እንተዋወስ(entewawes)
181 subscribers
52 photos
22 videos
12 files
140 links
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
Download Telegram
🌹የነብዩ ሰ.ዐ.ወ የአመጋገብ ሱና🌹

#22ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ምግብ የያዘን የምግብ ዕቃም ሆነ መጠጥ የያዘ መጠጫን ይከድኑ ነበር።የሚከድኑበት ነገር ካጡ ካላዩ ላይ ስንጥር ያስቀምጡ ነበር።
#23ተሰባስበው ለተቀመጡ ሰዎች የሚበላም ሆነ የሚጠጣ ነገር ሊያከፋፍሉ ሲፈልጉ ከቀኛቸው ይጀምሩ ነበር ።ከግሬቸው ለመጀመር ከፈለጉ ከቀኛቸው ያለውን ሰው ፍቃድ ይጠይቁ ነበር ።
#24ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ማታ የተሰራን ምግብ እስከጠዋት ፣ጠዋት የተሰራን ምግብ እሰከ ማታ አያቆዩም ነበር።(ለሚቀጥለው ምግባቸው በአላህ ላይ ይተማመኑ ነበር።
#25ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ሥጋ ወደቤት ሲያመጡ ለጎረቤት እንዲበቃ ተደርጎ እንዲሰራ ያደርጉ ነበር ።
#26ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ምግብም ላይ ሆነ መጠጥ ላይ ተንፍሰው (እፍ ብለው)አያውቁም። ምግብ ላይ መተንፈስን መጥፎ ልማድ አድርገው ይቆጥሩት ነበር ።
#27ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ሁለት ፍራፍሬዎችን በሁለት እጆችቻቸው ላይ አስቀምጠው ተራ በተራ ይመገቡ ነበር ።
#28ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ተምር ከተመገቡ በኋላ ፍሬውን በግራ እጃቸው ይጥሉት ነበር።ፍሬውን በሸሀዳ ጣታቸውና በመሀል ጣታቸው ጀርባ ላይ ላይ አድርገው ይወረውሩት ነበር።
#29የማያውቁት ምግብ ከገጠማቸው አስቀድመው ስለምግቡ ይጠይቁ ነበር።
#30የማያውቁት ሰው ምግብ ሲያመጣላቸው አስቀድመው እርሱ ከምግቡ እንዲበላ ያደርጉ ነበር።ይህንን ማድረግ የጀመሩት ጠላቶቻቸው መርዝ በምግብ ካበሉዋቸው ቦኋላ ነው።
#31ረሱል ሰ.ዐ.ወ የጎድን አጥንት በጣም ይወዱ ነበር።
#32ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ከተጠሩበት ቤት ሲሄዱ መንገድ ላይ ሰው ካጋጠማቸው ይዘውት ይሄዱና ጠሪዎችን ፍቃድ ይጠይቁዎቸው ነበር ።ከተፈቀደላቸው ይዘውት ይገባሉ።
#33ነብዩ ሰ.ዐ.ወ እንግዳቸውን በቃኝ እስኪላቸው ጠግቦ እንዲበላ ይገፋፉ ነበር።

#34ይቀጥላል https://t.me/leihte/299