Kokebe Tsibah General Secondary School
3.35K subscribers
2K photos
15 videos
123 files
89 links
Since 1924
Download Telegram
Forwarded from KOKEBE TSIBAH GENERAL SECONDARY SCHOOL GRADE 12 D/T EXAM QUESTIONS (ⓜ︎ⓤ︎ⓛ︎ⓔ︎)
ለ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተማሪዎች እንዲዘጋጁ የትሞህርት ሚኒስቴር አሳሰበ።


(ቀን ሚያዚያ 23/ 2016 ዓ.ም)የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ የአሰልጣኞች ስልጠና ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናና ኦላይን ለመስጠት ከሁሉም ክልሎች በተመረጡ 25 ከተሞች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።


በወረቀት ከሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና ጎን ለጎን በቴክኖሎጁ ተደግፎ የሚሰጠው የኦንላይን ፈተና ተማሪዎች ከቦታ ቦታ ሳይጓጓዙ በየአካባቢያቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር እያደሩ ፈተናውን እንዲወስዱ እንደሚያስችላቸው ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል።


በመሆኑም ፈተናው እንዲሰጥባቸው በተመረጡ ከተሞች ፈተናውን በኦንላይን የሚወስዱ የዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከወዲሁ እንዲዘጋጁ ወ/ሮ አየለች አሳስበዋል።


በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትም ከወዲሁ በቅንጅት በመስራት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ጠቁመዋል።


ወላጆች ስለፈተናው የተሻለ አረዳድና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ልጆቻቸውን እንዲደግፉና በራስ መተማመን ወደፈተናው ሊገቡ የሚችሉበትን ዕድል ሊፈጥሩ እንደሚገባም አመላክተዋል።


ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮም በኦን ላይን የሚሰጠውን ፈተና በተሻለ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታዋ ጠቁመዋል።


የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው ፈተናን ለተማሪዎች በኦንላይን መስጠት ምቹና ቀላል መሆኑን በዚሁ ጊዜ ጠቅሰው የኦንላይን ተፈታኞች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ደጋግመው እንዲለማመዱ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።
Kokebe Tsibah General Secondary School
Photo
በአዲስ አበባ በሁሉም የመንግስት እና የግል 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ፈተናዉ በኦን ላይን እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሚያዚያ 22/8/2016 ዓ.ም ይፋ አድርጓል::
👉 በመሆኑም የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች የሚሰጧችሁን መረጃዎች መሠረት በማድረግ ራሳችሁን ከወዲሁ ዝግጁ ማድረግ ይጠበቅባችሗል::
👉 አስፈላጊዉ መረጃ እና ልምምድ በወቅቱ የሚሰጣችሁ በመሆኑ ነገሮችን አክብዶ ማየት የለባችሁም::
👉 ፈተናዉ የሚሰጠዉ ከዚሁ በትምህርትቤታችን ነዉ::
/ቤቱ
ዉድ የት/ቤታችን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎች የምትሰሩበት ቻናል መክፈታችን ይታወቃል ታዲያ ምን ያህላችን ይሄን ቻናል ተቀላቅለዋል::

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/kokebetsibahexam 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Anonymous Poll
36%
አዎን
27%
አይ
37%
እስካሁን መከፈቱን አላዉቅም
በየካ ክ/ከተማ ክተማ ትምህርት ፅ/ቤት ስር የሚገኘዉ የኮከበ ፅባህ 2ኛ ደ/ት/ቤት የ2016 ዓ.ም የፋሲካ በዓልን በማስመልከት ለተለዩ የት/ቤቱ ሰራተኞች: በት/ቤቱ ሻይ ክበብ ተቀጥረዉ ለሚሰሩ ሰራተኞች እና በት/ቤቱ ዉስጥ በቀድሞ ተማሪዎች:ወተመህ እና የማታ በሚያስተምሩ መምህራን እና ተማሪዎች ለጊቢ እንክብካቤ ለተቀጠሩ ሰራተኞች በድምሩ ለ39 ሰዎች ከወረዳ 05 አስተዳደር ቀድም ሲል ለት/ቤቱ የተሰጡ እንቁላል ጣይ ደሮዎች በአሁኑ ሰዓት እንቁላል መጣል ስላቆሙ ለበዓል ከክ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ጋር በመነጋገር ማዕድ የማጋራት ስራ ዛሬ ሚያዚያ 24/8/2016 ዓ.ም ተከናዉኗል::
👉 መልካም የተንሳኤ በዓል ይሁንልን/ይሁንላችሁ!!!
/ቤቱ
⭐️መጨነቁን አቁምና ጥናቱን ጀምር!

🌟ፈተና ደረሰ ብለህ መጨነቁን አቁምና የምትችለውን ሁሉ አድርግ! ፈጣሪም የሚረዳህ የምትችለውን ስታደርግ ነው! ጊዜ ደግሞ አለህ!

ከዚህ በፊት አጥንተህ ጥሩ ውጤት ያመጣህባቸውን ወቅቶች አስብ እስኪ.... እርግጠኛ ነኝ አሁንም በቆራጥነት ያኔ የለፋኸውን ልፋት ከደገምከው  ማትሪክን ከ 500 በላይ  ሚኒስትሪን ከ50 በላይ ታመጣለህ። ዛሬውኑ ጥናታችሁን ከጀመራችሁ ያላችሁ ግዜ በቂ ነው ::

ዳይ ወደ 👉ጥናት

መልካም ጥናት 📚📖📖📚

via 👉ኮኮባ ፅባህ/ 2ኛ ደ/ት/ቤት           



12ኛ ክፍል
ለሌሎች ሸር እናድርግ!!
👇👇👇👇//7👇👇👇👇
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/dam76
Forwarded from Abebe Gesit
ውድ የ11ንዱም ክፍለ ከተማ የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ቡድን መሪዎች
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም በፍቅር አደረሳችሁ እያልኩ
 በየክፍለ ከተማችሁ ቤት ለመደራጀት እየፈለጉ በተለያየ ምክንያት ሳይመዘገቡ ቀርተው ለመደራጀት የሚፈልጉ መምህራን በየክፍለ ከተማችሁ እያመለከቱ ያሉትን በመመዝገብ፣
 ካሁን በፊት ከየወረዳውና ከክፍለ ከተሞች የትምህርት ባሙያዎችን ለማደራጀት የተላከው ስም ዝርዝር በወረዳ ት/ፅ/ቤት ኃላፊና በክፍለ ከተማ ት/ፅ/ቤት ኃላፊ በማረጋገጥና
 በጡረታ የተገለሉ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ቤት ለመስራት መደራጀት የሚፈልጉትን በወረደላችሁ መመሪያ መሰረት በማረጋገጥና መመዝገብ መረጃ በሃርድና በሶፍት ኮፒ በክፍለ ከተማ ት/ፅ/ቤት ኃላፊ ተረጋግጦና ተፈርሞ እጅግ ቢዘገይ እስከ ለቡዕ 30/2016 ዓ.ም ድረስ ብቻ ለመጨረሻ ጊዜ እንድትልኩልን ስንል እናሳስባለን፡፡
⭐️ማሳሰቢያ

⭐️ከበአል ማግስት ዛሬ ሰኞ ተማሪዎች ባለመገኘታቸው በአብዛኞቹ ት/ቤቶች  የመማር ማስተማር ሂደቱ በአግባቡ አለመከናወኑን አረጋግጠናል::

👍 በመሆኑም ነገ ማክሰኞ  ሙሉ በሙሉ መደበኛ መማር ማስተማሩ በሁሉም የክፍል ደረጃዎች በሁሉም ት/ቤቶች መጀመር ያለበት መሆኑን ለመምህራንና ተማሪዎች  እንድታሳውቁ እያሳሰብን የተገኙ እና ያልተገኙ መምህራንና ተማሪዎችን መረጃ  በመያዝ እንድታሳውቁን እየገለጽን ነገ የከተማ እና  የክ/ከተማ ባለሙያዎች ት/ቤት ተገኝተው ክትትል የሚያደርጉ መሆኑን እናሳውቃለን::


የየካ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት
ማሳሰቢያ!!
ለሁሉም ተማሪዎች/9-12/
👌 እንደሚታወቀዉ በ2016 ዓ.ም ያሉት የትምህርት ቀናት በበጀት ዓመቱ የትምህርት ካሌንደር በግልፅ ተቆጥረዉ ተቀምጠዋል::

👉 ይሁን እንጅ ተማሪዎች በህግ እና በአሰራር ባልተፈቀደ ሁኔታ ከበዓል ማግስት በራሳችሁ የተሳሳተ ዉሳኔ[አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት] ት/ቤት እየመጣችሁ አለመሆኑን ዛሬ ሚያዚያ 28/2016 ዓ.ም አረጋግጠናል::
👉 ስለሆነም ይህ አይነት አካሄድ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚበልጥ እንዲሁም በቀጥታ ተጎጅዎች ራሳችሁ ተማሪዎች በመሆናችሁ ከነገ ሚያዚያ 29/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሁላችሁም ተማሪዎች በትምህርት ገበታችሁ እንድትገኙ ስንል በጥብቅ እናሳዉቃለን::
👉 ወላጆች/አሳዳጊዎች ልጆቻችሁ ከበዓል ማግስት ከት/ቤት ሲቀሩ ለምን ብላችሁ በመጠየቅ ወደ ት/ቤት በሰዓቱ እንድትልኩ ስንል እናሳስባለን::
👉 ትምህርት ቤታችን ለመማር የሚመጡ ተማሪዎችን ለማስተማር ከበዓል ማግስት ጀምሮ ተዘጋጅቶ ሲጠብቅ የነበረ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳን::
👉 ከነገ ጀምሮ በትምህርት ገበታ ላይ የማይገኝ ተማሪን በተማሪዎች የዲስፕሊን አፈፃፀም መመሪያ መሠረት ተጠያቂ የምናደርግ መሆኑን እንገልፃለን::
👌 ያላግባብ የትምህርት ብክነትን በጋራ እንከላከል!!
ሚያዚያ 28/2016 ዓ.ም
/ቤቱ
ከበዓል ማግስት ሚያዚያ 29/2016 ዓ.ም ለመማር የመጡ ተማሪዎችን ልዩ ክፍሎች በየክፍል ደረጃዉ በማደራጀት የመማር ማስተማር ሂደቱን አስቀጥለናል::
👉 ዛሬ ለመማር የመጣችሁ ተማሪዎችን እና ወላጆችን/አሳዳጊዎችን እያመሠገን በተለያየ ምክንያት ያልተገኛችሁ ተማሪዎች ነገ መገኘት ይኖርባችሗል::
ት/ቤቱ