KOKEBE TSIBAH GENERAL SECONDARY SCHOOL GRADE 12 D/T EXAM QUESTIONS
743 subscribers
133 photos
2 videos
78 files
110 links
Download Telegram
ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል  የማህበራዊ ሳይንስ የቀን እና የማታ ተማሪዎች ፈተናቸዉን በወረቀት እና በኦን ላይን ተፈትነዉ  በሰላም አጠናቀዋል:: ፈተናቸዉን እንደጨረሱም በአግባቡ አቀባበል ተደርጎላቸዉ በተዘጋጀዉ ትራንስፓርት ለሁሉም  አማካኝ በሆነ ቦታ እንዲያደርሳቸዉ ተደርጓል::
👉 ተማሪዎቻችን በትምህርት ቤት ቆይታችሁ የነበራችሁን  መልካም ስነ-ምግባር በዩንቭርስቲ ቆይታችሁም ሰለደገማችሁ ከልብ እያመሠገን የጠበቃችሁትን  ዉጤት እንድታመጡ ፈጣሪ ይርዳችሁ::
👌  የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችም በዩንቭርስቲ ቆይታችሁ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ፈለግ እንደምትደግሙ እምነታችን የፀና ነዉ:: 
👉 ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መልካም የፈተና ጊዜ እንዲሆንላችሁ እየተመኘን ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ  መልካም የእረፍት ጊዜ ይሁንላችሁ::
               ሐምሌ 5/2016 ዓ.ም
                   
         /ቤቱ
Marif International.docx
18.2 KB
ማሪፍ ኢንተርናሽናል ት/ቤት በክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት ለመማር የተመዘገባችሁ ስማችሁ ከላይ የተያያዘ ተማሪዎች የፊታችን ሰኞ በቀን 08/11/2016 ዓ.ም ጥዋት 3:00 ላይ ማሪፍ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት እንድትገኙ እናሳስባለን::

አድራሻ:
ፈረንሳይ ለጋሲዮን ወደ ጉራራ በሚወስደው መንገድ ላይ የሃ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ይገኛል::
ቀን 06/11/2016

ማሳሰቢያ
ለ 12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች

የትምህርት ቤታችን የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎቻች ነገ እሁድ 07/11/2016 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲ የምትገቡበት ቀን ስለሆነ ጥዋት 12:00 ሰዓት በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ እንድትገኙ እናሳስባለን::

መልካሙን ሁሉ ይግጠማችሁ

መልካም ፈተና ይሁንላችሁ::

ት/ቤቱ
2017 የተከለሰ ምዝገባ Regitration Program.docx
17.5 KB
ቀን 07/11/2016 ዓ.ም የ2017 ዓ.ም የተከለሰ የተማሪዎች ምዝገባ ፕሮግራም
በነባሩ 9ኛ እስከ 11ኛ ክፍል የነበራችሁ ተማሪዎች በወጣላችሁ አዲሱ የተከለሰ ፕሮግራም መሰረት ተገኝታችሁ ምዝገባችሁን እንድታከናዉኑ እየተየቅን በወጣለት ፕሮግራም ተገኝቶ ምዝገባዉን የማያከናዉን ተማሪ ሃላፊነቱን የማንወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በተጨማሪም ከ10ኛ ወደ 11ኛ ክፍል የተዛወራችሁ ተማሪዎች ስትመጡ የstream / Natural and Social/ ምርጫ አጠናቃችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፡፡
አዲስ ተማሪዎች በቀጣይ በምናወጣለችሁ ፕሮግራም መሰረት ምዝገባ የምናከናዉን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
💥 ምዝገባዉ እንዲቀላጠፍ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልታችሁ ተዘጋጅታችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፡፡
👌 ምዝገባዉ በሁለቱም ስርዓተ ትምህርት/ በአፋን ኦሮሞ እና አማርኛ/ በእናንተ ምርጫ መሰረት የምናከናዉን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ት/ቤቱ
ቀን 07/11/2016 ዓ.ም ጥብቅ ማስታወቂያ
ለተመዝጋቢ ተማሪዎች

ነባር ከ9ኛ እስከ 11ኛ ክፍል ለነበራችሁ ለምዝገባ ስትመጡ
-👉 የባለፈዉን ዓመት መታወቂያ መመለስ ይጠበቅባችኋል
-👉 የባለፈዉን ዓመት መፅሀፍ በመመለስ አዲስ መፅሀፍ መዉሰድ ይጠበቅባችኋል፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን የማያሟላ ተማሪ የማይመዘገብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ት/ቤቱ
ማሳሰቢያ:-
የ2017 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት  ቤታችን ነባራዊ ሁኔታ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 8/2016 ዓ.ም እንደሚጀመር በማስታወቂያ ገልፀናል:: በመሆኑም የኦን ላይን ምዝገባዉ የሚካሄደዉ በትምህርት ቤቱ የአይሲቲ መምህራን በመሆኑ በወጣላችሁ ፕሮግራም መሠረት አስፈላጊዉ ቅድመ ሁኔታ አሟልታችሁ እንድትመዘገቡ ስንል እየገለፅን በየኢንተርኔት ቤቱ እየሄዳችሁ ለምዘገባ በሚል የምትከፍሉት ምንም አይነት ክፍያ መኖር የለበትም:: ስለሆነም በፕሮግራማችሁ ት/ቤት በአካል በመቅረብ የኦን ላይን ምዝገባ እንድትፈፅሙ ስንል እንገልፃለን::
                         /ቤቱ
2017 የተከለሰ ምዝገባ Regitration Program.docx
15.7 KB
Guyyaa 07/11/2016
Beeksisa
Mana Barumsaa Kookobaa Tsibaah waalii galaa Sad.2ffaa Sagantaa Galmee Barattoota Bara barnootaa 2017 ilaallata

💥 Sagantaa barnoota duraanii kutaa 9ffaa hanga 11ffaatti jirtan sagantaa galmee haaraa isiniif bahe irratti hundaa’uun itti gaafatamummaa keessan akka baatan isin beeksisna.
💥 Dabalaatan barattoota kutaa 1offaa gara 11ffaatti dabartan kutaa mummee saayinsii uumaamaa fi saayinsii haawasaa adda baafattanii murteeffattanii akka dhuftan isiin beeksiifnneerra.
💥 Galmeen barattoota haaraa sagantaa biroon isiin beeksifna.
💥 sagantaa galmeen saffisisuuf barattotni haalduree hunda guuttanii akka argamtan .
💥 Galmeen sagantaa Afaan Oromoo fi Afaan Amaaraan kan gaggeesinu ta’a.

Mana Barumsichaa
ማሳሰቢያ:-
ለወላጆች/አሳዳጊዎች እና ተማሪዎቻችን
👉 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ዛሬ ሐሙስ በ11/11/2016 ዓ.ም ፈተናቸዉን እንደጨረሱ ወደ ቤታቸዉ የሚመለሱ መሆኑን እንገልፃለን::
👌 ተማሪዎቻችን እንኳን በደህና ወደ ቤተሰቦቻችሁ በሰላም ተመለሳችሁ::
👉 ያቀዳችሁትን ዉጤት እንድታመጡ ፈጣሪ ይርዳችሁ::
                               /ቤቱ
የየ ክ/ከተማ ትምህርት /ቤት ኃላፊ የተከበሩ አቶ ፈይሳ ወዳጆ የትምህርት ትዉልድ ስራ በተጀመረበት ወቅት የትምህርት ቤታችን መሠረታዊ ችግሮች በዕቅድ እንዲካተቱ በማድረግ በጀት አስፈቅደዉ በ2016 ዓ.ም ከ28 ሚሊየን ብር በላይ የፈጀ የልማት ስራዎች እንዲሰሩ አድርገዋል::
👉 የተሰሩት ዋና ዋና ስራዎች
1ኛ, ከኳስ ሜዳ መመሪያ ክፍሎች ያለዉ የድጋፍ ግንብ እየፈራረሰ በተማሪዎች ላይ ጉዳት ሊያስከትል የነበረዉን እጅግ ጥራት ባለዉ ሽሮል ግንብ እንዲሰራ ተደርጓል:
2ኛ. በሁለት በኩል በጎርፍ እና ከአገልግሎት ዘመን ጋር በተያያዘ ወድቆ የነበረ አጥር በአዲስ እጅግ ጥራት ባለዉ መልኩ በሽሮል እንዲሰራ ተደርጓል:
3ኛ. የኳስ ሜዳ መቀመጫ አርጅቶ ሳር በቅሎበት የነበረ ደረጃ ግማሹ ባለበት ደረጃዉ ተጠብቆ እንዲጠገን እና በአዲስ መልክ መሠራት ያለበት በአዲስ እንዲሰራ ተደርጓል:
4ኛ. ግቢዉ በከፍተኛ ደረጃ ከላይ በሚመጣ ጎርፍ ይጠቃ የነበረዉ በ2ኩል ዉሃ መቀበል የሚያስችል ዲች እና ከዉስጥ በተለያየ መልኩ ተበታትኖ በመሄድ መሬቱ ላይ አልፎ አልፎም አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ይገባ የበነረዉ ጎርፍ ወደ ዲች ገብቶ እንዲሄድ ዋናዉ ዲች የሚያገናኙ መጠነኛ ዲቾች እንዲሰሩ ተደርጓል:
5ኛ. የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ኳስ ሜዳ:መመሪያ ክፍሎች እና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ቦታዎች የሚሸጋገሩባቸዉ መሸጋገሪያ ቦታዎች ተስተካክሎ እንዲሰራ ተደርጓል:
6ኛ. ለዘመናት ተማሪዎች በአስፓልት ከመኪና ጋር እየተጋፉ ይገቡበት የነበረዉን በር አሁን በነፃነት ደህነታቸዉ ተጠብቆ የሚገቡበት አዲስ በር ተሰርቶ ከ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ አገልግሎት እንዲሰጥ ክፍት እንዲሆን ተደርጓል::
👉 በትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ስም ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን::


/ቤቱ
ቀን 16/11/2016 ዓ.ም
ጥብቅ ማስታወቂያ
👉👉ለነባር ተማሪዎች👈👈
ነባር ከ9ኛ እስከ 11ኛ ክፍል የነበራችሁና ሳትመዘገቡ የቀራችሁ ተማሪዎች የማጣሪያ ምዝገባ ነገ 17/11/2016 ዓ. ም ስለምናከናውን ለምዝገባ ስትመጡ
-👉 የባለፈዉን ዓመት መታወቂያ መመለስ ይጠበቅባችኋል
-👉 የባለፈዉን ዓመት መፅሀፍ በመመለስ አዲስ መፅሀፍ መዉሰድ ይጠበቅባችኋል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን የማያሟላ ተማሪ የማይመዘገብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ት/ቤቱ
ን17/11/2016                                                                                  
             ጥብቅ ማስታወቂያ
       👉ከክፍል ክፍል ያልተዛወራችሁ ተማሪዎች👈

በት/ቤታችን ከ9ኛ እስከ 11ኛ ክፍል ስትማሩ የነበራችሁና ነባር የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች ከክፍል ክፍል ሳትዛውሩ የቀራችሁ/ደጋሚ/ ተማሪዎች ምዝገባ ነገ 18/11/2016 ዓ. ም ስለምናከናውን ለምዝገባ ስትመጡ
-👉  የባለፈዉን ዓመት መታወቂያ መመለስ ይጠበቅባችኋል
👉የደገማችሁበትን ሰርተፊኬት ይዛቺችሁ መገኘት
ከላይ የተጠቀሱትን የማያሟላ ተማሪ የማይመዘገብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

                  ት/ቤቱ
ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ
ለግንዛቤ እና ጥንቃቄ ይረዳ ዘንድ

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተሻሻሉ የቅጣት እርከኖችን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ከተማን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ፣ጽዱና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የአረንጓዴ ስፍራዎች ፣ፓርኮች መንገዶች እና የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡

ይህንን ተከትሎ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትና የልማቶቹን ዘላቂነት ለማስቀጥል ያግዛሉ የተባሉ አዳዲስ ደንቦች ይፋ ተደርገዋል፡፡

ደንቦችን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በጽዳትና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራት ዙሪያ ቀድሞ ሲጠቀምበት በነበረው ደንብ ቁጥር 150/2015 ላይ የነበረውን የቅጣት እርከኖቹን በማሻሻል ወደ ተግባር መግባቱን ተናግረዋል።

የቅጣት እርከኖቹን ለህብረተሰቡ ዝርዝር መረጃ በመስጠት በመረጃ እጦት ለቅጣት እንዳይዳረግ ግንዛቤ መፍጠር ይገባል ብለዋል።

በዚህም ከ2ሺ ብር እስከ 100ሺህ ብር የቅጣት እርከኖች በግለሰቦችና በተቋማት ላይ መጣሉን ተናግረዋል።

በዚህም መሠረት :-

*ማንኛውም ሰው ያመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በግቢው ውስጥ በአግባቡ አለመያዝ፤በዓይነት አለመለየት፤ ማዝረክረክ፤ ለጤናና የአካባቢ ገጽታ በሚጎዳ መልኩ ማከማቸት፤ ለግለሰብ 2 ሺህ ብር ለድርጅት 50 ሺህ ብር

*ማንኛውም የጽዳት አገልግሎት ሰጭ ድርጅት/ማህበር ደረቅ ቆሻሻ ሲሰበስብ ገጽታ ካበላሸ 25 ሺህ ብር

*በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ለደንበኛው ተገቢውን አገልግሎት ካልሰጠ 50 ሺ ብር

*ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እውቅና ውጭ የአገልግሎት ክፍያ ከደንበኛው ከተቀበለ  50 ሺ ብር

*ጊዜያዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስቀመጫ ቦታዎችን እስከ 5 ሜትር ዙሪያ ድረስ ጽዱ ካላደረገ 50 ሺ ብር 

* ማንኛውም በመንገድ የሚንቀሳቀስ ሰው የሲጋራ ቁርጥራጭ፣ የሶፍት ወረቀት፣ ፌስታል፣ የጫት ገለባ፣ የፍራፍሬ ተረፈ-ምርቶች፣የትራንስፖርት ቲኬት፣የሞባይል ካርዶችን፣ የማስቲካና ከረሜላ ሽፋኖች፣ የመሳሰሉት ጥቃቅን ደረቅ ቆሻሻን ባልተፈቀደ ቦታ ወይም በፓርኮች፣ በአረንጓዴ ቦታ፣ በኮሪደር ከጣለ 2 ሺ ብር

*ከመኖሪያ ቤት ወይም ከድርጅት ግቢ ውጭ ያለውን የአካባቢ ንጹህና አረንጓዴ አድርጎ አለመጠበቅ ከመኖሪያ ቤት አጥር ግቢ ውጭ እስከ 5 ሜትር ርቀት አለማጽዳት፤20 ሺ ብር

*ከድርጅት/ተቋም አጥር ግቢ ውጭ እስከ 10 ሜትር አለማጽዳት፤ 100 ሺ ብር

*ወቅታዊና ልዩ ዝግጅት አከናውኖ በዓሉ ሲጠናቀቅ በዕለቱና ወዲያው ዝግጅቱ የተከናወነበትን አካባቢ ከቆሻሻ ያላጸዳ የፕሮግራሙ አዘጋጅ፤ 50 ሺ ብር

*ዓመታዊ፤ ወርሃዊና ሳምንታዊ የእምነት በዓላት ሲከናወኑ ዝግጅቱ ሲጠናቀቅ የዝግጅቱ ባለቤት በዕለቱና ወዲያው አካባቢውን ካላጸዳ፤20 ሺ ብር የሚቀጡ መሆኑም ተመላክቷል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
በመሬት መሸራተት ለተጎዱ ወገኖቻችን የአቅማችሁን ድጋፍ ማድረግ ለምትሹ
Forwarded from Maf Digital
Grade 11 books (habesha_store).apk
166.1 MB
የ 11ኛ ክፍል ተማሪ ከሆናችሁ ይህ books መልሱን ያመጣላችኃል ይጠቅማችኃል ተጠቀሙት
Grade 10 books (habesha_store).apk
110.9 MB
የ 10ኛ ክፍል ተማሪ ከሆናችሁ ይህ books መልሱን ያመጣላችኃል ይጠቅማችኃል ተጠቀሙት
Grade 12 books (habesha_store).apk
148.1 MB
የ 12ኛ ክፍል ተማሪ ከሆናችሁ ይህ books መልሱን ያመጣላችኃል ይጠቅማችኃል ተጠቀሙት
Grade 9 books (habesha_store).apk
126.4 MB
የ 9ኛ ክፍል ተማሪ ከሆናችሁ ይህ books መልሱን ያመጣላችኃል ይጠቅማችኃል ተጠቀሙት