ጠበቃ ለምን አለው ?
መናፍቃን ክርስቶስን አማላጅ ከሚያደርጉበት ጥቅስ አንዱ ይሄ ነው ፦ "ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው " 1ኛ ዮሐ2:1 በመሰረቱ ቃሉን ላስተዋለው ክርስቶስ ለመለመኑ (#ለማማለዱ) የሚቀርብ አልነበረም ። ጠበቃ ሥራው አንድን ተከሳሽ የክሱ ነገር በእርሱ ላይ ቅጣት እንዳይፈፀም የሚከላከል ከጥፋት ፍርድም የሚያድን ማለት ነው ። ጠበቃ ተከሳሹን ነፃ የሚያወጣው ነው ። ለምሳሌ ያህል በዓለም ላይ ብዙ የፍርድ ሂደቶች ይከናወናሉ። ተከሳሽን ከፍርድ ነፃ ለማውጣት ከፍተኛውን ሚና የሚጫወተው ጠበቃው ነው ፤ ተከሳሹም ከፍርድ ነፃ ቢሆን የሚደነቀውና የሚመሰገነው ጠበቃው ነው ። እንግዲህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከፍርድ ነፃ ለማውጣት ሞቶአል ፣ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ተነስቷል
እርሱ ለኛ ባይቆምልን ኖሮ ኃጢአት ሰልጥኖብን ፣መንገድ ጠፍቶብን እንኖር ነበር እርሱ ዘወትር ኃጢአታችንን ይቅር ሊለንና ሊያነፃን የታመነ ነውና ከሳሻችን ዲያቢሎስ የሚያስነሳውን የሞትና የኃጢአት ሥራ በእርሱ ኃይል ነፃ እንደሚያወጣን የሚናገር ነው ።"ክርስቶስ ጠበቃ አለን " ሲል ዘወትር ለኛ ኃጢአት የሚለምን ማለት ሳይሆን የሚፈርድልን ነፃ የሚያወጣን ይቅር የሚለን ከሳሻችን ዲያብሎስን የሚያሳፍርልን አለን ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ሊሆን ይገባዋል ።ለምሳሌ ጌታ እግዚአብሔር አምላካችን ጠበቃ ሆኖ ኢያሱን ነፃ እንዳወጣው እንመለከታለን "እርሱም ታላቁን ካህን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ ሰይጣንም ይከሰው ዘንድ በስተቀኝ ቆሞ ነበረ
እግዚአብሔርም ሰይጣንን "ሰይጣን ሆይ እግዚአብሔር ይገስፅህ ኢየሩሳሌም የመረጠ እግዚአብሔር ይገስፅህ ፤ በውኑ ይህ ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይደለምን አለው ። ኢያሱም እድፋም ልብስ ለብሶ በመልዐኩ ፊት ቆሞ ነበር ። እርሱም መልሶ በፊቱ የቆሙትን እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቁ አላቸው እርሱንም አበሳህን ከአንተ አርቄዐለሁ ጥሩ ልብስም አለብስሃለው አለው ። ደግሞ ንጹህ ጥምጥም በራሱ ላይ አድርጉ አለ ። እነርሱም በራሱ ላይ ንጹህ ጥምጥም አደረጉ ልብስን አለበሱት የእግዚአብሔርም መልዐክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር " ትን.ዘካ 3:1-5 ከዚህ ጥቅስ የምንረዳው ራሱ እግዚአብሔር ከሳሹን ሰይጣንን እንዴት እንዳሳፈረው የሚያመለክት ነው ። ከዚህ እውነት በመነሳት ክርስቶስን ጠበቃ ሲለው አዳኛችን ፣ ከሳሻችን ዲያቢሎስን የሚያሳፍርልን ፣ አበሳችንን ሁሉ ያራቀልን አንዱ ጌታ አምላክ መድኀኒትና ፈራጅ እርሱ መሆኑን ለማመልከት ነው
ም/ቱም "በኃጢአታችን በመናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከአመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነ እና ጻድቅ ነው ።"ይላልና 1ኛዮሐ 1:9 ጠበቃ የሚለው ፈጽሞ ለምልጃ የሚጠቀስ አይደለም ም/ቱም እርሱ ይቅር የሚልና የሚያነፃ እንጂ የሚለምን አይደለም ። አይ ይለምናል(ያማልዳል) ካልን ከቃሉ ጋር ልንጋጭ ነው ። ይለምናል ካልን ወዴት ? ወደ ማን ? ወደ አብ እንዳንል ። "እኔና አብ አንድ ነን "ብሏል ዮሐ 10:30 ስለዚህ ጌታችን በስሙ አምነን ተጠምቀን ንስሀ ገብተን የምንቀበለው ስጋና ደሙ ከሀጢአታችን የሚያነጻን መሆኑን የንስሐችን መፈፀሚያ ፍፁም የሐጢአት ስርየት ማግኛ መሆኑን ለመናገር እንጂ "አማላጅ ነው " የሚያሰኝ ምንም አይነት ነገር የለውም
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ ? ማር 15:34 ለምን አለ ?
ሙስሊም ወንድሞቻችን እና የጆቫ ዊትነስ (የይሆዋ ምስክሮች) ክርስቶስ አምላክ ሳይሆን ፍጡር ነው ብለው ያምናሉ ። ይህንን እምነትና ሃሳባቸውንም በመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ለማስደገፍ ይሞክራሉ ። ከሚጠቅሷቸው ጥቅሶች መሀከልም አንዱ ይሄ ነው ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እራሱ አምላክ ነው እንጂ አምላክ ያለው ፍጡር አይደለም ። ታዲያ ለምን "አምላኬ አምላኬ " ለምን አለ ቢሉ ስለ 5 ነገሮች ይህን ተናግሯል ። እነሱም፦
#1ኛ.ፍጹም ሥጋ እንደተዋሀደ ለማጠየቅ ነው ። ጌታ አምላኬ ባይል ኖሮ ስጋን አልተዋሀደም ሰው አልሆነም ይሉ ነበር ። ሥጋ ደሞ ፍጡር ስለሆነ አምላኬ እንደሚል ይታወቃልና ፤ አላዋቂ ስጋን የተዋሀደ ስለሆነ ክርስቶስ ሥጋን እንደተዋሀደ ለማሳወቅ ለማስረዳት ለማረጋገጥ እንችል ዘንድ የስጋ ባህሪያትን ያሳየናል። ሲያድን ልትድን ትወዳለህን ? በማለት ሲጠይቅ የነበረው መዳን እንደሚፈልጉ ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም አንደኛ ፍቃዳቸውን ለማወቅ ሲሆን ሁለተኛ ግን አላዋቂ ስጋን ስለተዋሀደ ነው ።ስለዚህ በስጋው አምላኬ አለ
#2ኛ.አምላኬ አምላኬ ያለው ለአቅርቦተ ሰይጣን ነው ። ሰይጣን ሔዋንን በእባብ አድሮ አሳስቷል ። ስለዚህ ክርስቶስ ደግሞ በደካማ ስጋ ተዋህዶ ድል አደረገው ።ሰይጣን ክርስቶስ ሲጠመቅ ከላይ አብ ሲመሰክርለት ሲያይ ፣ እውር ሲያበራ ፣ ሙት ሲያስነሳ ሲያይ ይሄማ እግዚአብሔር ነው ይል ነበር ከዛ ደግሞ ሲራብ ሲጠማ ሲደክም ሲያየው ይጠራጠር ነበር ። ክርስቶስም መስቀል ላይ ሆኖ አምላኬ አምላኬ ሲል ሰይጣን ሲሰማው ውይ ይሄማ እሩቅ ብእሲ (ተራ ሰው ) ነው ብሎ እንደለመደው ነፍሱን ሊቀማ ወደ መስቀል ቀረበ ያኔ ጌታ በነፋስ አውታር አስሮ አስለፈለፈው .... ስለዚህ ለአቅርቦተ ሰይጣን ይሄን ተናግሮታል
#3ኛ.ሊቃውንት እንደሚያመሰጥሩት ለአዳም የተገባለትን 5ሺ 500 ዘመን መፈፀሙን አውቆ አዳም በሲኦል ሆኖ አምላኬ ለምን ተውከኝ የገባህልኝ ቀንና ሰዓት ተፈፀመ እያለ ይጮህ ነበርና የሱን የአዳምን ጩኸት ክርስቶስ በመስቀል ሆኖ አስተጋባው
#4ኛ.ለቤዛ ለካሳ ነው የአዳምን ሥጋ ለብሶአልና መከራን ቢቀበል ቢደክም አዳም መከራ ስለተቀበለ ለአዳም ቤዛነት መጥቷልና ጌታም መከራ መቀበል አለበት ለካሳ ቤዛ ለመሆን አምላክ ይህን አደረገ በአዳም ቦታ ተገብቶም አምላኬ አምላኬ አለ
#5ኛ.ለአብነት ለአርአያ (ለትምህርት) ነው ። ለምሳሌ እንዴት መፀለይ እንዳለብን ፀልዮ አሳይቶናል ፣ እንዴት መጾም እንዳለብንም ጾሞ አሳይቶናል ። ለዚህም ነው ያን ሁሉ መከራ ሲያደርሱበት የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ያለው ። እስጢፋኖስም ይህንን ትህትናት ከጌታ ስለተማረ ነው በድንጋይ ሲወግሩት ጌታ ሆይ የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ያለው ። ሐዋ 7:60 "እንግዲህ ክርስቶስ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላቹ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና " ጴጥ 2:21በዛ ላይ ክርስቶስ ይሄን ቃል የተናገረው በመስቀል ላይ በስቃይ ላይ ሆኖ ነው እኛም በከባድ መከራ ውስጥ ስንሆን መርዝ መጠጣት ፣ ገመድ መፈለግ ሳይሆን ያለብን "አምላኬ አምላኬ " ብለን ወደእሱ ነው መጮህ ያለብን ። በነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ጌታ አምላኬ አምላኬ አለ እንጂ አንዳንዶች እንደሚሉት አምላክ ስላልሆነ ይህንን አላለም። አምላክ ለመሆኑማ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልዕክቱ በግልፅ ቃል አስቀምጦቷል
"#ክርስቶስ_በሥጋ_መጣ_እርሱም_ከሁሉ_በላይ_ሆኖ #ለዘላለም_የተባረከ_አምላክ_ነው_አሜን " ሮሜ 9:5
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተ ነህ ለምን አለ ? ዮሐ 17:3
ሙስሊሞ እና የይሆዋ ምስክሮች የተባሉ ወገኖቻችን ክርስቶስ አምላክ አይደለም ብለው ከሚያቀርቡት ጥቅስ አንዱ ይሄ ነው ። ይህን ምዕራፍ ስንመለከት ጌታችን በዚህች ምድር ላይ በስጋው ወራት ሊሰራ ያቀደውን ጨርሶ ወደ ክብሩ ሊሄድ ሊሰቀል ሲል የተናገረው ቃል ነው ። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እርሱ ከአብ ጋር እኩል በመሆኑም "እኛ አንድ እንደሆንን "በማለት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል ስልጣን እኩል ጌትነት እንዳለው እንረዳለን ። ያላመኑት ግን "እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንክ አንተን የላከውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘለዓለም ሕይወት ናት " ዮሐ 17:3 የሚለውን በመጥቀስ ጌታ አምላክ እንዳልሆነ አብ ብቻ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ አሕዛብ ይናገራሉ። እስኪ በሌላ ስፍራ ላይ የተጠቀሱትን ጥቅሶች እንመልከት ፦
"ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚቻለው ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኀኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ግርማ ኃይልም ስልጣንም ይሁን አሜን " ይላል ይሁዳ 1:25 በዚህ አገላለፅ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ አምላክ እንደሆነ ተገልፇል ። በሌላም ስፍራ ፦ "ስለዚህ እላችዋለው ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል በመንፈስቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም " ማቴ 12:31 ቀጥሎ ደግሞ እንዲህ ይላል፦
"ብቻህን አምላክ የሆንህ አንተ የላከውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት " ዮሐ 17:3 ታዲያ ሶስቱም ብቸኛ ከተባሉ የቱን እንምረጥ ? ዳሩ ግን ይህ ለምን እንደተባለ ለኛ ለክርስቲያኖች ግልጥ ነው ። ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ እንዳለው ፦ "ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳን የተከደነባቸው ለሚጠፋ ነው " 2ኛ ቆሮ 4:3 ታዲያ ጌታችን ይህን ስለምን ተናገረው ቢሉ የዘላለም ሕይወት የሚገኝባት ሃይማኖት ይህች ናት አንተ የባህርይ አምላክ እንደሆንክ እኔም የባህርይ አምላክ እንደሆንኩ ያውቁ ዘንድ ቢያውቁ እውነተኛ ሃይማኖች ይህቺ ናት ማለቱ ነው ። ጌታ በአንዳንድ ቦታ ላይ አምላክ ወይም እግዚአብሔር ብሎ እንደ ሰው መጸለዩ በእውነት የሰውን ባህርይ ባህሪው ማድረጉን ሊያስረዳን ፈልጎ ነው እንጂ በባሕሪው ከአብ የሚያንስ ሆኖ አይደለም
እንደ ሰው አምላኬ ብሎ ባይፀልይ ኖሮ በእርሱ ዘንድ ሰውነት የለም ወይም መለኮት ተስብእትን(ሰውነትን) ውጦ አጥፍቶታል በተባለም ነበር ። ይህ የጌታችን አነጋገር በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድ #ለአጽድቆተ_ትስብእት ተብሎ ይተረጎማል፡ ስለዚህ እነርሱ እንደሚሉት ሳይሆን ጌታችን ስለዚህ ተናገረው እንጂ አምላክ ስላልሆነ አይደለም ። አምላክ ስለመሆኑማ ዮሐንሰ እንዲህ በማለት ገልጾታል ። "እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው " 1ዮሐ5:20 "የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ ዋህድ ነፍስንና ስጋን ነስቶ ሰው ሆነ ባልንም ጊዜ ስለዚህም ነገር ቢሆን እነዚያ እንደሚያምኑ መቀላቀል የለበትም የቃል ባህርይ የስጋን ባህርይ ወደ መሆን አልተለወጠም ሁለት ባህርይ ያለመለወጥ ባለመቀላቀል ጸንተው ይኖራሉ እንጂ " ሃይማኖተ አበው ዘ ኤራቅሊስ
"የእግዚአብሔር የባህርይ ልጅ ሲሆን ሰው ይባላል ፤ ዳግመኛም የአዳም ልጅ ይባላል ሰማያዊ ሲሆን በፈቃዱ ምድራዊ ሆነ ። በመለኮቱ መከራን መቀበል ሳይኖርበት ሰው በመሆኑ መከራ ተቀበለ ፈጽሞ አንዱ በአንዱ ያደረ ነው አይባልምና ለአንዱ ለእግዚአብሔር ልጅ ሁለት አካል ሁለት ገጽ ሁለት ባሕርይ የለውም " ሃይማኖተ አበው ዘ አትናቴዮስ ስለዚህ ክርስቶስ ፍፁም ሰው የሆነ ፍፁም አምላክ ነው አምላኬ ሲል ብትሰሙት በተዋሀደው ስጋ ነው እንጂ በመለኮቱስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ እኩል ነው
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
"ወደ አባቴና አባታችሁ ወደ አምላኬና አምላካችሁ አላረኩምና አትንኪኝ" ዮሐ 20:17 ለምን አላት ?
ሙስሊም እና ጆቫ ዊትነስ ወንድሞቻችን ክርስቶስ አምላክ አይደለም ብለው ከሚያቀርቧቸወ ጥቅሶች አንዱ ነው ። ጌታችን ይህንን የተናገረው በትንሳኤው እለት ለመግደላዊት ማርያም ነው ይህንን የጌታ አነጋገር በነጠላ ትርጉሙ ለመረዳት ቢሞከር ወደ ስህተት ያደርሳል። አንድን ጥቅስ እየመዘዙ ወደ ስህተት ከመነዳት በፊት ምስጢራዊ ትርጉሙን መረዳት ያስፈልጋል። ለምን አትንኪኝ አላት ? መፍቅሬ ሰብእ(ሰውን ወዳጅ) ኢየሱስ ክርስቶስ መግደላዊት ማርያምን "#አትንኪኝ" ያላት ጠልቷት ወይም ተጸይፎአት አይደለም ይህች ሴት ከሰባት አጋንንት ነፃ ያወጣት እርሱ ነው ሉቃ 8:2 ታዲያ ለምን አትንኪኝ አላት ቢሉ ፦
#1ኛ.ይህን ቃል ጌታ ከትንሳኤው በሁዋላ የተናገረው ሥጋን በመቃብር ትቶት እንዳልመጣ አሁንም የተዋሀደው መሆኑን ያን መዋቲ አካል ማስነሳቱን ለመጠየቅና የዛ የተዋሃደው አካል የስጋ ፈጣሪ እንዳለው ለማጠየቅ ነው ። ለዚህም ነው ቶማስን "ና ዳሰኝ መንፈስ እንደኔ ሥጋና አጥንት የለውም " ያለው ሉቃ 24:39 #አምላኬ ማለቱ የፈጠረውን ሥጋ መዋሃዱን ለማመልከት ነው #አባቴ ማለቱ ደግሞ ለእርሱ የባህርይ አባቱ ነውና ነው ለኛ ደሞ የፀጋ አባታችን ነው
#2ኛ. ሁለተኛው ምክንያት ጌታ ስሟን ጠርቶ ማንነቱን በገለጸላት ጊዜ እና ገና አላረኩም የሚለው ንግግር ስትሰማ የመሰናበቻው ማለትም ከምድር ወደ ሰማይ በሕልውና ወደ ባህርይ አባቱ በልዕልና የሚያርግበት ጊዜ የደረሰ መስሎት በእግሩ ላይ ወድቃ ልትስመው ነበር። ጌታችን ግን የማርግበት ጊዜ ገና አልደረሰምና ለመሰናበት ብለሽ አትንኪኝ ሲላት ነው
#3ኛ. ስርዓተ ካህናትን ሲመሰርትልን ነው ። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈ ምስጢር በተባለው መጽሐፋ እንዲህ ይላል ፦ "መግደላዊት ማርያምን በስርዓተ ምዕመናን አብነት አትንኪኝ ሲላት ሲሆን ለሐዋርያት ግን ተዳሰሰላቸው " ብሏል ማለትም ስልጣነ ክህነት የሌላቸዉ ስጋና ደሙን መፈተት አይችሉም ሲል ነው ። ዳግመኛም ሴቶች ስጋና ደሙን መፈተት እንደማይችሉ ስርዓትን ሲሰራልን ነው ። ለዚህም ማስረጃው ለቶማስ ሲዳሰስለት መግደላዊት ማርያምን ግን አትንኪኝ ማለቱ ነው ። ዮሐ20:26-30 ባጠቃላይ ጌታችን ይህን ጥቅስ በነዚህ ምክንያቶች ተናግሮታል እንጂ አንዳንድ የእምነት ተቋማት እንደሚሉት ለሱ አምላክ ኖሮት (ሎቱ ስብሐት) አይደለም
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
ልጁም ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል ለምን አለ ? 1ኛ ቆሮ 15:24
ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን መልዕክት ለምን እንደፃፈው ከመመልከታችን በፊት እስኪ የሚከተለውን ጥቅስ እንመልከት ፦ "በሚድኑትና በሚጠፋት ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና ለነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለነዚያ ለህይወት ለህይወት የሚሆን የህይወት ሽታ ነን ለዚህም ነገር የሚበቃ ማነው ? የእግዚአብሔርን ቃላት ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎች አይደለንምና በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን " 2ቆሮ 2:9 ታዲያ ይህንን አባባል ማለትም ለምን ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል አለ ሲባል ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጡር ስለሆነ አልያም አምላክ ስላልሆነ አይደለም
ታላቁ የቤተክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "እርሱ ከሁሉ አስቀድሞ የነበረ ነው ሰማያት ሳይዘረጉ፣ የየብስ ፊት ሳይታይ ፣ ተራሮች ሳይቆሙ፣ የአየር ርዝመት ሳይከፈት በባሕርይ የነበረ ነው " እንዳለው እርሱ ከሁሉ በፊት የነበረ አምላክ ነው ። አንድ ሃይማኖት ሃይማኖት አለኝ የሚልና ስለአለበት ሃይማኖት እውቀት አለኝ የሚል ሰው የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በመምዘዝ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ አይደለም እያሉ ከመቃዠቱ በፊት ለምን እንደተነገረ ማወቅ አለበት
ጥቅሱ ከላይ ስለሞት እየተናገረ መምጣቱን እንረዳለን ። የሁዋላ ጠላት የተባለው ሞት ነው ። ሞት ሁሉን ገዝቶአልና ነገር ግን ሁሉን ካስገዛለት ከወልድ(ከክርስቶስ) ሞት እንደሚያንስ ይታወቃልና ከሞት ስልጣን የክርስቶስ ስልጣነ መለኮት ይበልጣልና ። ሞት በሰው ልጆች ላይም እንዲሰለጥን ያደረገው ባለቤቱ ወልድ ነውና ። በዕለተ ምፅአት ሁሉ በተገዛለት ጊዜ (ለሞት) ያን ጊዜ ወልድም ሁሉን ላስገዛለት ለሞት ተገዝቷል ። መቼ ? በዕለተ ዓርብ ። ስለዚህ የዕለተ ዓርብን ሞቱን መናገሩ ነው ። በዕለተ ዓርብ በዘጠኝ ሰዓት ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ስጋው በገዛ ፍቃዱ ለይቷልና ሞት ለ3 መዓልትና ለ3 ለሊት ጌታን በቁጥጥር ስር አድርጎ ነበርና ይህም የጌታ ፍቃድ ስለሆነ እንጂ እንደ ሌሎች ሳይወድ በግድ አይደለም ። ስለዚህ ጥቅሱ #ክርስቶስ_ገዚ_አምላክ_ኖሮት_ይገዛል_ማለት #ሳይሆን_ለሞቱ_የተነገረ_ነው
👉 "ከግርማው የተነሳ የሞት ደጆች ይከፈታሉ የሲኦል በሮችም ባዩት ጊዜ ይደነግጣሉ ከሰማይ በታች ያለውም ስፋቱን ከሰማይ በላይ የሚሆነውንም እርሱ ያውቃል " ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሃይማኖተ አበው
👉 "የአንተን ስም ሰምቶ ሞት ይደንግጥ ቀላያትም ይሰንጠቁ ፣ ጠላትም ይረገጥ የጥፋት መንፈስ ይንቀጥቀጥ ከይሲም ይወገድ ፣ አለማመንም ይራቅ ወንጀለኛም ይቸገር ቁጣ ጸጥ ይበል ቅናት ጥቅም አያግኝ ፣ ኃጢአትን የሚያዘወትር ይገሰጽ ወርቅን የሚወዱ ይነቀሉ ድካም ይወገድ ሐሰተኛ ይጣል ፣ መርዝ ያላቸው የፍጥረቶች ወገን ሁሉ ይበተኑ ። " ቅዳሴ እግዚእ
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
ያችን ሰዓት ልጅም(ወልድም) ቢሆን ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም ለምን አለ ? ማቴ 24:36
ይህንን ጥቅስ በመጥቀስ አምላክ ቢሆን ሁሉን ያውቅ ነበር ይላሉ። በመሰረቱ ቀኒቱንና ሰዓቲቱን እርሱ ባያውቀው ኖሮ ምልክቱን ባልነገራቸው ነበር የተናገራቸው ምልክቶች በሙሉ ማወቁን የሚያሳዩን ናቸው። "ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው " ይላል ሮሜ9:5 ከሁሉ በላይ ከሆነ ደግሞ ማንም ከእርሱ በላይ የለም ። "ያለውና የነበረው ፣ ፊተኛውና መጨረሻው እርሱ ነውና '' ራዕ 1:9 ነገር ግን ይህንን ቃል ለምን ተናገረው ቢሉ ስለ ብዙ ምክንያት ተናግሮታል
#1ኛ.ፍጹም ሥጋ መዋሀዱን ሲያጠይቅ ነው ሥጋ ደግሞ በራሱ እውቀት የለውምና
#2ኛ.ወዲያው የሚመጣበትን ቀን ቢነግራቸው እንዳይደነግጡ ፈልጎ የምነግራችሁ ብዙ አለኝ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም አላቸው
#3ኛ.በኖህ ዘመን የነበሩ ሰዎች 120 ዓመታት የንስሐ ዘመን ቢሰጣቸው 100 ዓመት በልተን ጠጥተን ፣ ጨፍረን ፣ 20 ዓመት ሲቀረን ንስሐ እንገባለን ብለው እርኩሰትን ስለፈፀሙ በመሐል ከሀጢአታቸው የተነሳ በንፍር ውሃ ተጥለቅልቀው ጠፍተዋልና አሁንም በዚህ ዓመት በዚህ ወር እመጣለው ቢላቸው ሰንፈው ንስሐ ሳይገቡ ገና ነው እያሉ እንዳይሞቱ የሚመጣበትን ቀን መች እንደሆነ አልተናገረም " ተዘጋጅታችሁ ኑሩ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ በነቃ ቤቱም ሊቆፍር ባልተወው ነበር ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ የሰው ልጅ በማታስቡበት ጊዜ ይመጣልና"ማቴ 24:43
#4ኛ.ሌላው ጌታ ይህንን ቃል የተናገረው ዓለምንና ጊዜያትን ሁሉ የፈጠረና በሁዋላም ሊያሳልፋቸው የሚችል ፈጣሪ ብቻ ሁሉን የማወቅ ስልጣን እንዳለው ሊገልጽልን አስቦ ነው። ጌታም ከአብ ጋር አንድ ስለሆነና የአብ የሆነው ሁሉ እውቀትም ስልጣንም የእርሱ ስለሆነ ስለዚያች ቀን እርሱም ያውቃል ምክንያቱም ወልድ በመለኮቱ ከአብ ጋር እኩል ነውና (ዘእሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ)
እንግዲህ ክርስቶስ ሁሉን እያወቀ ራሱን ከአብ ለይቶ ያችን ቀን እንደማያውቅ የተናገረበት ምክንያት እርሱ ከአብ ተለይቶ ማለትም ወልድ በተለየ አካሉ ቅድመ ተዋሕዶ የነበረ አላዋቂ ሥጋን እንደተዋሀደ ለማስረዳት ነው ። ይህም ማለት ክርስቶስ ፍጹም ሰው በመሆኑ ለሰው ልጆች ሁሉ ወገናዊነቱን ያመለክተናል ፤ ከእኛ ጋር ያለውን ዝምድና ይገልጽልናል እርሱ ሰው ሆኗልና የሰው ልጅም ተብሏልና ። ክርስቶስ ፍጹም ሰውና ፍጹም አምላክ በመሆኑ በመለኮቱ ከአብ ጋር አንድ ሲሆን በሰውነቱ (ስጋን በመዋሀዱ) ከሰዎች ጋር አንድ ሆኗል ። ከዚህም የተነሳ ክርስቶስ ዳግማዊ አዳም ተብሏል ። ም/ቱም የአዳምን ስጋና ነፍስ ተዋህዷልና
የምድር ስርዓት ይሻራል ፍጥረት ሁሉ አንድ መንጋ ይሆናሉ ፣ በአንድ እረኛ ይሰማራሉ ስለጌታችን መምጣት ከቅዱሳት መጽሐፍት እንደተማርነው ጊዜውንና ሰዓቱን የሚያውቅ ከፍጡር ወገን ከቶ አይገኝም ሆኖም ቅዱሳት መጽሐፍት እንደነገሩን መምጣቱ የማይቀር ነው እስከዛ የድህነት ስራ መስራትና ወንጌልንም ለዓለም መስበክ ያስፈልጋል "እነሆ በቶሎ እመጣለው ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ አልፋና ኦሜጋ ፊተኛውና ሁዋለኛው መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ "ራዕ 22:12
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
አፅናኝ የተባለው ማነው ?
ሙስሊም ወንድሞቻችን ይህንን ጥቅስ ከመፅሐፍ ቅዱስ በመውሰድ አፅናኝ የተባለው ነብይ (ነብዩ መሀመድ) እንጂ መንፈስቅዱስ አይደለም ይላሉ። በመሰረቱ እነሱ አሉ እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ አላለም ። ጌታም ነብይ እልክላቹዋለው አላለም ። ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን ተቀበልን ሁሉን ነገረን አሉ እንጂ ነቢይ ተላከልን አላሉም ። ታዲያ ጌታችን እልክላቹዋለው ያለው ማንን ነው ? ከተባለ ያለ ምንም ጥርጥር እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ነው
ይህንንም መጽሐፍ ቅዱስ በማያሻማ መልኩ በግልጽ አስቀምጦታል የተስፋውም ፍፃሜ እንዲህ ነበር ፦ "በዓለ ሀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉ በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ ተቀምጠውም የነበሩበትን ቤት ሁሉ ሞላው እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጡባቸው በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር "የሐዋ 2:1-4 ታዲያ ከየት መጥቶ ነው መንፈስ ቅዱስ ነቢይ የሚሆነው ? በጭራሽ ነቢይ አይደለም
ያልተባለን ማውራት ላም ካልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደሚሉት አበው ይህንን ትምህርት ሐዋርያትም ፣ ነብያትም፣ ሊቃውንትም አላስተማሩም። መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው መካከል አንዱ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ነበር ። እርሱም ከሐዋርያት ጋር በፆም በፀሎት የተጉ 120ዎቹን ቤተሰብ በመወከል ከተለያየ አገራት በበዓሉ ላይ ለመገኘት ለመጡት ሰዎች ልብን የሚነካ መንፈሳዊ ክፍተትን የሚሞላ ፣ ጥያቄን የሚመልስ ንግግር አደረገላቸው። የንግግሩ ዋና ማዕከል ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን የንግግሩ ርዕስ እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ነበር ። ፈሪና ከሀዲ የነበረው ቅዱስ ጴጥሮስ ታላቅ ድፍረትን ተሞልቶ የመጀመሪያውን የምስራች አወጀ ከዚያም በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት 3000 ሰዎች ያለ ምንም የጦር መሳሪያ ኃይል ወዲያው ለወንጌል ተሸነፋ
የጌታችን የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶክ ፍቅሩ ፣ ሞቱ፣ ትንሳኤው ፣ ለሰው ልጆች ያደረገውን ቤዛነት ሲሰሙ በወንጌል አምነው ተጠመቁ የሐዋ 2:41 ይህ ይላካል የተባለው የአጽናኙ የመንፈስ ቅዱስ ጅማሬ ነበር ። ከዚህም የተነሳ የጥበበኞች ጥበበኛ እግዚአብሔር አሕዛብ ያለ ሐዋርያት ስብከት በሥላሴ ማመን እንደማይችሉ ሐዋርያትም ዳግመኛ ያለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ መስበክ እንደማይቻላቸው ያውቃልና በሰናኦር ሜዳ የተበተኑትን የዓለም ቋንቋዎች በሐዋርያት አንደበት ውስጥ ሰብስቦ ያኖር ዘንድ የጽድቅ መንፈስ ጰራቅሊጦስ ተላከ
መንፈስ ቅዱስ በወረደበት ዕለት የበዓሉ ታዳሚዎች በየራሳቸው ቋንቋ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ከሰሙ በዋላ ደቀ መዛኑርቱን ሰክረው ነው እንጂ ይህ ያልተለመደ ምንድነው ? እያሉ በመደነቅ ማጉረምረም ጀመሩ ። ጴጥሮስም "ለእናንተ እንደመሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም ከቀኑ 3:00 ነውና ነገር ግን በነብዩ ኢዩኤል የተባለው ነው " የሐዋ 2:14 በማለት አስረዳቸው ። ከጠዋቱ 3:00 መጠጥ አይጠጣም ነበርና ከሐዋርያው ከቅዱስ ጴጥሮስ ንግግር የምንረዳው ወይም የምንማረው እንደ መሰለን የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን ከአተረጓጎም ስርዓት ውጪ አጽናኙ መንፈስ ቅዱስን ነብይ ነው ብሎ መገመትና መተርጎም አግባብ አይደለም ። እንደመሰለን መተርጎም አላዋቂነት ነው 1ጴጥ 4:11
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
ወላዲተ አምላክ ስለመሆኗ
ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ መሆኗን እናምናለን ። ይኸውም ወልደ አብ ኢየሱስ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ በሥጋ ወልዳዋለችና ። ለዚህ ማስረጃ የሚሆኑንን ጥቅሶች እንመልከት ምክንያቱም ድንግል ማርያምን እንደ ማህደር ተጠቀመባት እንጂ ወላዲተ አምላክ አትባልም ብለው የሚያምኑ ስላሉ ፦ "እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች " ትን ኢሳ 7:14 ይህ ቃል የሚወለደው ሕፃን አማኑኤል ተብሎ ይጠራል የወለደቺውም ድንግል ናት ካልን ከቃሉ ከፍ ብሎ እንዲህ ይለናል፦
"እርሱም አለ እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ ስሙ በውኑ ሰውን ማድከማችሁ ቀላል ነውን አምላኬ ደግሞ የምታደክሙ ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣቹዋል " ኢሳ 7:13 ይህን ቃል ልናጤነው ይገባል የእስራኤል ቤት ብቻ ሳይሆን አለሙ ሁሉ ለመትረፍ በሰው ድካም አልሆነም ። አሁን ግን አምላክ ሊደክም የኛን መከራ ተሸክሞ ሊያድነን መጣ ። እርሱም #ምልክት ሰጠን #ምልክታችንም ድንግል ማርያም ነች አምላኬን የምታደክሙ ያለው ደግሞ ከድንግል የሚወለደው አምላክ መሆኑን ለማመልከት ነው
እናቱንም ወላዲተ አምላክ ያልናት ለዚህ ነው ። ሌላ ጥቅስ እንይ ፦ "ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል "ኢሳ 9:6 ሕፃን ተወልዶልናል እርሱ ደግሞ ኃያል አምላክ ነው ። ስለዚህ የወለደቺው ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ እንላታለን ። ይኸውም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በ#ተዋህዶ ከብሮ ተወልዷልና ። ሌላም ጥቅስ እንጨምር ፦ "የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል " ሉቃ 1:43 አስተውሉ ስራው የመንፈስ ቅዱስ ነው ኤልሳቤጥ አክስት መሆኗን እንጂ ድንግል ማርያም የጌታ እናት ትሁን አትሁን የምታውቀው ነገር የለም
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ተሞልታ ስለነበር የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆናል ስትል የጠየቀቺው ስለዚ ነው ። መንፈስ ቅዱስን የተሞላ ድንግልን ያውቃታል ፣ ያከብራታል ፣ ያመሰግናታል እርሱ ጌታ ነውና ወላዲተ እግዚዕ እርሷ ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ ያልናት ለዚህ ነው ። ሌላም እንይ ፦ "ቃል ሥጋ ሆነ ፀጋንና ክብርን ተመልቶ በኛ አደረ " ዮሐ 1:14 ያ ቃል ይለናል መጽሐፍ ቅዱስ በዮሐ 1:1 ላይ "ቃል እግዚአብሔር ነው " ስለዚህ የተወለደው የኛን ሥጋ የተዋሀደውን ክርስቶስ ኢየሱስን በሥጋ የወለደቺው ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት ። ሌላ ፦ "ነገር ግን የዘመኑ ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ " ገላ 4:4 ሴቲቱ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ነች
በአጭሩ ፦
👉 እርሱ አምላክ ስለሆነ እርሷም የአምላክ እናት ትባላለች
👉 እርሱ እግዚአብሔር ስለሆነ የእግዚአብሔር እናት ትባላለች
👉 እርሱ ጌታ ስለሆነ እርሷም የጌታ እናት ትባላለች
👉 እርሱ ብርሃን ስለሆነ እርሷም የብርሃን እናት /እመብርሃን/ ትባላለች። ጌታ አምላክ እናቱን ማደሪያው ስላደረጋት ከፈጣሪ በታች በሰማይና በምድር ከከበሩ ሁሉ የከበረች ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን ናት ስለዚህም ትውልድ ሁሉ ብፅዕት እያሏት እያመሰገንዋት ይኖራሉ ስሟንም እየጠሩ በደስታ እየዘለሉ ይዘምራሉ ሉቃ 1:39-55 ልጇ አምላክ ነው እርሷ እናቱም ወላዲተ አምላክ ናት
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
ዮሴፍ ለምን እጮኛዋ ተባለ ?
እጮኛ የሚለው ቃልና ፍቺ ለሚያባት ሴት ብቻ የተሰጠ ሳይሆን በጠባቂነትም ላለ ይሰጣል። መናፍቃን እጮኛዋ የሚለውን ቃል በመያዝ ዮሴፍ ድንግልን እንዳገባትና ከሷም ልጅ እንደወለደ ይናገሩ (እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጣቸው) ነገር ግን እንደዛ አይደለም እስቲ ድንግል ማርያም የዮሴፍ እጮኛ የተባለችበትን ምክንያቶች እንመልከት፦
#1ኛ. የዳዊት ልጅ ተብሎ ይጠራ ዘንድ ነው ። ምክንያቱም በሴት ትውልዱ ቢቆጠር አይሁድ አይቀበሉም ማቴዎስ ትውልዱን የፃፈው በዮሴፍ ነው ። ለዚህም ነው መልዐኩ "ዮሴፍ ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት በአሰበ ጊዜ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ እጮኛህ ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ "ያለው ማቴ1:10 ለባልነት ቢሆን ኖሮ ግን በስውር ሊተዋት ፈጽሞ አያስብም ነበር። እዛው ም 1:16 ላይ ስንሔድ በኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ ውስጥ ተፅፎ የምናገኘው ዮሴፍን እንጂ ማርያምን አይደለም ።
#2ኛ.እንዲጠብቃት ነው ለዚህም ነው መልዐኩ ዮሴፍ ትቷት እንዳይሄድ የተናገረው
#3ኛ.እንዲያገለግላት ነው ። በስደቷ ጊዜ ይዞ እንዲሄድ የታዘዘው ዮሴፍ ነውና ። ለሚስትነት ታጭታ ቢሆን ግን ከወለደች ቡሃላ ለዮሴፍ ሚስትህን ይዘህ ሂድ ይለዋል እንጂ ሕፃኑንና እናቱን ብሎ አይናገረውም ነበር ። እንደውም ከወለደች ቡሃላ ዮሴፍን እጮኛህንም ይዘህ ሂድ ሲለው አንመለከትም ። ለዚህም ነው እንዲያገለግላት በእጮኝነት የተሰጠው ማቴ2:13
#4ኛ.እርሷ ከሰው ዘር ከሰው ወገን መሆኗ ይታወቅ ዘንድ ነው ። መጽሐፍ ቅዱስም "የአብርሃም ዘር ይዞአል "ያለው ለዚ ነው ዕብ 2:15 ምክንያቱም እርሷን ኃይለ አርያማዊት ክርስቶስን መልዐክ ብለው የሚነሱ መናፍቃን አሉና ። በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንዴት ትወልዳለች እንዳይሉ
#5ኛ.በዘፀ 5:23 መሰረት "ሴት ወንድ ካጠገቧ ሳይኖር ፀንሳ ብትገኝ ተወግራ ትገደል " የሚል ሕግ አይሁዳውያን ስላላቸው ተወግራ እንዳትገደል ነው ። እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች እጮኛ አሰኝተዋታል እንጂ እጮኛነቱ ለመገናኘት ለባልና ለሚስት ግንኙነት አይደለም

"የበኩር ልጅዋን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም " ለምን አለ ? ማቴ 1:25
አላወቃትም ማለቱ አዳም ከገነት ከወጡ በሁዋላ ሄዋንን እንዳወቃት አወቃት ማለት ሳይሆን እመቤታችን አምላክ በማህፀንዋ ሳለ የእመቤታች መልኳ ይለዋወጥ ስለነበር በውስጧ ይህ ነው የማይባል ህብር ያለው እና ቀለሙ የሚነገርለት አይደለም እና በውስጧ ያለው እሳተ መለኮት ክርስቶስ እርሱ መልኩን በለወጠ ቁጥር እርሷንም ይለውጥ ነበርና ነው ፤ ለምሳሌ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን በደብረ ታቦር ሲገለጥ ፊቱም ልብሱም አጣቢ ከሚያነፃው በላይ ነጭ ሆነ ። ይህንንም በማህፀንዋ ሊያደርገው ቻለ ምክንያቱም ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና ። ስለዚህ የእመቤታችን ፊትዋ ብርሃን ሲሆንበት ዮሴፍ ይህች ማናት ብሎ ግራ ይገባው ነበር
ስለዚህ እስክትወልድ ድረስ የፊትዋን ብርሃን በማየት አላወቃትም ስትወልድ ግን በማህፀኗ ሆኖ ፊትዋን የሚለውጠው ጌታ ተወልዷልና አወቃት
#1ኛ. በኦሪ.ዘፀ 34:35 - 39 እንደ ተፃፈው ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋግሮ ሲመለስ ፊቱ እንደ ጸሀይ ያበራ ስለነበር አሮንና ህዝቡ ስለፈሩ ፊቱን ይሸፈን እንደ ነበር እናነባለን እንዲሁም ጸጋንና ኃይልን ተመልቶ ሳይፈራ በአይሁድ ሸንጎ ፊት ስለጌታ የመሰከረው ቅዱስ እስጢፋኖስ "በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኩር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት " ተብሎ ተነግሮለታል የሐዋ 6:15 ስለዚህ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት በመቆሙ ፊቱ ካንፀባረቀ ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስም ፊቱ የመልአክን ፊት ከመሰለ ፤ ሁሉን የፈጠረ እግዚአብሔር ወልድን በማህፀኗ የተሸከመች እመቤታችን ከወትሮው ሁኔታ የመልኳ መለወጥ የገጿ መንጸባረቅ ይህም ለዮሴፍ እንግዳ መሆኑ የተገባ ነው
#2ኛ.ጌታ ሲወለድ የተደረገውን ተአምራት ተመልክቶ ማለትም፦
ሀ.ሰብአ ሰገል እጅ መንሻ ወርቅ ፣ ዕጣን ፣ ከርቤ ይዘው በመምጣት ሰግደው መገበራቸውን
ለ.የኮከቡ ሰብአ ሰገልን መርቶ ማምጣት
ሐ.የእግዚአብሔር ክብር በቤተልሔም ዙሪያ ማብራት
መ.የቅዱሳን መላእክት ዝማሬና የቤተልሔም አካባቢ በአእላፍ መላዕክት መሞላት
ሠ.የእረኞች መጎብኘትና ምስክርነት ማቴ2:1-12 ሉቃ 2:5-14
#3ኛ.እንደ መናፍቃኑ አተረጓጎም #አላወቃትም የሚለውን ቃል በቀጥታ እንኳን ብንመለከተው " እስክትወልድ ድረስ " ማለቱ ከወለደች በሁዋላ አወቃት ብሎ ለመደምደም አይቻልም ። ምክንያቱም በዕብራይክጡ #እስከ ወሰን ድንበር የሌለው ፈጽሞ ከቶ ማለት ይሆናልና ። ለዚህም ማስረጃ እንይ ፦
ሀ."የሳኦል ልጅ ሜልኮል እስከሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም " 2ኛሳሙ 5:23 ይላል ። ታዲያ ይህ ሜልኮል ፈፅሞ አልወለደችም ማለት እንጂ ከሞተች ቡሃላ በመቃብር ወለደች ማለት አይደለም
ለ.ቅዱሳን ሐዋርያትን "እኔ እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ " ማቴ 23:19 ብሏቸዋል ይህ ማለት ከዚያ ቡሃላ ይለያቸዋል ማለት አይደለምና እመቤታችንም "የበኩር ልጅዋን #እስከምትወልድ ድረስ አላወቃትም " ማለት ፈፅሞ በእደ ዮሴፍ አልተዳሰሰችም ለዘለዓለም ድንግል ናት እርሷም ወንድ ሳላውቅ እንዴት ይሆንልኛል እንዳለች ወንድ አታውቅም ማለት ነው

Forwarded from ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
የቤተክርስቲያን ንዋየተ ቅድሣት እና ትርጉማቸው
#ለማያውቁ የማሳወቅ ግዴታዎን ይወጡ❗❗❗
#ሌሎች_እንዲያነቡትና_እንድማሩበት_አስተማሪ_ሆኖ_ካገኛችሁ_ሼር_ያድርጉ
#ታቦት
🔹ታቦት ማለት እግዚአብሔር አስርቱ ትዕዛዛትን በእጁ ፅፎ ያስቀመጠበትና ለሙሴ የሰጠው ቅዱስ ንዋይ ነው
🔸በቤተክርስቲያንም ፃህሉን እና ፅዋውን በዚህ ላይ በማስቀመጥ መስዋዕቱን እናከብርበታለን
🔹ይህም ማለት ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ የሚዘጋጀው በዚህ ላይ ነው
መስቀል
🔸ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶ በቀራንዩ የተሰቀለበት ሰይጣን ድል የተነሳበት የመዳናችን አርማ ነው
🔹መስቀል ምዕመናንን እና ንዋየ ቅዱሣትን ለመባረክ ያገለግላል፤ የተለያዩ የመስቀል አይነቶች አሉ። ከእነዚህም መካከል
የእጅ መስቀል
🔹ይህ የክህነት ማዕረግ ያላቸው አባቶች ብቻ የሚይዙት ሲሆን ምዕመናንን ለመባረክ ይጠቀሙበታል
የመፆር መስቀል
🔸ይህ ዲያቆናት በቅዳሴ ጊዜ የሚሠብኩበት ሲሆን በመጠኑም ከፍ ያለ ነው
መብራት
🔹መቅረዝ የሻማ ማብሪያ ነው፤ ቀንዲል ደግሞ ሻማ ወይም የዘይት መብራት ነው
🔸የመቅረዙ አገልግሎት ለሻማ ማብሪያነት ሲሆን ቀንዲሉ ደግሞ ቅዱሣት መፃህፍት፣ መልዕክታት፣ ወንጌል ሲነበቡ ይበራሉ
አልባሳት
🔹በቤተክርስቲያን የአገልግሎት ልብስ እንደ ግለሠቡ የስልጣን ሁኔታ ይለያያል፤ የመነኮሣት ልብስ፣ ከካህናት ልብስ የካህናትና ዲያቆናት ይለያል
👉የጳጳሳት ልብስ፣
👉የመነኮሳት ልብስ፣
👉የካህናት ልብስ፣
👉የዲያቆናት ልብስ
🔺ቀሚስ 🔺ቀሚስ
🔺ካባ ላንቃ 🔺ለምድ
🔺ሞጣህት 🔺ድግድጋት
🔺ቆብ 🔺ስአክሊል
ማኅፈድ
🔹የጨርቅ መሸፈኛ ነው፤ ታቦቱን እና ጻህሉን ለመሸፈን ያገለግላል
🔸ከምስራቅ ወደ ምዕራብ፤ ከሰሜን ወደ ደቡብ፤ ከመስዕ/ ከሰሜን ምሥራቅ /ወደ አዜብ /ደቡብ ምዕራብ/ ሆኖ ይለበሳል
መንጦላዕት
🔹በሶስቱም የመቅደስ በር የሚጋረዱ መጋረጃዎች ናቸው፤ ቀለማቸውም ቀይ ነው
መጎናፀፊያ
🔸ይህ በቅዳሴ ጊዜ መንበሩ (መሠዊያው) የሚለብሰው ሲሆን፤ ታቦት በሚወጣበት ጊዜ የሚጎናፀፈው ነው
መንበር
🔹የጽላቱ (የታቦቱ) መቀመጫ ዙፋን ነው፤ ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙ የሚዘጋጀውም በዚህ ላይ ሆኖ ነው
🔸ካህን ያልሆነ ሠው መንበሩን መንካት የማይችል ሲሆን መንበሩ እና ታቦቱ ወዳለበት ክፍል (መቅደስ) መግባት የሚችሉት ዲያቆናት፣ ካህናት፣ ኤጲስ ቆጳሳት ጳጳሳት ናቸው
ጻህል
🔹የቅዱስ ሥጋው ማስቀመጫና ማክበሪያ ነው፤ ከወርቅና ከብር፣ ከነሀስና ከብረት የሚሠራ
ሲሆን የተለየ ቅርፅና የተለየም ምልክት ያለው ነው
ፅዋ
🔸የክርስቶስ ክቡር ደም የሚቀርብበት ነው፤ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከመዳብ፣ ከነሀስ፣ ከብረት
የሚሠራ ነው
ዕርፈ መስቀል
🔹ማንኪያ ዓይነት ሆኖ ጫፉ ላይ መስቀል ያለው ነው
🔸ፅዋው ከተሠራበት ቁስ የሚሠራ ሲሆን አገልግሎቱም የክርስቶስን አማናዊ ደም ለመቀበል የሚያገለግል ነው
ዐውድ
🔸በድርገት ጊዜ ጻህል የሚቀመጥበት ሰፋ ያለ ጻህል ነው፤ ሥጋው እንዳይነጥብ መጠበቂያ ነው፤ የሚሠራው ከብረት፣ ከነሀስ፣ ከእንጨት ነው
አጎበር
🔹በዐውድ ላይ የሚደፋ አራት ማዕዘን ሦስት እግር ያለው እንጨት ወይም ብረት ሊሆን ይችላል፤ ይህም ቅዱስ ሥጋውን ልብሱ እንዳይነካው ከፍ አድርጎ የሚይዝ ነው
ጽንሃ
🔸የዕጣን ማሣረጊያ ነው፡፡ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከብረት፣ ይሠራል፤ ይህን ንዋይ ምዕመናን መጠቀም (መንካት) አይገባቸውም
🔹ዲያቆናት ይይዙታል ይነኩታል ነገር ግን ካህናት የሚይዙበት ቦታ ላይ መያዝ አይችሉም (አያጥኑም)
መሶበ ወርቅ
🔹የአነስተኛ መሶብ ቅርፅ አለው፤ አገልግሎቱም ቅዱስ ቁርባኑን ከቤተልሄም ወደ ቤተ-መቅደስ ለማምጣት ነው፤ በሚመጣበት ጊዜም በመጎናፀፊያ ተሸፍኖ ነው
ሙዳይ
🔸ለማዕጠንት አገልግሎት የሚያስፈልግ ዕጣን የሚቀመጥበት ነው
ቃጭል
🔹በቅዳሴ ጊዜ የሚቃጨልና ድምፅ የሚሠጥ ነው፤ በቅዳሴ ጊዜ አራት ጊዜ ቃጭል ይደወላል
👉ቅዳሴ ሲገባ
👉ፃኡ ንዑሰ ክርስቲያን ሲባል
👉በእግዚኦታ ጊዜ
👉ድርገት በሚወርድበት ጊዜ
ጥላ
🔸ይህ ከተለመደው ጥላ የሚለየው የተለያየ አንፀባራቂ ቀለም ባላቸው ጨርቆች መሠራቱ ነው
🔹አገልግሎቱ በቅዳሴ ጊዜ ምስባክ ሲሰበክ እና ወንጌል ሲነበብ ይዘረጋል
🔹ንግስ በሚሆንበት እለትም ከፊት እና ከኋላ በታቦቱ ዙሪያ ይዘረጋል
ድባብ
🔹በመጠኑ ከጥላ ሠፋ ያለ ሲሆን በንግስ በዓላት ቀን በታቦቱ ላይ ይዘረጋል፤ ይዞ በታቦቱ አጠገብ መቆም የሚችለው ካህን ብቻ ነው
ከበሮ
🔸ከበሮ ከእንጨት እና ከበሬ ቆዳ ተሠርቶ በጨርቅ የሚሸፈን ከፍተኛ ድምፅ የሚሠጥ መሣሪያ ነው፤ ይሁንና ከነሃስ እና ከብርም ተሠርቶ ቆዳው ሊወጠር ይችላል
🔹ሁለት ጎኖች ሲኖሩት በእነዚህ ሁለት ጎኖች የሚወጣው ድምፅ የተለያየ ነው፤ አገልግሎቱም በማህሌት ጊዜ ለመዝሙር ማጀቢያነት ነው
ፅናፅል
🔸ከነሃስ ወይም ከብር ሊሠራ ይችላል፤ ድምፅ የሚሠጡት በውስጡ ያሉት 5 ወይም 7 የሚሆኑ የነሀስ ወይም የብር ቁርጥራጮች ናቸው
🔹አገልግሎቱም በእጅ ተይዞ ወደ ላይ እና ወደታች በማወዛወዝ መዝሙሩን ማጀብ ነው
መቋሚያ
🔹ከእንጨት ከነሀስ ከብር ይሰራል
🔸አገልግሎቱም በመዝሙር ጊዜ በትከሻ በመሸከም ወይም በእጅ በማወዛወዝ መዝሙሩን ይጅባል፤ ለመደገፊያነትም ያገለግላል
🔗 @Z_TEWODROS

The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 27 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.
The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 7 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.