Konso Zone gov't communication affairs dep't (ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚንከሽን ጉዳዮች መምሪያ)
1.12K subscribers
6.29K photos
40 videos
4 files
1.13K links
Communication is the bridge between people and Government !
www.konsozone.org
https://t.me/KonsoZone
Download Telegram
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የጋራ የሠላም እና አንድነት በሚጠናከርበት እሳቤ ዙሪያ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ የጋራ መድረክ አካሄዱ፣

‎የኮንሶ፣ የኧሌ እና የጋርዱላ ዞኖች የፊት አመራሮች እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የጋራ ሠላምና አንድነት በሚጠበቅባቸው ጉዳዮች ላይ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ የሶስትዮሽ የምክክር መድረክ አካሂደዋል፣

‎በምክክሩ ላይ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር-ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ የተከበሩ አቶ አዳማ ትንጳዬ ህዝባችን ከተቀናጀ በጣም ከፍተኛ ውጤት ማምጣት የሚችል ህዝብ ነው ሲሉ ገልጸው፤ ለዚህም ለጋራ ለውጥ የሚሆንን ብልሃት በመፍጠር፣ እንደዚሁም እንደ ምሁርና እንደ አመራር ከመቼውም ጊዜ በላይ ቆርጦ በመነሳት ለህዝብ አንድነት መስራት ይጠበቅብናል፤ የተለያዩ ኮሚቴዎችን በማቋቋምም የተጠናከረ ስራ መስራት ይገባናል ብለዋል።

‎የተከበሩ አቶ አዳማ ትንጳዬ እና የክልሉ ረዳት የመንግስት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ኢንጂነር ፍሬዘር ኮርባይዶ በጋራ ባደረጉት ንግግር የሦስቱን ዞኖች ህዝቦች በማቀራረብና ዘላቂ ጉርብትናን በማጠናከር፣ ብሎም አመራሩ ወጥ የሆነ አስተሳሰብ በመያዝ የህዝቡን አንድነት እና የቀድሞ ቤተሰባዊነት ማደስ ይጠበቅበታል ብለዋል።

‎ኢንጂነር ፍሬዘር ኮርባይዶ በበኩላቸው የየመዋቅሩ አመራሮች እና ምሁራን ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ያካተተ ተከታታይ ውይይቶችን በማካሄድና ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜደዎችን በመጠቀም ህዝባዊ ትስስሮችን ለልማት መጠቀም ይኖርባቸዋል ብለዋል።

‎የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን፣ ስፖርታዊ ውድድሮችን እና የባህል ልውውጦችን እንደዚሁም ህዝብን የሚያሰባስቡና SEEMORE https://web.facebook.com/share/p/1BFFrJHTvC/
3
“አመራር ችግርን ወደ እድል መቀየር አለበት” – ኮሚሽነር ሐልገዮ ጂሎ

በኮንሶ ዞን አመራሮች በዓለምና በሀገር የተፈጠሩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር አካሄዱ።

በውይይቱ የነዳጅ እጥረት፣ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እና የአካባቢ ተፅዕኖዎች ተነሱ፤ እርምጃ መውሰድ እንዳስፈለገ ተጠቁመዋል።

አመራሮች ፈተናን ወደ እድል በመቀየር እና በአንድነት በመስራት መፍትሔ ማምጣት እንዳስፈለገ አጠናክረዋል።

ለበለጠ መረጃ :- https://www.facebook.com/share/1Eg12viCnU/
3
#THE_ICON በኮንሶ ዞን ለአሽከርካሪዎች የደህንነት ሥልጠና ተሰጠ።

የትራንስፖርት መምሪያ “Safety First” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው ሥልጠና አሽከርካሪዎች የታሪፍ ህግ መከበር፣ ፍጥነት መቆጣጠርና አደጋ መከላከል ላይ እንዲተኩሩ አሳስቧል።

በዞኑ በ9 ወራት 20 አደጋዎች ተከስተው 8 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ ሥልጠና ተሳታፊዎችም የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

ለበለጠ :- https://www.facebook.com/100069055695172/posts/1276259868019191/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
🤯1
በኮንሶና ቦረና ዞኖች መካከል ያለው ታሪካዊ ትስስር በቀጣይነት በማጠናከር በሰላም፣ በልማትና በኢኮኖሚ ዘርፎች የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ተገለጸ።

የኮንሶና የቦረና ዞኖች አመራሮች በጋራ በልማትና በሰላም ጉዳዮች ላይ ተስማምተው የህዝቦች አንድነት ማጠናከርና ሰላማዊ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ገለጹ።

Read More:
https://www.facebook.com/share/1B7x5HXajR/

https://www.facebook.com/share/1CmwyMcbqt/

በትክቶክ ይመልከቱ https://vt.tiktok.com/ZS9HBddpQ/
1🔥1
#THE_ICON ምስክርነት በብልጽግና ተግባር ላይ

“በአይኔ ባየሁትና በተጨባጭ በታዘብኩት ልክ፣ ብልጽግና በአዲስ አበባ ከተማ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሌሎች መንግሥታት ለ27 ዓመታት ማከናወን ያልቻሉትን ስራዎች አከናውኗል።

ቢያንስ በቀጣይ 20 ዓመታት የማይሰሩ የልማት ስራዎች መሰራታቸውን እያየሁ፣ በአዲስ አበባ የተጀመረው ልማት ወደ ሌሎች ከተሞችም እንዲስፋፋ እያልኩ የእኔ ምርጫ ብልጽግና ነው።

ብልጽግና በሰባት ዓመታት ውስጥ የሰራቸው ስራዎች በርካታ ናቸው፤ ወደፊት ደግሞ ምን እንደሚሰራ በጉጉት እጠብቃለሁ።

በዞናችንም ቢሆን ለዘመናት የነበሩ የህዝብ ጥያቄዎች እየተመለሱ ይገኛሉ፤ ለአብነት የኮንሶ–ሰገን መንገድ ጥገና ስራ ማንሳት ይቻላል።

“ትላንት ስንገዛ የነበርን ህዝብ፣ ዛሬ እኩልነትን ያገኘ ህዝብ ሆነናል፤ ይህንን ጉዞ ማስቀጠል አለብን” ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

#ኮንሶ #ካራት
#THE_ICON "ፓርቲያችን ብልጽግና የህዝባችንን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ አበክሮ እየሰራ ይገኛል። ሰው ተኮር የሆነውን የብልጽግና እሳቤ በመላበስ የተጀመሩ ተግባራትን በጋራና በትብብር የምንሰራቸውን ስራዎች አጠናክረን በማስቀጠል የህዝባችንን ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን"

አቶ ገለቦ ጎልቶሞ
የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ