KOKEBE TSIBAH GENERAL SECONDARY SCHOOL GRADE 12 D/T EXAM QUESTIONS
908 subscribers
207 photos
3 videos
140 files
165 links
Download Telegram
ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ
ለግንዛቤ እና ጥንቃቄ ይረዳ ዘንድ

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተሻሻሉ የቅጣት እርከኖችን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ከተማን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ፣ጽዱና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የአረንጓዴ ስፍራዎች ፣ፓርኮች መንገዶች እና የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡

ይህንን ተከትሎ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትና የልማቶቹን ዘላቂነት ለማስቀጥል ያግዛሉ የተባሉ አዳዲስ ደንቦች ይፋ ተደርገዋል፡፡

ደንቦችን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በጽዳትና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራት ዙሪያ ቀድሞ ሲጠቀምበት በነበረው ደንብ ቁጥር 150/2015 ላይ የነበረውን የቅጣት እርከኖቹን በማሻሻል ወደ ተግባር መግባቱን ተናግረዋል።

የቅጣት እርከኖቹን ለህብረተሰቡ ዝርዝር መረጃ በመስጠት በመረጃ እጦት ለቅጣት እንዳይዳረግ ግንዛቤ መፍጠር ይገባል ብለዋል።

በዚህም ከ2ሺ ብር እስከ 100ሺህ ብር የቅጣት እርከኖች በግለሰቦችና በተቋማት ላይ መጣሉን ተናግረዋል።

በዚህም መሠረት :-

*ማንኛውም ሰው ያመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በግቢው ውስጥ በአግባቡ አለመያዝ፤በዓይነት አለመለየት፤ ማዝረክረክ፤ ለጤናና የአካባቢ ገጽታ በሚጎዳ መልኩ ማከማቸት፤ ለግለሰብ 2 ሺህ ብር ለድርጅት 50 ሺህ ብር

*ማንኛውም የጽዳት አገልግሎት ሰጭ ድርጅት/ማህበር ደረቅ ቆሻሻ ሲሰበስብ ገጽታ ካበላሸ 25 ሺህ ብር

*በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ለደንበኛው ተገቢውን አገልግሎት ካልሰጠ 50 ሺ ብር

*ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እውቅና ውጭ የአገልግሎት ክፍያ ከደንበኛው ከተቀበለ  50 ሺ ብር

*ጊዜያዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስቀመጫ ቦታዎችን እስከ 5 ሜትር ዙሪያ ድረስ ጽዱ ካላደረገ 50 ሺ ብር 

* ማንኛውም በመንገድ የሚንቀሳቀስ ሰው የሲጋራ ቁርጥራጭ፣ የሶፍት ወረቀት፣ ፌስታል፣ የጫት ገለባ፣ የፍራፍሬ ተረፈ-ምርቶች፣የትራንስፖርት ቲኬት፣የሞባይል ካርዶችን፣ የማስቲካና ከረሜላ ሽፋኖች፣ የመሳሰሉት ጥቃቅን ደረቅ ቆሻሻን ባልተፈቀደ ቦታ ወይም በፓርኮች፣ በአረንጓዴ ቦታ፣ በኮሪደር ከጣለ 2 ሺ ብር

*ከመኖሪያ ቤት ወይም ከድርጅት ግቢ ውጭ ያለውን የአካባቢ ንጹህና አረንጓዴ አድርጎ አለመጠበቅ ከመኖሪያ ቤት አጥር ግቢ ውጭ እስከ 5 ሜትር ርቀት አለማጽዳት፤20 ሺ ብር

*ከድርጅት/ተቋም አጥር ግቢ ውጭ እስከ 10 ሜትር አለማጽዳት፤ 100 ሺ ብር

*ወቅታዊና ልዩ ዝግጅት አከናውኖ በዓሉ ሲጠናቀቅ በዕለቱና ወዲያው ዝግጅቱ የተከናወነበትን አካባቢ ከቆሻሻ ያላጸዳ የፕሮግራሙ አዘጋጅ፤ 50 ሺ ብር

*ዓመታዊ፤ ወርሃዊና ሳምንታዊ የእምነት በዓላት ሲከናወኑ ዝግጅቱ ሲጠናቀቅ የዝግጅቱ ባለቤት በዕለቱና ወዲያው አካባቢውን ካላጸዳ፤20 ሺ ብር የሚቀጡ መሆኑም ተመላክቷል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
በመሬት መሸራተት ለተጎዱ ወገኖቻችን የአቅማችሁን ድጋፍ ማድረግ ለምትሹ
Forwarded from Maf Digital
Grade 11 books (habesha_store).apk
166.1 MB
የ 11ኛ ክፍል ተማሪ ከሆናችሁ ይህ books መልሱን ያመጣላችኃል ይጠቅማችኃል ተጠቀሙት
Grade 10 books (habesha_store).apk
110.9 MB
የ 10ኛ ክፍል ተማሪ ከሆናችሁ ይህ books መልሱን ያመጣላችኃል ይጠቅማችኃል ተጠቀሙት
Grade 12 books (habesha_store).apk
148.1 MB
የ 12ኛ ክፍል ተማሪ ከሆናችሁ ይህ books መልሱን ያመጣላችኃል ይጠቅማችኃል ተጠቀሙት
Grade 9 books (habesha_store).apk
126.4 MB
የ 9ኛ ክፍል ተማሪ ከሆናችሁ ይህ books መልሱን ያመጣላችኃል ይጠቅማችኃል ተጠቀሙት
ቀን 27/11/2016 ዓ.ም
                 ማስታወቂያ
በ2016  , 12ኛ ክፍል ለነበራችሁ ተማሪዎች በሙሉ
ጉዳዩ:-  የመፅሐፍት መመለሻ ቀን ስለማሳወቅ
1 .የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ረቡዕ ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 ሰዓት -6:00 ሰዓት  ከሰዓት ከ7:30ሰዓት -10:30 ሰዓት ይሆናል::
2 .የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሐሙስ ነሐሴ  02/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30ሰዓት -6:00 ሰዓት
ከሰዓት  7:30ሰዓት-10:30 ሰዓት ይሆናል::
   ማሳሰቢያ :-
1,መፅሀፍቱን ይዛችሁ ስትመጡ በጋራ   የወሰዳችሁ  አንድ ሰው የሁሉንም መመለስ  ይችላል።
2, መፅሐፍቱ ስለሚፈለግ በዕለቱ  ፕሮግራም ያልመለሰ ተማሪ  ዉጤቱ ተይዞ በቅጣት  የሚመልስ/የምትመልስ ይሆናል::
3, 12ኛ ክፍል ስትገለገሉበት የነበረዉ  የትምህርት ቤቱ መታወቂያ በዕለቱ ይመለሳል::
                        /ቤቱ
ከሌላ የክፍል ደረጃ የተወሰደም መፅሐፍት ካለ በዕለቱ አብሮ ይመለሳል:: የጠፋበት ተማሪ ካለ መፅሐፍቱ አዲስ እና ገና አንድ ዓመት እንኳ ያገለገለ ባለመሆኑ በምን ምክንያት እንደጠፋ ከታወቀ በሗላ የት/ቤቱ ማኔጅመንት የወሰነዉን የገንዘብ መጠን ይከፈላል ወይም መፅሐፍቱን ገዝቶ/ገዝታ እንዲመልስ/እንድትመልስ ይደረጋል::
የሌላ ክፍል ደረጃ ማለት 12ኛ ክፍል ሆኖ ለማጥናት የ9ኛ:10ኛ እና 11ኛ ክፍል መፅሐፍት የወሰደ ማለት ነዉ::
ቀን 06/12/2016 ዓ.ም
          ማስታወቂያ
ለ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል  ተማሪዎች በሙሉ
ጉዳዩ:- የመፅሐፍት እና መታወቂ መዉሰጃ ቀን ስለማሳወቅ

👉 ከነሐሴ 8-10/2016 ዓ.ም ማለትም ከረቡዕ አስከ ዓርብ ባሉት 3 ተከታታይ የስራ ቀናት መፅሐፍት እና መታወቂያ ስለሚሰጥ አንድ(1) 3በ4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ በመያዝ መጥታችሁ እንድትወስዱ ስንል እየገለፅን የመዉሰጃ ሰዓት በተመለከተ ጠዋት ከ2:30 ሰዓት አስከ 6:30 ሰዓት ሲሆን ከሰዓት 7:30 ሰዓት -10:00 ሰዓት መሆኑን እናሳዉቃለን::
ማሳሰበያ:- 1,መፅሐፍትም ሆነ መታወቂያ በዉክልና ስለማይሰጥ እራሱ ተማሪዉ በአካል ቀርቦ መዉሰድ ይጠበቅበታል::
2, በወጣለት ፕሮግራም መጥቶ ያልወሰደ ተማሪን በሌላ ቀን የማናስተናግድ መሆኑን እናስገነዝባለን::
                     /ቤቱ
ቀን 06/12/2016 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለአዲስ ገቢ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች
👉 በኮከበ ፅባህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተመደባችሁ ተማሪዎች የሚኒስትሪ ዉጤት መግለጫ ካርድ እስኪመጣላችሁ በትዕግስት እን ድትጠብቁን እየገለፅን ዉጤታችሁ በደረሰን ቀን የምንመዘግባችሁ መሆኑን እንገልፃለን::
👉 በተጨማሪም የክፍልና ሴክሽን ድልድላችሁን ስለጨረስን ምዝገባችሁን የምናከናዉን በተመደባችህበት ክፍልና ሴክሽን መሆኑን እንገልፃለን
ት/ቤቱ
ቀን 8/12/2016 ዓ.ም
           አስደሳች መረጃ!!
ለት/ቤቱ ማህበረሰብ በሙሉ
ጉዳዩ
:- በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ላይ እንድትገኙ ጥሪ ስለማቅረብ
ነገ ሐሙስ ነሐሴ 9/2016 ዓ.ም ከየካ ክ/ከተማ አስተዳደር የተሰጡነን 10,000/አስር /የፍራፍሬ  ችግኞች  ለመትከል ፕሮግራም ይዘናል::
👉 በመሆኑም መምህራን:የአስተዳደር ሰራተኞች: ወላጆች : ተማሪዎች/የቀድሞ ተማሪዎች ጨምሮ/  : የአካባቢዉ የሰላም ሰራዊት: የአካባቢዉ የእድር አመራሮች : የትምህርት ቤቱን ሜዳ ስትጠቀሙ የነበራችሁ የጤና ስፓርት ቡድን  እና የታዳጊ ስፓርት ቡድን አባላት ሁላችሁም 1:00 ሰዓት ት/ቤት በመገኘት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ -ግብሩ ተሳታፊ እንድትሆኑ ስንል ጥሪያችን እናቀርባለን::
👉 በምትወዱት እና በምታከብሩት ት/ቤት ስም አሻራ ማስቀመጥ የማይገኝ ዕድል በመሆኑ በተለይ ተማሪዎቻችን ይህ መልካም አጋጣሚ ሊያመልጣችሁ አይገባም::
👉  የፍራፍሬ ችግኞችን ትምህርት ቤቱ ተከባክቦ ይይዛል በማለት እምነት ጥላችሁ ለሰጣችሁን የየካ ክፍለ ከተማ  ጉዳዩ ለሚመለከታችሁ ተቋማት አመራሮች እና ባለሙያዎች  በሙሉ ምስጋና እናቀርባለን::
                           /ቤቱ
ቀን 8/12/2016 ዓ.ም
                       ማስታወቂያ
   ጉዳዩ :- የስብሰባ ጥሪን ይመለከታል
የት/ቤቱ ማኔጅመንት ከ2014 ዓ.ም ግንቦት ወር ጀምሮ ተበታትሎ ለየራሱ ይቀሳቀስ የነበረዉ የት/ቤቱ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት ወደ አንድ እንዲመጣ በተደጋጋሚ በተናጠል እና በጋራ በማግኘት ዉይይት ሲያደርግ የነበረ መሆኑ ይታወቃል:: በመሆኑም በ2015 ዓ.ም የጋራ ስምምነት በመድረስ አንድ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት እንዲመሠረት ተደርጓል::
በዕለቱ በተደረገ ጉባኤም ዋና እና ምክትል አስተባባሪ በድምሩ 9 አባላት ያሉት የስራ አመራር ኮሚቴ ከነባሩ እና ከአዲሱ የተዉጣጣ ተመርጧል:: ከዚህ በተጨማሪም የማህበሩ የበላይ ጠባቂዎች ተመድበዉ ነበር:: ይሁን እንጅ ምክንያቱ በግልፅ ባልታወቀ ሁኔታ አንድም ቀን ኮሚቴዉ የጋራ ስብሰባ ሳያደርግ እና ጠቅላላ ጉባኤ ሳይጠራ ድፍን ሁለት የበጀት ዓመት አስቆጥሯል:: በመሆኑም ይህ አይነቱ ተናጠላዊ እና ግልፅነት የጎደለዉ አካሄድ ትምህርት ቤቱ አንጋፋ እና ቀደምት እንደመሆኑ መጠን ከቀድሞ ተማሪዎች ማግኘት ያለበትን ድጋፍ በሚፈለገዉ ልክ እንዳያገኝ አድርጎታል:: አሠራሩም ወጥነት እና ግልፅነት  የሌለዉ በመሆኑ ለተለያዩ ህገወጥ አሠራሮች በር ከፋች ሆኗል:: በመሆኑም የትምህርት ቤቱ ማኔጅመንት በጉባኤ የተመረጠዉ እና በእነ አቶ ያኪን ሃይለማሪያም የሚመራዉን ኮሚቴ ነሐሴ 12/12/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት አግኝቶ በጉዳዩ ዙሪያ ለመወያየት ፕሮግራም ይዟል:: ስለሆነም በተጠቀሰዉ ቀን እና ሰዓት ሁላችሁም በስራ አመራርነት የተመረጣችሁ የኮሚቴ አባላት እንድትገኙ ስንል ጥሪያችን እያቀረብን በዕለቱ በተገኙት የኮሚቴ አባላት መቼ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ሪፓርት እንደሚቀርብ እና የስራ አመራር ለዉጥ እንደሚደረግ የምንወሰን መሆኑን በጥብቅ እናሳዉቃለን::
ማሳሰቢያ:- በአገር ዉስጥ እና በዉጭ ለምትገኙ የቀድሞ ተማሪዎች በሙሉ   አንድ ህጋዊ እና ወጥ የሆነ ማህበር መስረተን እስክንገልፃላችሁ ድረስ በተናጠል ለሚቀርብ የድጋፍ ጥያቄ ምላሽ ባለመስጠት ትብብር እንድታደርጉ ሲል የት/ቤቱ ማኔጅመንት  በክብሮት ጥሪዉን አቅርቧል::
👉 ጉዳዩ ያገባኛል የምትሉ ለምታዉቋቸዉ መረጃዉን በማጋራት ትብብር እንድታደርጉ ስንል በትህትና እንጠይቃለን::
                                /ቤቱ
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥ የሆነ የአካዳሚክ ካላንደር መተግባር እንደሚጀምር ተሰምቷል።

በትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተፃፈ ደብዳቤ ተመልክተናል።

ደብዳቤው ከትምህርት ሚኒስቴር የወጣ እና ትክክለኛ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ደብዳቤው ከደረሳቸው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አረጋግጧል።

ደብዳቤው ከ2017 ትምህርት ዘመን ጀምሮ ወጥ የሆነ የአካዳሚክ ካላንደር በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መተግባር እንደሚጀምር ይገልፃል።

በዚህም፦

- የ1ኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ፦ መስከረም 7 እና 8/2017 ዓ.ም

- የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሁሉም መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ፦ መስከረም 9 እና 10/2017 ዓ.ም

- የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሁሉም መርሐግብር የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት መስከረም 13/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

የ2017 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 18 እስከ ሰኔ 27 ድረስ ይሰጣል።

(ሙሉው የ2017 ትምህርት ዘመን የአካዳሚክ ካላንደር ከላይ ተያይዟል።)

ምንጭ ➡️ @tikvahuniversity
ቀን 10/12/2016 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለ2017 ዓ.ም የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ
ጉዳዩ:- የመፅሐፍት እና መታወቂ መዉሰጃ ቀን ስለማሳወቅ

👉 ነሐሴ 13 እና 14/2016 ዓ.ም ማለትም ሰኞ እና ማክሰኞ ብቻ የተደለደላችሁበትን ክፍል በማወቅ መፅሐፍት እና መታወቂያ የምትወስዱበት ስለሆነ አንድ(1) 3በ4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ በመያዝ መጥታችሁ እንድትወስዱ ስንል እየገለፅን የመዉሰጃ ሰዓት በተመለከተ ጠዋት ከ2:30 ሰዓት አስከ 6:30 ሰዓት ሲሆን ከሰዓት 7:30 ሰዓት -10:00 ሰዓት መሆኑን እናሳዉቃለን::
ማሳሰበያ:- 1,መፅሐፍትም ሆነ መታወቂያ በዉክልና ስለማይሰጥ እራሱ ተማሪዉ በአካል ቀርቦ መዉሰድ ይጠበቅበታል::
2, በወጣለት ፕሮግራም መጥቶ ያልወሰደ ተማሪን በሌላ ቀን የማናስተናግድ መሆኑን እናስገነዝባለን::
ት/ቤቱ
ቀን 15/12/2016 ዓ.ም
ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ
እንድትሳተፉ ስለመጋበዝ
👌 ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ያለ መሆኑ ይታወቃል:: በመሆኑም ትምህርት ቤታችን እስካሁን በርካታ ለምግብነት እና ለዉበት የሚሆኑ ችግኞችን እየተከለ የመጣ ቢሆንም የአንድ ጀንበር መርሐ -ግብሩ ከታቀደዉ በላይ የተሳካ እንዲሆን እኛም እንደ አንድ የት/ቤት ማህበረሰብ የድርሻችን መወጣት ስላለብን ለዚሁ መርሐ-ግብር በተዘጋጀዉ የችግኝ መትከያ ቦታ ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት /ቤት በመገኘት የመርሐ-ግብሩ ተሳታፊ እንድትሆኑ ስንል በማክበር ጥሪያችን እንገልፃለን::
/ቤቱ