KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /
4.2K subscribers
249 photos
4 videos
180 files
63 links
Kotebe University of Education Community / አዲስ ነገር መረጃ /
Download Telegram
ለአንደኛ ዓመት የማስትርስ ዲግሪ ተማሪዎች የምዝገባ ማስታወቂያ
Updated: Saturday, 21 November 2020
የአንደኛ ዓመት ማስተርስ ዲግሪ ተማሪዎች ምዝገባ በርካታ ሂደቶችን አልፎ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡ በዚህ መሰረት ህዳር 12-13/2013ዓ.ም የOnline ምዝገባና የትምህርት ክፍያ ይከናወናል፡፡ ለOnline ምዝገባው username እና password የተዘጋጀ ሲሆን በት/ክፍሎች በኩል ይሰጣል፡፡ የOnline ምዝገባ ሂደቱ ሁለት ደረጃዎች አሉት፡፡ በመጀመሪያው ደረጃ Bio Data ይሞላል (ሂደቱን የሚገልፁ ማስታወቂያዎች ጊቢ ውስጥ ተለጥፈዋል እንዲሁም ከታች የተገለጸውን ዝርዝር የምዝገባ ሂደት (steps) ማንበብ ይቻላል፡፡ )፡፡ በሁለተኛው ደረጃ ደግሞ የትምህርት ምዝገባ እና ክፍያ ይከናወናል፡፡ የትምህርት ክፍያ የሚፈፀመው በCBE Birr ነው፡፡

የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ዳይሬክቶሬት



Steps of Registration

1. Write: estudent.kmu.edu.et on the address bar of your Web-Browser and then Press on Enter

2. Write: your User Name and Password and then click LogIn

3. Go to Academics -> Registration link

4. You will get courses and registration fees

5. Press on Continue

6. You will get the following, system generated, information:

Dear "a"

You have submitted "b" courses for "c" registration. Please use CBE Birr payment system before the registration deadline, otherwise you are not registered.

Your Bill Reference Code:"d"

a. Your full name

b. Number of course/s you will take

c. Academic Year Semester

d. 7 Digit code

7. Use/write the 7 digit bill reference code to make the payment and enter the amount of Birr mentioned on the payment slip.

8. The Registration is complete.

9. Print the Payment Slip (if you need one)

How to pay using CBE Birr



1. Dial *847#

2. Choose Pay Bill

3. Choose Input Short Code

4. Enter 303030

5. Enter Your Bill Reference Code

6. Approve
የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ለነበሩ ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ ተገለጸ
***************************
በ2012 ዓ.ም ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ከነገ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ ከአንድ ሳምንት በኋላ ሌሎች ቀሪ ተማሪዎች እንዲገቡ እና በዚህ የትምህርት ዘመን የሚጠበቅባቸውን ሦስት የትምህርት ሴሚስቴር እንዲያጠናቅቁ በቂ ድጋፍ እና ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል ሲል ገልጿል።

ተማራቂ ተማሪዎች በቀሪዎቹ አጭር ወራት ውስጥ ያልተጠናቀቁ የትምህርት እና ሥልጠና ተግባራትን በተቻለ ቅልጥፍና እና ዝግጁነት በማጠናቀቅ ተመርቀው ወደ ሥራ ዓለም እንዲትቀላቀሉ እና የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ላይ አሻራቸውን እንዲያኖሩ አሳስቧል።

ሌሎች በ2013 ትምህርት እና ሥልጠና ዘመን ሙሉ ዓመቱን በተቋማት ቆይታ የሚደርጉት ተማሪዎች በሙሉ፣ ትምህርታቸውን በአግባቡ እየተማሩ ለአገራችን እና ለሕዝባችን አንድነት እና ኅብረት እንዲሁም ብልጽግና ጉዞ ፋይዳ ያላቸው ሰብአዊ እና ማኅበራዊ በጎ አድራጎት ተግባራት እና አገልግሎቶች በንቃት በመሳተፍ ወገንተኝነታቸውን እንዲገልጹ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጥሪ አድርጓል።

የከፍተኛ ትምህርት እና ሥልጠና ማኅበረሰብ በሙሉ የተለመደውን ቀና ድጋፍ እና ትብብር በማከል የ2013 ትምህርት እና ሥልጠና ዘመን የተሳካ እንዲሆን የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ከአደራ ጭምር አሳስቧል።

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
በፎቶ የሚቀርቡ መረጃዎችን ለማግኘት ኢንስታግራም ገጻችንን ይጎብኙ
https://www.instagram.com/ebcnews1
ለ2013 የዩኒቨርስቲያችን እጩ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ
--------------------
የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በሁለተኛው ሴሚስተር በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጡውን ትምህርት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሰጠው አቅጣጫ መሠረት 2013 ዓ.ም ለማስጀመር የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎቹን አጠናቋል፡፡
ስለሆነም

- ህዳር 25 እና 26/2013 ዓ.ም የዕጩ ተመራቂ የመደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ይሆናል፡፡
- ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም በትምህርት መልሶ መከፈት አተገባበር ላይ ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ጠቅላላ ገለፃ ይደረጋል፡፡
- ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት የሚጀመር መሆኑን አቀውቃችሁ በወጣው ማስታወቂያ መሠረት ሪፖርት በማድረግ ትምህርት እንድትጀምሩ እናሣስባለን፡፡
Forwarded from Addis Shiferaw
የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የተከታታይና ርቀት ትምህርት ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የገፅ ለገፅ ትምህርት መቀጠል የሚያስችላቸውን ስልጠና ወሰዱ፡፡
-------------------------------------------------
የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የተከታታይና ርቀት ትምህርት ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የገፅ ለገፅ ትምህርት መቀጠል የሚያስችላቸውን ስልጠና 09/04/2013 ዓ.ም ወሰዱ፡፡
የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው እንዳሉት፤ ኮቪድ 19 በዓለም አቀፍ ብሎም በሃገር ደረጃ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ቢሆንም የተለያዩ ቅድመ ጥንቃቄዎችን በማድረግ የገፅ ለገፅ ትምህርቱ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡ በዚህም መሠረት ባለችው ጥቂት ሳምንታት ግዜያችሁን በአግባቡ በመጠቀም ለምርቃታችሁ እንደምንገናኝ ተስፋ አደርጋለው ብለዋል፡፡
እንደ ዶክተር ብርሃነመስቀል ገለፃ፤ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለአንዳንድ ጊዜያቸውን በአግባቡ ለሚጠቀሙ ተማሪዎች መልካም አጋጣሚን የፈጠረ ቢሆንም ነገ ሌላ ቀን እንደሆነ ላላሰቡ ተማሪዎች ግን በትምህርታቸው ላይ ከፍተኛ ጫናን እንደሚያሳድርባቸው ተናግረዋል፡፡
የተከታታይና ርቀት ትምህርት ዳይሬክቶሬት የሆኑት አቶ ሮቤል ሳህሉ ለዕጩ ተመራቂ ተማሪዎቹ በቀሩት አጭር ሳምንታት ውስጥ በምን አግባብ ትምህርታቸውን መከታተል እንዳለባቸው ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል፡፡
የፀጥታና ደህንነት ዳይሬክቶሬትና የግቢው የፌዴራል ፖሊስ አመራር አካላት ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎቹ ወደ ተቋሙ ሲገቡና ሲወጡ ከወቅታዊ ሁኔታ አንፃር በምን አግባብ መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የመጣ መመሪያን መሠረት በማድረግ አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም ከዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የተለያዩ
Forwarded from Meron Worku
ተመራቂ ካልሆኑ ተማሪዎች ጋር ኮርስ አድ አድርጋችሁ የምትወስዱ ተማሪዎች እሁድ ጥር 16 2013 ዓ.ም አጭር ስብሰባ ስላለን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ተከታታይና ርቀት ት/ት ዳይሬክቶሬት ቢሮ እንድትገኙ እናሳስባለን!
ለማታና እረፍት ቀናት ዲፕሎማና ዲግሪ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች ተመራቂ ካልሆኑ ተማሪዎች ጋር ኮርስ አድ አድርጋችሁ የምትወስዱ ተማሪዎች እሁድ ጥር 16 2013 ዓ.ም አጭር ስብሰባ ስላለን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ተከታታይና ርቀት ት/ት ዳይሬክቶሬት ቢሮ እንድትገኙ እናሳስባለን!
19/05/2013ዓ.ም

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

ተመራቂ ካልሆኑ ተማሪዎች ጋር ኮርስ “Add” የምታደርጉ የማታና እረፍት ቀናት የዲፕሎማና ዲግሪ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች

ተመራቂ ካልሆኑ ተማሪዎች ጋር ኮርስ “Add” ያደረጋችሁ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች ቱቶሪያል እንዲሰጣችሁ የተወሰነ በመሆኑ ቱቶሪያል ለመውሰድ የምትፈልጉ ተማሪዎች የተመዘገባችሁበትን ስሊፕ እና ኮርስ “Add” ስታደርጉ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ በመያዝ ሰኞ ጥር 24 እና ማክሰኞ ጥር 25/2013 ዓ.ም የቱቶሪያል ክፍያ እንድትከፍሉ እያሳሰብን፤ ዝርዝር መረጃውን ከተከታታይና ርቀት ትምህርት ዳይሬክቶሬት የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እንድታዩ እናሳስባለን፡፡
Forwarded from ማሪያም ሆይ ሁሌም ከኔ አትራቂ ታስፈልጊኛለሽ
ከዩኒቨርሲቲው የፌስቡክ ገጽ የተገኘ መረጃ

ለማታና እረፍት ቀናት ተማሪዎች በሙሉ
-------------------------
በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የ2012 ዓ.ም ሁለተኛ መንፈቅ ዓመት የገፅ ለገፅ መማር ማስተማር ቆሞ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ዩኒቨርሲቲያችን የማታና እረፍት ቀናት የዲፕሎማና ዲግሪ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በ26/05/2013 ዓ.ም እንዲጀምሩ ወስኗል፡፡
በመሆኑም የሚወጣላችሁን ሳምንታዊ የትምህርት ፕሮግራም በመመልከት በትምህርት ገበታችሁ ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡
• ወደ ክፍል ስትመጡ የአፍ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ እና ሳኒታይዘር መያዝ ግዴታ ነው፡፡

ከኮሌጅ/ፋኩልቲ/አካዳሚ የማታና እረፍት ቀናት ትምህርት አስተባባሪዎች ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል!

የኮ.ሜ.ዩ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ዳይሬክቶሬት

ምንጭ፦ የዩኒቨርሲቲው የፌስቡክ ገጽ
Forwarded from ZzZ W
Urgent Call for Proposal Development competition: Deadline February, 4th, 2021: Applications venue : Academics Vice Dean/ Dean Office.