቡ ነበር
#5ተመግበው ሲጨርሱ ጣቶቻቸውን አፋቸው ውስጥ ከትተው ያፀዱዋቸው ነበር ።ከመሀል ጣታቸው ጀምርው አውራ ጣታቸው ላይ ያቆማሉ ።
#6በገበታው ላይ ያለው ምግብ ከመሀል ጀምሮ የተደረደረ ከሆነ ከፊታቸውና ከሥር ካለው ይጀምሩ ነበር። የምግብ በረካ ወደ መሀል እየቀነሰ ይሄዳል ብለዋል።
#7ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በብዙ ሰሀኖች የሚቀርብ የተለያየ አይነት ምግብ አይወዱም ነበር ።
#8ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሀለዋ (ጣፋጭ) ማር ፣ኮምጣጤ፣ተምር ፣ሀብሀብ ፣ኪያር እና ዝኩኒ ይወዱ ነበር ።
#9ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሽንጥ ፣የአንገት የትከሻ ስጋ ይወዱ ነበር።
#10ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንዳንድ ግዜ ሁለት ምግቦችን ይመገቡ ነበር ፤ሀብሀብ ና ተምር ፣ኪያር ና ተምር....


#11ይቀጥላል