ቅንጭብጭብ
7.2K subscribers
412 photos
9 videos
4 files
501 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
#ቅንጭብጭብ
#BcrAzyKid

ስለ #ቴዎድሮስ_ካሳሁን ኮንሠርት መከልከል እና እና የሙዚቃው አልበም ምርቃት መሠረዝ. . .

ጷጉሜ 5 በሚሊንየም አዳራሽ ሊዘጋጅ ታስቦ የነበረው የታላቁ ሙዚቀኛ የሙዚቃ ድግስ በሌላ የሙዚቃ እና ሌሎች ዝግጅቶች ምክንያት እንዳይደገስ መከልከሉ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በትችት እና ግልፅ በሆነ መልኩ የተወራበት ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል። ይሁን ይሁን ብለን አለፍን. . .

የሙዚቃው አልበም ምርቃትም ዛሬ ነሐሴ 28/2009 ዓ.ም ከምሽቱ በ 1:00 ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም ዝግጅቱ እንዳይቀርብ መታገዱ እና የሙዚቃ መሳሪያዎች ከመኪና እንዳይወርዱ መደረጉንም ሠማን. . . ይሁን ይሁን አልን። . . . የድግሡ ጠሪ ቴዲ አፍሮም የጋበዛቸውን ወዳጅ አድናቂዎች በዝግጅቱ መሠረዝ የይቅርታ ደብዳቤ ፅፎ በface book ግድግዳው ላይ መለጠፉን አየን ብዙኃኖችም ደብዳቤውን ተቀባበሉት Telegram channel ያላቸውም ደጋግመው ለጠፉት #ቅንጭብጭብ'ም ታዘበ የተለጠፈ ከሚደገም ብለን ይቺን ፃፍን...

እነሆ #ቅንጫቢ

በሂልተን ሆቴል ከምሽቱ 1:00 ተገኝተን ምን አለ ለምንስ ተሠረዘ? አሁንስ ምን አይነት ዝግጅት አላቸው ለሚለው በምስል የተደገፈ መረጃ ለቅንጭብጭብ ወዳጆች ለማድረስ ብንሞክርም ባለው የአየር ፀባይ ምክንያት የመለውን ድባብ ለናንተ ማድረስ ሳንችል ቀርተናል። የሆነች ቦታም ቁጭ ብለን ይቺን አሰብን

B፦ የተከበሩ ... የሙዚቃው አልበም ምርቃት ለምን ተሠረዘ?!ማለቴ ለምን ተከለከለ

የተከበሩ፦ አይናቸውን አጉረጥርጠው ጠረጴዛው ላይ ተደፉ ደንግጬ ቀና አልኩ
እህህ ጉሮሮአቸውነረ ጠራረጉ

እኚ ሠው ምን አስበዋል?! 😳 ወደ በሩ አፈጠጠኩ የወዳጄ አባባል ትዝ አለኝ the first self defence is runing.

እህህ
ምን ባክህ ሙዚቃ ተመረቀ አልተመረቀ ምን ሊጠቅም
ባይገርምህ ብዙ ተመራቂ ተማሪዎች አሉን ምን አለ ብለን ሙዚቃ እንመርቃን? አፈጠጡ

እዚች ጋር ቴዲዬ አቋረጠኝ

ስማ ስማ. . .

ወዳጄ አስቴር መደንገጤን አየች መሠለኝ ፦ አቤት አቤት አለችልኝ

ኡፎይ... አልኩ

ቴዲሾ ቀጠለ ... ጌትሽን ክፈቱልኝ ... ጌትሽ ተቀላቀለ

የፈረሡን ምግብ ለውሻ ቢሠጠው. . .

የተከበሩ . . . አሁን በደንብ አፈጠጡብኝ

ከሃሳቤ ተመለስኩ

እእ... እ

አይ እንግዲ. . . እንከባበር . . ሙዚቃው ግን ቀጠለ...


ደሞ ይቺንም ቦለቲካ ናት ብላችሁ እኔንም እንዳልፅፍ አስከልክሉኝ አሏችሁ

. . .እንከባበር!

ከተመቻችሁ 👍 ከደበራችሁ 👎

አስተያየት ካላችሁ @bcrAzykid

Join us
@kinchebchabi @kinchebchabi
ቅንጭብጭብ via @like
#ቅንጭብጭብ #እርቃን_ገላዎች በአሁን ግዜ ወንዶችም ሴቶችም እንደ ፋሽን እየተከተሉት ነው። እርቃንን መታየት ስልጣኔ እና ውበት ነውን??? ለራስ ክብር አለመስጠት ስልጣኔ ከሆነ አልሠልጥን 🙅 እርቃን መሄድ ውበት እና ስልጣኔ ነው የምትሉ 👍 አይደለም የምትሉ 👎 ሃሳባችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።
#ቅንጭብጭብ
#እርቃን_ገላዎች በሚል ርዕስ ላይ የተለያዩ አወያይ ሀሳብ ላነሳችሁ እና ግላዊ አመለካከታችሁን ላካፈላችሁን ወዳጆቻችን #እናመሠግናለን
ከተነሡት ግላዊ እይታዎችም የተመረጡትን ለእናንተ ለማድረስ ወደድን ሃሳቡን ቋጭቶ ለማለፍ ሲባል ስለ ቅንጭብጭብ አስተያየት የጠየቅንበትን መልእክት ስላጠፋን ይቅርታ እንጠይቃለን።

የተመረጡ ሃሳቦች እና ግላዊ አመለካከቶች እነሆ #ቅንጫቢ

Join us
@kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ
© #እርቃን_ገላዎች ሃሳብና አስተያየት

#እርቃን_ገላዎች በሚል ርዕስ በተነሣው ሃሳብ ላይ የተሠነዘሩ እና የተመረጡ ሃሳቦች እነሆ #ቅንጫቢ

#azi_dead shot
ከአዲስ አበባ ጦር ኃይሎች

እርቃን መሄድ ውበት እና ስልጣኔ ነው የሚሉ ሰዎች መገኘታቸው በጣም አሳዛኝ ነው(የሚሰማቸውን ሳይደብቁ በመናገራቸው ባከብራቸውም)።
በነሱ logic ከሆነ እንስሳት እና በጋርዮሽ ዘመን የነበሩ ሰዎች ከነሱ የተሻለ ስልጡን ናቸው ማለት ነው።እባካችሁን ስንሰለጥን ሰውን ሰው የሚያስብሉትን ማንነቶች አንርሳ!ከዚህ ጋር በተያያዘ አላስፈላጊ(እርቃናቸውን ያሉ ሰዎች ያሉባቸውን) ቪዲዮዎችን እና ፎቶዎችን መመልከት እንዲሁም በነዚህ ተግባሮች መሳተፍ እራስን ወደታች ዝቅ ማድረግ እንጂ ወደላይ ከፍ ማድረግን አይጠይቅም።ሌሎችን እንዲሁም ራሳችንን እንደዕቃ አንቁጠር እላለው።

#neju
ከ ናዝሬት

yteshefenech set teflagi nech coz manm selalayat.

Merabyawyan rasu bezi albabsachw btam bzu chgr nw eko midrsbachw gn egha ya ngr aytaynm
Yeset lj wbtua stshfafn nw just like St.Merry

#Amesiyas

I guss people are confusing b/n 'sltane'&'syetane',,,in no circumstances being naked is civilization, just cause the European and the western world is obsessed wiz such idiouscy doesn't necessarily mean we got go crazy


ስለ ሃሳብ አስተያየቶቻችሁ እናመሠግናለን።

@kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ
© #እርቃን_ገላዎች ሃሳብና አስተያየት

#እርቃን_ገላዎች በሚል ርዕስ በተነሣው ሃሳብ ላይ የተሠነዘሩ እና የተመረጡ ሃሳቦች እነሆ #ቅንጫቢ

#senait
ከአዲስ አበባ

Hulum setoch bayhonum anidadochu gin ende silitane Ena ende wibet megelecha siyadergut yitayal. Yenesun confidence badenikilachewim Lemin endelebesut Ena purposezun bakew desi yilegnal coz anidanid ehitochachin erasachewin wym betesebachewin lemasitedader bemil mikiniyat wede setegna adarinet yigebalu ahun enesu erikanachewin yemihonut purpose alachew biye asibalew beterefe gin yerasachin wib bahil alenina enikurabet elalew


ስለ ሃሳብ አስተያየቶቻችሁ እናመሠግናለን።

@kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ 🇪🇹 #ኢትዮጲያ
#ልዩ_ዝግጅት

#ውሳኔ

ቅድሚያ ለዳኝነት ስለመረጣችሁን እናመሠግናለን።
የሁላችሁንም ፍላጎት ያሟላ ሚዛናዊ የሆነ #ውሳኔ ያልነውን እነሆ

1. ሙሉ ቁጥር ሻሞ
1. ጎዶሎ ቁጥር ሻሞ
1. ጥያቄ

ለሃሳብ አስተያየታችሁ #እናመሠግናለን

ትንሽ ካዝናናኝ አስተያየት #ቅንጫቢ

፨ በእውን ያጣነውን ዲሞክራሲ ቅንጭብጭብ እንኳን ይስጠን እንጂ

፨ በግዕዝ ይላሉ ይሄኔ'ኮ ቢጠየቁ አያውቀቱም እኔም በፊት ለፈተና አጥንቼ ደፍኜ ነበር አሁን ግን ምንም ትዝ አይለኝም

Join us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጲያ
#ለፈገግታ

መቼም አለቃ ገብረ ሃና ሲባል በብዙዎቻችን አዕምሮ የሚመጣው እየቆየ ሲገባን እንደ እብድ ብቻን የሚያስቀው ቀልድ እና ቅኔ ነው ለዛሬ እነሆ #ቅንጫቢ

አንድ ሴት ዉሀ ልትቀዳ ጎንበስ ስትል አንድ ጊዜ ያመልጣትና ድዉ ታደርገዋለች። ዘወር ብላ ስታይ አለቃ ገብረሀና ከኋላዋ ቆመዋል። ከዛም ደንገጥ ብላ «አለቃ ለመሆኑ ሰአት ስንት ሆነ ስትላቸው?» «አይ አንች ካላወቅሽዉ ለምን ደወልሽዉ?» አሏት ይባላል።

ፅሁፎችን ለሌሎች ማጋራት አንርሳ!


Join.us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጲያ
#ግራኝ_ሰዎች

ጠቅላላ ዕውቀት
ከ አንድ ወቅት ብጫቂ #ማስታወሻዬ ላይ

እነሆ #ቅንጫቢ

ግራኝ የሆኑ ሠዎች በቀኝ የአዕምሯቸው ክፍል ስለሚያስቡ እጅግ ስኬታማ ዘዴኛ እና የፈጠራ ችሎታቸውም ከፍተኛ ነው።

እነዚህ ነጥቦች አንዳንዶቹ በጥናት እና ምርምር የተደገፉና የተረጋገጡ ናቸው።

1. የአለማችን 10 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ግራኝ ነው። ግራኝነት ከሴቶች ይልቅ በወንዶች የተለመደ ነው።

2. በዘር የመተላለፍ እድሉ 25 በመቶ ብቻ ነው። ተመሳሳይ ጂን ያሏቸው መንትዮች ሳይቀሩ አንድ አይነት እጃቸውን ላይጠቀሙ ይችላሉ። በዘር ከመተላለፉ ይልቅ አካባቢያዊ ተፅዕኖ ግራኝ የመሆን እጣ ፈንታን በ75 በመቶ ይፈጥራል ተብሎ ይታመናል።

3. በየአመቱ ከ2 ሺህ 500 በላይ ግራኝ እጅ ተጠቃሚዎች ቀኝ እጃቸውን በሚጠቀሙ ሰዎች ግልጋሎት ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶችን ሲጠቀሙ ለህልፈት ይዳረጋሉ።

10.3 % በመቶ ግራኝ ሰዎች (ሴቶችም ሆኑ ወንዶች) ሲያሽከረክሩ ጉዳት ይደርስባቸዋል፤ 31.6 የሚሆኑት ደግሞ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ይጎዳሉ ተብሏል።

4. ጥናቶች ካለጊዜያቸው የሚወለዱ ህፃናት ግራኝ የመሆን እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

5. የአዕምሮ ብቃታቸው (አይ ኪው) ከ140 በላይ የሆኑ ግራኝ ሰዎች ቁጥር ከቀኛ እጀ ተጠቃሚዎቹ ይበልጣል። ጥናቱ ለዚህም ቻርለስ ዳርዊን፣ አልበርት አንስታይን፣ አይዛይክ ኒውተን እና ቤንጃሚን ፍራንክሊንን ይጠቅሳል።

6. 40 በመቶ የስኪዞፍሪኒያ (የአዕምሮ ሕመም) ተጠቂዎች ግራኞች ናቸው።

7. በኮምፒውተር ጌሞች እና ስፖርቶች ግራኞች በፍጥነት የማገናዘብ ብቃት አላቸው።

8. በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የተደረገ ጥናት የግራኞች አማካይ ደመወዝ ከቀኛሞቹ ከ9 እስከ 19 በመቶ ዝቅ ያለ ነው።

9. ግራኞች በፍርሃት የመጠቃት እድላቸው ከቀኛሞች የበለጠ
ነው።

10. ከተለመደው አስተሳሰብ በተቃራኒ ግራኞች ቀኝ እጃቸውን ከሚጠቀሙት በበለጠ በፈጠራ የተካኑ ናቸው።

11. ግራኞች ቁጡዎች እና ስሜታቸውን ለመቆጣጠር የሚከብዳቸው ሆነው ተገኝተዋል።

12. በስፖርቱ አለም ግራኝ አትሌቶች ተፎካካሪያቸውን የማሸነፍ እድላቸው ከፍ ያለ ነው።

13. እንደ አወሮፓውያኑ ከ1996 ጀምሮ በየአመቱ ነሀሴ 13 “የግራኞች ቀን” ተብሎ ይከበራል።

14. ከታዋቂ የአለማችን ግራኞች መካከል ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ ኦፕራ ዊንፍሬይ፣ ቢል ጌትስ፣ አርስቶትል፣ ናፖሊዮን ቦናፓርቴ እና ሊዮናርዶ ዳቪንቺ ይጠቀሳሉ።

Join.us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ዛሬ ደሞ ከታዘብነው ፍልስፍናዎች መሀል በብዙዎች የሚፈራና "የሱ መፅሀፍ ያሳብዳል"
ከሚባልለት የኦሾ ፍልስፍናዎች መሀከል

እንሆ #ቅንጫቢ

<<ያለ እግሮች ተራመዱ
ያለ ክንፎች ብረሩ
ያለ አዕምሮ አስቡ>>
ከሚለው መርህ ውስጥ ከብዙው በጥቂቱ በተከታታይነት ሁኔታ እናቀርባለን፡-
ቅርሽም ፣ ድቅቅ ፣ ፍስስ ፣ ሙትት ፧ ያለ በድን ገላ ፥ ላይ ፥ የቀኑ ፥ መጨፍገግና ፥ ቆዳ ፥ ከሚሸበሽብ ውርጭ : ጋር ተደምሮ ፧ በታፋዬ መሀል እኩል ፥ ለኩል የሚታየውን ፥ መቀንዘሪያዬን ፧ ብርድ እንደ ፥ መጋኛ በጥፊ ሲያጮለኝ ፧ ከእንቅልፌ ፥ ባነንኩ ሚስቴ ቁርስ ለመስራት ጉድጉድ ፥ ላይ ነች ፥ ከጀርባዋ ሄጄ ፥ የአንገቷን ስር ጥብቅ ፥ አርጌ ሳምኳት ፧ ሁለቱን እጆቼን ፥ በጡት ፥ ስሯ አሾልኬ ፧ የተቆዘረውን ሆዷን እዳብሳቸው ጀመር ፥ የሞሸሸው እየነቃ ፧ የነቃውም እየጋለ የሚስቴም ፥ የመቀንዘር ሲቃ ፥ ጨመረ ፥
በሆዷ ፧ የታቀፈችው የ7 ወሯን ሴት ልጄን ነበር ፥ እደጊልኝ ብዬ ፧ ያሸሸኃት ፥ እንደ አለመታደል ፥ ሆኖ ልጄ የእናቷን ሆድ ፥ ተከራይታ ነበርና ፧ የልጄን ፀጉር ዳበስኩ ፥ ብዬ የእናቷን ፥ ሆድ በመዳበሴ ነበር ፥ የሚስቴ ፥ የወሲብ አምሮት ፥ በሲቃ መልክ ፥ የወጣው

እነሆ ሴት ልጄም ፥ በአጥንት ላይ ስጋ ፥ ለብሳ የገፄን ቅርፅ ይዛለች።

ሚስቴም ፥ የእርግዝና አምሮት ፥ ሆኖባት በወሲብ እንዳረካት ትፈልጋለች።

።።።።።።።።። ግን ግን።።።።።።።።

#ሚስቱንም_ልጁንም_ያረከሰ_እባል_ይሆን_?

ሱራ ቢራቢሮ 🦋

@surabirabiro🦋


።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

1980__1998 ፥ ድረስ ፥ ብዕሮችን ይከትባል ፥ ይጭራል ፥ ይሞነጭራል ፥ ይዋትታል ፥ በነዚህ ፥ መንገድ ፥ ውስጥም ፥ የብርሀን ተጓዥ ፥አበዮተኛም ነውር ፥ብዙ መፅሀፎችን ፅፎ ፥ ለእትም ፥ አልበቁለትም፥ ነበር ።

የአፃፃፍ ፥ ዘዬው ፥ ቀለሙም ፥ይለያል ድህረ ፥ ዘመናዊን ከላይ ፥ድህረገጾች ባህላዊው ፥ አጋምዶ ፥ አምጥቶታል በሀገራችን ፥ ብዙ ፥አልተለመደም።

ደራሲና ፣ሃያሲ አለማየሁ ገላጋይ ስለ አዳም ሲጠየቅ?

ለረዥም አመት ልታነብ ትችላለህ
ለረዥም አመት ግን መፅሀፍ ፅፈህ ጨርሰህ አለማሳተም ኤጅግ ጠንካራነትን ይጠይቃል
አዳም ግን አረገው
ከረዥም አመት በኃላም ሲታተም ሰው ልብ ዘልቀው የገቡ ናችው አዳም ራሱ አዳም ነው። ይላል አሌክሶ


በወፍ በረር ከመፅሀፊ ሁለቱን የማረሳቸውን ልጋብዛችሁ


"የፊደል ገብታ ሳይ፣ የአቡጊዳን ሰራዊት፤ የ ሀ ግዕዝ ሁ ካዕብን ዜማ ስሰማ የዓለም ካርታ በእጄ ያለ መሰለኝ።

'በ' መሰለችኝ ጨዋ ሴት፤ በደበተኝ ጠዋት በሰላምታዋ ደግፋ ያነቃችኝ፣ በአንደበቷ ከዘራ ያቆመችኝ

'ቀ' መሰለችኝ እማማ ወገቧን ይዛ ስትገስፀኝ

'ፀ' መሰለችኝ ፀሐይ፣ እቶን፣ ሞገድ፣ ብርሃን፣ ታላቅነት፣ ቀለማት፣ ነገሥታት፣ ሩቅ ዘመን፣ አዲስ ዘመን፣ ዝርውና ምሳሌው

በእያንዳንዱ ሆሄ ውስጥ አገሮች፣ ሰዎች፣ እንስሳት፣ ማዮችና አየራት ታዩኝ።

#የስንብት_ቀለማት

አንድ ጨቅላ ተደፍራ ባየ ግዜ በልጅነት አንደበቱ ይህንን ተናገረ
በምኗ ምን የማይገባ ልጅ አኮላሻት

#ግራጫ_ቃጭሎች
ብቻዬን ያስፈግገኛል

የኔ አዳም እንኳንም ተወለድክልን

ሱራ ቢራቢሮ 🦋

@surabirabiro🦋


።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

አልሃምዱሊላሂ ደህና ናት
""""""""""""""""""""''''''''''''''''''''
አያታለሁ ሁሌ
አምራ ተንቆጥቁጣ
ከመንገዱ ቆሜ፤

ለሰው ቀልብ በማይስብ
ቆሻሻ ....አዳፋ
ልብሴን አገልድሜ፤

ባረጀ ወዘና
በገጠጠ አጥንቴ
በከሲታ አቋሜ፤

ለአለም የከበደ
ፍቅር ተሸክሜ፤

አልሃምዱሊላሂ አያታለሁ ሁሌ!

(አለሁ)

አለች
ከተንቆጠቆጠው
ከዚያ ማዶ ህንፃ፤

በህይወቴ ማህደር
የውበት ማህተብ
እንዳይጠፋ ቀርፃ፤

የልጅነት ፍቅር
የማይዘም የማይፈርስ
ልቤ ላይ አንፃ፤

አለች እንደዋዛ
በደመቀ ውበት
ህይወቴን አፍዝዛ!
.
.
አልሃምዱሊላሂ እኔም አያታለሁ
.
.
ሄጄ ለሰላምታ
እጆቼን ደፍሬ
ሰጥቻት ባላቅም፤

እሷን እሷን ብዬ
የፍቅር ስካር ይዞኝ
አቅፌያት አውርቻት
ደስ ብሎኝ ባልስቅም፤

በወዝአደርነት
እቃ ተሸክሜ
ካለችበት ህንፃ
ሳልፍና ሳገድም፤

ሰርቄ አያታለሁ
ሰርቄ ሳላያት
ጀንበር አዘቅዝቃ ፀሀይ አትጠልቅም!
.
.
አልሃምዱሊላሂ ደህና ናት
.
.
እሷ የጠፋች ለታ
ዕውቀት ብርሃኔ
በከንቱ ቢቀርም፤

ከንዋይ ጎድዬ
ከኑሮ መቀመቅ
ዘቅጬ ብቀርም፤

አይቻት ውላለሁ
አይቻት አድራለሁ
አልሃምዱሊላሂ ከቶ አላማርርም!
.
.
አልሃምዱሊላሂ ደህና ናት
.
.
አፍቅሪያት መውደቄን
አይታና ተረድታ
ገምታኝ ባታውቅም፤

ለፍቅር ባከነ
የሚል ስም አልብሶኝ
በዱንያ ዓለም ሰዉ ቢሳለቅም፥

እውነተኛ ፍቅር
መስጠት ብቻ እንጂ
መቀበል አያውቅም፤

ውለታ አይጠይቅም!

(አለሁ ....አለሁ እኔ)

በኑሮ እስርስር
በህይወት ውትፍትፍ
ችግር ተጣልፌ፤

እስከምሞት ድረስ
የፍቅሯን ዘምዘም
ለልቤ አጠንፍፌ!

ሲርበኝ ሲጠማኝ
ከህንፃዋ ማዶ
ሄጄ ተመልሼ፤

የችምችሙ ጥርሷን
የሂጃቧን ጥምጣም
የዓይኖቿን ንጣት
የጉንጮቿን ቅላት
በሩቁ አይቼ አካሌን አርሼ፤

አልሃምዱሊላሂ
እኔ እንዳለሁ አለሁ
ፍቅሯን ተንተርሼ!
.
.
አልሃምዱሊላሂ ደህና ናት
.
.
ደስ ብሎኝ ውላለሁ
ደስ ብሎኝ አድራሁ
ከሩቅ ስመለከት ስትስቅ አይቼ፤

ኑሮ ድባቅ መትቶኝ
ከህይወት ጎድዬ
ከፍቅር ሞልቼ፤

የህይወት መጥፎ እጣ
የዓለም ክፉ ፅዋ
አላግባብ ተግቼ፤

እየተገላበጥኩ
በውበቷ ዱላ
ልምጭ ተመትቼ!

(አለሁ ....እናማ)

ንገሩልኝ ስሞት
ጅናዜ ወደ አፈር
እንደተቀበረ፤

በሉልኝ ሄዳችሁ
በጣም የሚያፈቅርሽ
አንድ ሰው ነበረ፤

ከውበትሽ ቀምሶ
በአይን ፍቅር ፈዞ
ቀልቡ እንደሰከረ፤

ስምሽን ሲያነሱለት
አልሃምዱሊላሂ ደህና ናት እያለ፤

በሳቅሽ የሳቀ
በሀዘንሽ ያዘነ
ዱኒያን ካንቺ ላይ
ገንብቶ የኖረ፤

አንድ ሰው ነበረ....!

(ብላችሁ ንገሯት)

አልሃምዱሊላሂ ደህና ናት!
.
.
.
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@Run_Viva_Run


ከአሌክስ አብርሃም ዙቤይዳ መፅሀፍ ከ"አልሃምዱሊላሂ ደህና ናት"በሚለው አጭር ልብ ወለድ ፅሁፍ የተመሰረተ


።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
ጭላንጭል ብርሀን : በጨቅላ : አእምሮ : ላይ ተስሎ የቀረ። ስዕሉ በልቡ ውስጥ የተሞነጫጨረ : ተሞነጫጭሮም : በከፊል የደማ ፣ ደምቶም የረጋ : የረጋውም ደም ቀይ ቀለምን ይረጫል። በእስራስ : የሞነጨረውን ስዕል : በደሙ ጠብታ እየነከረ ትላንቱን ይጭራል : ዛሬውን ይተልማል : ነገውን ግን እንጃ : እሱም አያውቀው........

ዘመም : እንዳለ የልጅነት : ገጿን ይስላል አዎ : ክብ ፊት : ፀጉሮቿ የተዘናጠፉ : የአይኗቿ ሽፋሽፍት መስለምለም : የሚያሳሳ : ምጥን ጎራዳ አፍንጫ ያላት
: ከናፍርቶቿ የኖህ : መርከብን ይመስላሉ : ንፍር ውሀውን : ለማምለጥ : ብለው የተከደኑ ሲከፈቱ : ግን ነጭ : ርግብን : ይዘዋል የሷም ከናፍር ሲገለጥ : ነጭ ጥርሷን : ስትፈለቅቀው ድንቡሽቡሽ : ያሉ ጉንጮቿ ውብ የተፈጥሮ ስርጉዷ : ወይም ዲምፕሏ : ጎሎቶ ይታያል።
ያ የልጅነት መልኳ: ናፈቀኝ የምር የምር : የልቤን በልቤ ሰድሬ በፍቅሯ ክታብ ተንሳፈፍኩ

አይ ልጅነት ግን እንደ ዥረት ይነጉዳል
እንደ ብራና :በጭንቀት የተወጠረው የጨቅላ አምሮዬ :እንደምወዳት ለመንገር ከልቤጋ ሙግት ይገጥማል
ምሳ ሰአት ላይ ለ ጓደኛዬ : ሚስጥሩን ብነግረውጭራሽ ሆዱ መቋጠር አቅቶት ጉድ አረገኝ ለምወዳት ልጅ : ጓደኛ ነግሮ አሸማቀቀኝ

9 ሰአት ላይ : ወደ ጓሮ ሄደን ለምወዳት ልጅ ሁሉንም : ነገሩአት
በነገሩም ተቆጣች :ያን ሰአት ጨዋታና ትምህርት : እንጅ ፍቅርን የት : እናውቀውና ገና በ
#3ተኛ ክፍል አይታሰብም ነበር በእውነቱ

የምወዳት ልጅም : በቁጣ ነገ ለ English : አስተማሪያችን እንደምትናገር ነግራኝ ተለያየን አቤት ያን ማታ የልጅነት : ልብ ሲጨነቅ ና ሲርድ አደረ
መቸም መሽቶ : አይቀርም ነጋ
እየፈራሁ ሄድኩኝ ከወትሮ በተለየ :
ሁሉም ፊት ነስቶኛል

ከሰውነት ተራ የዘቀትኩ ያህል ተሰማኝ
#english አስተማሪያችን #መምህርት_አልማዝ ክፍላችን ገብታ ትምህርት : ከመጀመሯ በፊት : ጠርታኝ ከተማሪዎች ፊት : አስቆመችኝ
የሰው : አይን ምንኛ ይከብዳልን?

በትንሽ ሰው : የሚታወቀው የማፍከር : ኩነኔ ይፋ ወጣ ምን ቃል አለኝ ፍቅሬንም : ስሜንም በማጣጤ : ሆድ ቢብሰኝ የልጅነት : እንባ ከአንጀቴ አነባሁ : ያቺን እንባ አፈር እስኪጫነኝ ድረስ : ምረሳት አደለችም : ሁሉም መሳቂያ አርጎኝ ነበር ሳልፈልግ ፌመስ ሆንኩ : ብወዳትም ግዴታ መራቅ : አለብኝ የግድ : መራራዋን ፅዋ : ቢመረኝም በልጅ አንጀቴ ተጋትኩት

የሚገርመው : ነገር ስጠጋት : ትጠጋኛለች ስቀርባት : ትቀርበኛለች በቃሏ : ምሳሌን አሳየችኝ : ለፊደል "ሀ",
ለአሳር "ዋ" ይሉት ነገር።

እሷኮ ያኔ : ፍቅርን አታውቅም : እኔ ድኩም : አካሌን ይዤ : እባዝናለሁ ትምህርት ቤት : በጠዋት ሄጄ ጠብቄያት : ስትዘገይ ስብር እላለው : አረፋፍዳም ቢሆን ስትመጣ : የልጅነት ተስፋዬ : ይለመልማል የነፍስ ምግቤ ናታ።

ግንኮ አሁን ላይ እሷ : የለችም መፈቀሯን አላወቀች ሞኝነቷ.....
ያወቀች ግዜናስ?
ብን ትላለች ልክ እንደድሮው
በጭላንጭል ገፅ ትከሰታለች ልክ እንደ አሁኑ

1... 2.. 3 ... 4 ..16 አመት ሙሉ ስዕሏ በልቤ ላይ እንደተቀረፀ : ነው ንግግሯንና : ሳቋ በፅልመት ምልክ እየተደጋገመ : ያቃጭልብኛል።

አሁን ላይ ጨለማ ውስጥ ነኝ ላምባ ዲናዬ ሰምታኝ ትመጣ ይሆን? እንጃ ....

#ግንኮ_መፈቀሯን_አታውቅም

የተኖረ እየተኖረም ያለ

ሱራፌል ጌትነት🦋
🦋ሱራ ቢራቢሮ🦋
🦋
@surabirabiro🦋


።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ፀበል ፥ በሚፀበሉ ፥ የጋኔን ፥ ማደሪያ ፥ በሆኑ ፥ ሰዎች : መሀል : ተከብቤያለው ፥ እንደርቢ ፣ ቡዳ ፣ አዛዝኤል : መተት ፣ ሰላቢ ፣ ድግምት...ወ..ዘ.ተ..........እዝጎ: ብዛታቸው ፥ ግን : እግዜሩ : ብዙ : ተባዙ ያለው : እነሱን ፥ ሳይሆን ፥ አይቀርም። እንዲህ : አንደ : ምድር : አሸዋ : ያበዛቸው። ምናልባት :ውስጣቸው :ስለማይገኝ : ይሆናላ : ብዬ ፥ የጥያቄም ፥ አባት ፥ የመልሱም ፥ እናት ፥ ሆኜ ፥ ቁጭ አልኩ።

እኩለ : ሌት : ላይ ጋደም : ብዬ : ሳለ እማሆይ በደጃፌ : አለፉ ብሩኬ...... ብሩኬ........ በለሆሳስ : ተጣሩ

እ......... አቤት : እማሆይ .... በመደነባበር : ስሜት

አንት : ሙዠሌያም : በሩን : ክፈት .....

ቀጭን : ትእዛዝ ......

እጄ ፥ ወደበሩ ፥ መክፈቻው ፥ አኮበኮበ..... ሲጢጢጢጢጥ... በሩ ፥ ተከፈተ።

እማሆይ ፥ እርቃናቸውን ፥ ናቸው ደነገጥኩ ራሴን እማሆይ : ፃድቅ : ናቸው : የፀጋ : ልብስ : (ፀጉር) ፈጣሪ : አከናንቧቸዋል : ብዬ ራሴን : መሸወድ ፈለኩ።

በርግጥ ፥ እሳቸው ፥ አፍላ ፥ እድሜ ላይ ናቸው። ቁንጅናቸውም ፧ እንኳን ለንደኔ ፥ አይነቱ አለማዊ መናኝንም ፥ ከአቋሙ ፥ ያዋዥቃል።

የጌታ ፥ ፍቃድ : ሆነና : እማሆይም : በውበታቸው ማርከው : መደቡ : ላይ : አጋድመው ፧ ደጋግመው : ነጠሩብኝ....

መቼም ልጄ ነገር በሶስት ይፀናል አሉኝ...... ልክ አንደኛውን ፧ ዙር እንደጨረሱ....

በተወደደ ፥ መቅኔ ፥ መተኪያ በማይገኝበት ፥ ቦታ ላይ ምን ፥ ኩነኔ ፧ ገባሁ? ፥ ጃል! አዎንታዬን ፥ ራሴን በመነቅነቅ ፧ ሶስት ግዜ ፧ እንጢነጥሩብኝ ፈቀድኩላቸው።


ስብሀት ለአብ_____ ቸፍ
ስብሀት ለወልድ_____ ቸፍ
ስብሀት ለመንፈስ ቅዱስ____ ቸፍ

ጠበል ፥ የሚረጩኝ ፥ ግርማ ፧ የ ሞገስ ፥ ተላበሱ አባት በመስቀላቸው ፧ ጀርባዬን እየደለቁ። አንተ ማነህ ?
ፈርጠም ፧ ብለው ፧ በነጎድጓድ ፧ ድምፃቸው....

ሴት ነኝ ያውም መነኩሴ.....

ሴት......ምንድነሽ?

ሴት አይነጥላ ፣ ሴት ሳር

የምንኩስና ስምሽ ማነው?

#እማሆይ_ረታ_ነጠረች

ወደሲኦል ትገቢዘንድ በእግዚአብሄር ስም አዝሻለው ጮኸሽ ውጪ..

ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ ጮሄ ወደኩኝ .

ከወደኩበት ስነሳ ብዙ ምዕመን በቤተክርስቲያን ውስጥ ታድሞ የሚሆነውን በጥሞና ይመለከታል

ስምህ ማነው አሉኝ ግርማቸው የሚያስፈራ አባት

#ካሳ_ውቤ_ልዋጥህ

ህምምም ¡ አለ ነገር......

ፀሀፊ
ሱራፌል ጌትነት
ሱራ ቢራቢሮ
@surabirabiro🦋

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
አልችልበት አልኩ ፡፡ የተሸነፍኩ ይመስለኛል ፡፡ለሊቱን ሙሉ እንቅልፍ ባይኔ ሳይዞር ነጋ ፡፡ልተኛ አይኔ ሩቡ ሲከደን ነው ደውላ ያስደነገጠችኝ ፡፡ ጭንቅ ባለው ድምፅ ስታወራኝ አንጀቴ ስፍስፍ አለ፡፡ከስንት ጊዜ በኋላ እንዲህ አወራችኝ ፡፡ ያወራችበት ድምፀት እሷም ድክም ብቅት እንዳላት ያሳብቃል፡፡ ስልኩ ጠርቶ ደዋዩዋ እሷመሆኗን ሳውቅ ተስገብግቤ ነው ያነሳሁት ፡፡ ከምኔው ከአልጋዬ ተስፈንጥሬ እንደወረድኩኮ…
“ይቅርታ ተኝተህ ነበር መሰለኝ ረበሽኩህ እንዴ!...”
“አ..አይ አልረበሽኝም እረ.. ምነው ከመሸ ችግር አለ”
“ምን ባክህ ድጋሚ … “
“ ተጣላችሁ!!...”
“እ… በናትህ የአሁኑን የዛሬን ብቻ … አንተ ጋ ነው አይደል አሁን “
አፈር ይብላና ይሄ ጋንድያ አጠገቤ ተጋድሞ ያንኮራፋል … ዛሬም እንደተለመደው ተጣልተው ነው እኔ ጋ የመጣው ፡፡ ሌላ መሄጃ የለውም፡፡ምን እንድየብኝ እንጃ እንዲሁ ያምነኛል፡፡ያለምክንያት ፡፡ ሲጨንቅ!! ፡፡
የማደንቅለት ነገር የፈለገ ቢናደድ ቢበሳጭ መሸሽ እንጂ እጁን ሰው ላይ ማንሳት አደለም ክፉ ቃል ከአንደበቱ እንዲወጣ አይፈልግም ፡፡
እኔ ደግሞ ይሉኝታ ይዞኝ እንጂ ሁለቱም ባላያቸው አጠገቤ ዝር ባይሉ እወዳለሁ ፡፡ ባልና ሚስት ተብዬውን፡፡
ችግር አለብኛ ፡፡ እሷን የማውቃትን ያህል አያውቃትማ ፡፡ የመረረ ነገር ተፈጥሮ ተለያይተን እንጂ ፍቅረኛሞች እንደነበርን ኣያውቅማ ፡፡ ላንለያይ የተለያየን፡፡ እህል ውሃችን አጓጉል የተጋጠመ፡ ፡ ርቀታችን አጋጣሚ በሚባል በማይታመን የብረት ገመድ ተተብትቦ እንደተያያዘ አያውቅም፡፡ ቢያውቅማ …..!!
እሸሻለሁ ብዬ መያዜን.. አመልጣለሁ ብዬ ጭራሽ ለኢላማ መመቻቸቴን ሳውቅ ባይደክመኝ ነበር የሚገርመው፡፡
ኡፍፍፍፍፍፍ ….
ሚስቱ ፍቅረኛዬ ነበረች፡፡ እብድ ያልኩላት ፍቅረኛዬ ፡፡ ይህንን እሱ አያውቅም ፡፡ ከተለያየን ከዓመታት በኋላ ነው እሱ የልብ ጓደኛዬ ሆኖ አንድ ቀን ቤቱ ጋብዞኝ ጉዴን ያየሁት ፡፡ጉዴን ልበል እንጂ… የጉዴ ፍላጭ አይን ውስጥ የምወደው አባቴ …. የአገጯ ጉድጓድ እህቴን … ምን መአት ነው !!
እጣፋንታዬን መበላሸቱን ባውቅም ላለማየት ያደረኩት ጥረት አልሳካ አለኝ፡፡ መጥፎ እድሌ በግድህ እየኝ አለኝ ፡፡ያውም እየደጋገምኩት፡፡ያውም እየተመላለስኩ ፡፡ ባንዱ ጥፋቴ ሚሊየን ጊዜ ተቀጣሁ ፡፡ ባንድ ጥይት ሁለቴ ስትሞት አሟሟትህ አያሳዝንህም ፡፡ አለ አይደል እየጠላኸውም የሚናፍቅህ ስቃይ …ቀባጠርኩ … ጭንቀቴ ነውኮ
“ሚጣዬ ማነው ስምሽ!” አልኳት ህፃኗን እጇን እየሳምኳት
“መክደሽ ….”አለችኝ ፡፡ አፏ ይጣፍጣል፡፡ ቀና ብዬ እናቷን አየኋት፡፡ከእንባዬና ከድንጋጤዬ ጋ እየታገልኩ፡፡
መቅደስ የሴተኛ አዳሪዋ እናቴ ስም ነው፡፡ ታውቃታለች፡፡ ኮረንቲ ተበጥሶ ሞታብኝ … እሷ ናት ያፅናናችኝ ፡፡ እናቴን እወዳት ነበር፡፡”ወይ ሙትና የእድር ገንዘብ አብላኝ !” ብትለኝም ስትሰክር ፡፡ ታውቃለች እንደምወዳት ፡፡
“ ልጃችንን ስሟን መቅደስ እልልሃለው !” ብለኝ ነበር ፡፡
“ሌላ ቀን ምን ላምጣልሽ? “ አልኳት
“ቲኒሽዬ ወንድም አምጣልኝ…. እናቴ ቲኒሽዬ ወንድም አምጥታልኝ ነበረ… እዝጋቤር ና ብሎት ሄደ ..ታመጣልኛለህ አባቢኮ… ?”
“ሂጂ ውጪና ተጫወቺ !!”
ቀና ብዬ እናቲቱን አየኋት ….አሁን እሷው ነች ከእምባዋና ከድንጋጤዋ የምትታገለው ፡፡ አውቅባታለሁ፡፡
ከምኔው ይሄ ሁሉ በሷ ሆነ???… እኔ የት ሄጄ ??
ኡፍፍፍ ደክሞኛል በቃ!! ትክት ብሎኛል !! ይሄ ባሏ አጠገቤ ተጋድሞ ያንኮራፋል ፡፡ ወንድም አገኘሁ ብሎ፡፡
በዚህ ሁሉ ሃሳብ አለመሞቴ ደንቆኛል ፡፡
እውነት!!! “መቅደስ!” ልጄ ባትሆን እስካሁን አቅም አይኖረኝም ነበር፡፡


ዘምሽ✍️

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
ፀሎቴን ባሰማ ፥ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ፥ ወሰዱት መሰለኝ
.......
የእቴሜቴ ጀምበር
©ሲራክ ወንድሙ
.
እረኛ አይዘምርም ፥ ዝም ነው አድባሩ
ፋኖስ ክሩን አጥቷል ፥ መሸ ደህና እደሩ
ቡሬ መንደር ራቃት ፥ የለችም ከቤቷ
በሌት አልዘመረች ፥ ከፍቷታል ወፊቷ
ማልዶ ሌት ሚያነቃኝ ፥ ዶሮ በጉድ ወጣ
የሌት ድምፁን ሸጦ ፥ መውዜር ይዞ መጣ
ወዲያም ወደ ሰማይ
ከጎጆዬ በላይ
ፀሎቴን ባሰማ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ወሰዱት መሰለኝ
.
የዛች የእዝነት አርማ ፥ የህዋ ላይ ሰንደቅ
እንዴት ቀን ከፍቶባት ፥ ውብ ጀምበሯ ትጥለቅ
ከዛች ከገራገር ፥ ከደጊቱ ዳሴ
እንደምን ብርቅ ይሁን ፥ ሰላም ለእለት ጉርሴ
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን
እኔን አፈር ይብላኝ ፥ ለእኔ ቀኑ ይክፋ
አንቺን ያሳጣችሽ ፥ ያች አለም ትደፋ
እስከ መች አስከ መች ፥ የአረር ሙዳይ ቋጥረን
እንደጃኖ ኩታ ፥ ዝናር ጥለት አርገን
ሀገር እያጠፋን ፥ ያልፋል እንላለን ?
እንዴት ነው መሰንበት ?
መውዜር እንደነዶ በሚመዘዝበት?
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን?
.
ከጩኸትሽ ማዶ ፥ ካኮረፈው ሰማይ
ቄራ ከመሰለው ፥ ከአድማስሽ ሸራ ላይ
እብሪት ያጠላበት ፥ ምስል ድንገት ካየው
ለቸር አንመስለኝም ፥ ያን ጊዜ ፈራለሁ
አርብ አርቡን አመሻሽ
የሰማዩ ገላ ሲመስል የደም ሻሽ
ንትብ የለበሰ
ከወደ አንገቱ ዘሞ የተዘለሰ
ይሁዳሽን ባላይ ፥ ወድቆ ሲያንሰራራ
መስቀል ሆኗል ለሻጭ ፥ ገዢ ራሱን ያኩራ
ከክርስቶስ ይልቅ ፥ ይሁዳ ነውና ሚረከብ መከራ
ምክኒያቱም ......
ዘመን እያሰፉ
ትውልድ ለሚነቅፉ
ነገር ጠንቷል ዛሬ ፥ አውቀውት ይረፉ
ለሻጭ መስቀል ሊሆን ፥ ምሏልና ዛፉ
.
በኑረት ቀራንዮ ፥ በህይወት ጎለጎታ
ከገዳይሽ ቀዬ ፥ አንቺ ሆነሽ ጌታ
በሰማያ አኮርባጅ ፥ ወዲያ ስትላጊ
የመከራን መስቀል በሌት ተሸክመሽ ፥ መንገድ ስትፈልጊ
ጨረቃዋ ገባች ፥ ከደመና ጉያ
ከዋክቶች ሸሽተው ፥ እንደሰደድ ቋያ
ጠረንሽን ገፍተው ፥ ከገላሽ ሲርቁ
በንቄት ሸምቀው ፥ ሊጥሉሽ ዘለቁ
.
ዞር ብንል ወዲያ ፥ አራራይ መረዋ
ቀና ብንል ኦና ፥ የጠቆረ ህዋ
የፀሎትሽ ጩኸት ፥ ካልደረሰው ያ ' ቃል
እሱም እንደሰዉ ዘምቶልሽ ይሆናል።
..................... //// ..............
©ሲራክ ወንድሙ @siraaq
የእቴሜቴ ጀምበር
ህዳር ፳፻፲፬ ዓ.ም
http://t.me/kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#አበባ_አየሁ

©ሲራክ ወንድሙ

እሩቅ ለሩቅ ሆነን
ይጠባል መስከረም ፥ ይታጠናል ህዳር
ፀደይ እየዳኸ
ክረምት ይጋልባል ፥ ተስፋዬን ሳሳምር

አምና በዚህ ሰዓት ፥ ጠበቅኩሽ በውርጩ
እስኪያልፍብኝ ሀሩር ፥ ወፎች እስኪንጫጩ

ጠበቅኩሽ ፥ ጠበቅኩሽ
የሌት ውብ እንቅልፌን ፥ በናፍቆት መጅ ድጬ
በመምጣትሽ እርሾ ፥ ልቤን አሳብጬ።

የአንቺ ሀገር ወዴት ነው የአድማስሽ አቀበት ?
እግሬን ላወላዳ ፥
ይቆምልኝ እንደው የልቤ ትኩሳት
ተይ ንገሪኝ ባክሽ ፥ ወዴት ነው ባዕቱ
ካቻምና ላይ ቆሜ ፥ መነነ ዘመኑ ከነፈ ጊዜያቱ

የተራራው ደረት በአደይ ፂም ጎልምሶ
የሀምሌ ጨለማ
ባባረረው ብርሃን ፥ ሲሄድ ተለሳልሶ
እንደው ለአዲስ ዓመት ፥ ትጋቴን አስታውሰሽ
ናፍቆት ፣ ተስፋ ፣ ፍቅርን - አንድ ላይ ታቅፈሽ
በሬን ከፍተሽ ግቢ ፥ አበባ - አየሁ ብለሽ
....
©ሲራክ @siraaq
https://t.me/kinchebchabi
ይመስላል ፍለጋ

@siraaq
.

ለበራድ ፡ ጎጆዬ ፡ እንዲሆናት ፡ ብዬ ፥ ፍሙን ፡ ብልክላት፣
ያቺ ፡ የአደራ ፡ ፍሜ ፥ በመንገድ ፡ አግኝታ ፡ ቦታ ፡ ብትጠይቃት ፣
አላውቃትም ፡ ብላ ፥ ዘማ ፡ አሳለፈቻት።
ፍም ፡ አላት ፡ ይሉኛል ፥ አይሞቃትም ፡ ዳሴን፣
ነብስ ፡ አለህ ፡ ይሉኛል ፥ አልሞላም ፡ በድኔን።
ፈልጌ ፡ አስሼ ፡ አገኛት ፡ እንደሆን ፥ ውብ ፡ ቀኔን ፡ ብሰዋ፣
አልተገናኘችም ፡ ከጥንት ፡ እስከዛሬ ፥ ነብሴ ፡ ከስጋዋ።
....****......*****.....
መስከረም ፳፻፲፭ ዓ.ም
''''''''''''''''' ' " ''''''''''''''''''''''''''
©ሲራክ ወንድሙ
https://t.me/kinchebchabi
ንጥል ፥ ተጓዥ አዳም
.
©ሲራክ ወንድሙ
.
ነብሴ የግጥም ድርድር
ልቤ የ' ዋ ባህር
ስሜ አፈር ገፊ - ኮስታራ ፏፏቴ
አደዬን አክስሜም - አልደርስም ከቤቴ
°°°°°°°°°
መስከረም ፳፻፲፭ ዓ.ም
-------------
https://t.me/kinchebchabi