Kokebe Tsibah General Secondary School
3.35K subscribers
2K photos
15 videos
123 files
89 links
Since 1924
Download Telegram
Kokebe Tsibah General Secondary School
ዉድ የት/ቤታችን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎች የምትሰሩበት ቻናል መክፈታችን ይታወቃል ታዲያ ምን ያህላችን ይሄን ቻናል ተቀላቅለዋል::

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/kokebetsibahexam 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ከላይ ባቀረብነው መጠይቅ መሰረት የትምህርት ቤታችን የ12 ክፍል ተማሪዎች ለ12 ክፍል የተለያዩ የማትሪክ ጥያቄዎች÷ አጫጭር ማስታዎሻዎችን የምንለቅበት የቴለግራም ቻናል መክፈታች የማታዉቁ ተማሪዎች መኖራችሁን መረዳት ችልናል:: ስለሆነም ከዚህ በታች በተጠቀሰው ሊንክ/link በመግባት እንድትጠቀሙ እናሳስባለን::


ይከታተሉ እና ለበለጠ ያካፍሉ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/kokebetsibahexam
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
በ2017 ዓ.ም 11ኛ ክፍል በሚጀመረዉ የስራ እና ተግባር ትምህርት የሙያ አይነት ምርጫ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ከግንቦት 6-7/2016 ዓ.ም ለተማሪዎች እና ወላጆች/አሳዳጊዎች የተፈጠረላችሁን ግንዛቤ መሠረት አድርጋችሁ ትመርጣላችሁ::በመሆኑም ይህ የተለጠፈላችሁ የመምረጫ ቅፅ በሃርድ ኮፒ ማክሰኞ ተሰጥቶአችሁ ከወላጅ/አሳዳጊ ጋር በመመካከር ሞልታችሁ ግንቦት 8/2016 ዓ.ም ሐሙስ እንድትመልሱ ይደረጋል::
👉 በመሆኑም ሁሉም የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ነገ ማክሰኞ ግንቦት 6/2016 ዓ.ም የምርጫ ፎርሙን መዉሰድ ይጠበቅባችሗል::
ት/ቤቱ
👌ዛሬ ግንቦት 6/2016 ዓ.ም
1ኛ.ጠዋት የህፃናት ማቆያ ስፍራ ለህፃናቱ ምቹ በሆነ ሁኔታ በግብዓት አሞልተን ስራ ለመጀመር ምቹ አድርገናል::
👉መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች 20 ህፃናት እንዲቆዩላቸዉ አስመዝግበዋል::
👉 ሰኞ ግንቦት 12/2016 ዓ.ም ህፃናትን ተቀብለን ማቆየት እንጀምራለን::
2ኛ. ለ800 የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች የክ/ከተማዉ ትምህርት ፅ/ቤት ሱፐርባይዘሮች በተገኙበት የስራ እና የተግባር ትምህርት የመምረጫ ፎርም ለተማሪዎች ስለቅፁ አሞላል ገለፃ በማድረግ ሰጥተናል::
/ቤቱ
ቀን 7/9/2016 ዓ.ም
አስደሳች ዜና!!

ለተማሪዎች በሙሉ
ነገ ግንቦት 8/2016 ዓ.ም ብክለት ይብቃ ዉበት ይንቃ በሚል በክ/ከተማ ደረጃ በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የአቋም መፈተሻ ስፓርታዊ ዉድድሮች ይከናወናሉ::
1ኛ.በኮከበ ፅባህ እና በትስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል የወንዶች እግር ኳስ ዉድድር ይደረጋል::
2ኛ. በኮከበ ፅባህ እና በብርሃን ጉዞ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል የጠረጴዛ ቴነስ ዉድድር በወንዶች ይደረጋል::
3ኛ. በኮከበ ፅባህ እና በከፍተኛ 12 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል የወንዶች የመረብ ኳስ ዉድድር ይደርጋል::
4ኛ. በቼዝ ከግል ት/ቤቶች ጋር ዉድድር ይደረጋል::
5ኛ. ሴቶች የጠረጴዛ ቴነስ የአቋም መፈተሻ ጫዎታ እንዲያደርግ የተጋበዘዉ ት/ቤት ከመጣ ዉድድሩ ይደረጋል::
👉 በመሆኑም ሁሉም ተማሪዎች በጫዎታ ሰዓት በተዘጋጀላችሁ ቦታ በመሆን ለተወዳዳሪዎች ድጋፋችሁን እንድትሰጡ ስንል እንገልፃለን::
👉 በሁሉም የአቋም መፈተሻ ዉድድሮች አሸናፊ ሆነን እንድንወጣ ሃላፊነት የተሰጣችሁ የዘርፉ መምህራን እና ተወዳዳሪ ተማሪዎች በሁሉም ረገድ ዝግጁ ሁናችሁ መቅረብ ይጠበቅባችሗል::
👌 መልካም ዕድል !!
/ቤቱ
እንኳን ደስ አለን!!

👌ግንቦት 8/2016 ዓ.ም ለት/ቤታችን ትልቅ ድምቀት እና ድል የተገኘባት ቀን ነች::
👉 የት/ቤቱ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ከተስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ጋር የአቋም መፈተሻ ጫዎታ አድርጎ በጀግኖች የትምህርት ቤታችን ተጫዋቾች 4ለ2 ማሸነፍ ተችሏል::
👉 ጫወታዉ እጅግ ያማረ እና የደመቀ ነበር::
👉 የተስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መጥታችሁ በመሳተፋችሁ እናመሠግናለን::
👉 ዉድ የዉድድሩ ድምቀት የነበራችሁ ደጋፊ ተማሪዎች የእናንተም ድርሻ ከፍተኛ ስለነበር ምስጋና ይገባችሗል::
👉የትምህርት ቤቱ [HPE] መምህራን በአጠረ ጊዜ ይህን የመሰለ ጠንካራ እና የአሸናፊነት ስነ-ልቦናዉ ከፍ ያለ ቡድን አደራጅታችሁ ት/ቤቱን ለአሸናፊነት ስላበቃችሁ ኮርተንባችሗል: ክብር እና ምስጋና ይገባችሗል::
👉ዉድ ተወዳዳሪዎች በቀጣይ በአዲስ አበባ University በሚደረገዉ ዉድድር አሸናፊ ሆናችሁ ራሳችሁን እና ት/ቤታችሁን እንድታስጠሩ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን::
👌 በድጋሜ እንኳን ደስ አለን!!
/ቤቱ