ኢየሱስ ማን ነው ?
መግቢያ
በዚህ ባለንበት ወቅት ይህ ጥያቄ የሁሉ ጥያቄ ነው ።ሁሉም በዚህ ጉዳይ ላይ ትክክለኛውን መልስ ለመስጠት እንዲያስችለው እውነተኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ምን እንደሆነ በአግባቡ መረዳት አለበት ። ይህ ጥያቄ የእኛ እያንዳንዳችን ዓለም እንደሚጠይቀው ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስም ስለ እርሱ ማንነት ሰዎች ምን እንደሚሉ ጠይቋቸዋል ። ለሐዋርያትም የቀረበው ጥያቄ ይህ ነበር " ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ?" እነርሱም "አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ ሌሎችም ኤልያስ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነብያት አንዱ ነው ይላሉ " አሉት ። ማቴ16:14 ይህ ሰዎች የሚሉት ትክክለኛ ማንነቱን ያልተረዱት መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን "እናንተስ እኔን ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ ? " አላቸው ። ይህ ጥያቄ እጅግ በጣም ወሳኝ ነበር ። የእርሱን ማንነት እንዴት እንደሆነ የሚናገሩበት ጥያቄ ነበርና ሲመልሱም " አንተ በእውነት የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ " በማለት ነበር ። ማቴ 16:16-18 ጌታም መልሶ " ይህን ሥጋና ደምህ አልገለጠልህም የሰማዩ አባቴ እንጂ " ሲል ለጴጥሮስ ነግሮታል። እዚህ ጋር 1 ነገር በጣም እናስተውላለን
አንደኛ ፦ ሰዎች እነርሱ እንደመሰላቸው ብዙ ዓይነት መግለጫ ለርሱ እንዳቀረቡ
ሁለተኛ ፦ ትክክለኛውን መልስ ላገኙት ለሐዋርያት ለተሰጣቸው ምላሽ ሥጋና ደም መግለጥ የሚችለውን ሳይሆን ከሰማዩ አባት የተሰጠ መልስ መሆኑን እንረዳለን
የሰማዩ አባታችን ስለ ልጁ የሚገልጥልን እውቀት የማይሻር የማይለወጥ ነውና ወደዚህ ግልጽ እውነት መምጣት ይኖርብናል ።እኔን ማን ትሉኛላቹ ? ተብለን ስንጠየቅ እንደ ሐዋርያቱ መመለስ አለብን
በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተዛባ አመለካከት የሚያራምዱ ብዙ ግለሰቦችና የሃይማኖት ድርጅቶች አሉ ። ኢየሱስ ለምን ሰው ሆነ ? ለምን መከራ ደረሰበት ? ለምን ሞተ ? ለምን በፈጠረው ፍጡር ተቀለደበት በማለት ይጠይቃሉ። እውነትን ለመቀበል ከተዘጋጁ ግን ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ለዚህ ሁሉ ጥያቄ ከበቂ በላይ መልስ አላት ። በምስጢረ ሥላሴ ፣ በምስጢረ ስጋዌ (በአምላክ ሰው መሆን ) ዙሪያ ለሚነሱ ማንኛውም ጥያቄ በቂ መልስ አላት ። እኛም በተከታታይ ክፍል ለጥያቄዎቹ መልስ እንሰጣለን
💚 @Kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️

"ኢየሱስም እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም " አለ ዮሐ 14:6
#ይህን_ለምን_አለ ?
ጌታችን እኔ መንገድ ነኝ ማለቱ የአንድነትና የሶስትነት መገለጫ እኔ ነኝ ማለቱ ነበር ። ምክንያቱም ጌታችን በስጋ ከመወለዱ በፊት እግዚአብሔርን አንድ እግዚአብሔር ከማለት ውጪ የአካል ሶስትነት ማለትም አብ፣ ወልድ ፣ መንፈስቅዱስ አይታወቅም ነበርና ። ጌታችን በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ያለው ታዲያ ለምንድነው ? ያልን እንደሆነ ፦ የወልድን ልጅነት ያላመነ የአብን አባትነት አያምንም ፤ የላከውን ልጁን ያልተቀበለ አብን አያውቅምና የአባትነት ማንነት በልጅ ስለሚታወቅ የእኔን ወልድነት "#ተወላዲነት" ካላመነ አብ በደመና የምወደው ልጄ ይህ ነውና በእርሱ እመኑ ብሎ ሲመሰክር ሰምቶ ካላመነ አይድንም ሲል ነው ።ዮሐ 14:7፣ 14:1 ፣14:21 ይመልከቱ ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብዙ ቦታ ላይ ስለ #መንገድ ተጠቅሷል ። መናፍቃን ስለሌላው መንገድ በሚገባ ለምን እንደተባለ ሳያብራሩ ጌታ የተናገረውን በመጥቀስ ብቻ እኔ መንገድ ነኝ ማለቱ አማላጅ ነኝ ማለቱ ነው ይላሉ። እስቲ ከመጽሐፍ ቅዱስ ስለመንገድ ከተጠቀሱት ጥቂቱን እንመልከት፦
#1."እግዚአብሔር እንዲህ ይላል #በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም የቀደመችውንም #መንገድ ጠይቁ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ በእርሷም ላይ ሂዱ ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላቹ " ት.ኤር 6:16
#2."ሀሳቤ እንደ ሀሳባችሁ #መንገዳችሁም እንደ #መንገዴ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር " ኢሳ 55:8
#3."ካዘዝኀቸው #መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ "ዘዳ 32:8
#4."በሕይወት እንድትኖሩ መልካምም እንዲሆንላችሁ በምትወርሷትም ምድር እድሜአችሁ እንዲረዝም አምላካችሁ ባዘዛችሁ #መንገድ ሁሉ ሂዱ " ዘዳ 5:33
#5."ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ #መንገዱም ትልቅ ነውና ወደ እርሱ የሚገቡ ብዙዎች ናቸው " ማቴ 7:13 እንግዲህ #መንገድ የሚለው በጥሬው አገላለጽ በርካታ ትርጉሞችን ይዞ እናገኘዋለን መናፍቃን እንደሚሉት ግን በዚህ ጥቅስ ውስጥ ስለ አማላጅነት የተነገረ አንዳችም ነገር የለም ይልቅ በወልድ ልጅነት በማመን ወደ አብ መድረስ እንደሚቻል የተነገረ የሕይወት ቃል ነው ። ከላይ ባየናቸው ጥቅሶች መንገድ ሃይማኖት ነው ፣ መንገድ ትዕዛዘ እግዚአብሔር ነው ፣ መንገድ ፍቃደ እግዚአብሔር ነው ፣ መንገድ ወንጌል ነው
ደግሞም ምልጃ የሚያስፈልገው ምህረትን ለማግኘት ነው
ምሕረት ደግሞ ለመዳን ሲሆን መዳን ማለት ደግሞ የዘላለም ሕይወት ማለት ከሆነ ጌታችን ደግሞ "እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ "እያለ "በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም " የሚለው ቃል እንዴት አማላጅ ተብሎ ይተረጓማል ? መናፍቃን እንደሚሉት አማላጅ ተብሎ የሚተረጎም ከሆነ ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወትን የሚሰጥ ሕይወት መሆኑ ቀርቶ ሕይወት አሰጪ መሆኑ ነው ይሄ ደግሞ የክህደት ክህደት ነው። ጌታችን መንገድ ነኝ ያለበት ሌላው ም/ት፦ መንገድ ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ስፍራ የሚያደርስ ፣ የሚወስድ ማለት ነው ። ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለኛ በመገረፋ ፣ በመቁሰሉ ፣ በመመታቱ ፣ መስቀል ላይ ስለኛ ሀጢአት በመሰቀሉ ፣ በደላችንን ሁሉ ተሸክሞ በፍቅሩ እኛን ወደ እርሱ በመጥራቱ ከነበርንበት የዘላለም ሞት አውጥቶ ወደ ዘላለም ሕይወት አሻገረን አደረሰን
ይህም እውነተኛውና ብቸኛው የመዳናችን መንገድ እርሱ በመሆኑ ነው ።አዳምና ሔዋን ዕፀ በለስን እንደበሉ ከተፈረደባቸው ቡሃላ "እግዚአብሔር አምላክም አለ ...እጁን እንዳይዘረጋ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ ...ከገነት አስወጣው ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም #መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔደን ገነት ምስራቅ አስቀመጠ። " ዘፍ 3:22 እንግዲህ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደው #መንገድ ስለተዘጋ ወደ ሕይወት የሚያደርሰን #መንገድ ያስፈልገን ነበር ። ስለዚህም እርሱ ሕይወት ነውና #መንገድ በመሆኑ ተዘግታ የነበረችውን ገነት አስከፈተልን መከፈቱንም ሊያረጋግጥልን በቀኙ ተሰቅሎ የነበው ወንበዴ " በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ " ሲለው "ኢየሱስ እውነት እልሃለው ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ "አለው ሉቃ 23:42
ሌላው መንገድ ነኝ ያለበት ፦ "ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው " ዮሐ6:5 ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ እኛን ከኀጢአት ሞት ወደ ዘልዓለማዊ ሕይወት የሚያሻግረን ስለሆነ እኔ መንገድ ነኝ አለ እንጂ መናፍቃን እንደሚሉት ለምልጃ የተጠቀሰ ቃል አይደለም
ለአስተያየት 👉 @kokuha_haymanot_bot
💚 @Kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
#ስለኛ_የሚማልደው_ለምን_አለ ?
መናፍቃን ክርስቶስን አማላጅ አድርገው ከሚያቀርቡበት ውስጥ አንዱ ጥቅስ ይሄ ነው ፦ "የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኮንንስ ማነው ? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞም ስለኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው " ሮሜ 8:34 ከላይ እንደ ተገለጠው #ኮነነ የሚለው ቃል የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ፈረደ ገዛ ማለት ነው ። የሚኮንን ማነው ? ሲል የሚገዛ የሚፈርድ ማነው ? ማለት ነው ። ምላሹም በጥቅሱ እንደተገለጸው #ክርስቶስ_ኢየሱስ ነው ። መጻሕፍት እንደሚመሰክሩት እኛም እንደምናምነው መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛው አስታራቂ መሆኑ አማላጅ አያሰኘውም አይደለምም
የእርሱ የማስታረቅ ስራ ከአማላጅነት ጋር የሚነጻጸር አይደለም ። ሁልጊዜ ስለ ክርስቶስ ስናስብ ከአብና ከመንፈስቅዱስ ጋር ያለውን አንድነት መዘንጋት የለብንም ። እንግዲህ ይሄ ጥቅስ መናፍቃን እንደሚሉት የክርስቶስን አማላጅነት የሚገልጥ ሳይሆን የክርስቶስን ፈራጅነት የሚያሳይ ነው ። ጌታችን ኃጢአትን ይቅር የሚል ፣ በደልን የሚደመስስ ፣ ምሕረትን የሚሰጥ ከራሱ ጋር ያስታረቀን አስታራቂያችን ፣ የታረቅንበት መታረቂያችን ፣ የታረቅንበት ታራቂያችን ነው እንጂ አማላጃችን አይደለም ። " እርሱ ክርስቶስ ገዢ ነው ፈራጅ ነው " ሮሜ 14:10 እንግዲህ ጌታ ፈራጅ ከሆነ እንዴት አማላጅ ሊሆን ይችላል ? ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ መባሉ እግዚአብሔር ስለሆነ ሲሆን እግዚአብሔር ከሆነ እንዴትና ከማን ይማልዳል ? #ቀኝ የሚለው ቃል ሥልጣንን፣ ክብርን፣ ሃይልን የሚያሳይ ነው
ከአብ ጋር ያማልደናል እንዳንልም "እኔና አብ አንድ ነን "ዮሐ10:30 ብሏል ። ታዲያ ስለኛ የሚማልደው የሚለው እንዴት ነው ቢሉ መጽሐፍ ቅዱስ የሚጠነቀቀው ከዘይቤ ይልቅ ለምስጢር ነው ። ለምሳሌ ቅዱስ ጳውሎስ የሚማልደው ሲል ጌታችን ከመወለዱ ከ700 ዓመት በፊት የነበረው ኢሳያስ ደግሞ ስለ አመፀኞች ማለደ ብሎአል ። ኢሳ 53:12 ኢሳያስ ገና ወደ ፊት የሚፈፀመውን እንደተፈፀመ አድርጎ ሲናገር ጳውሎስ ደግሞ የተፈፀመውን ገና ወደፊት እንደሚፈፀም አርጎ ተናገረ። ያውም በቃላት ሳይሆን እራሱን አሳልፎ በመስጠት አንዴ ለዘላለም የተፈፀመ ስለሆነ ማለደ ብሎ ደመደመው "ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይሄን አንድ ጊዜ ፈፅሞ አድርጓልና " ዕብ7:27 ይህም በመስቀሉ ከራሱ ጋር ከባህርይ አባቱ ከአብ ጋር ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሱ ቤዛነት ፣ በሱ ካሳነት ለዘልዓለም መዳናችንን ለመግለፅ እንጂ መናፍቃን እንደሚሉት እሱ ከአብ አንሶ ስለኛ ምህረትና ይቅርታ የሚጠይቅ አማላጅ አይደለም
በሌላ መልኩ ደግሞ ከ1938 ዓ.ም የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስለኛ #ይፈርዳል በማለት ነበር የተቀመጠው ። በ1980 የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ግን ስለኛ #የሚማልደው ይላል ። የ1938 ፈረደ የሚለውን ኀላ ቀላል አማርኛ በማለት ማለደ ተብሎ ሆን ተብሎ የተቀየረ ነው
እንግዲህ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ 8:34 ያሰፈረውን ፍሬ ሃሳብ ለመረዳት እስቲ ኢየሱስ አማላጅ ነው ለሚሉት ጥቂት ጥያቄዎችን እናንሳ የሚያጸድቅ መኮነን አይችልም ? የሚኮንንስ ለማጽደቅ ምን ይሳነዋል ? በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጥስ የሚችል ማነው ? ክርስቶስ በሞቱ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ እኛን የሚያድንበት ስልጣን አጥቶ ነው ስለኛ የሚማልደው ? ክርስቶስ ሁሉን የሚችል ኤልሻዳይ ነው ። ለሰውም እንደየስራው መክፈል የሚቻለው ፤ የሁሉ ዋጋ በእጁ ያለ የሚተካከለው የሌለ ባለ ጸጋ እውነተኛ ፈራጅ ዳኛም ነው ። እስቲ በመጽሐፍ ጥቅስ እናስደግፈው "እነሆ በቶሎ እመጣለው ለእያንዳንዱም እንደ ስራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ " ራዕ 22:12 ሌላ እንጨምር "እነሆ ዋጋው ከእርሱ ጋር ደሞዙም በፊቱ ነው "ኢሳ 40:10 ክርስቶስ ፈራጅ ከሆነ ታዲያ የሚለምን የሚያማልድ ማነው ? ከተባለ ከተለማኙ ጋር በቅርብ የሚተዋወቅ እውነቱን ለማስረዳት ይቅርታን ሊያሰጥ የታመነ ከተማላጁም ባለሟልነትን ያገኘ ነው ። ይሄንንም ስራ የሚሰሩት ከእግዚአብሔር በጸጋ የከበሩ ቅዱሳን ናቸው
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚

"አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው #መካከለኛ ደግሞ አንድ አለ እርሱም ሰው የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው "1ጢሞ 2:5
ይህንን ጥቅስ መናፍቃን ክርስቶስን አማላጅ ለማለት ከሚጠቅሱት አንዱ ነው ። ለመሆኑ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ማለት ምን ማለት ነው ?
1ኛ.ጌታችንን የነሳው ስጋና ነፍስ የሰው ነው። ይኸውም ትምክህታችን ከምትሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም ነው ሉቃ 1:26-45 ስጋውን ከሰው ባይነሳው ኖሮ "#ሰው" ሊባል አይችልም ነበር ። የሰውና የእግዚአብሔር መካከለኛ ሊባልም አይገባውም ነበር። አምላክ የሆነ ሰው ፤ ሰው የሆነ አምላክ ከእርሱ በቀር የለምና "#መካከለኛ" የተባለ ወልደ እግዚአብሔር የነሳው ስጋ የሰው ስለሆነ ነው
ጌታችን ከድንግል ከተወለደ በኀላ ከሁለት አካል አንድ አካል ፣ ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ ሆኗል ። በመለኮት ብቻ እንዳይጠራ የሚዳሰስ ፣ የሚጨበጥ፣ የሚበላ ፣ የሚጠጣ፣ የሚራብ፣የሚጠማ የሚደክም ሰው ሇኗል ። "#ሰው" ብቻ እንዳንል ነፋሳትን ማዕበላትን እንደ ነቢያት እንደ ሐዋርያት በእግዚአብሔር ስም ሳይሆን በራሱ ስልጣን ጸጥ የሚያደርጋቸው አጋንንትንም በስልጣኑ የሚያስወጣቸው በደረቅ ግንባር ላይ ዐይንን የፈጠረ ውሃውን ወደ ወይን የለወጠ ነው ። ስለዚህም ሰው ብቻ ነው አምላክ ብቻ ነው ማለት አይቻልም
ከዚህም የተነሳ እርሱ አንድ ጊዜ #በተዋህዶ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነውና #መካከለኛ ተባለ ።ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔርን በመበደሉ በመከራና በጩኸት መካከል የነበረውን የሰውን ልጅለማዳን በመካከል በመሆን ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ራሱ መስዋዕት ተቀባይ ፣ ራሱ መስዋዕት አቅራቢ ሆኖ አስታረቀን ። አስታረቀን ስንል ከራሱ ጋር ከባህርይ አባቱ ከአብ ከባህርይ ሕይወቱ ከመንፈስቅዱስ ጋር ነው ። የታረቅነውም በክርስቶስ ሞት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነው ። "ነገር ግን የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው እግዚአብሔርም በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ" 2ኛቆሮ 5:18-20 ስለዚህም መካከለኛ የሚለው ቃል ወልድ ዋሕድ ማለት እንጂ አማላጅ ማለት አይደለም
ሌላው ክርስቶስ መካከለኛ መባሉ በእለተ አርብ በተሰቀለ ጊዜ ራሱን መስዋዕት አድርጎ በሰጠ ጊዜ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለውን ኀጢአት ለማፍረስ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል በመስቀል ላይ በመዋሉ ነው ። "እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልኩ እንደሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለው "ዮሐ 12:32 "እግዚአብሔር ከዓለም አስቀድሞ ንጉስ ነው በምድር መካከልም መድኀኒትን አደረገ "መዝ 73:14 ከዚህ የተነሳ ንጉስ የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን ሊሽር በምድር ማዕከል በምትሆን በቀራንዮ በመስቀል ላይ በመካከል ቆመ ። ስለዚህ በዚህ ምክንያት መካከለኛ ተባለ እንጂ መናፍቃን እንደሚሉት በሰውና በእግዚአብሔር ለምልጃ የሚቆም መካከለኛ አይደለም

ስለ እነርሱም ሊያማልድ ለምን አለ?
"እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው እርሱ ግል ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው ። ስለ እነርሱም ሊያማልድ በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላልና። " ዕብ 7:23-25
ይህ ጥቅስ የሚያወራው የብሉይ ኪዳን ካህናትና የአዲስ ኪዳን እውነት ፈጽሞ በደሙ ያዳነን ሊቀ ካህናታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንዳደረገና በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት በማነፃፀር የፃፈው ነው ። ስለ እነርሱም የተባለው የብሉይ ኪዳንን ሊቀ ካህናት ነው ። በመጀመሪያ ብሉይ ማለት የድሮ ማለት የቀደመውን ኪዳን እግዚአብሔር ለነብያት ሰጥቶ ነበርና ነው ። ይህም ኪዳን ያለ ደም ሥርየት የለምና ። በጎችን፣ፍየሎችን፣ዋነሶችን፣ ፍየሎችን፣ጥጆችን... በማቅረብ የሚያገኙት የሀጢአት ሥርየት ነበር። ይህም #ብሉይ_ኪዳን በመባል ይታወቃል። እነዚህ ሁሉ መስዋዕቶች የሚፈፀሙት #በሊቀ_ካህኑ ነበር ። ሊቀ ካህኑ ራሱ ሁሌ እንዳይገባ ያለ መስዋዕትም እንዳይቀርብ ታዞ ነበር ።የመጀመሪያው የብሉይ ሊቀ ካህን የነበረውን አሮንን እግዚአብሔር ለሙሴ በመንገር እንዲህ ብሎታል፦
"እኔ በሥርየት መክደኛው ውስጥ በመጋረጃው ውስጥ በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ሥርየቱ መክደኛ ወደ ተቀደሰው ሥፍራ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው ። እንዲሁ አሮን ለኃጢአት መሥዋዕት ወይፈን ለሚቃጠል መሥዋዕትም አውራ በግ ይዞ ወደ ተቀደሰ ሥፍራ ይግባ " ዘሌ 16:2 ወደ እግዚአብሔር ያለ መሥዋዕት መቅረብ አይቻልም ነበር ። ሊቀ ካህኑ ኃጢአት ካለበት እዛው ይገድለው ስለነበር ወደ ውስጥ የሚገባው ሰው እግሩ በገመድ ይታሰር ነበር ። ም/ቱም ቢሞት በገመድ ጎትተው ያወጡት ነበር እንጂ ሬሳውን ገብቶ የሚያወጣ አልነበረም ። እንግዲህ በብሉይ ኪዳን ይህ ሁሉ ድካም ሊኖርባቸው የቻለው ኃጢአት ባለመወገዱ በዘላለም ሞት የታሰሩ በመሆናቸው ነው
እነርሱ ማለት ሊቃነ ካህናቱ በመጀመሪያ ለራሳቸው ኃጢአት መወገድ መሥዋዕት ካቀረቡ በኀላ ለሰው ደግሞ ያቀርቡ ነበር ። ለጊዜው በሚያቀርቡት መስዋዕት እግዚአብሔር ባያጠፋቸውም ካህናቱ ግን እንደማንኛውም ሰው በሞት የታሰሩ ነበሩ ። ከፍ ብለን ዕብ 7:23 እንደምናየው "እነርሱ ግን ሞት ስለከለከላቸው ካህናት የሆኑ ብዙ ናቸው " ይላል ። ይህ አገላለጽ አንድ ያስረዳናል ። ሞትን ሊያስወግድ የሚችል መስዋዕት አልነበረም ።ከጊዜያዊ መቅሰፍት ይድኑበት ነበር እንጂ ።ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ በተገለጠ ጊዜ የፍየልና የበግ ደም ሳይሆን በራሱ #ደም_አነፃን ። በነዚህ የእንስሳት ደም ፈንታ የእርሱ ደም በመቅደሱ ቆመ ። ያ የጥል ግድግዳ መፍረሱን ለማመልከት የመቅደሱ መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ። እኛም በእርሱ ደም ዳንን
የሊቃነ ካህናቱ ያ ሁሉ ድካም ቀረ ። ሊቃነ ካህናቱ አሁን በየዕለቱ መስዋዕት ይዞ መግባት አያስፈልገውም ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ ይህን ሁሉ አስወግዶ ራሱን በማቅረብ ፈጽሞታልና ። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይለናል ፦ "እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በሁዋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕት ያቀርብ ዘንድ አያስፈልገውም ፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጓልና" ይላል ዕብ7:26 ስለዚህም ክርስቶስ ያን የሊቃነ ካህናቱን ድካም አስወግዷልና ስለነርሱ #ሊያማልድ ማለትም ድካሙን መስዋዕቱን ሁሉ አስቀርቶ ለነርሱ ፈርዶላቸዋልና ከሞትም አድኖአቸዋልና ስለዚህ ካህናት ዛሬ የበግ፣የፍየል...ሳይሆን ይዘው የሚቀርቡት የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው
ቤተክርስቲያንም "ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው "ዮሐ 6:53 ባለው አማናዊ ቃሉ መሰረት ካህናቱ ሥጋውን ብሉ ደሙን ጠጡ ብለው ያውጃሉ ሕይወት እንድናገኝ ከርሱም ጋር ያለን ሕብረት በዚህ ይፈፀማልና። ስለዚህ #ይማልዳልና ያለው ለነሱ #ፈርዶላቸው ድካማቸውን አስቀርቷል የበጎችና የፍየሎች ደም ተወግዶ በደሙ ነፅተናል የሚል ፍቺ ነው ያለው እንጂ #አማላጅ ማለት አይደለም እነሱ እንደሚሉት እንየው ቢባል እራሱ እነዛ ካህናት አልፈዋል ሞተዋልና ለነዚህ የብሉይ ካህናት ይለምንላቸዋል የሚል ፍቺ ሊሰጥ ነው ። ይሄ ደሞ አያስኬድም

ጠበቃ ለምን አለው ?
መናፍቃን ክርስቶስን አማላጅ ከሚያደርጉበት ጥቅስ አንዱ ይሄ ነው ፦ "ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው " 1ኛ ዮሐ2:1 በመሰረቱ ቃሉን ላስተዋለው ክርስቶስ ለመለመኑ (#ለማማለዱ) የሚቀርብ አልነበረም ። ጠበቃ ሥራው አንድን ተከሳሽ የክሱ ነገር በእርሱ ላይ ቅጣት እንዳይፈፀም የሚከላከል ከጥፋት ፍርድም የሚያድን ማለት ነው ። ጠበቃ ተከሳሹን ነፃ የሚያወጣው ነው ። ለምሳሌ ያህል በዓለም ላይ ብዙ የፍርድ ሂደቶች ይከናወናሉ። ተከሳሽን ከፍርድ ነፃ ለማውጣት ከፍተኛውን ሚና የሚጫወተው ጠበቃው ነው ፤ ተከሳሹም ከፍርድ ነፃ ቢሆን የሚደነቀውና የሚመሰገነው ጠበቃው ነው ። እንግዲህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከፍርድ ነፃ ለማውጣት ሞቶአል ፣ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ተነስቷል
እርሱ ለኛ ባይቆምልን ኖሮ ኃጢአት ሰልጥኖብን ፣መንገድ ጠፍቶብን እንኖር ነበር እርሱ ዘወትር ኃጢአታችንን ይቅር ሊለንና ሊያነፃን የታመነ ነውና ከሳሻችን ዲያቢሎስ የሚያስነሳውን የሞትና የኃጢአት ሥራ በእርሱ ኃይል ነፃ እንደሚያወጣን የሚናገር ነው ።"ክርስቶስ ጠበቃ አለን " ሲል ዘወትር ለኛ ኃጢአት የሚለምን ማለት ሳይሆን የሚፈርድልን ነፃ የሚያወጣን ይቅር የሚለን ከሳሻችን ዲያብሎስን የሚያሳፍርልን አለን ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ሊሆን ይገባዋል ።ለምሳሌ ጌታ እግዚአብሔር አምላካችን ጠበቃ ሆኖ ኢያሱን ነፃ እንዳወጣው እንመለከታለን "እርሱም ታላቁን ካህን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ ሰይጣንም ይከሰው ዘንድ በስተቀኝ ቆሞ ነበረ
እግዚአብሔርም ሰይጣንን "ሰይጣን ሆይ እግዚአብሔር ይገስፅህ ኢየሩሳሌም የመረጠ እግዚአብሔር ይገስፅህ ፤ በውኑ ይህ ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይደለምን አለው ። ኢያሱም እድፋም ልብስ ለብሶ በመልዐኩ ፊት ቆሞ ነበር ። እርሱም መልሶ በፊቱ የቆሙትን እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቁ አላቸው እርሱንም አበሳህን ከአንተ አርቄዐለሁ ጥሩ ልብስም አለብስሃለው አለው ። ደግሞ ንጹህ ጥምጥም በራሱ ላይ አድርጉ አለ ። እነርሱም በራሱ ላይ ንጹህ ጥምጥም አደረጉ ልብስን አለበሱት የእግዚአብሔርም መልዐክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር " ትን.ዘካ 3:1-5 ከዚህ ጥቅስ የምንረዳው ራሱ እግዚአብሔር ከሳሹን ሰይጣንን እንዴት እንዳሳፈረው የሚያመለክት ነው ። ከዚህ እውነት በመነሳት ክርስቶስን ጠበቃ ሲለው አዳኛችን ፣ ከሳሻችን ዲያቢሎስን የሚያሳፍርልን ፣ አበሳችንን ሁሉ ያራቀልን አንዱ ጌታ አምላክ መድኀኒትና ፈራጅ እርሱ መሆኑን ለማመልከት ነው
ም/ቱም "በኃጢአታችን በመናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከአመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነ እና ጻድቅ ነው ።"ይላልና 1ኛዮሐ 1:9 ጠበቃ የሚለው ፈጽሞ ለምልጃ የሚጠቀስ አይደለም ም/ቱም እርሱ ይቅር የሚልና የሚያነፃ እንጂ የሚለምን አይደለም ። አይ ይለምናል(ያማልዳል) ካልን ከቃሉ ጋር ልንጋጭ ነው ። ይለምናል ካልን ወዴት ? ወደ ማን ? ወደ አብ እንዳንል ። "እኔና አብ አንድ ነን "ብሏል ዮሐ 10:30 ስለዚህ ጌታችን በስሙ አምነን ተጠምቀን ንስሀ ገብተን የምንቀበለው ስጋና ደሙ ከሀጢአታችን የሚያነጻን መሆኑን የንስሐችን መፈፀሚያ ፍፁም የሐጢአት ስርየት ማግኛ መሆኑን ለመናገር እንጂ "አማላጅ ነው " የሚያሰኝ ምንም አይነት ነገር የለውም
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ ? ማር 15:34 ለምን አለ ?
ሙስሊም ወንድሞቻችን እና የጆቫ ዊትነስ (የይሆዋ ምስክሮች) ክርስቶስ አምላክ ሳይሆን ፍጡር ነው ብለው ያምናሉ ። ይህንን እምነትና ሃሳባቸውንም በመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ለማስደገፍ ይሞክራሉ ። ከሚጠቅሷቸው ጥቅሶች መሀከልም አንዱ ይሄ ነው ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እራሱ አምላክ ነው እንጂ አምላክ ያለው ፍጡር አይደለም ። ታዲያ ለምን "አምላኬ አምላኬ " ለምን አለ ቢሉ ስለ 5 ነገሮች ይህን ተናግሯል ። እነሱም፦
#1ኛ.ፍጹም ሥጋ እንደተዋሀደ ለማጠየቅ ነው ። ጌታ አምላኬ ባይል ኖሮ ስጋን አልተዋሀደም ሰው አልሆነም ይሉ ነበር ። ሥጋ ደሞ ፍጡር ስለሆነ አምላኬ እንደሚል ይታወቃልና ፤ አላዋቂ ስጋን የተዋሀደ ስለሆነ ክርስቶስ ሥጋን እንደተዋሀደ ለማሳወቅ ለማስረዳት ለማረጋገጥ እንችል ዘንድ የስጋ ባህሪያትን ያሳየናል። ሲያድን ልትድን ትወዳለህን ? በማለት ሲጠይቅ የነበረው መዳን እንደሚፈልጉ ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም አንደኛ ፍቃዳቸውን ለማወቅ ሲሆን ሁለተኛ ግን አላዋቂ ስጋን ስለተዋሀደ ነው ።ስለዚህ በስጋው አምላኬ አለ
#2ኛ.አምላኬ አምላኬ ያለው ለአቅርቦተ ሰይጣን ነው ። ሰይጣን ሔዋንን በእባብ አድሮ አሳስቷል ። ስለዚህ ክርስቶስ ደግሞ በደካማ ስጋ ተዋህዶ ድል አደረገው ።ሰይጣን ክርስቶስ ሲጠመቅ ከላይ አብ ሲመሰክርለት ሲያይ ፣ እውር ሲያበራ ፣ ሙት ሲያስነሳ ሲያይ ይሄማ እግዚአብሔር ነው ይል ነበር ከዛ ደግሞ ሲራብ ሲጠማ ሲደክም ሲያየው ይጠራጠር ነበር ። ክርስቶስም መስቀል ላይ ሆኖ አምላኬ አምላኬ ሲል ሰይጣን ሲሰማው ውይ ይሄማ እሩቅ ብእሲ (ተራ ሰው ) ነው ብሎ እንደለመደው ነፍሱን ሊቀማ ወደ መስቀል ቀረበ ያኔ ጌታ በነፋስ አውታር አስሮ አስለፈለፈው .... ስለዚህ ለአቅርቦተ ሰይጣን ይሄን ተናግሮታል
#3ኛ.ሊቃውንት እንደሚያመሰጥሩት ለአዳም የተገባለትን 5ሺ 500 ዘመን መፈፀሙን አውቆ አዳም በሲኦል ሆኖ አምላኬ ለምን ተውከኝ የገባህልኝ ቀንና ሰዓት ተፈፀመ እያለ ይጮህ ነበርና የሱን የአዳምን ጩኸት ክርስቶስ በመስቀል ሆኖ አስተጋባው
#4ኛ.ለቤዛ ለካሳ ነው የአዳምን ሥጋ ለብሶአልና መከራን ቢቀበል ቢደክም አዳም መከራ ስለተቀበለ ለአዳም ቤዛነት መጥቷልና ጌታም መከራ መቀበል አለበት ለካሳ ቤዛ ለመሆን አምላክ ይህን አደረገ በአዳም ቦታ ተገብቶም አምላኬ አምላኬ አለ
#5ኛ.ለአብነት ለአርአያ (ለትምህርት) ነው ። ለምሳሌ እንዴት መፀለይ እንዳለብን ፀልዮ አሳይቶናል ፣ እንዴት መጾም እንዳለብንም ጾሞ አሳይቶናል ። ለዚህም ነው ያን ሁሉ መከራ ሲያደርሱበት የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ያለው ። እስጢፋኖስም ይህንን ትህትናት ከጌታ ስለተማረ ነው በድንጋይ ሲወግሩት ጌታ ሆይ የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ያለው ። ሐዋ 7:60 "እንግዲህ ክርስቶስ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላቹ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና " ጴጥ 2:21በዛ ላይ ክርስቶስ ይሄን ቃል የተናገረው በመስቀል ላይ በስቃይ ላይ ሆኖ ነው እኛም በከባድ መከራ ውስጥ ስንሆን መርዝ መጠጣት ፣ ገመድ መፈለግ ሳይሆን ያለብን "አምላኬ አምላኬ " ብለን ወደእሱ ነው መጮህ ያለብን ። በነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ጌታ አምላኬ አምላኬ አለ እንጂ አንዳንዶች እንደሚሉት አምላክ ስላልሆነ ይህንን አላለም። አምላክ ለመሆኑማ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልዕክቱ በግልፅ ቃል አስቀምጦቷል
"#ክርስቶስ_በሥጋ_መጣ_እርሱም_ከሁሉ_በላይ_ሆኖ #ለዘላለም_የተባረከ_አምላክ_ነው_አሜን " ሮሜ 9:5
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተ ነህ ለምን አለ ? ዮሐ 17:3
ሙስሊሞ እና የይሆዋ ምስክሮች የተባሉ ወገኖቻችን ክርስቶስ አምላክ አይደለም ብለው ከሚያቀርቡት ጥቅስ አንዱ ይሄ ነው ። ይህን ምዕራፍ ስንመለከት ጌታችን በዚህች ምድር ላይ በስጋው ወራት ሊሰራ ያቀደውን ጨርሶ ወደ ክብሩ ሊሄድ ሊሰቀል ሲል የተናገረው ቃል ነው ። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እርሱ ከአብ ጋር እኩል በመሆኑም "እኛ አንድ እንደሆንን "በማለት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል ስልጣን እኩል ጌትነት እንዳለው እንረዳለን ። ያላመኑት ግን "እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንክ አንተን የላከውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘለዓለም ሕይወት ናት " ዮሐ 17:3 የሚለውን በመጥቀስ ጌታ አምላክ እንዳልሆነ አብ ብቻ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ አሕዛብ ይናገራሉ። እስኪ በሌላ ስፍራ ላይ የተጠቀሱትን ጥቅሶች እንመልከት ፦
"ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚቻለው ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኀኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ግርማ ኃይልም ስልጣንም ይሁን አሜን " ይላል ይሁዳ 1:25 በዚህ አገላለፅ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ አምላክ እንደሆነ ተገልፇል ። በሌላም ስፍራ ፦ "ስለዚህ እላችዋለው ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል በመንፈስቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን በሚመጣው አይሰረይለትም " ማቴ 12:31 ቀጥሎ ደግሞ እንዲህ ይላል፦
"ብቻህን አምላክ የሆንህ አንተ የላከውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት " ዮሐ 17:3 ታዲያ ሶስቱም ብቸኛ ከተባሉ የቱን እንምረጥ ? ዳሩ ግን ይህ ለምን እንደተባለ ለኛ ለክርስቲያኖች ግልጥ ነው ። ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ እንዳለው ፦ "ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳን የተከደነባቸው ለሚጠፋ ነው " 2ኛ ቆሮ 4:3 ታዲያ ጌታችን ይህን ስለምን ተናገረው ቢሉ የዘላለም ሕይወት የሚገኝባት ሃይማኖት ይህች ናት አንተ የባህርይ አምላክ እንደሆንክ እኔም የባህርይ አምላክ እንደሆንኩ ያውቁ ዘንድ ቢያውቁ እውነተኛ ሃይማኖች ይህቺ ናት ማለቱ ነው ። ጌታ በአንዳንድ ቦታ ላይ አምላክ ወይም እግዚአብሔር ብሎ እንደ ሰው መጸለዩ በእውነት የሰውን ባህርይ ባህሪው ማድረጉን ሊያስረዳን ፈልጎ ነው እንጂ በባሕሪው ከአብ የሚያንስ ሆኖ አይደለም
እንደ ሰው አምላኬ ብሎ ባይፀልይ ኖሮ በእርሱ ዘንድ ሰውነት የለም ወይም መለኮት ተስብእትን(ሰውነትን) ውጦ አጥፍቶታል በተባለም ነበር ። ይህ የጌታችን አነጋገር በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድ #ለአጽድቆተ_ትስብእት ተብሎ ይተረጎማል፡ ስለዚህ እነርሱ እንደሚሉት ሳይሆን ጌታችን ስለዚህ ተናገረው እንጂ አምላክ ስላልሆነ አይደለም ። አምላክ ስለመሆኑማ ዮሐንሰ እንዲህ በማለት ገልጾታል ። "እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው " 1ዮሐ5:20 "የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ ዋህድ ነፍስንና ስጋን ነስቶ ሰው ሆነ ባልንም ጊዜ ስለዚህም ነገር ቢሆን እነዚያ እንደሚያምኑ መቀላቀል የለበትም የቃል ባህርይ የስጋን ባህርይ ወደ መሆን አልተለወጠም ሁለት ባህርይ ያለመለወጥ ባለመቀላቀል ጸንተው ይኖራሉ እንጂ " ሃይማኖተ አበው ዘ ኤራቅሊስ
"የእግዚአብሔር የባህርይ ልጅ ሲሆን ሰው ይባላል ፤ ዳግመኛም የአዳም ልጅ ይባላል ሰማያዊ ሲሆን በፈቃዱ ምድራዊ ሆነ ። በመለኮቱ መከራን መቀበል ሳይኖርበት ሰው በመሆኑ መከራ ተቀበለ ፈጽሞ አንዱ በአንዱ ያደረ ነው አይባልምና ለአንዱ ለእግዚአብሔር ልጅ ሁለት አካል ሁለት ገጽ ሁለት ባሕርይ የለውም " ሃይማኖተ አበው ዘ አትናቴዮስ ስለዚህ ክርስቶስ ፍፁም ሰው የሆነ ፍፁም አምላክ ነው አምላኬ ሲል ብትሰሙት በተዋሀደው ስጋ ነው እንጂ በመለኮቱስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ እኩል ነው
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
"ወደ አባቴና አባታችሁ ወደ አምላኬና አምላካችሁ አላረኩምና አትንኪኝ" ዮሐ 20:17 ለምን አላት ?
ሙስሊም እና ጆቫ ዊትነስ ወንድሞቻችን ክርስቶስ አምላክ አይደለም ብለው ከሚያቀርቧቸወ ጥቅሶች አንዱ ነው ። ጌታችን ይህንን የተናገረው በትንሳኤው እለት ለመግደላዊት ማርያም ነው ይህንን የጌታ አነጋገር በነጠላ ትርጉሙ ለመረዳት ቢሞከር ወደ ስህተት ያደርሳል። አንድን ጥቅስ እየመዘዙ ወደ ስህተት ከመነዳት በፊት ምስጢራዊ ትርጉሙን መረዳት ያስፈልጋል። ለምን አትንኪኝ አላት ? መፍቅሬ ሰብእ(ሰውን ወዳጅ) ኢየሱስ ክርስቶስ መግደላዊት ማርያምን "#አትንኪኝ" ያላት ጠልቷት ወይም ተጸይፎአት አይደለም ይህች ሴት ከሰባት አጋንንት ነፃ ያወጣት እርሱ ነው ሉቃ 8:2 ታዲያ ለምን አትንኪኝ አላት ቢሉ ፦
#1ኛ.ይህን ቃል ጌታ ከትንሳኤው በሁዋላ የተናገረው ሥጋን በመቃብር ትቶት እንዳልመጣ አሁንም የተዋሀደው መሆኑን ያን መዋቲ አካል ማስነሳቱን ለመጠየቅና የዛ የተዋሃደው አካል የስጋ ፈጣሪ እንዳለው ለማጠየቅ ነው ። ለዚህም ነው ቶማስን "ና ዳሰኝ መንፈስ እንደኔ ሥጋና አጥንት የለውም " ያለው ሉቃ 24:39 #አምላኬ ማለቱ የፈጠረውን ሥጋ መዋሃዱን ለማመልከት ነው #አባቴ ማለቱ ደግሞ ለእርሱ የባህርይ አባቱ ነውና ነው ለኛ ደሞ የፀጋ አባታችን ነው
#2ኛ. ሁለተኛው ምክንያት ጌታ ስሟን ጠርቶ ማንነቱን በገለጸላት ጊዜ እና ገና አላረኩም የሚለው ንግግር ስትሰማ የመሰናበቻው ማለትም ከምድር ወደ ሰማይ በሕልውና ወደ ባህርይ አባቱ በልዕልና የሚያርግበት ጊዜ የደረሰ መስሎት በእግሩ ላይ ወድቃ ልትስመው ነበር። ጌታችን ግን የማርግበት ጊዜ ገና አልደረሰምና ለመሰናበት ብለሽ አትንኪኝ ሲላት ነው
#3ኛ. ስርዓተ ካህናትን ሲመሰርትልን ነው ። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈ ምስጢር በተባለው መጽሐፋ እንዲህ ይላል ፦ "መግደላዊት ማርያምን በስርዓተ ምዕመናን አብነት አትንኪኝ ሲላት ሲሆን ለሐዋርያት ግን ተዳሰሰላቸው " ብሏል ማለትም ስልጣነ ክህነት የሌላቸዉ ስጋና ደሙን መፈተት አይችሉም ሲል ነው ። ዳግመኛም ሴቶች ስጋና ደሙን መፈተት እንደማይችሉ ስርዓትን ሲሰራልን ነው ። ለዚህም ማስረጃው ለቶማስ ሲዳሰስለት መግደላዊት ማርያምን ግን አትንኪኝ ማለቱ ነው ። ዮሐ20:26-30 ባጠቃላይ ጌታችን ይህን ጥቅስ በነዚህ ምክንያቶች ተናግሮታል እንጂ አንዳንድ የእምነት ተቋማት እንደሚሉት ለሱ አምላክ ኖሮት (ሎቱ ስብሐት) አይደለም
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
ልጁም ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል ለምን አለ ? 1ኛ ቆሮ 15:24
ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን መልዕክት ለምን እንደፃፈው ከመመልከታችን በፊት እስኪ የሚከተለውን ጥቅስ እንመልከት ፦ "በሚድኑትና በሚጠፋት ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና ለነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለነዚያ ለህይወት ለህይወት የሚሆን የህይወት ሽታ ነን ለዚህም ነገር የሚበቃ ማነው ? የእግዚአብሔርን ቃላት ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎች አይደለንምና በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን " 2ቆሮ 2:9 ታዲያ ይህንን አባባል ማለትም ለምን ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል አለ ሲባል ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጡር ስለሆነ አልያም አምላክ ስላልሆነ አይደለም
ታላቁ የቤተክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "እርሱ ከሁሉ አስቀድሞ የነበረ ነው ሰማያት ሳይዘረጉ፣ የየብስ ፊት ሳይታይ ፣ ተራሮች ሳይቆሙ፣ የአየር ርዝመት ሳይከፈት በባሕርይ የነበረ ነው " እንዳለው እርሱ ከሁሉ በፊት የነበረ አምላክ ነው ። አንድ ሃይማኖት ሃይማኖት አለኝ የሚልና ስለአለበት ሃይማኖት እውቀት አለኝ የሚል ሰው የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በመምዘዝ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ አይደለም እያሉ ከመቃዠቱ በፊት ለምን እንደተነገረ ማወቅ አለበት
ጥቅሱ ከላይ ስለሞት እየተናገረ መምጣቱን እንረዳለን ። የሁዋላ ጠላት የተባለው ሞት ነው ። ሞት ሁሉን ገዝቶአልና ነገር ግን ሁሉን ካስገዛለት ከወልድ(ከክርስቶስ) ሞት እንደሚያንስ ይታወቃልና ከሞት ስልጣን የክርስቶስ ስልጣነ መለኮት ይበልጣልና ። ሞት በሰው ልጆች ላይም እንዲሰለጥን ያደረገው ባለቤቱ ወልድ ነውና ። በዕለተ ምፅአት ሁሉ በተገዛለት ጊዜ (ለሞት) ያን ጊዜ ወልድም ሁሉን ላስገዛለት ለሞት ተገዝቷል ። መቼ ? በዕለተ ዓርብ ። ስለዚህ የዕለተ ዓርብን ሞቱን መናገሩ ነው ። በዕለተ ዓርብ በዘጠኝ ሰዓት ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ስጋው በገዛ ፍቃዱ ለይቷልና ሞት ለ3 መዓልትና ለ3 ለሊት ጌታን በቁጥጥር ስር አድርጎ ነበርና ይህም የጌታ ፍቃድ ስለሆነ እንጂ እንደ ሌሎች ሳይወድ በግድ አይደለም ። ስለዚህ ጥቅሱ #ክርስቶስ_ገዚ_አምላክ_ኖሮት_ይገዛል_ማለት #ሳይሆን_ለሞቱ_የተነገረ_ነው
👉 "ከግርማው የተነሳ የሞት ደጆች ይከፈታሉ የሲኦል በሮችም ባዩት ጊዜ ይደነግጣሉ ከሰማይ በታች ያለውም ስፋቱን ከሰማይ በላይ የሚሆነውንም እርሱ ያውቃል " ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሃይማኖተ አበው
👉 "የአንተን ስም ሰምቶ ሞት ይደንግጥ ቀላያትም ይሰንጠቁ ፣ ጠላትም ይረገጥ የጥፋት መንፈስ ይንቀጥቀጥ ከይሲም ይወገድ ፣ አለማመንም ይራቅ ወንጀለኛም ይቸገር ቁጣ ጸጥ ይበል ቅናት ጥቅም አያግኝ ፣ ኃጢአትን የሚያዘወትር ይገሰጽ ወርቅን የሚወዱ ይነቀሉ ድካም ይወገድ ሐሰተኛ ይጣል ፣ መርዝ ያላቸው የፍጥረቶች ወገን ሁሉ ይበተኑ ። " ቅዳሴ እግዚእ
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
ያችን ሰዓት ልጅም(ወልድም) ቢሆን ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም ለምን አለ ? ማቴ 24:36
ይህንን ጥቅስ በመጥቀስ አምላክ ቢሆን ሁሉን ያውቅ ነበር ይላሉ። በመሰረቱ ቀኒቱንና ሰዓቲቱን እርሱ ባያውቀው ኖሮ ምልክቱን ባልነገራቸው ነበር የተናገራቸው ምልክቶች በሙሉ ማወቁን የሚያሳዩን ናቸው። "ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው " ይላል ሮሜ9:5 ከሁሉ በላይ ከሆነ ደግሞ ማንም ከእርሱ በላይ የለም ። "ያለውና የነበረው ፣ ፊተኛውና መጨረሻው እርሱ ነውና '' ራዕ 1:9 ነገር ግን ይህንን ቃል ለምን ተናገረው ቢሉ ስለ ብዙ ምክንያት ተናግሮታል
#1ኛ.ፍጹም ሥጋ መዋሀዱን ሲያጠይቅ ነው ሥጋ ደግሞ በራሱ እውቀት የለውምና
#2ኛ.ወዲያው የሚመጣበትን ቀን ቢነግራቸው እንዳይደነግጡ ፈልጎ የምነግራችሁ ብዙ አለኝ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም አላቸው
#3ኛ.በኖህ ዘመን የነበሩ ሰዎች 120 ዓመታት የንስሐ ዘመን ቢሰጣቸው 100 ዓመት በልተን ጠጥተን ፣ ጨፍረን ፣ 20 ዓመት ሲቀረን ንስሐ እንገባለን ብለው እርኩሰትን ስለፈፀሙ በመሐል ከሀጢአታቸው የተነሳ በንፍር ውሃ ተጥለቅልቀው ጠፍተዋልና አሁንም በዚህ ዓመት በዚህ ወር እመጣለው ቢላቸው ሰንፈው ንስሐ ሳይገቡ ገና ነው እያሉ እንዳይሞቱ የሚመጣበትን ቀን መች እንደሆነ አልተናገረም " ተዘጋጅታችሁ ኑሩ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ በነቃ ቤቱም ሊቆፍር ባልተወው ነበር ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ የሰው ልጅ በማታስቡበት ጊዜ ይመጣልና"ማቴ 24:43
#4ኛ.ሌላው ጌታ ይህንን ቃል የተናገረው ዓለምንና ጊዜያትን ሁሉ የፈጠረና በሁዋላም ሊያሳልፋቸው የሚችል ፈጣሪ ብቻ ሁሉን የማወቅ ስልጣን እንዳለው ሊገልጽልን አስቦ ነው። ጌታም ከአብ ጋር አንድ ስለሆነና የአብ የሆነው ሁሉ እውቀትም ስልጣንም የእርሱ ስለሆነ ስለዚያች ቀን እርሱም ያውቃል ምክንያቱም ወልድ በመለኮቱ ከአብ ጋር እኩል ነውና (ዘእሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ)
እንግዲህ ክርስቶስ ሁሉን እያወቀ ራሱን ከአብ ለይቶ ያችን ቀን እንደማያውቅ የተናገረበት ምክንያት እርሱ ከአብ ተለይቶ ማለትም ወልድ በተለየ አካሉ ቅድመ ተዋሕዶ የነበረ አላዋቂ ሥጋን እንደተዋሀደ ለማስረዳት ነው ። ይህም ማለት ክርስቶስ ፍጹም ሰው በመሆኑ ለሰው ልጆች ሁሉ ወገናዊነቱን ያመለክተናል ፤ ከእኛ ጋር ያለውን ዝምድና ይገልጽልናል እርሱ ሰው ሆኗልና የሰው ልጅም ተብሏልና ። ክርስቶስ ፍጹም ሰውና ፍጹም አምላክ በመሆኑ በመለኮቱ ከአብ ጋር አንድ ሲሆን በሰውነቱ (ስጋን በመዋሀዱ) ከሰዎች ጋር አንድ ሆኗል ። ከዚህም የተነሳ ክርስቶስ ዳግማዊ አዳም ተብሏል ። ም/ቱም የአዳምን ስጋና ነፍስ ተዋህዷልና
የምድር ስርዓት ይሻራል ፍጥረት ሁሉ አንድ መንጋ ይሆናሉ ፣ በአንድ እረኛ ይሰማራሉ ስለጌታችን መምጣት ከቅዱሳት መጽሐፍት እንደተማርነው ጊዜውንና ሰዓቱን የሚያውቅ ከፍጡር ወገን ከቶ አይገኝም ሆኖም ቅዱሳት መጽሐፍት እንደነገሩን መምጣቱ የማይቀር ነው እስከዛ የድህነት ስራ መስራትና ወንጌልንም ለዓለም መስበክ ያስፈልጋል "እነሆ በቶሎ እመጣለው ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ አልፋና ኦሜጋ ፊተኛውና ሁዋለኛው መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ "ራዕ 22:12
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
አፅናኝ የተባለው ማነው ?
ሙስሊም ወንድሞቻችን ይህንን ጥቅስ ከመፅሐፍ ቅዱስ በመውሰድ አፅናኝ የተባለው ነብይ (ነብዩ መሀመድ) እንጂ መንፈስቅዱስ አይደለም ይላሉ። በመሰረቱ እነሱ አሉ እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ አላለም ። ጌታም ነብይ እልክላቹዋለው አላለም ። ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን ተቀበልን ሁሉን ነገረን አሉ እንጂ ነቢይ ተላከልን አላሉም ። ታዲያ ጌታችን እልክላቹዋለው ያለው ማንን ነው ? ከተባለ ያለ ምንም ጥርጥር እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ነው
ይህንንም መጽሐፍ ቅዱስ በማያሻማ መልኩ በግልጽ አስቀምጦታል የተስፋውም ፍፃሜ እንዲህ ነበር ፦ "በዓለ ሀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉ በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ ተቀምጠውም የነበሩበትን ቤት ሁሉ ሞላው እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጡባቸው በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር "የሐዋ 2:1-4 ታዲያ ከየት መጥቶ ነው መንፈስ ቅዱስ ነቢይ የሚሆነው ? በጭራሽ ነቢይ አይደለም
ያልተባለን ማውራት ላም ካልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደሚሉት አበው ይህንን ትምህርት ሐዋርያትም ፣ ነብያትም፣ ሊቃውንትም አላስተማሩም። መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው መካከል አንዱ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ነበር ። እርሱም ከሐዋርያት ጋር በፆም በፀሎት የተጉ 120ዎቹን ቤተሰብ በመወከል ከተለያየ አገራት በበዓሉ ላይ ለመገኘት ለመጡት ሰዎች ልብን የሚነካ መንፈሳዊ ክፍተትን የሚሞላ ፣ ጥያቄን የሚመልስ ንግግር አደረገላቸው። የንግግሩ ዋና ማዕከል ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን የንግግሩ ርዕስ እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ነበር ። ፈሪና ከሀዲ የነበረው ቅዱስ ጴጥሮስ ታላቅ ድፍረትን ተሞልቶ የመጀመሪያውን የምስራች አወጀ ከዚያም በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት 3000 ሰዎች ያለ ምንም የጦር መሳሪያ ኃይል ወዲያው ለወንጌል ተሸነፋ
የጌታችን የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶክ ፍቅሩ ፣ ሞቱ፣ ትንሳኤው ፣ ለሰው ልጆች ያደረገውን ቤዛነት ሲሰሙ በወንጌል አምነው ተጠመቁ የሐዋ 2:41 ይህ ይላካል የተባለው የአጽናኙ የመንፈስ ቅዱስ ጅማሬ ነበር ። ከዚህም የተነሳ የጥበበኞች ጥበበኛ እግዚአብሔር አሕዛብ ያለ ሐዋርያት ስብከት በሥላሴ ማመን እንደማይችሉ ሐዋርያትም ዳግመኛ ያለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ መስበክ እንደማይቻላቸው ያውቃልና በሰናኦር ሜዳ የተበተኑትን የዓለም ቋንቋዎች በሐዋርያት አንደበት ውስጥ ሰብስቦ ያኖር ዘንድ የጽድቅ መንፈስ ጰራቅሊጦስ ተላከ
መንፈስ ቅዱስ በወረደበት ዕለት የበዓሉ ታዳሚዎች በየራሳቸው ቋንቋ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ከሰሙ በዋላ ደቀ መዛኑርቱን ሰክረው ነው እንጂ ይህ ያልተለመደ ምንድነው ? እያሉ በመደነቅ ማጉረምረም ጀመሩ ። ጴጥሮስም "ለእናንተ እንደመሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም ከቀኑ 3:00 ነውና ነገር ግን በነብዩ ኢዩኤል የተባለው ነው " የሐዋ 2:14 በማለት አስረዳቸው ። ከጠዋቱ 3:00 መጠጥ አይጠጣም ነበርና ከሐዋርያው ከቅዱስ ጴጥሮስ ንግግር የምንረዳው ወይም የምንማረው እንደ መሰለን የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን ከአተረጓጎም ስርዓት ውጪ አጽናኙ መንፈስ ቅዱስን ነብይ ነው ብሎ መገመትና መተርጎም አግባብ አይደለም ። እንደመሰለን መተርጎም አላዋቂነት ነው 1ጴጥ 4:11
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
ወላዲተ አምላክ ስለመሆኗ
ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ መሆኗን እናምናለን ። ይኸውም ወልደ አብ ኢየሱስ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ በሥጋ ወልዳዋለችና ። ለዚህ ማስረጃ የሚሆኑንን ጥቅሶች እንመልከት ምክንያቱም ድንግል ማርያምን እንደ ማህደር ተጠቀመባት እንጂ ወላዲተ አምላክ አትባልም ብለው የሚያምኑ ስላሉ ፦ "እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች " ትን ኢሳ 7:14 ይህ ቃል የሚወለደው ሕፃን አማኑኤል ተብሎ ይጠራል የወለደቺውም ድንግል ናት ካልን ከቃሉ ከፍ ብሎ እንዲህ ይለናል፦
"እርሱም አለ እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ ስሙ በውኑ ሰውን ማድከማችሁ ቀላል ነውን አምላኬ ደግሞ የምታደክሙ ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣቹዋል " ኢሳ 7:13 ይህን ቃል ልናጤነው ይገባል የእስራኤል ቤት ብቻ ሳይሆን አለሙ ሁሉ ለመትረፍ በሰው ድካም አልሆነም ። አሁን ግን አምላክ ሊደክም የኛን መከራ ተሸክሞ ሊያድነን መጣ ። እርሱም #ምልክት ሰጠን #ምልክታችንም ድንግል ማርያም ነች አምላኬን የምታደክሙ ያለው ደግሞ ከድንግል የሚወለደው አምላክ መሆኑን ለማመልከት ነው
እናቱንም ወላዲተ አምላክ ያልናት ለዚህ ነው ። ሌላ ጥቅስ እንይ ፦ "ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል "ኢሳ 9:6 ሕፃን ተወልዶልናል እርሱ ደግሞ ኃያል አምላክ ነው ። ስለዚህ የወለደቺው ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ እንላታለን ። ይኸውም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በ#ተዋህዶ ከብሮ ተወልዷልና ። ሌላም ጥቅስ እንጨምር ፦ "የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል " ሉቃ 1:43 አስተውሉ ስራው የመንፈስ ቅዱስ ነው ኤልሳቤጥ አክስት መሆኗን እንጂ ድንግል ማርያም የጌታ እናት ትሁን አትሁን የምታውቀው ነገር የለም
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ተሞልታ ስለነበር የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆናል ስትል የጠየቀቺው ስለዚ ነው ። መንፈስ ቅዱስን የተሞላ ድንግልን ያውቃታል ፣ ያከብራታል ፣ ያመሰግናታል እርሱ ጌታ ነውና ወላዲተ እግዚዕ እርሷ ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ ያልናት ለዚህ ነው ። ሌላም እንይ ፦ "ቃል ሥጋ ሆነ ፀጋንና ክብርን ተመልቶ በኛ አደረ " ዮሐ 1:14 ያ ቃል ይለናል መጽሐፍ ቅዱስ በዮሐ 1:1 ላይ "ቃል እግዚአብሔር ነው " ስለዚህ የተወለደው የኛን ሥጋ የተዋሀደውን ክርስቶስ ኢየሱስን በሥጋ የወለደቺው ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት ። ሌላ ፦ "ነገር ግን የዘመኑ ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ " ገላ 4:4 ሴቲቱ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ነች
በአጭሩ ፦
👉 እርሱ አምላክ ስለሆነ እርሷም የአምላክ እናት ትባላለች
👉 እርሱ እግዚአብሔር ስለሆነ የእግዚአብሔር እናት ትባላለች
👉 እርሱ ጌታ ስለሆነ እርሷም የጌታ እናት ትባላለች
👉 እርሱ ብርሃን ስለሆነ እርሷም የብርሃን እናት /እመብርሃን/ ትባላለች። ጌታ አምላክ እናቱን ማደሪያው ስላደረጋት ከፈጣሪ በታች በሰማይና በምድር ከከበሩ ሁሉ የከበረች ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን ናት ስለዚህም ትውልድ ሁሉ ብፅዕት እያሏት እያመሰገንዋት ይኖራሉ ስሟንም እየጠሩ በደስታ እየዘለሉ ይዘምራሉ ሉቃ 1:39-55 ልጇ አምላክ ነው እርሷ እናቱም ወላዲተ አምላክ ናት
Comment @kokuha_haymanot_bot
💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
ዮሴፍ ለምን እጮኛዋ ተባለ ?
እጮኛ የሚለው ቃልና ፍቺ ለሚያባት ሴት ብቻ የተሰጠ ሳይሆን በጠባቂነትም ላለ ይሰጣል። መናፍቃን እጮኛዋ የሚለውን ቃል በመያዝ ዮሴፍ ድንግልን እንዳገባትና ከሷም ልጅ እንደወለደ ይናገሩ (እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጣቸው) ነገር ግን እንደዛ አይደለም እስቲ ድንግል ማርያም የዮሴፍ እጮኛ የተባለችበትን ምክንያቶች እንመልከት፦
#1ኛ. የዳዊት ልጅ ተብሎ ይጠራ ዘንድ ነው ። ምክንያቱም በሴት ትውልዱ ቢቆጠር አይሁድ አይቀበሉም ማቴዎስ ትውልዱን የፃፈው በዮሴፍ ነው ። ለዚህም ነው መልዐኩ "ዮሴፍ ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት በአሰበ ጊዜ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ እጮኛህ ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ "ያለው ማቴ1:10 ለባልነት ቢሆን ኖሮ ግን በስውር ሊተዋት ፈጽሞ አያስብም ነበር። እዛው ም 1:16 ላይ ስንሔድ በኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ ውስጥ ተፅፎ የምናገኘው ዮሴፍን እንጂ ማርያምን አይደለም ።
#2ኛ.እንዲጠብቃት ነው ለዚህም ነው መልዐኩ ዮሴፍ ትቷት እንዳይሄድ የተናገረው
#3ኛ.እንዲያገለግላት ነው ። በስደቷ ጊዜ ይዞ እንዲሄድ የታዘዘው ዮሴፍ ነውና ። ለሚስትነት ታጭታ ቢሆን ግን ከወለደች ቡሃላ ለዮሴፍ ሚስትህን ይዘህ ሂድ ይለዋል እንጂ ሕፃኑንና እናቱን ብሎ አይናገረውም ነበር ። እንደውም ከወለደች ቡሃላ ዮሴፍን እጮኛህንም ይዘህ ሂድ ሲለው አንመለከትም ። ለዚህም ነው እንዲያገለግላት በእጮኝነት የተሰጠው ማቴ2:13
#4ኛ.እርሷ ከሰው ዘር ከሰው ወገን መሆኗ ይታወቅ ዘንድ ነው ። መጽሐፍ ቅዱስም "የአብርሃም ዘር ይዞአል "ያለው ለዚ ነው ዕብ 2:15 ምክንያቱም እርሷን ኃይለ አርያማዊት ክርስቶስን መልዐክ ብለው የሚነሱ መናፍቃን አሉና ። በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንዴት ትወልዳለች እንዳይሉ
#5ኛ.በዘፀ 5:23 መሰረት "ሴት ወንድ ካጠገቧ ሳይኖር ፀንሳ ብትገኝ ተወግራ ትገደል " የሚል ሕግ አይሁዳውያን ስላላቸው ተወግራ እንዳትገደል ነው ። እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች እጮኛ አሰኝተዋታል እንጂ እጮኛነቱ ለመገናኘት ለባልና ለሚስት ግንኙነት አይደለም

"የበኩር ልጅዋን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም " ለምን አለ ? ማቴ 1:25
አላወቃትም ማለቱ አዳም ከገነት ከወጡ በሁዋላ ሄዋንን እንዳወቃት አወቃት ማለት ሳይሆን እመቤታችን አምላክ በማህፀንዋ ሳለ የእመቤታች መልኳ ይለዋወጥ ስለነበር በውስጧ ይህ ነው የማይባል ህብር ያለው እና ቀለሙ የሚነገርለት አይደለም እና በውስጧ ያለው እሳተ መለኮት ክርስቶስ እርሱ መልኩን በለወጠ ቁጥር እርሷንም ይለውጥ ነበርና ነው ፤ ለምሳሌ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን በደብረ ታቦር ሲገለጥ ፊቱም ልብሱም አጣቢ ከሚያነፃው በላይ ነጭ ሆነ ። ይህንንም በማህፀንዋ ሊያደርገው ቻለ ምክንያቱም ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና ። ስለዚህ የእመቤታችን ፊትዋ ብርሃን ሲሆንበት ዮሴፍ ይህች ማናት ብሎ ግራ ይገባው ነበር
ስለዚህ እስክትወልድ ድረስ የፊትዋን ብርሃን በማየት አላወቃትም ስትወልድ ግን በማህፀኗ ሆኖ ፊትዋን የሚለውጠው ጌታ ተወልዷልና አወቃት
#1ኛ. በኦሪ.ዘፀ 34:35 - 39 እንደ ተፃፈው ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋግሮ ሲመለስ ፊቱ እንደ ጸሀይ ያበራ ስለነበር አሮንና ህዝቡ ስለፈሩ ፊቱን ይሸፈን እንደ ነበር እናነባለን እንዲሁም ጸጋንና ኃይልን ተመልቶ ሳይፈራ በአይሁድ ሸንጎ ፊት ስለጌታ የመሰከረው ቅዱስ እስጢፋኖስ "በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኩር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት " ተብሎ ተነግሮለታል የሐዋ 6:15 ስለዚህ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት በመቆሙ ፊቱ ካንፀባረቀ ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስም ፊቱ የመልአክን ፊት ከመሰለ ፤ ሁሉን የፈጠረ እግዚአብሔር ወልድን በማህፀኗ የተሸከመች እመቤታችን ከወትሮው ሁኔታ የመልኳ መለወጥ የገጿ መንጸባረቅ ይህም ለዮሴፍ እንግዳ መሆኑ የተገባ ነው
#2ኛ.ጌታ ሲወለድ የተደረገውን ተአምራት ተመልክቶ ማለትም፦
ሀ.ሰብአ ሰገል እጅ መንሻ ወርቅ ፣ ዕጣን ፣ ከርቤ ይዘው በመምጣት ሰግደው መገበራቸውን
ለ.የኮከቡ ሰብአ ሰገልን መርቶ ማምጣት
ሐ.የእግዚአብሔር ክብር በቤተልሔም ዙሪያ ማብራት
መ.የቅዱሳን መላእክት ዝማሬና የቤተልሔም አካባቢ በአእላፍ መላዕክት መሞላት
ሠ.የእረኞች መጎብኘትና ምስክርነት ማቴ2:1-12 ሉቃ 2:5-14
#3ኛ.እንደ መናፍቃኑ አተረጓጎም #አላወቃትም የሚለውን ቃል በቀጥታ እንኳን ብንመለከተው " እስክትወልድ ድረስ " ማለቱ ከወለደች በሁዋላ አወቃት ብሎ ለመደምደም አይቻልም ። ምክንያቱም በዕብራይክጡ #እስከ ወሰን ድንበር የሌለው ፈጽሞ ከቶ ማለት ይሆናልና ። ለዚህም ማስረጃ እንይ ፦
ሀ."የሳኦል ልጅ ሜልኮል እስከሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም " 2ኛሳሙ 5:23 ይላል ። ታዲያ ይህ ሜልኮል ፈፅሞ አልወለደችም ማለት እንጂ ከሞተች ቡሃላ በመቃብር ወለደች ማለት አይደለም
ለ.ቅዱሳን ሐዋርያትን "እኔ እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ " ማቴ 23:19 ብሏቸዋል ይህ ማለት ከዚያ ቡሃላ ይለያቸዋል ማለት አይደለምና እመቤታችንም "የበኩር ልጅዋን #እስከምትወልድ ድረስ አላወቃትም " ማለት ፈፅሞ በእደ ዮሴፍ አልተዳሰሰችም ለዘለዓለም ድንግል ናት እርሷም ወንድ ሳላውቅ እንዴት ይሆንልኛል እንዳለች ወንድ አታውቅም ማለት ነው

Forwarded from ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
የቤተክርስቲያን ንዋየተ ቅድሣት እና ትርጉማቸው
#ለማያውቁ የማሳወቅ ግዴታዎን ይወጡ❗❗❗
#ሌሎች_እንዲያነቡትና_እንድማሩበት_አስተማሪ_ሆኖ_ካገኛችሁ_ሼር_ያድርጉ
#ታቦት
🔹ታቦት ማለት እግዚአብሔር አስርቱ ትዕዛዛትን በእጁ ፅፎ ያስቀመጠበትና ለሙሴ የሰጠው ቅዱስ ንዋይ ነው
🔸በቤተክርስቲያንም ፃህሉን እና ፅዋውን በዚህ ላይ በማስቀመጥ መስዋዕቱን እናከብርበታለን
🔹ይህም ማለት ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ የሚዘጋጀው በዚህ ላይ ነው
መስቀል
🔸ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶ በቀራንዩ የተሰቀለበት ሰይጣን ድል የተነሳበት የመዳናችን አርማ ነው
🔹መስቀል ምዕመናንን እና ንዋየ ቅዱሣትን ለመባረክ ያገለግላል፤ የተለያዩ የመስቀል አይነቶች አሉ። ከእነዚህም መካከል
የእጅ መስቀል
🔹ይህ የክህነት ማዕረግ ያላቸው አባቶች ብቻ የሚይዙት ሲሆን ምዕመናንን ለመባረክ ይጠቀሙበታል
የመፆር መስቀል
🔸ይህ ዲያቆናት በቅዳሴ ጊዜ የሚሠብኩበት ሲሆን በመጠኑም ከፍ ያለ ነው
መብራት
🔹መቅረዝ የሻማ ማብሪያ ነው፤ ቀንዲል ደግሞ ሻማ ወይም የዘይት መብራት ነው
🔸የመቅረዙ አገልግሎት ለሻማ ማብሪያነት ሲሆን ቀንዲሉ ደግሞ ቅዱሣት መፃህፍት፣ መልዕክታት፣ ወንጌል ሲነበቡ ይበራሉ
አልባሳት
🔹በቤተክርስቲያን የአገልግሎት ልብስ እንደ ግለሠቡ የስልጣን ሁኔታ ይለያያል፤ የመነኮሣት ልብስ፣ ከካህናት ልብስ የካህናትና ዲያቆናት ይለያል
👉የጳጳሳት ልብስ፣
👉የመነኮሳት ልብስ፣
👉የካህናት ልብስ፣
👉የዲያቆናት ልብስ
🔺ቀሚስ 🔺ቀሚስ
🔺ካባ ላንቃ 🔺ለምድ
🔺ሞጣህት 🔺ድግድጋት
🔺ቆብ 🔺ስአክሊል
ማኅፈድ
🔹የጨርቅ መሸፈኛ ነው፤ ታቦቱን እና ጻህሉን ለመሸፈን ያገለግላል
🔸ከምስራቅ ወደ ምዕራብ፤ ከሰሜን ወደ ደቡብ፤ ከመስዕ/ ከሰሜን ምሥራቅ /ወደ አዜብ /ደቡብ ምዕራብ/ ሆኖ ይለበሳል
መንጦላዕት
🔹በሶስቱም የመቅደስ በር የሚጋረዱ መጋረጃዎች ናቸው፤ ቀለማቸውም ቀይ ነው
መጎናፀፊያ
🔸ይህ በቅዳሴ ጊዜ መንበሩ (መሠዊያው) የሚለብሰው ሲሆን፤ ታቦት በሚወጣበት ጊዜ የሚጎናፀፈው ነው
መንበር
🔹የጽላቱ (የታቦቱ) መቀመጫ ዙፋን ነው፤ ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙ የሚዘጋጀውም በዚህ ላይ ሆኖ ነው
🔸ካህን ያልሆነ ሠው መንበሩን መንካት የማይችል ሲሆን መንበሩ እና ታቦቱ ወዳለበት ክፍል (መቅደስ) መግባት የሚችሉት ዲያቆናት፣ ካህናት፣ ኤጲስ ቆጳሳት ጳጳሳት ናቸው
ጻህል
🔹የቅዱስ ሥጋው ማስቀመጫና ማክበሪያ ነው፤ ከወርቅና ከብር፣ ከነሀስና ከብረት የሚሠራ
ሲሆን የተለየ ቅርፅና የተለየም ምልክት ያለው ነው
ፅዋ
🔸የክርስቶስ ክቡር ደም የሚቀርብበት ነው፤ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከመዳብ፣ ከነሀስ፣ ከብረት
የሚሠራ ነው
ዕርፈ መስቀል
🔹ማንኪያ ዓይነት ሆኖ ጫፉ ላይ መስቀል ያለው ነው
🔸ፅዋው ከተሠራበት ቁስ የሚሠራ ሲሆን አገልግሎቱም የክርስቶስን አማናዊ ደም ለመቀበል የሚያገለግል ነው
ዐውድ
🔸በድርገት ጊዜ ጻህል የሚቀመጥበት ሰፋ ያለ ጻህል ነው፤ ሥጋው እንዳይነጥብ መጠበቂያ ነው፤ የሚሠራው ከብረት፣ ከነሀስ፣ ከእንጨት ነው
አጎበር
🔹በዐውድ ላይ የሚደፋ አራት ማዕዘን ሦስት እግር ያለው እንጨት ወይም ብረት ሊሆን ይችላል፤ ይህም ቅዱስ ሥጋውን ልብሱ እንዳይነካው ከፍ አድርጎ የሚይዝ ነው
ጽንሃ
🔸የዕጣን ማሣረጊያ ነው፡፡ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከብረት፣ ይሠራል፤ ይህን ንዋይ ምዕመናን መጠቀም (መንካት) አይገባቸውም
🔹ዲያቆናት ይይዙታል ይነኩታል ነገር ግን ካህናት የሚይዙበት ቦታ ላይ መያዝ አይችሉም (አያጥኑም)
መሶበ ወርቅ
🔹የአነስተኛ መሶብ ቅርፅ አለው፤ አገልግሎቱም ቅዱስ ቁርባኑን ከቤተልሄም ወደ ቤተ-መቅደስ ለማምጣት ነው፤ በሚመጣበት ጊዜም በመጎናፀፊያ ተሸፍኖ ነው
ሙዳይ
🔸ለማዕጠንት አገልግሎት የሚያስፈልግ ዕጣን የሚቀመጥበት ነው
ቃጭል
🔹በቅዳሴ ጊዜ የሚቃጨልና ድምፅ የሚሠጥ ነው፤ በቅዳሴ ጊዜ አራት ጊዜ ቃጭል ይደወላል
👉ቅዳሴ ሲገባ
👉ፃኡ ንዑሰ ክርስቲያን ሲባል
👉በእግዚኦታ ጊዜ
👉ድርገት በሚወርድበት ጊዜ
ጥላ
🔸ይህ ከተለመደው ጥላ የሚለየው የተለያየ አንፀባራቂ ቀለም ባላቸው ጨርቆች መሠራቱ ነው
🔹አገልግሎቱ በቅዳሴ ጊዜ ምስባክ ሲሰበክ እና ወንጌል ሲነበብ ይዘረጋል
🔹ንግስ በሚሆንበት እለትም ከፊት እና ከኋላ በታቦቱ ዙሪያ ይዘረጋል
ድባብ
🔹በመጠኑ ከጥላ ሠፋ ያለ ሲሆን በንግስ በዓላት ቀን በታቦቱ ላይ ይዘረጋል፤ ይዞ በታቦቱ አጠገብ መቆም የሚችለው ካህን ብቻ ነው
ከበሮ
🔸ከበሮ ከእንጨት እና ከበሬ ቆዳ ተሠርቶ በጨርቅ የሚሸፈን ከፍተኛ ድምፅ የሚሠጥ መሣሪያ ነው፤ ይሁንና ከነሃስ እና ከብርም ተሠርቶ ቆዳው ሊወጠር ይችላል
🔹ሁለት ጎኖች ሲኖሩት በእነዚህ ሁለት ጎኖች የሚወጣው ድምፅ የተለያየ ነው፤ አገልግሎቱም በማህሌት ጊዜ ለመዝሙር ማጀቢያነት ነው
ፅናፅል
🔸ከነሃስ ወይም ከብር ሊሠራ ይችላል፤ ድምፅ የሚሠጡት በውስጡ ያሉት 5 ወይም 7 የሚሆኑ የነሀስ ወይም የብር ቁርጥራጮች ናቸው
🔹አገልግሎቱም በእጅ ተይዞ ወደ ላይ እና ወደታች በማወዛወዝ መዝሙሩን ማጀብ ነው
መቋሚያ
🔹ከእንጨት ከነሀስ ከብር ይሰራል
🔸አገልግሎቱም በመዝሙር ጊዜ በትከሻ በመሸከም ወይም በእጅ በማወዛወዝ መዝሙሩን ይጅባል፤ ለመደገፊያነትም ያገለግላል
🔗 @Z_TEWODROS

The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 27 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.
The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 7 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.