እንተዋወስ(entewawes)
181 subscribers
52 photos
22 videos
12 files
140 links
وذكر فإن الذكرى تنفع المؤمنين
(አስታውስ ማስታወስ ሙኡሚኖችን ትጠቅማለችና)
Download Telegram
🌹የነብዩ ((ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) )የአመጋገብ ሱና🌹

#11ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ምግቡን ካልወደዱት ስለምግቡ ምንም ሳይናገሩ መመገብ ይተዉ ነበር ።
#12ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያልበሰለ ሽንኩርት ፣ነጭም ይሁን ቀይ በልተው አያውቁም ።
#13ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የተነፋ ዱቄት አይበሉም ነበር ።(ነገር ግን አልከለከሉም)
#14ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ቀጭን ቂጣ (መለዋ) በልተው አያውቁም፣ነገር ግን በስጋ ወይም በአትክልት ሶስ(ቁሌት )ከተነከረ ይመገቡ ነበር።
#15ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እርሾ የሌለው ዳቦ በልተው አያውቁም ።
#16ተምር ወይም ዳቦ ንፁህ ቦታ ላይ ከወደቀ ጠርገው ይበሉ ነበር ።
#17በጣም የሞቀ ምግብ አይመገቡም ነበር፤መጀመሪያ ያቀዘቅዙት ነበር። አላሁ ተዓላ እሳት አይመግበንም። ይሉ ነበር።በጣም በሞቀ ምግብ ውስጥ በረካ የለውም ብለዋል።
#18ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ምግባቸውን አሽትተው አያውቁም። ጥሩ ያልሆነ ልምድ እንደሆነም ይቆጥሩታል።
#19ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲበሉም ሆነ ሲጠጡተቀምጠው ነው ።ነገር ግን ፍራፍሬዎች ቆመውም ሆነ እየተራመዱ በልተው ነበር።
#20ነብዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ምግብ እንደቀረበ ወድያው በእጃቸው ከምግቡ አይቆነጥሩም ነበር ።እጃቸውን ምግቡ ላይ ያስቀምጡ ነበር።
#21 አንዳንዴ የበሰለን ሥጋ በቢላዋ ቆርጠው ይበሉ ነበር።
#22ይቀጥላል......