እንተዋወስ(entewawes)
181 subscribers
52 photos
22 videos
12 files
140 links
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
Download Telegram
🌹የነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአመጋገብ ሱና🌹

#34ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከሰዎች ጋር እየበሉ ከሆነ ከገበታው የሚነሱት በመጨረሻ ነበር ። ይህንን የሚያደርጉት አንዳንድ ሰዎች ቀስ ብለው ስለሚመገብ ሌሎቹ ሲነሱ አፍረው መመገባቸውን እንዳያቆሙ ነበር ።ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እነዚህ ሰዎች እስኪጨርሱ ቀስ እያሉ እየተመገብ ይጠብቁዋቸው ነበር።
#35ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በመጀመሪያዎች ሦስት ጉርሻዎች ቢስሚላህ ይሉ ነበር።
#36አንድ ሰው ቢስሚላህ ሳይል ከበላ እጁን ይይዙትና ቢሰሚላህ እንዲል ያደርጉት ነበር።
#37ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንድ ሰው በግራ እጁ ሲበላ ካዩት እጁን ይይዙትና ምግቡን ያስጥሉታል፣ከዚያም በቀኝ እጁ እንዲበላ ይነግሩታል።
#38አንድ አይነት ምግብ ከቀረበላቸው ከፊታቸው ብቻ ይበሉ ነበር ።ነገረ ግን ከአንድ በላይ ምግብ ከቀረበላቸው ከሰዎች ፊት ሄደው ከመብላት አይቆጠቡም ነበር።
#39ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የቀይ ተምሮችን ውስጣቸውን ካፀዱ በኋላ ይበሉ ነበር ።
#40በልተው ጨርሰው ከታጠቡ በኋላ በጺማቸውና በራስ ፀጉራቸው ላይ ያደርቁ ነበር።
#41ዶሮ መብላት ከፈለጉ ቤታቸው ውስጥ ለብዙ ቀን ካቆዩት በኋላ አርደዋት አብስለው ይበሉ ነበር።
#42ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሾርባ ውሰጥ ቂጣ ከተው መብላት ይወዱ ነበር።
#43ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ቅቤ ከተምር ጋር መመገብ ይወዱ ነበር ።ተምርም ከወተት ጋር ይመገቡ ነበር፤ሁለቱም ምርጥ ምግቦች ናቸው ብለዋል።


https://t.me/leihte