Kokebe Tsibah General Secondary School
3.2K subscribers
1.77K photos
15 videos
122 files
85 links
Since 1924
Download Telegram
በ2017 ዓ.ም 11ኛ ክፍል በሚጀመረዉ የስራ እና ተግባር ትምህርት የሙያ አይነት ምርጫ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ከግንቦት 6-7/2016 ዓ.ም ለተማሪዎች እና ወላጆች/አሳዳጊዎች የተፈጠረላችሁን ግንዛቤ መሠረት አድርጋችሁ ትመርጣላችሁ::በመሆኑም ይህ የተለጠፈላችሁ የመምረጫ ቅፅ በሃርድ ኮፒ ማክሰኞ ተሰጥቶአችሁ ከወላጅ/አሳዳጊ ጋር በመመካከር ሞልታችሁ ግንቦት 8/2016 ዓ.ም ሐሙስ እንድትመልሱ ይደረጋል::
👉 በመሆኑም ሁሉም የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ነገ ማክሰኞ ግንቦት 6/2016 ዓ.ም የምርጫ ፎርሙን መዉሰድ ይጠበቅባችሗል::
ት/ቤቱ
👌ዛሬ ግንቦት 6/2016 ዓ.ም
1ኛ.ጠዋት የህፃናት ማቆያ ስፍራ ለህፃናቱ ምቹ በሆነ ሁኔታ በግብዓት አሞልተን ስራ ለመጀመር ምቹ አድርገናል::
👉መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች 20 ህፃናት እንዲቆዩላቸዉ አስመዝግበዋል::
👉 ሰኞ ግንቦት 12/2016 ዓ.ም ህፃናትን ተቀብለን ማቆየት እንጀምራለን::
2ኛ. ለ800 የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች የክ/ከተማዉ ትምህርት ፅ/ቤት ሱፐርባይዘሮች በተገኙበት የስራ እና የተግባር ትምህርት የመምረጫ ፎርም ለተማሪዎች ስለቅፁ አሞላል ገለፃ በማድረግ ሰጥተናል::
/ቤቱ
ቀን 7/9/2016 ዓ.ም
አስደሳች ዜና!!

ለተማሪዎች በሙሉ
ነገ ግንቦት 8/2016 ዓ.ም ብክለት ይብቃ ዉበት ይንቃ በሚል በክ/ከተማ ደረጃ በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የአቋም መፈተሻ ስፓርታዊ ዉድድሮች ይከናወናሉ::
1ኛ.በኮከበ ፅባህ እና በትስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል የወንዶች እግር ኳስ ዉድድር ይደረጋል::
2ኛ. በኮከበ ፅባህ እና በብርሃን ጉዞ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል የጠረጴዛ ቴነስ ዉድድር በወንዶች ይደረጋል::
3ኛ. በኮከበ ፅባህ እና በከፍተኛ 12 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል የወንዶች የመረብ ኳስ ዉድድር ይደርጋል::
4ኛ. በቼዝ ከግል ት/ቤቶች ጋር ዉድድር ይደረጋል::
5ኛ. ሴቶች የጠረጴዛ ቴነስ የአቋም መፈተሻ ጫዎታ እንዲያደርግ የተጋበዘዉ ት/ቤት ከመጣ ዉድድሩ ይደረጋል::
👉 በመሆኑም ሁሉም ተማሪዎች በጫዎታ ሰዓት በተዘጋጀላችሁ ቦታ በመሆን ለተወዳዳሪዎች ድጋፋችሁን እንድትሰጡ ስንል እንገልፃለን::
👉 በሁሉም የአቋም መፈተሻ ዉድድሮች አሸናፊ ሆነን እንድንወጣ ሃላፊነት የተሰጣችሁ የዘርፉ መምህራን እና ተወዳዳሪ ተማሪዎች በሁሉም ረገድ ዝግጁ ሁናችሁ መቅረብ ይጠበቅባችሗል::
👌 መልካም ዕድል !!
/ቤቱ
እንኳን ደስ አለን!!

👌ግንቦት 8/2016 ዓ.ም ለት/ቤታችን ትልቅ ድምቀት እና ድል የተገኘባት ቀን ነች::
👉 የት/ቤቱ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ከተስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ጋር የአቋም መፈተሻ ጫዎታ አድርጎ በጀግኖች የትምህርት ቤታችን ተጫዋቾች 4ለ2 ማሸነፍ ተችሏል::
👉 ጫወታዉ እጅግ ያማረ እና የደመቀ ነበር::
👉 የተስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መጥታችሁ በመሳተፋችሁ እናመሠግናለን::
👉 ዉድ የዉድድሩ ድምቀት የነበራችሁ ደጋፊ ተማሪዎች የእናንተም ድርሻ ከፍተኛ ስለነበር ምስጋና ይገባችሗል::
👉የትምህርት ቤቱ [HPE] መምህራን በአጠረ ጊዜ ይህን የመሰለ ጠንካራ እና የአሸናፊነት ስነ-ልቦናዉ ከፍ ያለ ቡድን አደራጅታችሁ ት/ቤቱን ለአሸናፊነት ስላበቃችሁ ኮርተንባችሗል: ክብር እና ምስጋና ይገባችሗል::
👉ዉድ ተወዳዳሪዎች በቀጣይ በአዲስ አበባ University በሚደረገዉ ዉድድር አሸናፊ ሆናችሁ ራሳችሁን እና ት/ቤታችሁን እንድታስጠሩ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን::
👌 በድጋሜ እንኳን ደስ አለን!!
/ቤቱ